🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Музыка


ድምጻችን ለተዋህዶ ሐይማኖታችን ለኢትትዮጲያ አገራችን

የእግዚአብሔር ሰላም የእናታች የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ፀሎት የመላእክት ጥበቃና የቅዱሳን በረከት ከናንተ
ጋር ይሁን አሜን!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Музыка
Статистика
Фильтр публикаций


✝️እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk


🗓" እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ " (ሉቃ 1:19)


        
✝️ ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው ???

❤️ ገብርኤል:- ማለት የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና ከሊቀ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ ስልጣን የተሰጠው ታላቅ መልአክ ነው።

​​እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ❣️

👑" እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ " (ሉቃ 1:19)


         ✝️ ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው ???

❤️ ገብርኤል:- ማለት የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና ከሊቀ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ ስልጣን የተሰጠው ታላቅ መልአክ ነው።

❤️ለእመቤታችን ለቅስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም የዓለም ድኅነትን የሚሆን ልጅ እንደ ምትወልድ በታላቅ ምስጋና ያበሠረ! የነቢያትንም ትንቢት የፈጸመ ድንቅ መልአክ ነው።

✨🌿 ለካህኑ ዘጋርያስ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን መወለድን ያበሰረ  አብሳሪ መልአክ ነው።

🌹✨ሐምሌ  19  ቀን  ህጻኑን ቅዱስ ቂርቆስን እና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳነበት ታላቅ ቀን ነው።

🌹🍃ታህሳስ  19  ቀን  ሃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሠልስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነበት ታላቅ ቀን ነው።

✝️ ዳንኤልን ከአናብስት አፍ ያዳነም ሃያል መልአክ ነው ሰብአ ሠገልን በኮከብ ምልክት የመራ መልአክም ነው በጨለማ በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃንን የገለጸ ሃያል መልአክ ነውና ክብር እና ምስጋና ይገባዋል።

✝️ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት፣ ፍቅር፣ ምልጃ አይለየን ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን።


🌺እንኳን አደረሳችሁ✝️
🙏

✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


🗓እንኳን ሃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል
ሠልስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ላዳነበት ታላቅ ቀን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።


✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


#ድምፅ_መስጠት_ተጀመረ!

#አንቴክስ_ፉድ_ኤይድ_ፕላስ ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን የሰላም ዘርፍ እጩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በሰላም ዘርፍ ከአምስት እጩዎች ውስጥ ተክትተዋል የዘርፉ አሸናፊ ከሆኑ #10ሚሊየን ብር ይሸለማሉ!!!

ብፁዕነታቸውን BIWን በማስቀደም ኮድ08 (BIW08) በማስገባት በSMS 9355 ላይ አሁኑኑ ይምረጡ!!! 

ድምጽ መስጠቱ እስከ ሐሙስ ታህሳስ 17/2017 ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

በSMS 9355 ላይ BIW08 በማለት ብፁዕነታቸውን አሁኑኑ  ይምረጡ!!!

#10ሚልዮን #አንቴክስ #ፉድኤይድፕላስ #biwsprize #BTM #ብፁዕአቡነኤርምያስ  #ይምረጡ

Vote Abune Ermias now for the BIWs prize!

#AbuneErmias
#10million #BIWS2024 #Prize  #ANTEXETHIOPIA  #ANTEXTEXTILE  #FOODAIDPLUS #BESHATUTOLEMARIAMMULTIMEDIA


🗓  😊ታፍራለች ⭐️
ልጅቷ ባል ትፈልጋለች ሃይማኖቷ በሚፈቅደው ሕግና ስርዓት መሠረት ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች።

ዳሩ ግን አንድም ቀን እግዚአብሔርን በቀጥታ ጥሩ ባል ጥሩ ትዳር እንዲሰጣት ለምናው አታውቅም። ለምን ቢባል ታፍራለች። "እግዚአብሔር እንዴት ስለ ባል ይጠየቃል?"
የሚል ደካማ አመለካከት አላት። እግዚአብሔርንም ጥሩ ባል ስጠኝ ብላ መለመን ያሳፍራታል። እንዳትተወው ደግሞ ባል ያስፈልጋታል። ታድያ አንድ ቀን ሲጨንቃት እንዲህ ብላ ጸለየች፤ "ፈጣሪዬ እባክህን ለእናቴ ጥሩ አማች ስጣት"

በእርግጥ እግዚአብሔርን ስንለምን "የምትለምኑትን አታውቁምን" ተብለው እንደተወቀሱት ሰዎች እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን። ለብዙዋች ግን የሚያሳፍረው ሳያሳፍራቸው፤ የማያሳፍረው ያሳፍራቸዋል

