ድንህ ህይወትህ ነው


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"ድንህ ህይወትህ ነውና ከምንጩ ጥለቅ፤ ጭፍን ወገንተኝነትንና ሰዎችን ያለአግባብ መውደድህ ሐቅን እንዳይጋርድብህ ተጠንቀቅ

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ነገ ጁሙዐህ ሻዕባን 1/1446 ዓ.ሂ.
ለረመዷን 30 ወይም 29 ቀናቶች ይቀሩናል ማለት ነው።
የረመዷን ቀዷእ ያለባቸው በፍጥነት ለማጠናቀቅ ሞክሩ
አሏህ ረመዷንን በሰላም ያድርሰን !!

t.me/dinhhiwothnew


Репост из: Yusuf App
•የአፑ ይዘት በከፊል


Репост из: Yusuf App
ሪያዱ ሷሊሒን ቁጥር 3_1.0.apk
399.2Мб
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」
  
    ╭──────╮
╭📲 ቁጥር ➌
│ ╰──────╯
│❏ ሪያዱ ሷሊሒን رياض الصالحين

ከክፍል 129-መጨረሻው
╰────────────────╯   
╭🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├────⟢
│🎧 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
╰──────────────
╭⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

├🖇http://t.me/Yusuf_App1
╰─╼───────────────╯


Репост из: Yusuf App
ሪያዱ ሷሊሒን ቁጥር 2_1.0.apk
401.0Мб
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」

    ╭──────╮
╭📲 ቁጥር ➋
│ ╰──────╯
│❏ ሪያዱ ሷሊሒን رياض الصالحين

│ ከክፍል 65-128
╰────────────────╯   
╭🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├────⟢
│🎧 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
╰──────────────
╭⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

├🖇http://t.me/Yusuf_App1
╰─╼───────────────╯


Репост из: Yusuf App
ሪያዱ ሷሊሒን ቁጥር 1_1.0.apk
370.3Мб
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」
  
    ╭──────╮
╭📲 ቁጥር ➊
│ ╰──────╯
│❏ ሪያዱ ሷሊሒን رياض الصالحين

ከክፍል 01-64
╰────────────────  
╭🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├────⟢
│🎧 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
╰──────────────
╭⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

├🖇http://t.me/Yusuf_App1
╰─╼───────────────╯


Репост из: Yusuf App
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」

╭┄┈┈
ሪያዱ ሷሊሒን رياض الصالحين

│🎙የደርሱ አቅራቢ »
│⚊⚊
│» ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
╰─────────────────╯
🏷በ3 አፕሊኬሽን ተዘጋጅቶ የቀረበ
╭𑁍──────────────
│➺ቁጥር 1 ከክፍል 01-64
│🖇 https://t.me/Yusuf_App1/550
├𑁍──────────────

│➺ቁጥር 2 ከክፍል 65-128
│🖇 https://t.me/Yusuf_App1/551
├𑁍──────────────

│➺ቁጥር 3 ከክፍል 129-መጨረሻው
│🖇 https://t.me/Yusuf_App1/552
╰𑁍──────────────

  ⎙   አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ!
  ↻ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
   ⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀሉን
𑁍
   http://t.me/Yusuf_App1


ያለንበትን ህይወት ማማረርም ይሁን መጥላት ካለንበት ችግር ቅንጣት አይቀይርልንም ። ምስጋና እና ዱዓእ ነው ሊቀይረው የሚችለው። በተሰጠን ጸጋ ከልባችን አመስጋኞች እንሁን፣ የምንፈልገውንም ይሁን ያጣንውን ጌታችን እንደሚሰጠን እርግጠኞች ሁነን ዱዓእ እናድርግ !

http://t.me/dinhhiwothnew




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በአፍንጫ ሀሳስያ የምትሰቃዩ ወንድሞችና እህቶች

