ስኬት እነዚህን 6 ነገሮች ይፈልጋል(ሚስጥራዊ ቀመር)
1.
ጠንክሮ መሥራት(hard work)
በእድል አትመኑ,ከዚያ ይልቅ ግን በትጋትና በጥረት እመኑ.
➡️ ሂደቱን ለማፋጠን መሞከር ወይም አቋራጭ መፈለግ አቁሙ ምክንያቱም ''ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል'' ስለሚሆን መሰረቱ የደከመ ያደርግባቹሀል።
2.
ትዕግስት(patience)
ትዕግስት ካጣህ ጦርነቱን እየተሸነፍክ ነው።
በመጀመሪያ ምንም ነገር አይከሰትም, ነገሮች መከሰት የሚጀምሩት ቀስ ብሎ እና በድንገት ባልተዘጋጀህበት ጊዜ ነው።ስለዚህ ትዕግስትህን የሚፈታተን ምንም ነገር ቢፈጠር
ታግሰህ ተጋፈጠው
አብዛኛው ሰው በመጀመሪያው ፈተና ላይ ተስፋ ይቆርጣል።አንዳንዱ ደግሞ እስከመጨረሻው ይፋለምና አሸናፊ ይሆናል።
3.
መስዋዕትነት(sacrifice)
ለምትፈልገው ነገር አስፈላጊውን ዋጋ ካልከፈልክ የፈለግከው ነገር ዋጋ ያስፈልግሀል።
ሁሉም ነገር የራሱ ዋጋ አለው። ጥያቄው:ለምትፈልገው ነገር ምን ለመክፈል ዝግጁ ነህ? ነው።
4.
ወጥነት(consistency)
ወጥነት አማካዩን ወደ የላቀ ደረጃ የሚቀይር ነው።
ወጥነት ከሌለህ የላቀ ስኬት በጭራሽ አታገኝም።ምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆን እራስህን አጠንክረህ መቀደል አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው።
5.
ተግሣፅ(discipline)
መነሳሳት(motivation) እንድትጀምር ያደርግሃል፣ነገር ግን ተግሣጽ (discipline) እንድታድግ እና እንድትቀጥል ያደርግሃል።
➡️ ማድረግ የማትፈልግባቸው ቀናት ይኖራሉ።
የሚሰማህ ምንም ይሁን ምን በእነዚያ ቀናት ውስጥ አንድ ደረጃ ወደፊት መግፋት አለብህ።
6.
በራስ መተማመን(self confidence)
በራስ መተማመን ማለት አንተ ውስጥ እራስህና ሰዎች ከሚያስቡህ በላይ ትልቅ አቅም መኖሩን ማመን ነው።
አንተ ያላመንክበት ማንነትህ ማንም አያምንበትም።''ትችላለህ ታሳካዋለህ''
መልካም ቀን!
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
Telegram💡
@bright_ethiopia1▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█