    📣📣📣📣📣
#ድምፀ_ተዋህዶ
     📣📣📣📣📣


🗓 ነገ ማለትም
#ዕለት:- ረቡዕ
#ቀን:- ታኅሣሥ ፪  ፳፻፲፯ ዓ.ም

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን
ሐዋርያዉ ታዴዎስ ፣ ሠለስቱ መዕት ፣ ቅድስት አትናስያ ፣ አቡነ እንድርያኖስ ፣ ቅድስተ ዜና ማርቆስ ፣ አባ ጉባ

አክብረን እና አስበን እንውላለን።

📣📣📣
✔️ የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። ምሳ ፲፤፯

✔️  መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.፻፳፮፥፮


✔️ "ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? ፩ኛ ቆሮ ፮:፪

የመላዕክት ፣ የቅዱሳን ፣ የሰማዕታት ተራዳይነት እና በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን።

✨#ድምፀ_ተዋህዶ✨


✨አንድ ትእቢተኛና ልብ አውልቅ ተማሪ
መምህሩን ሊሳለቅባቸው አሰበና "የኔታ ገሀነም በየት በኩል ነው ?"

አላቸው።የኔታም የውስጡን አውቀው "ልጄ እመንገዱህ ላይ ነህ ......"አሉት ይባላል

✨#ድምፀ_ተዋህዶ✨


🗓ድጓ ከምን ያድናል❓🧠
አንድ መናፍቅ  ታላቁን የድጓውን መምህር የናቀ መስሎት "የኔታ ድጓ ከምን ያድናል "ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም ቀበል አድርገው "እንዲህ ከማለት ያድናል" አሉት ይባላል።
↗️#ድምፀ_ተዋህዶ ↗️


~ኅዳር 21~

እንኳን-ለቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏

  ~ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች ~።

በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን  አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

#ድምፀ_ተዋህዶ


ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::

     (መልክዐ ገብርኤል)

"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †

       (ዳን. ፱፥፳)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#አቤቱ የሆነብንን አስብ

#ድምፀ_ተዋህዶ


የቀድሞው ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቀደመው የአባቱ ቤት ወደሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ተመልሷል
***

በተ*ዶሶ እንቅስቃሴ ላይ የነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘማሪ የነበረው ሐዋዝ ተገኝ

ቀድሞ ያገለግልባት ወደነበረችው ቅድስት እና ንጽሕት ወደሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ መቅደስ በንሰኃ ጥምቀት ተመልሷል።

እግዚአብሔር ይመስገን !!!

#ድምፀ_ተዋህዶ


+++ድንቅ ልዩነት ተመልከቱ+++

በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ፈርዲናንድ ማጄላን ዓለምን በመርከብ ዞረ።

👉ሐዋርያቱ ደግሞ መርከባቸውን ጥለው ዓለምን ዞሩ!

ዛሬ ይዘንባል እያሉ ትንቢት የሚተነብዩ ሜትሮሎጂስቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ ዳግመኛም ዝናብን ያዘነበ ከቶ የለም።

በላብራቶሪው ተመራምሮ ህሙማንን የፈወሰ ሞልቷል።

👉እንደ ጴጥሮስ ጥላው ድውይ የፈወሰ ከቶ አላየሁም።

በዘፈኑ አጋንንትን የጠራ እንደ ማይክል ጃክሰን ሞልቷል።

👉እንደ ዳዊት በበገና መዝሙሩ አጋንንትን ያስወጣ እስከ ዛሬ አልተገኘም።

ከረቫትና ሱፉን ለብሰን የምንጎራደድ ሞልተናል።

👉የልብሱ ቁጨት አጋንንት ያስወጣ እንደ ጳውሎስ ከቶ አልተገኘም።

የግብጽ ነገሥታት አጽማቸው በክብር ይቀመጣል።

👉ዐጥንቱ ሙት ያስነሳ እንደ ኤልሳዕ ከቶ አላየንም።

በአሜሪካ የነገሥታትን ምሥጢር የሚሰልሉ ድርጅቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልሳዕ በእስራኤል ሆኖ በሶሪያ ቤተመንግሥት የሚደረገውን ምሥጢር ያወቀ አልተገኘም።

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን በእግሩ የረገጠ ዩሪ ጋጋሪ ዛሬ ብዙዎቹ አድርገውታል።

