https://t.me/combankethofficial/7831ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ በአግባቡ ሊተገብሯቸው የሚገቡ
የጥንቃቄ እርምጃዎች
=========
ደንበኞች እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ኤቲኤም፣ ፖስ፣ ሲቢኢ ብር የመሳሰሉ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚከተሉትን የደህንንት መጠበቂያ ተግባራት ሊተገብሩ ይገባል፡
• የሚስጢር ቁጥርዎን በስልክዎ ውስጥ አለማስቀመጥ፣ በወረቀት ወይም በማስታወሻ ደብተር ላይ አለመፃፍ እና በአጠቃላይ ለሌላ ሰው አለማሳየት ወይም በቀላሉ በሚታይበት ቦታ ላይ አያስቀምጡ፤
• የተንቀሳቃሽ ስልክዎን በተቻለ መጠን ለሌላ ሰው አይስጡ (አያውሱ)፡፡ ነገር ግን ለሌላ ሰው የሚሰጡ ወይም የሚቀይሩ ከሆነ ግን ስልኩ ላይ ያለውን የየዲጂታል ባንክ አገልግሎት መጠቀሚያ መተግበሪያ እና ሌሎች የግል መረጃዎን የያዙ ጽሑፎችንና ኢሜሎችን ያጥፉ፤
• የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ በሚያደርጉት ነገር ላይ ብቻ ያተኩሩ፤ ትኩረትዎን የሚያስተጓጉሉ እንደ ሞባይል ስልክ እና መሰል ነገሮቸን አይጠቀሙ፤
• የኤቲኤም ማሽን ላይ ሲጠቀሙ የሚስጢር ቁጥርዎ እንዳይታይ፤ የኤቲኤም ቁልፍ ሰሌዳውን ሰውነትዎን ተጠቅመው በመሸፈን በቅርብ የቆሙ ሰዎች እንይመለከቱ ይከላከሉ፣ ከግብይት በኋላ ካርዱን መቀበሎን ያረጋግጡ፤
• የተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ የሚጭኗቸውን መተግበሪያዎች ሲያወርዱ አፕስቶር እና ፕሌይስቶርን ብቻ ይጠቀሙ፤
• ደኅንነቱ ያልተረጋገጠ ድረ-ገጽ እና የማኅበራ ሚዲያ ገፆችን አይጠቀሙ፣ አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን (links) አይክፈቱ፤
• ግብይትዎን በሚያካሂዱበት ጊዜ ችግር ቢያጋጥምዎ ከሚመለከታችው የባንኩ ሠራተኞች ውጪ የማንንም እገዛ አይጠይቁ፤
• የሚስጢር ቁጥርዎን በየጊዜው ይቀያይሩ፤
• ተከታታይ የሆኑ ወይም የስልክ ቁጥርዎን የመጨረሻ ዲጂቶች፣ ማንኛውም የግል መረጃ ለምሳሌ የልደት ቀን የሚስጥር ቁጥር አድርገው አይጠቀሙ፤
• በስልክ ምንም አይነት የባንክ መረጃዎን አይስጡ፣
• ሞባይል ሲጠፋብዎ ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እንዲቋረጥ ያስደርጉ፤
• የሚጠቀሙበት ኮምፒዩተር ሁሌም የቫይረስ መከላከያ እንዳለው ያረጋግጡ፤
• ሂሳብዎ ላይ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲኖር ለባንኩ ወዲያውኑ ያሳውቁ፤
• የባንክ አገልግሎት በሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮች እና ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የማይታወቁ መተግበሪያዎችን አይጫኑ፤
• አገልግሎት ካገኙ በኋላ አስፈላጊውን ቅደም ተከተል በመከተል ዘግተው ይውጡ፡፡