Фильтр публикаций


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
"ሕፃን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሠጥቶናል ስሙም

ድንቅ!!!!!!!

መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል" ኢሳ.6:9

#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
“ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ... በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ” ፊልጵ. 2:12

#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile


"የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው" ዕብ.

13:7

A blessed meeting With His Grace Abune Fanuel, Archbishop of Washington DC Diocese. A great reunion With My beloved Spritual Father and Mentor Kesis Hibret Yeshitla, With Our Mezmur Legend, Liqë Mezemiran Yilma Hailu, With the pioneer of dogmatic books Melake

Ariyam Birhanu Gobena

#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile












በአንቺ ዘንድ ያለው ደስታ ከኤልሳቤጥ ደስታ የሚበልጥ ሲሆን የምሥራቹን ሳትንቂ ደስታዋን ልትካፈይ ወደ እርስዋ የገሰገስሽው እመቤታችን ሆይ አንቺ የደረሰብሽ ኀዘን ከኀዘናችን እጅግ ቢበልጥም ፣

አንቺ ያሳለፍሽው ስደት ከስደታችን እጅግ ቢልቅም ፣ ዐርብ ዕለት ያለቀስሽው ልቅሶሽ ከልቅሶአችን ብዙ እጥፍ ቢሆንም የምናዝነውና መከራን የምንታገሠው በአቅማችን ነውና ኀዘናችንን ለመካፈል ወደ እኛም ከመምጣት እንዳትቀሪ፡፡

እርግጥ ነው እኛ እንደ ኤልሳቤጥ ለአንቺ የሚሰግድ ፅንስ በሆዳችን የለም፡፡ በእኛ ዘንድ የተፀነሰው 'ለፀነሱ ወዮላቸው' 'ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች' ተብሎ የተነገረለት የኃጢአት ፅንስ ነው፡፡ እንደ ኤልሳቤጥ በደስታ የሚያስጮኸን ሳይሆን በኀዘን የሚውጠን የበደል ፅንስ ይዘናልና ድንግል ሆይ እኛን ለመርዳት ፍጠኚ፡፡ በሆዳችን የያዝነውን የኃጢአት ፅንስ ነቢዩ ዳዊት እንደተመኘው በሆድሽ ውስጥ በያዝሽው ዓለት ላይ እስክንፈጠፍጠውና ዕረፍት እስክናገኝ ድረስ ጓጉተናልና ወደ ኤልሳቤጥ እንደመጣሽ ወደ እኛም ነዪ፡፡

በተራራማው ሀገር በአስቸጋሪ መንገድ ወደ ኤልሳቤጥ የገሰገስሽው እመቤታችን ሆይ ወደ እኛ ነይ ስንልሽም መንገዱ እንደማይመችሽ እናውቃለን፡፡ 'ተራራው ዝቅ ይበል' ተብሎ የተነገረለት ተራራማው ልባችን በትዕቢት ተራሮች ስለተሞላ ከይሁዳ ተራሮች በላይ ወደ እኛ መምጣት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሉቃ. ፫፥፫ ድንጋይ ብቻ የሆነው ጭንጫው ልባችን ለመንገደኛ የማይመች እንደሆነ እናውቃለን፡፡

የኃጢአት ወኃ ገብ የሆነው ሕሊናችንም አቋርጠሽ ለመምጣት የሚያስቸግር የበደል ጭቃ የሚበዛው መሆኑን እናውቃለን፡፡ ሆኖም ወደ ተራራ ልባችን ፣ ወደ ጭቃው ሕይወታችን እንድትመጪ እንሻለንና ከአባቶቻችን ጋር 'ንዒ ኀቤየ' 'ንዒ ርግብየ' ከእናቶቻችን ጋር 'ነይ ነይ እምዬ ማርያም' ማለትን አናቆምም፡፡

ልባችን ምንስ ዓይነት ተራራ ቢሆን ላንቺ ምንሽ ነው? 'ይህን ተራራ ወደዚያ ሒድ' የምትይበት የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት 'ካመንሽው ብፅዕት' ዘንድ ይጠፋልን?

እንደ ዘሩባቤል 'ታላቁ ተራራ ሆይ አንተ ምንድርን ነህ? በማርያም ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ' የምትዪበት የልዑል ኃይል በሆድሽ አይደለምን? ሕይወታችን ምንም

እንኳን ቢጨቀይም አንቺ እንደሆንሽ ከነ ልጅሽ በሚሸት በረት ውስጥ እንኳን ለመምጣት አልተጸየፍሽም:: ሕይወታችን እንደ እንስሳ ቢሆንብሽ እንኳን ልጅሽን ከእንስሳት መካከል ለማስተኛት ፈቃድሽ አልነበረምን? ወደ እኛ መምጣትሸን ተስፋ እያደረግን ቅዱሳኑ ሁሉ 'ወደ እኔ ነይ' 'ወደ እኛ ነይ' ብለው የደረሱልሽን ዜማ እያደረስን መምጣትሽን እንጠባበቃለን፡፡
#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile




Репост из: Janderebaw Media
በጃን ማዕተብ የተሰናዳውን "ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ" የተሰኘውን ዘጋቢ ፊልም በጃንደረባው ሚድያ አሁን መመልከት ይችላሉ:: ኦርቶዶክስ ማለት ርትዕት የቀናች ማለት እንደመሆኑ ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ ማለት "ወደ ርትዕት ሃይማኖት መመለስ" ማለት ነው::