👉እንደ ኢያሱ ፀሐይን ያቆመ ከቶ አልተገኘም።

በነገራችን ላይ በተፈጥሮ ሕግ መሰረት ፀሐይ በመሃል ቆማ መሬት ዙሪያውን ትዞራለች። በፀሐይ ፊት ያለው የመሬት ክፍል ቀን ሲሆን ሌላኛው ጎን ደግሞ ማታ ይሆናል።

እነ ኢያሱ በሚዋጉበት ጊዜ መሬት ከፀሐይ ፊቷን አዙራ ቀኑ ሊጨልም ነበር።

👉ኢያሱ ግን መሬት እንዳትዞር አደረጋት! ፀሐይን በገባኦን አቆመ ተባለ! መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ

ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።

👉 እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና ((እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።))
የዓለም መሪዎች ከአስር በላይ ቋንቋ መናገራቸውን እንጃ፤

👉ሐዋርያቱ ግን 72 ቋንቋ ተገለጠላቸው።

ኃያላን ነገሥታት ድውይ እንኳን መፈወስ አይችሉም።

👉ቅዱሳኑ ግን የ70 የ80 ዘመን ሬሳ አስነሱ።

👉ጠቢባን ነን የሚሉ ጸሐፍት ፈሪሳዊያንን ምላሽ ያሳጣቸው ዘንድ ጥበብ ያልነበራቸውን ዓሳ ወጋሪ የነበሩ ሐዋርያትን መረጠ።

ኃያላን ነገሥታት የመሰሉ መሪ ዳዊትን የመሰሉ ነገሥታትን የወለዱ የከበሩ እናቶች ሞልተዋል።

👉የነገሥታትን ንጉሥ ክርስቶስን የወለደች እናት ግን አንድ ብቻ ናት።

ይህችውም ከሴቶች መካከል ተለይታ የተባረከችው ድንግሊቱ 👉 ማርያም ናት 👈

           
ስብሐት ለእግዚአብሔር!

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo


➣ አንተኑ ሚካኤል ዘአውረድከ መና ➢

    ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

🙏 እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤል ነጻነት ያወጣበትን ዕለት አደረሰነ 🙏

✤ ኅዳር ፲፪(12) ሚካኤል ወአስተርእዮተ ዮሐንስ መጥምቅ ውስተ ደብረ ማኀው ወፊላታዎስ ሊቀ ጳጳስት ወበእደ ማርያም ንጉሥ ዘኢትዮጵያ ✤

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ
ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኀኖትከ
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ

✤ ትርጉም ✤

አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል
በማዳንህ እጅግ ሐሤትንና ያደርጋል
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው

            መዝ ፳-፩
                 20   1

✤ ወንጌል ✤

ሉቃ ም ፲፱ ቁ ፲፩-፳፰
           19    11  28

✝ የቅዳሴ ምንባባት ✝

ሮሜ ም ፱ ቁ ፲፯-፳፬
ይሁዳ ም ፩ ቁ ፱-፲፬
ግብ.ሐዋ ም ፳ ቁ ፳፰-፴፩

❖ ምስባክ ❖

ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ
ለእለ ይፈርህዎ ወያድኀኖሙ
ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር

🙏 ትርጉም 🙏

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሰፍራል ያድናቸውማል
እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ እዩም

              መዝ ፴፫-፯
                     33   7

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፲፰ ቁ ፲፭-፳፩
            18     15  21

❖ ቅዳሴ

ያዕቆብ ዘሥሩግ አው ባስልዮስ

" አቤቱ የሚያረጅ የሚጠፋ ይህ ተስፋ ዓለም ለእኛ ለክርስቲያን ወገኖችህ አይደለም፤የሚመጣውን ተስፋ እናደርጋለን ደጅም እንጠናለን እንጂ "
     ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
              ም ፩ ቁ ፹፯
                  1      87

✝ በዓሉ በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ በዓለ በረከት ያድርግልን ቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅ በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ቅድስት ቤተክርስቲያን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን ከሊቀ መላዕክቱ ከቅዱስ ሚካኤል በረከት ይክፈልን በቅዱሳኑ ፀሎት ሁላችንም ይማረን ለቅዱሳኑ ሁሉ የተለመነች እመቤታችን ማርያም ለሁላችንም በረከት በምህረት ትለመነን ለሃገራችን ለህዝባችን ስላም ይስጥልን ደም ሰማዕታት ቅዳሴ መላዕክት ዝማሬ ዳዊት የተቀበለ አምላክ ቅዱሳን የኛንም ፆም ፀሎት ምሕላ ምስጋና ይቀበልልን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ✝️