እስኪ ሞክሩት አላህ ሰበብ ቢያደርግላችሁ

t.me/dinhhiwothnew


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቢግ ባንግ.pdf
2.0Мб
መፈንቅለ ቢግባንግ
-
ከ 5 አመት በፊት በ2009 የቢግባንግ ንድፈ ሐሳብን በተመለከተ የከተብኩት ፅሁፍ ነው፡፡ ከ 170 በላይ ገፆች አሉት፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ኢንተረስቱ ያላችሁ መፅሐፉን ካያያዝኩት ሊንክ በማውረድ በትዕግስት ታነቡት ዘንድ እጋብዛለሁ።
=
ቃል አሚን ተስፋዬ


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
መውሊድ በማን ተጀመረ?
~
የመውሊድ ደጋፊዎች ከሚያነሷቸው ነጥቦች አንዱ መውሊድ “ታላቅ ዓሊም፣ ተቂይ፣ ሷሊሕና ጀግና በነበሩት” ንጉስ ሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚል ነው። ሙዞፈር የሞተው በ630 ሂጅሪያ ነው። ሰዎቹ ሙዞፈር ላይ ችክ የሚሉት እጅግ አፈንጋጭ በሆኑት “ፋጢሚያ” ሺዐዎች ነው የተጀመረው የሚለውን ለመሸሽ ነው። ነገር ግን በነዚህ ሺ0ዎች እንደተጀመረ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ማስረጃዎች በጨባጭ አሉ። ለሐቅ እጅ ለሚሰጡ፣ ከመንጋዊ አስተሳሰብ አግልለው ህሊናቸውን ለሚያከብሩ ሰዎች ብቻ ማስረጃዎቹን አሰፍራለሁ።

1. ኢብኑል መእሙን (587 ሂ.):—

በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መውሊድ ተጠቅሶ የተገኘው በኢብኑል መእሙን ስራ ነው። የኢብኑል መእሙን አባት የ“ፋጢሚያ” ንጉስ ከፍተኛ ባለሟል ነበር። የታሪክ ፀሐፊው አልመቅሪዚ (845 ሂ.) ኢብኑል መእሙንን በማጣቀስ በ517 ሂጅሪያ የተካሄደውን መውሊድ አስመልክተው እንዲህ የሚል መረጃ አስፍረዋል፡-
“የ‘ፊጢሚያ’ ገዢዎች በዓላትና ለተገዢዎቻቸው ነገሮችን ሰፋ የሚያደርጉባቸው እንዲሁም ችሮታ የሚበዘባቸው ዓውደ-አመታት” ካሉ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- ለፋጢሚያ ገዢዎች በአመቱ ውስጥ በዓላትና ዓውደ አመታት አሏቸው። እነሱም … የዓሹራእ ቀን፣ የነብዩ ﷺ ልደት (መውሊድ) ቀን፣ የዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ ልደት ቀን፣ የሐሰን የልደት ቀንና የሑሰይን የልደት ቀን (ሰላም በነሱ ላይ ይሁንና)፣ የፋጢመቱ ዘህራእ ዐለይሃ ሰላም ልደት ቀን፣ ስልጣን ላይ ያለው ገዢ የልደት ቀን፣ … የገዲር ዒድ (የሺዐዎች ነው)” እያሉ ይዘረዝራሉ። ከውስጣቸው የፋርስ መጁሳዎች፣ የሺዐና ከክርስትና ደግሞ እንደ ገና እና ትንሳኤ ያሉ በዓላት የተካተቱበት ሲሆን ባጠቃላይ 28 በዓላት ናቸው የተዘረዘሩት። [አልኺጦጥ፡ 1/436]
መውሊድ ከምን አይነት በዓላት ጋር እንደተጀመረ ተመልከቱ። በሌላ ኪታባቸው ላይም “በረቢዐል አወል ላይ (የ“ፋጢሚዮቹ” ንጉስ) ሌሊት ላይ በጎዳናዎችና መንገዶች ላይ ጧፎች እንዲበሩ ያስገድድ ነበር” ይላሉ። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 2/48] ሌላ ቦታ ደግሞ “ረቢዐል አወል ላይ የነብዩን ﷺ ክቡር ልደት መፈፀም ብሄራዊ ልምድ ሆኖ ቀጠለ” ይላል። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 3/101] ልብ በሉ! ይህንን መረጃ የሰጠን ኢብኑል መእሙን የሞተው መውሊድን ጀመረ የሚባለው ንጉስ ሙዞፈር ገና በተሾመ በአመቱ ነው፡፡ እያስተዋላችሁ!!

