እናስተዋውቅዎ!
ውድ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾቻችን ተከታዮች በዛሬው የእናስተዋውቅዎ ጽሑፋችን የምናስተዋውቃችሁ በምክትል ፕሬዝዳንት ኢንዱስትሪ ፋይናንሲንግ ዘርፍ በኢንዱስትሪ ክላስተር ከተቋቋሙት የደንበኞች ግንኙነት ማኔጅመንት /CRM/ 5 ክፍሎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የፉድ ኤንድ አግሮ ፕሮሰሲንግ ዳይሬክቶሬት /Food and Agro Processing Directorate/ ይሆናል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ ምን? ምን? ዋና ዋና ሥራዎችን ያከናውናል? የሚለውን ከክፍሉ ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ከበደ መረጃ በመውሰድ አሰናድተንላችኋል፡፡
የክፍሉ ዋና ሥራ የደንበኞች ግንኙነት እንደመሆኑ ቀጥታ ግንኙነታቸው ከደንበኞች ጋር ሲሆን፣ ለደንበኞች ብድር ከመስጠትና ብድር ከመሰብሰብ ጋር የተገናኙ ሥራዎች ይሠራሉ፡፡ ዳይሬክቶሬቱ በዋናነት ከሚሠራቸው ሥራዎች መካከልም፡-
ኢንትግሬትድ አግሮ ፕሮሰሲንግ /integrated Agro-processing/፤ የእንስሳት መኖ፣ የወተት እና ወተት ተዋጽዖ፣ ስታርች እና ግሉኮስ ምርት፣ ፉድ ፕሮሰሲንግ /food processing/፤ ዳቦ ቤት፣ የጣፋጭ ምግብ ማምረቻዎች፣ ዘይት መጭመቂያዎች፣ ቡና እና የመሳሰሉት፣ ሊከር ኤንድ ቢቨሬጅ /liquor and beverage/፤ የታሸገ ውሃ፣ ለስላሳ መጠጦች፣ አልኮል ነክ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ መጠጦች ላይ የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን የብድር አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ደንበኞች ለብድር አገልግሎት ወደ ባንኩ ሲመጡ ሰነዶች በሚፈለገው ጥራትና ቁጥር ልክ ይዘው መቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ያልተሟላ ሰነድ ይዞ የሚቀርብ ደንበኛ መመላለሶች ሊገጥሙት እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም ደንበኞች ጥናት የሚያደርግላቸውና ሰነድ የሚያደራጅ ባለሙያ ሲመርጡ ልምድና ብቃት ያለው ባለሙያ ቢያሠሩ ያለምንም ችግር አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛቸዋል፡፡
ደንበኞች የሚፈለግባቸውን መስፈርቶች ባንኩ በሚፈልገው የጥራት ደረጃ አሟልተው እስከመጡ ድረስ ሁሉንም እኩል የሚያስተናግድ ሲሆን ከተለያዩ ምንጮች የተዛቡ መረጃዎችን ከውጭ በመስማት እንዳይታለሉ መጠንቀቅና ተጨማሪ መረጃዎችን በባንኩ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃና ትክክለኛውን አሠራር ለመረዳት ወደ ባንኩ በአካል በመምጣት የሚመለከተውን አካል ማነጋገር አልያም የባንኩን ትክክለኛ የማኅበራዊ ድኅረ ገጾች ላይ ብቻ የሚለቀቁ መረጃዎችን ብቻ እንደ መረጃ ምንጭ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሠራር በአንድ ሰው ብቻ የሚወሰን ውሳኔ የሌለ በመሆኑ ሁሉም ብድር ሂደቱን፣ አሠራሩና ደረጃውን ጠብቆ በሚመለከታቸው ክፍሎችና ኃላፊዎች እየታየ ውሳኔ እየተሰጠበት የሚያልፍበት ሂደትን የሚከተል በመሆኑ ደንበኞች ይህንኑ አሠራር ተከትለው ጉዳያቸውን ማስፈፀም ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
ዌብሳይት፡-
www.dbe.com.etፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/dbethiopiaቴሌግራም፦
https://t.me/DBE1900ትዊተር፡-
https://twitter.com/DBE_Ethiopiaሊንክድኢን፡-
https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ዩቱብ:-
https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopiaየኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!