በዚህ ዘለግ ያለ ፊልም ላይ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን የተመለሱ ልጆች "ለምን ሔዱ? ለምን መጡ? እንዴት እንመናቸው?" የሚሉ አንገብጋቢ ጥያቄዎችና በአጠቃላይ ተቅዋማዊ ዕቅበተ እምነት ላይ ዝርዝር መረጃዎች ቀርበዋል:: ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የምትጨነቁ የሚመለሱ ሰዎችም አመላለሳቸው ምን መምሰል እንዳለበት የሚገዳችሁ ሁሉ ይህንን ዘለግ ያለ ዘጋቢ ፊልም በትዕግሥት ተመልከቱ::

https://youtu.be/HqyhPq_Jf-g


መላእክት ከጌታ ጋር ነበሩ:: በዲያቢሎስ በተፈተነ ጊዜ “ቀርበው አገለገሉት” (ማቴ. 4:11) ወደ መስቀል ሲሔድ ተጨንቆ ሲጸልይ “የሚያበረታው መልአክ ታየው” (ሉቃ. 22:43) ዕርቃኑን ሲሰቀል አዝነው “በማይታይ ክንፋቸው ጋረዱት” (መጽሐፈ ቅዳሴ) ከሞት ሲነሣ በባዶ መቃብሩ ነጭ ለብሰው ቆሙ:: እንደሞተ አስበው ሽቱ ሊቀቡት ለመጡት ሰዎች “ሕያዉን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል” ብለው መለሱአቸው:: ሲያርግም በእልልታና በመለከት ድምፅ አጀቡት::

መላእክት ለክርስቲያን ሁሉ እንዲህ ናቸው:: በዲያቢሎስ ስትፈተን ቀርበው ይደግፉሃል:: በመከራ ስትጨነቅ ያበረቱሃል:: ዓለም ዕርቃንህን ስትሰቅልህ ከውርደት በክንፋቸው ጥላ ይከልሉሃል:: ከኃጢአት ሞት በንስሓ ስትነሣ እንደ ሰርገኛ ነጭ ይለብሳሉ:: “ሞቶአል ሸትቶአል” ብለው ሽቶ ሊቀቡህ ለሚመጡ ሰዎች “ሕያዉን ከሙታን መካከል ለምን ትፈልጉታላችሁ? ተነሥቶአል!” ብለው ትንሣኤህን ያበሥራሉ:: ከንስሓ በኋላ ከምድር ከፍ ልበል ብለህ ወደ ቅድስና ሥራ ያረግህ እንደሆነ በእልልታ ያጅቡሃል::

መላእክት ያላጀቡት ክርስቶስ መላእክት የሌሉበት ክርስትና የለም!


#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile


አህያና ግርዛት

አሁን ሐዲስ ኪዳን ነው:: መገረዝ ግዴታ አይደለም:: ዋናው ጥምቀት ነው:: ባንገረዝ ምንም አይጎድልብንም:: በዚህ ጉዳይ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ተነሣ:: አሕዛብ ሳይገረዙ ኖረዋልና ጸረ ግዝረት ሆኑ:: አይሁድ ደግሞ እንዴት ግዝረት እንተዋለን አሉ::

ወደ ክርስትና የተጠሩት እነዚህ ሁለት ወገኖች ሁለቱም ከራሳቸው አመጣጥ አንጻር እውነት አላቸው:: አሕዛብ የማያውቁትን ነገር መቀበል ሊገደዱ አይችሉም:: ክርስትናም አላስገደዳቸውም:: አይሁድ ደግሞ የኖሩበትን መተው አይችሉም:: ክርስትናም ግዝረትን ባይጠይቅም አልከለከለም::

በመጨረሻ በብዙ ምክር የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አሕዛብንም ያላገለለ እስራኤልንም ያላቃለለ ውሳኔ ወሰነች:: ውሳኔውን በጥሩ ቃል በመልእክቱ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል::

“ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ፡፡ ... እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር" 1 ቆሮንቶስ 7:18፣ 20

በዚህ መሠረት ኦሪትን ተቀብለው ተገርዘው ወደ ክርስትና የተጠሩት እስራኤል በመገረዛቸው ይቀጥሉ እንጂ ወደ አለመገረዝ አይመለሱ ተባለላቸው:: ሳይገረዙ የተጠሩት አሕዛብ ግን መገረዝ የእነርሱ ልማድ አልነበረምና አይገረዙ ተባለ:: ይህ ለእስራኤል የተወሰነ ውሳኔም እንደ ኢትዮጵያ ኦሪትን ተቀብላ ለኖረችና ተገርዛ ሳለ የተጠራች (ሐውልቶችዋ ሳይቀር የተገረዘ ወንድን የሚያሳዩባት) ሀገርም ላይ ይጸናል::

ይህ ውሳኔ ለሁሉም እንደ ግዝረት ያሉ ሕግጋት ይሠራል::

“ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ”

"ማንም አህያ እየበላ ተጠርቶ እንደ ሆነ አህያ ወዳለመብላት አይመለስ ፤ ማንም አህያ ሳይበላ ተጠርቶ እንደሆነም አህያ አይብላ"

እስራኤል በግዝረት ቀጥሉ ሲባሉ ደስ አላቸው አሕዛብም አትገረዙ ሲባል ደስ አላቸው:: ለእስራኤል ሔደህ የአሕዛብን ዜና ብትነግራቸው ምንም እንኩዋን ግዝረት ግድ ባይሆንም ቅር ይላቸዋል:: የአህያ መበላት ዜናም የሚያስደስተው አህያን እንዴት ልንተው እንችላለን ብለው ለተጨነቁ አሕዛብ ብቻ እንጂ ለእኛ ሆድ የሚበጠብጥ ዜና ነው::

ከዚያ ውጪ እንደ ክርስቲያን ብሉ ብለን ልንሰብከው የሚገባን የሕይወት እንጀራ ሥጋ ወደሙ ብቻ ነው::

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት ይኑር!

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ቄራ(የበሬ)

#share

▫️ @diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile



Показано 14 последних публикаций.