2. ኢብኑ ጡወይር (617 ሂ.):—

ሌላኛው መውሊድን ከ“ፋጢሚዮች” ጋር በማያያዝ የጠቀሰው ጥንታዊ የታሪክ ፀሐፊ ኢብኑ ጡወይር ነው። ኢብኑ ጡወይር ለነዚህ “ለፋጢሚያ” መንግስት ፀሐፊ ሆኖ አገልግሏል። ኋላ በሶላሑዲን አልአዩቢ ሲደመሰሱም በአይኑ ተመልክቷል። በዚህኛው ስርኣትም ውስጥ ዳግም አገልግሏል። በ“ፋጢሚያዎች” መንግስት ስለሚዘጋጀው መውሊድና ስለተትረፈረፈ ምግቡ “ኑዝሀቱል ሙቅለተይን ፊ አኽባሪ ደውለተይን” በተባለ ኪታቡ ላይ በዝርዝር አትቷል። “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” ይላል ያገራችን ሰው። ለናሙና ያክል ቀንጨብ ላድርገው፡-
ذكر جلوس الخليفة في الموالد الستة في تواريخ مختلفة، وما يطلق فيها، وهي مولد النبي صلى الله عليه وسلم، ومولد أمير المؤمنين علي بن أبي طالب، ومولد فاطمة عليها السلام، ومولد الحسن، ومولد الحسين عليهما السلام، ومولد الخليفة الحاضر
“ኸሊፋው በተለያዩ ጊዜያት በስድስቱ መውሊዶች ላይ የሚያደርጋቸውን መስሰየምና ምን ተብለው እንደሚታወቁ ማውሳት፡- እነሱም የነብዩ ﷺ መውሊድ፣ የአሚረል ሙእሚኒን ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ መውሊድ፣ የፋጢማ ዐለይሃ ሰላም መውሊድ፣ የሐሰን መውሊድ፣ የሑሰይን - ዐለይሂመ ሰላም - መውሊድና የዘመኑ ኸሊፋ መውሊድ ናቸው፡፡ …” [ኑዝሀቱል ሙቅለተይን፡ 217-219]

3. አሕመድ ብኑ ዐሊይ አልቀልቀሸንዲ (821 ሂ.):—

ስለ “ፋጢሚያ” መሪዎች ጉባዔ ሲያወሩ “ሶስተኛው ጉባዔ በረቢዐል አወል ወር 12ኛ ቀን ላይ በነብዩ ﷺ መውሊድ ላይ የሚኖረው ጉባዔ ነው” ካሉ በኋላ ዝርዝር አፈፃፀሙን ይተርካሉ፡፡ [ሱብሑል አዕሻ፡ 3/576]

