🚹 አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ በማዕበል ተመታና መርከቡ ተሰባብሮ በባህሩ ውስጥ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል ... ምግብን ዓሳ እያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ።
አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ እየሄደ በመሀል እዛች ባህር ላይ ጭስ ይሸተዋል ዞር ብሎ ሲመለከት ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው ... እየሮጠ ቢመለስም ጎጆውን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዶታል አለቀሰ ፈጣሪውን ወቀሰ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ጥለሀኝ ከቤተሰቦቼ ነጠልከኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰረሀትን ጎጆ ታቃጥልብኝ አለህ ብሎ አለቀሰ አማረረ ...
ከደቂቃዎች በኃላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ ተደሰተ... የመርከብ ሶዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት ከዚያም ለመርከብ ሰዎች ጠየቃቸው !
እንዴት አገኛቹኝ እዚህ አከባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት መጣቹ አላቸው ...
መርከበኞቹም እኛም በዛኛው በከል ዙረን እየሄድን ነበር ከዝያ በኩል ጭስ አየን እና እዚ ሰው ይኖራል ብለን መጣን አንተ አገኘን አሉት ።
አቤት ጌታዬ ለካ ከዚ ከስቃ ልታወጣኝ ፈልገህ ነው ትንሽዋ ጎጆዬን ያፈረስከው ወደ ትልቁ ቤት ልትወስደኝ ነው አለ።
አንዳንዴ የሆነ ነገር ስንጣ ሲበላሽብን ፈጣሪዬንም ሰውንም ስናማርር እንኖራለን ግን ካጣነው ነገር ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን በችግራችን ግዜ መጠጋት ያለብንን እግዚአብሔርን እንረሳልን ከዝያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን አንኮንነዋለን።
ያጣነውን የሰጠን እግዚአብሔር ! አእምሮቻን ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን!
“አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።”
— 1ኛ ሳሙኤል 2፥3
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE |
@CHRIST_TUBESHARE |
@CHRISTFAMILY