🔹የራስን ስህተት እያቃለሉ የሌሎችን ስህተት መለቃቀምና ማግዘፍ መንሐጅ ሰለፍ አይደለም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
👉 የዘመኑ ዘመናዊ ሙሪዶች የራሳቸው ስህተት አይታያቸውም የሚወዷቸው ሰዎችም ችግር እንዲወራ አይፈልጉም ፣ ስህተታቸውን ቁልጭ አድርገህ ብታሳያቸው ከስህተታቸው ከመመለስ ይልቅ ለምን እነ እከሌስ የእነሱ ስህተት ለምን አይነገርም ይሉሀል አልያም ትልልቅ ስህተቶች እያሉ ትንንሹን ለምን ትለቃቅማለህ ይላሉ ሱብሃ ረቢ ‼
👉 ጥቃቅን ስህተት የሚሉት እውነት ስህተቱ አነስተኛ ሆኖ ሳይሆን ስህተቱ እነሱ ላይ ስለተገኘ ነው ፣ ሌላው ላይ ከተገኘ ከባድ አደገኛ አጥፊ ወንጀል ሲሆን እነሱጋ ሲሆን ግን ተራ ስህተት ይሆናል
👉 ሰለፎች ከምንም በላይ የራሳቸው ሁኔታ ያሳስባቸው ነበር ፣ ስለሆነም ሁልግዜ ነፍስያቸውን ይተሳሰቡ ነበር። የነርሱን ነውር የነገራቸውን ሰው ዱአ ያደርጉለት ነበር
وكان عمر بن الخطاب رضي الله عنه يقول: "رحم الله امرأً أهدى إلي عيوبي"
ኡመር ቢን አል ኸጣብ እንዲህ ይሉ ነበር
[ነውሬን ለነገረኝ ሰው አላሁ ተአላ ይዘንለት ]
👉 ሰለፎች ወንጀልን አግዝፈው ነበር የሚመለከቱት
عنْ أَنَس قالَ: "إِنَّكُمْ لَتَعْملُونَ أَعْمَالًا هِيَ أَدقُّ في أَعْيُنِكُمْ مِنَ الشَّعَرِ، كُنَّا نَعْدُّهَا عَلَى عَهْدِ رسولِ اللَّهِ ﷺ مِنَ الْمُوِبقاتِ" رواه البخاري
[አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላሉ
እናንተ የምትሰሩትን ስራ ከፀጉረችሁ አሳንሳችሁ የምትመለከቱትን እኛ በነብያችን ዘመን ከባድ አጥፊ ወንጀል አድርገን እንቆጥረው ነበር ] የቡኻሪ ዘገባ
👉 ሰለፎች አቋማቸው እንዲህ ሆኖ ሳለ ዛሬ ላይ ግን ለራሳችን ሲሆን በራሳችን ላይ ሲመጣብን ሀቅን ከመያዝ ይልቅ የተለያዩ ማስተባበያዎች ስንደረድር እንስተዋላለን
👉 🟣 የለተሞ ሸይኽና ሙሪዶቻቸው ከወደቁባቸው የመንሐጅና የስነምግባር ችግሮች መሀከል በጥቂቱ
① ቢድአ የሰራን ሙብተዲእ እንለዋለን የሚል አደገኛ የሀዳዲያ ቃኢዳን መናገራቸውና ተግባራዊም ማድረጋቸው ነው
② ከሀዳዲያ መንሐጅ መገለጫ አንዱ በሆነው ሰዎችን በተሰልሱል ከመንሐጅ አሰለፍ ማስወጣታቸው
③ የተለያዩ የቢድአ ንግግሮችን መናገራቸው
~ የሰዎችን የአቂዳ ደረጃ በፐርሰንት መመደባቸው
~ በኢስላም ታላቅ ደረጃ ባለው ምፅዋት ሰደቃ ላይ መቀለዳቸው
~ ሙስሊምን ከካፊር ጋር ማመሳሰላቸው
~ ወደ አላህ መቃረቢያ ከሆነው አንዱ
በተውበት ላይ ማሾፋቸው
④ መስአላ ፊቅሂያ በሆነ ነጥብ ላይ ሰዎችን በተብዲእ መፈረጃቸው
⑤ ተሳዳቢ ፣ ተራጋሚ ፣ ተዛላፊ መሆናቸው
⑥ መስፈርቱ ባልተሟላ ሁኔታ በተብዲእ ላይ መሰማራታቸው
⑦ ከሂዝብያ መሰረትና መገለጫ በሆነው ውሸት ላይ መዘፈቃቸው
~ ተውሂድ አያስተምሩም
~ ሽርክና ቢድአን አያስጠነቅቁም
~ አዲስ ዲን ይዘው መተዋል
~ ከቢድአ ሰዎች ጋር አንድ ሆነዋል
~ ስለ ጠመሙ አንጃዎች ላለማውራት ስምምነት ፈፅመዋል ።
👉 🟣 በእውነቱ የሚቀጥፏቸው ቅጥፈቶች ብዙ ናቸው ብልህ ለሆነ አንድ ጥቆማ ብቻ በቂው ነው ።
⑧ እርማት የሚያስፈልገውን ፈትዋቸውን እያወቁ እስከነ ስህተቱ ማሰራጨታቸው
⑨ ውስን በሆኑ የኢጅቲሐድ መስአላ ላይ የተቃረኗቸውን ሱኒ ወንድሞች ከየሁዳና ነሳራ የባሱ ናቸው ብለው መፈረጃቸው
👉 ይህንና ይህን የመሰሉ ከባባድ ስህተቶች ቀላልና ተራ ስህተቶች ተደርገው ይቆጠራሉ ፣ ተራ ትችት ብለው ያጣጥላሉ ፣ ደግሞ ራስ ምታታቸው ሲጨምር ሰው የመንሐጅ ርዕስ እያወራ ስለ አረብኛ አፃፃፍ ስህተት ያወራሉ እያሉ ርዕስ ያስቀይሳሉ የዚህ ሁሉ ምክንያቱ እነዚህ አደገኛ የሆኑ ስህተቶች የተገኙት በእነሱ ጉያ ስር ስለሆነ ብቻ ነው ።
👉 እነዚህንና ሌሎችንም የመንሐጅና የስነምግር ችግራቸውን ከነድምፁ አያይዤ ከዚህ በፊት በተለያየ ርእስ ላይ ለቅቄዋለው ማረጋገጥ የፈለገ ድምፆቹን ማግኘት ይችላል
👉 ሰለፍያን የሞገተ ሁሉ ሰለፊ አይደለም፣ ለሰለፍያ የተቆረቆረ ሁሉ ትክክል ነው ማለት አይደለም
ኢንተቢሁ‼
T.me/dawudyassin