ስናጠቃልል የመውሊድ በዓል ጀማሪዎች “ፋጢሚያ” ሺዐዎች እንደነበሩ ለጥርጣሬ ቀዳዳ የማይሰጡ መረጃዎች አሉን ማለት ነው፡፡ ልብ በሉ! የመጨረሻው የ“ፋጢሚዮች” ንጉስ አልዓዲድ ሊዲኒላህ የሞተው በ 567 ሂጅሪያ ነው፡፡ ሱፍዮች “መውሊድ ጀመረ” የሚሉት ሙዞፈር የተሾመው ደግሞ ከ19 ዓመታት በኋላ በ586 ሂ. ነው፡፡ ይህንን ተጨባጭ ታሪካዊ መረጃ እያየ “አይኔን ግንባር ያርገው” የሚል ካለ የለየለት ቂላቂል ነው፡፡ መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ የሚጠቁሙ ግልፅ ማስረጃዎች እየቀረቡ እያዩ “እከሌ እንዲህ ብለዋል” “እንቶኔ እንዲህ ብለዋል” እያሉ ነገር መዘብዘብ ራስን መሸወድ ብቻ ነው፡፡
“ሙዞፈር ነው የጀመረው” ያሉት እንደ ሲዩጢ ያሉ የኋለኛው ዘመን ሰዎች ከመሆናቸውም በላይ ያጣቀሱት ተጨባጭ ማስረጃ የለም፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህ መውሊድ በሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚሉ አካላት ኢብኑ ከሢርን ሲያጣቅሱ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ኢብኑ ከሢር የሙዞፈርን መውሊድ ከመጥቀሳቸው ውጭ “ጀማሪ ነው” አላሉም፡፡
መቅሪዚ እንደጠቀሱት እነዚህ የሺዐዎቹ መውሊዶች ኋላ ላይ ለተወሰኑ ጊዜያት ተቋርጠው ነበር፡፡ [አልመዋዒዝ ወልኢዕቲባር፡ 1/432] ኋላ ላይ በተተካው የ“ፊጢሚዮቹ” ንጉስ አልኣሚር ቢአሕካሚላህ (524 ሂ.) ነው የተጀመሩት፡፡ ልብ በሉ! ይህ ዳግም የተጀመረው መውሊድ እራሱ ከሙዞፈር መውሊድ በዓል ብቻ ሳይሆን ከራሱ ሙዞፈር መወለድም የቀደመ ነው፡፡
በነገራችን ላይ ሱፍዮች መውሊድን ጀመረ የሚሉትን ሙዞፈርን ቅዱስ አድርገው የሚጠቅሱት ወይ ታማኞች ስላልሆኑ ነው፡፡ ወይ ደግሞ በሰውየው ላይ የቀረቡ ሂሶችን ያልተመለከቱ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የሚያደርጉት ለገበያቸው የሚሆናቸውን እየመረጡ ማቅረብ ነው፡፡ ንጉሱ በከፊል የታሪክ ፀሐፊዎች ከመወደሱም ጋር የሰላ ሂስ የሰነዘሩበትም አሉ፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡-
ያቁት አልሐመዊ ይባላሉ፡፡ በ626 ሂ. የሞቱ ታዋቂ የታሪክ ምሁር ናቸው፡፡ ሙዞፈርን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡-
“የዚህ ሰውየ ባህሪ እርስ በርሱ የሚቃረን ነው፡፡ እሱ ሲበዛ በዳይ፣ ህዝቦቹ ላይ ጨካኝ እንዲሁም አግባብ ባልሆነ መልኩ ገንዘቦችን የሚወስድ ነበር፡፡ ይህ ከመሆኑ ጋር ለድሃዎች የሚቸርና ለእንግዶች በብዛት የሚሰድቅ ነበር፡፡ እጅግ በርካታ ገንዘቦችን አፍስሶ ከከሃዲዎች እጅ ምርኮኞችን ነፃ ያወጣ ነበር፡፡ በዚህ ላይ ባለቅኔው እንዲህ ይላል፡-

‘ልክ እንደዚያች ወጥ ረገጥ
በብልቷ ነግዳ ለበጎ ስራ የምትሮጥ
መስሚያ ካለሽ ወዮ ላንቺ!
ምፅዋትሽ ይቅር ይልቅ አትዘሙቺ፡፡’ ” [ሙዕጀሙዑል ቡልዳን፡ 1/138]

ያቁት አልሐመዊ ከሙዞፈር ጋር አንድ ዘመን የኖሩ በመሆናቸው ዘግይተው መጥተው ስለ ንጉሱ አድናቆት ብቻ ከሰፈሩ ፀሐፊዎች በተሻለ ምስክርነታቸው ሚዛን የሚደፋ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሙዞፈር ፃድቅ እንኳ ቢሆን፣ አይደለም እንጂ መውሊድ በሱ የተጀመረ ቢሆን እንኳ ይሄ ከቢድዐነት አያወጣውም፡፡ ከነቢዩ ﷺ ህልፈት በኋላ ስድስት መቶ አመታት ዘግይቶ የሚጀመር አዲስ ፈሊጥ ጥመት እንጂ ፈፅሞ ፅድቅ ሊሆን አይችልም፡፡ እምነታችን ከቁርኣንና ከሐዲሥ የሚቀዳ እንጂ እንደ ሌሎች እምነቶች ማንም እየተነሳ አዳዲስ ነገሮችን የሚለጥፍበት አይደለም፡፡
=
https://t.me/IbnuMunewor


