Ethio Coronavirus (COVID 19)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


All the latest information updates you need
STAY SAFE YOUR SAFETY IS OUR NUNBER 1 PRIORITY
#ለበለጠ_ትኩስ_መረጃ_የቻናሉ_ቤተሰብ_ይሁኑ
@COVID_19updat

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የታማሚዎች ሁኔታ፦

- በኮሮና ቫይረስ የተያዙት 2 ግለሰቦች የ30 ዓመትና የ36 ዓመት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ በመጋቢት 15/2012 ዓ/ም ወደ ሀገር የገቡ ሲሆን በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን የበሽታውን ምልክት ታይቶባቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- 3ኛዋ ታማሚ የ60 ዓመት እድሜ ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ መጋቢት 6/2012 ዓ/ም ከፈረንሳይ የተመለሱና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ሶስቱም የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

#DrLiaTadesse

@COVID_19updat


#UPDATE

ሁለቱ (2) የቫይረሱ ተጠቂዎች፦

- በአማራ ክልል ባህር ዳር ነዋሪ የሆኑ የ37 ዓመት ሴትና የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የአዲስ ቅዳም ነዋሪ የሆኑ የ32 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

#DrLiaTadesse

@COVID_19updat


2 የኮቪድ-19 ተጠቂዎች አገግመዋል!

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠቂዎች መካከል ሁለት (2) ሰዎች ማገገማቸውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

@COVID_19updat


የኮቪድ-19 ተጠቂዎች 23 ደረሱ!

በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ ሶስት (23) መድረሱን ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ዐቢይ «ከ800 በላይ ሰው እስካሁን ምርመራ ያደረገ ቢሆንም 23 ሰው ገደማ በዚህ ቫይረስ መጠቃቱ ተረጋግጧል» ብለዋል
ከ DW tv
#ለበለጠ_ትኩስ_መረጃ_የቻናሉ_ቤተሰብ_ይሁኑ


@COVID19updat


"ከዛሬ 21/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በመቱ ከተማ የትራፊክ (የትራንስፖርት) እንቅስቃሴ የከተማ ባጃጅ ፣ ከአጎራባች ወረዳ የሚመጡ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ታግዷል።" - አቶ ቀልቤሳ ቶሌራ

@COVID_19updat


Guys ahune new tenachenen metebek

Ye sport ena abelal be nesa .... @uplift_fitness


በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው - 884
• ዛሬ 20/07/2012 በበሽታው የተያዙ - 3
• በአሁን ሰዓት በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 16
• ፅኑ ህሙማን - 1
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 1
• በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ድምር - 19

@COVID_19updat


በኮቪድ-19 የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 19 ደረሰ!

በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 87 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በቫይረሱ የተያዙ ሶስት ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

#MoH

@COVID_19updat


በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ መንገዶች ውስጥ ዋና ዋና ተብለው በተለዩ 13 መንገዶች ላይ ነው የፀረ ተዋህሲያን መድሃኒት ርጭቱ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
#ለበለጠ_ትኩስ_መረጃ_የቻናሉ_ቤተሰብ_ይሁኑ

@COVID_19updat


ከሰላም ሚኒስቴር የተላከ መልዕክት፦

በመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሥም እናመሰግናለን!

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ቦትላንት እና በዛሬው እለት በጎ አድራጊ ወገኖች በሰላም ሚኒስቴር ተገኝተዉ አበርክተዋል፡፡

- ንብ ባንክ የ5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን) ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

- ንብ ኢንሹራንሽ ኩባንያ ለዚሁ ዓላማ የሚውል የ1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን) ብር

- ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ በበኩሉ የ3,500,000.00 (ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) ብር

- የዋን ውኃ አምራች ድርጅት የሆነው አባ ሐዋ ትሬዲንግ የ1ሚሊየን ብር ድጋፍ

- አብሃም ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት 1 ሚሊየን ብር

- አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

- እናት ባንክ 2 ሚሊየን ብር

- አዋሽ ባንክ 10 ሚሊየን ብር

- የኤንስሪ ኤች ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት 1500 ጠርሙስ የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር

- የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የ10,000,000.00 (አስር ሚሊዮን) ብር ድጋፍ በሰላም ሚኒስቴር በኩል አድርጓል፡፡

የሀገርን ጥሪ አክብራችሁ ላደረጋችሁት ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እጅግ እናመሰግናለን!

የሰላም ሚኒስቴር!
#ለበለጠ_ትኩስ_መረጃ_የቻናሉ_ቤተሰብ_ይሁኑ

@COVID_19updat






#DrLia_Tadesse

አንድ (1) ሰው ከኮሮና ቫይረሱ ማገገሙን የጤና ሚንስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ ባወጡት መረጃ አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው - 797
• በአሁን ሰዓት በለይቶ ማቆያ ያሉ - 13
• ፅኑ ህሙማን - 0
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 1
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 16
#ለበለጠ_ትኩስ_መረጃ_የቻናሉ_ቤተሰብ_ይሁኑ

@COVID_19updat


Ethio Coronavirus (COVID 19):
የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የተላለፈው መልእክት ላይ የተለያዩ ብዥታዎች ታይቷል ።
ነገር ግን የምርምሩን ሂደት በድጋሜ ለመግለጽ እንወዳለን

የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱ ለማከም የሚያስችል መድሀኒት የመጀመሪያ የቤተ ሙከራ መሰረታዊ የምርምር ሂደት ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ በስኬት አልፏል፡፡

ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን የመጀመሪያ ምርምር ሂደትን አልፎ ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ስራዎች እንዲሸጋገር ተደርገዋል።


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና ከኢትዮጵያዊያን የባህል ሃኪሞች ጋር እና የህክምና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን የሀገር በቀል እውቀቶችን በሳይንሳዊ ሂደቶች በማሳለፍ ለዘመን አመጣሹ ኮሮና ቫይረስ( ኮቪድ -19) ወረርሽኝ ለማከም መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ መድሃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

ወደቀጣይ የምርምር ሂደት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን ሙሉ መልእክቱን በትላንትናው እለት ባያያዝነው ቪዲዮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ሌሎች ተጨማሪ የምርምሩ ሂደት መረጃዎችንም በቀጣይ የምንገልጽ ይሆናል።

#ለበለጠ_ትኩስ_መረጃ_የቻናሉ_ቤተሰብ_ይሁኑ

@COVID_19updat


በስተመጨረሻም ደስ የሚል ዜና👆👆👆👆

#ለበለጠ_ትኩስ_መረጃ_የቻናሉ_ቤተሰብ_ይሁኑ

@COVID_19updat


Ethio Coronavirus (COVID 19):

#ጥንቃቄ_ይደረግ...! አስቸኳይ ስለሆነም ለፈጣሪ ብላችሁ #ሼር_ሼር_ሼር አድርጉት😭
እባካችሁ እባካችሁ ....ጥንቃቄ ይደረግ
ኮሮናን ለመከላከል በሚል አልኮል የተቀባ እጅ እሳት ያለበት አካባቢ መገኘቱ አደገኛ ነው።

ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን ኮሮናን ለመከላከል በሚል አልኮል የተቀባ እጇን ባለማወቅ እሳት አካባቢ በማስጠጋቷ ጉዳት ደርሶባታልና እባካችሁ ላልሰማ አሰሙ ጥንቃቄም አድርጉ! ነግ በኔ ይባላልና ላልሰሙት ሼር✔
#ለበለጠ_ትኩስ_መረጃ_የቻናሉ_ቤተሰብ_ይሁኑ

@COVID_19updat


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአውሮፕላን ተሳፋሪዎችን የሚወስድበት አውቶቡስ ጉዳይ ይታሰብበት። አሁን የአገር ውስጥ በረራ ነው የምሰራው ብሎ መዘናጋት ይቅር። ይህ የትላንት ምሽት ፎቶ ነው።

#ለበለጠ_ትኩስ_መረጃ_የቻናሉ_ቤተሰብ_ይሁኑ

@COVID_19updat


#Thanks_for_all_who_contributed!!!!

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያቀረበው ጥሪ ተከትሎ በዛሬው እለት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡

በዚህም ፦

1. አርቲስት ቴዲ አፍሮ 1.2 ሚሊዮን ብር
2. ታፍ ኦይል 2 ሚሊዮን ብር
3. VSO 1.2 ሚሊዮን ብር
4. አማጋ ኃ/የተ/ግ/ማ 1 ሚሊዮን ብር
5. ለገሃር ሳይት ኮንትራክተርስ 3 ሚሊዮን ብር
6. ካን ቤቢ ዳይፐር 500 ሺ ብር
7. GMM ጋርመንት ኃ/የተ/ግ/ማ 500 ሺ ማስክ
8. ሚአን አግሮ ኢንዱስትሪ 20 ሺ ብር
9. የወልዋሎ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ 30 ሺ ብር
10. አንበሶ ወ/ገብርኤል መኖሪያ ቤታቸውን
11. ኢትዮጲስ ኮሌጅ ኮሌጃቸውን
12. ቤተልሄም ጥላሁን የመስርያ ቦተታቸውን
13. ውብሸት ተክሌ ዋቅጂራ ህንጻቸውን
14. አስራት ካሳዬ ሆቴላቸውን
15. ቫኮም ኢንጂነሪንግ 5 ኩንታል እህል
16. ካህናት አለምአቀፍ ቤ/ክርስቲያን የአምልኮ ስፍራ
17. ሂንዲያን ትምህርት ቤት ት/ቤታቸውን
18. ሄኖክ ፣ ፍትሃዊና ተመስገን እህልና የንጽህና መጠበቂያ
19. አድዋ ዱቄት ፋብሪካ 13ሺ ካሬ ስፋት ያለው አዳራሽ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበውን ጥሪ ተከትለው ድጋፍ እያደረጉ ላሉ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡


#UPDATE

ባህላዊ ሕክምናን ከዘመናዊ ሕክምና ጋር በማቀናጀት ለኮሮና ቫይረስ መድኃኒት ለማግኘት የምርምር ሥራ እየሠራ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የምርምር ሂደቱ ተስፋ ያለው መሆኑንም ነው የጤና ሚኒስቴር የገለጸው።
#ministry_of_health_ethiopia
#etv

@COVID_19updat


ዶክተር ሊያ ታደሰ፦

"የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ባዘጋጀው የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) መከታተያና መቆጣጠሪያ መረብ ሲስተም ላይ በትናንትናው እለት በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 20 ተብሎ የተጠቀሰው በስህተት መሆኑን እያሳወቅን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 12 መሆኑን እናረገግጣለን።"

@COVID_19updat

Показано 20 последних публикаций.

330

подписчиков
Статистика канала