የዓሹራን ፆም እንድንፆመው

አሏህ ከወፈቀን የዘንድሮው የዓሹራእ ዕለት የሚውለው ከነገ በኋላ ዕለተ ማክሰኞ ሐምሌ 09/2016 ነው።

ይህን ዕለት ማለትም የዓሹራእን አስረኛውን ቀን በፆም ማሳለፍ የአንድ ዓመት ወንጀልን ያስምራል።

ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንድህ ብለዋል
« የዓሹራእን ዕለት መፆም የአንድ ዓመት ወንጀልን ያስምራል፤
አስረኛውን ቀን ( ዓሹራእን )ብቻውን መፆም አይጠላም »
الفتاوى الكبر ى ٣٧٨/٥

መፆም የሚችል ዘጠነኛውን እና አስረኛውን ዕለት ቢፆም ይበልጥ ይወደድለታል። መፆም የማይችል ሰው ግን አስረኛውን ቀን ብቻ ቢፆም ጾሙ ትክክል ነው የአንድ ዓመት ወንጀሉም ይማርለታል ከተባለው ውስጥ ይካተታል።

አሏህ ለመፆም ይወፍቀን፣ተቀባይነትም ያለው ያድርግልን !
Ibnu Seid ✍
t.me/dinhhiwothnew


በሒጅራው አቆጣጠር ዛሬ
ዕለተ እሁድ ሙሐረም 1/1/1446ዓ.ሂ.ነው
አድሱን ዓመት ምክንያት በማድረክ የምናከብረው ምንም ዓይነት በዓል ባይኖርም አሏህ ዓመቱን የሰላም የጤና የተቅዋ... እንዳደርግልን እንለምነዋለን !
✍ Ibnu Seid

t.me/dinhhiwothnew


ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ
« ከዱንያ የተፈቀደልን ያዝ ከእሷም እጣህን አትርሳ፤ ነገር ግን በእጅህ ላይ አድርጋት በልብህ ውስጥ አታድርጋት » ይላሉ
شرح رياض الصالحين ٣٦٩/٣
__ __
ዱንያ፦ አኼራችንን ለመገንባት የምንሸጋገርባት አጭር ድልድይ ናት ።በዱንያ ውስጥ ስንኖርና አኼራን ለማሳካት ሲባል ሐላል የሆኑ ነገሮችን መጠቀምና አኼራችንን የማያስረሱን ህይወትን መኖር አስፈላጊና መሰረታዊ ነው።ዱንያን ብቻ በማሳደድ አኼራን መርሳትና ሁሌም ለዱንያ ብቻ መጨነቅ ግን ትልቅ የሆነ አደጋና አኼራንም ዱንያንም ሊያሳጣን የሚችል ተግባር ነው።
✍ Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew


ምርጧ ሚስት ማለት፦

የአሏህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ
«  ከሴቶች ምርጧ ( በላጯ) ሴት፦
ስትመለከታት የምታስደስትህ፣
በምታዛት ጊዜ የምትታዘዝህ( እሽ የምትልህ)
ከእሷ በራክ ጊዜ እራሷንና ገንዘብህን የምትጠብቅልህ» ነች
           [ ሶሒሑል ጃሚዕ 3299]
    _    __  _

ሚስትነት ከባድ ሀላፍትና ነው በተለይም አማኝና ጌታዋን ለምትፈራዋ  እንስት።
አማኟ እህቴ ሆይ ! ውጭ ላይ የምታያቸው ዱንያዊ ነገሮች፣የፈረንጆችና የካ^ፊ°ሮች መጥፎ ባህልና ልምዶች ፣..... ድንሽን እንዳያስረሱሽ፣የሴትነት ክብርሽንም እንዳያሳጡሽ ።
✍ Ibnu Seid

t.me/dinhhiwothnew


🔴 رفقا بالرجال   
-- معظم النساء لا تعرف قيمته الا بعد فقدانه
-- اذا كانت الام تحمل أطفالها 9 اشهر في احشائها فالاب يحملهم في عقله وقلبه العمر كله.
--فالعالم بأسره بخير مادام الأب بخير
-- احترموا كل رجل أو اب في حياتكم فأنتم لن تعلموا ابدا كم التضحيات التي يبذلها
-- ارحموه لأنكم لن تعوضوه اذا ذهب
-- تمسكوا به لا تتركوه اذا ضاقت عليه الدنيا وضغطت عليه هموم الحياه فهو بشر
-- تحية لكل رجل (الأب.... الأخ... الزوج... الابن)
يا أيتها الزوجة توددي لزوجك بالاسلوب الحسن والكلام الطيب ...ابتسمي في وجه حين يدخل المنزل ...العالم في الخارج متوحش ومتعب ولا تدرين كيف يأتي بلقمة العيش في هذة الأيام الصعبة ..
كانت أمّي تقول لنا دائمًا: إضحكوا في وجهِ أبيكم عندما يعودُ إلى البيت، فالعالمُ في الخارجِ موحشٌ يُحطم الآباء."
عندما مات أبي تحطم الجدارُ الذي يفصلني عنِ العالم الموحشّ ، علمتُ حقاً أني فقدتُ سَندي فقدتُ ذلكَ الرجُل الذي يغزو الشيبَ شبابةُ ....
أحنُ لأبي.....

منقول
t.me/dinhhiwothnew


ሐላል የትዳር አጋሬ ነው በሚል ምክንያት በክላሳችሁ ብቻ የምትፈጽሙትን ጉዳይ በኢሞም ይሁን በዋትሳፕ በሌሎችም ፕላትፎርሞች የምትልኩ እህቶች ጥፋትንና ውርዴትን በፍላጎታችሁ እንደፈጸማችሁ እወቁት

ዛሬ ሃላሌ ብለሽ ሐፍረተ ገላሽን የላክሽለት ወንድ ነገ ጠላትሽ ሁኖ ገንዘብሽን በመቶሺዎች እንድትልኪለት ፣ደም እንድታለቅሽ፣የአዕምሮ ታማሚ እንድትሆኝ ነው የሚያደርግሽ።

እናም በጊዜያዊ ፍቅር ብቻ መውደቅሽን ሳይሆን ፍፃሜው የት ሊጥልሽ እንደሚችል አርቀሽ መመልከትን አትርሽ
✍ Ibnu Seid

t.me/dinhhiwothnew


🌺 ወርቃማ ምክር
🎙በታላቁ ሙፈሲር የተከበሩ ሸይኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ رحمه.الله
http://t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8


ዒድኩም ሙባረክ
ተቀበለሏሁ ሚና ወ ሚንኩም ሷሊሃል አዕማል
عيدكم مبارك
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال


ነገ ዙልሒጃህ ዘጠኝ የዓረፋህ ዕለት ነው። የነገውን ዕለት መፆም የሁለት ዓመት ወንጀልን ያስምራል።ስለዚህ አላህ ይወፍቀንና ለመፆም እንወስን።

ፆም ብቻ ሳይሆን ዱዓዎችም ተቀባይነት የሚያገኙበት ፣በቀኑ ክፍለ ጊዜም አሏህ ወደ ቅርቧ ሰማይ የሚወርድበት ታላቅ ዕለት ነው።በዚህ ዕለት የዱንያም የአኼራም ጉዳዮቻችንን ወደ ጌታችን የምናሰማበት የተከበረ ልዩ ቀን ነውና በቻልንው መጠን ጠንክረን በዒባዳህ እንድናሳልፍ። የምናውቅ ለማያውቁት በመተዋወስ በመልካም ነገር ላይ እንተባበር

አሏህ በመልካም ነገራቶች ላይ ያበርታን !

✍ Ibnu Seid

t.me/dinhhiwothnew

Показано 20 последних публикаций.