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo


ጾም በእግዚአብሔር ታዟል፤ተፈቅዷልም ።
++++++++++++++++++++++++++
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾምን እንድንጾም ባርኮ የሰጠን እሱ ነው ።ለዚህም ማረጋገጫ ፦
"ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።"
ማቴ 9:15
በዚህ መሰረት ፦
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ የጾም ህግና ስርዓት አላት ።
"ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን ።"እንዲል
1ኛ ቆሮ 14፥40
በቤተክርስቲያናችን ህግና ሥርዓት ተሰርቶላቸው
ከሚጾሙ 7 የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ጾመ ነብያት ይባላል ።የጾሙ ጊዜ ከህዳር 15-እስከ ጌታ ልደት ታህሳስ 28 ድረስ ያለው ነው ።ይህን ጾም የምንጾመው ነቢያት በየዘመናቸው ስለክርስቶስ መምጣት ንጽህት ከምትሆን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን በናፍቆት ይጾሙና ይጸልዩ ስለነበር የእነርሱን አርአያ ተከትለን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ከማክበራችን ቀደም ብለን ይህን ጾም እንድንጾም በሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ሥርዓት ተሰርቷል። (ፍት.መ.ን.አንቀጽ 15)
ስለሆነም እኛም ክርስቲያኖች ይህን ተከትለን ብልቶቻችንን ሁሉ(አይን ይጹም ፤እጅ ይጹም፤ እግር ይጹም ፤አንደበት ይጹመ...እንዳለ ቅዱስ ያሬድ) ከኃጢአት ጠብቀን፤እግዚአብሔርን ከማያስደስቱ ማናቸውም ነገሮች ራሳችንን አርቀንና ፤በወንድሞቻችን በማናቸውም ላይ ቂም በቀልን በማስወገድ ይቅርም በመባባል ፤ጸሎትን ስግደትን ምጽዋትንም በመጨመር በንጹህ ልቦና መጾም ይገባናል።ይህን ካደረግን ዘወትር የሚዋጉንና የሚፈታተኑን የአጋንንት ሰራዊት በሙሉ ይደመሰሳሉ፤ኃይላቸውም ይደክማል ።ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ፍቅርን ሰላምና በረከትንም እንቀበላለን ።
"የጌታ ቃል የታመነ ነውና።"ቲቶ 3:8
".....ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
ማቴ 17:21

#ድምፀ_ተዋህዶ

        📹📹📹📹
   ✨ፊላታዎስ ሚዲያ✨
               👇👇
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW


ከአባቶች አንደበት
       
      ➕
፩ "ፀሎት የሚያፈቅር ሰው ብታይ
     ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለህ ፤ ወደ እግዚያአብሔር የሚፀልይ ከሆነ መንፈሳዊነቱን ሞቷል ህይወትም የለውም "
           ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፪ "ፀሎት ችላ የሚል ሰው እንዲሁም ለንስሐ የሚያበቃ ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሎአል "
              ማር ይሳቅ

፫ "ፀሎት አእምሮን ወደ እግዚያአብሔር ማቅረብ ነው "
              ማር ይሳቅ

፬ "ፀሎት ፀጋን ይጠብቃል ፤ ቁጣንም ያሸንፋል ትቢትንም የመከላከል ዝንባሌ ያሳድርብናል "
                ከአባቶች

✝️፭ "የመንፈስ ፍሬዎች ያለ ፀሎት ገንዘባችን ልናደርጋቸው አንችልም "
          ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፮ "ፀሎት የማያረጅ ትዕግስትን ገንዘብ የምናደርግባት ታላቅ የጦር መሣሪያ ነው"
                ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

#ድምፀ_ተዋህዶ

        📹📹📹📹
   ✨ፊላታዎስ ሚዲያ✨
               👇👇
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW


የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጥገና መዘግየት በቅርሱ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋትን አስከትሏል ሲል የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት አስታወቀ !


የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ  ከጥቅምት 24 እስከ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ሐዋርያዊ ጉዞ ማድረጋቸውን ተከትሎ የቅዱስ ላሊበላ ደብር የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት፣ የእድር አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በመሪ እቅድ አተገባበር፣ በቅርሱ ጥገናና እንክብካቤ ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል ተብሏል።

የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት መጠለያ አለመነሣቱና የቅርሱ ጥገና መዘግየት እንዲሁም በአካባቢው የሚተኮሰው ከባድ መሣሪያ ያስከተለው ንዝረት በቅርሱ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች ማንሳታቸው ተገልጿል።

የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አስተዳዳሪ መ/ር አባ ሕርያቆስ ጸጋዬ (ቆሞስ) በበኩላቸው አካባቢው የጦርነት ቀጠና ቢሆንም ቤተ ክርስቲያኗ በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የአስተዳደር ዘርፎች ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንድታስፋፋ ታልሞ የተዘጋጀውን መሪ እቅድ ለማሳካት ደብሩ የአስተዳደር ደንብና መዋቅር እያጠና መሆኑን አብራርተዋል።

በደብሩ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠትና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን ለማሻሻል የሚያግዝ የአስተዳደር ደንብ በባለሞያዎች እየተዘጋጀ ስለመሆኑም አስተዳዳሪው አክለዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ባስተላለፉት መልእክት በፈተናዎች ውስጥ ብንሆንም እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የተዘጋጀውን የሀገረ ስብከት ሥልታዊ እቅድ እስከ አጥቢያ ድረስ ማውረድ ተችሏል ብለዋል።

በቅዱስ ላሊበላ ቅርስ ደኅንነት፣ በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግሥት ስምምነት የተጀመረው የዘላቂ ላሊበላ  ቅርስ ጥገና ፕሮጀክት መዘግየት፣ በመዳረሻ ልማትና ማስተዋወቅ ዙሪያ ከባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ባለፈው ሳምንት ውይይት በማድረግ የመፍትሔ አቅጣጫ መቀመጡንም ብፁዕነታቸው ተናግረዋል ሲል የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ዘግቧል፡፡

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo




በሶሪያ ኦርቶዶክስ  ያዕቆባዊት ቤተክርስቲያን የሕንድ ሜትሮፖሊታን የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሞር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ

  ብፁዕ አቡነ ሞር ባስልዮስ ቶማስ ቀዳማዊ እ.ኤ.አ ሐምሌ 22 ቀን 1929 ዓ.ም ቡቸንክሩዝ በተባለ የሕንድ ግዛት የተወለዱ ሲሆን እ.ኤ.አ ከሐምሌ 26 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥር የምትተዳደረውን የሕንድ ቤተ ክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በሊቀ ጵጵስና መርተዋል።

ብፁዕነታቸው በዕድሜና በሕመም ምክንያት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዕረፍት በማድረግ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት አመሻሽ ላይ በሕንድ ኮቺ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ሞር አግናጢዮስ ኤፍሬም ዳግማዊ፣ ለሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ለመላው የቤተ ክርስቲያን አባላት፣ ቀሳውስትና ምእመናን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። 

የብፁዕነታቸው በረከት አይለየን !!!

© ተሚማ

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo


#ጥቅምት21 በዚህች ቀን 'ከይሁዳ ተራሮችና ኮረብቶች ጣፋጭ ሣርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ይመነጫል ' ብሎ ለእመቤታችንን ትንቢት የተናገረላት የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው 

« ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘመነ ጽጌ እንግዳ 
ወዘመነ ፍሬ ጽጋብ ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ
ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ
ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ
ፀቃውዓ መዓር ጥዑም ወሃሊብ ፀዓዳ»    [ ማኅሌተ ጽጌ ]

ትርጉም

«በመከር ጊዜ አበባ በአበባ ጊዜ ደግሞ መከር አዝመራ ማጨድና መሰብሰብ የለም፡፡ ምክንያቱም ጊዜያቸው የተለያየ ስለሆነ፡፡ ለምሳሌ በመስከረም ወር የአበባ ጊዜ በመሆኑ አዝመራ መሰብሰብ የለም፡፡»

«የትንቢት መከር መካተቻ የሆንሽ. እንደ ዘመነ ጽጌ የረሃብን ዘመን ያስወገድሽ ማርያም ሆይ የኤልዳ ነቢዩ ኢዩኤል /ከይሁዳ ተራሮች ጣፋጭ ማርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ብሎ/ የተናገረው ትንቢት በአንቺ ታወቀ፤ ተፈጸመ፡፡»
እመቤታችን ነቢያት የተናገሩት የትንቢት ዘር ተፈጸመባት፡፡ ማለትም ነቢያት የአምላክን ሰው የመሆን ነገር በተለያየ ሁኔታ ተናግረዋል፡፡ ጌታችን ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መፈጸሙንና ይህንን ፍጻሜ ለማየት የታደሉት ሐዋርያት መሆናቸውን «አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል እውነት ሆኖአል፡፡ እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኳችሁ፡፡ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ» በማለት ተናግሮአል፡፡/ዮሐ.4፡37/፡፡ ይህም ነቢያት የዘሩት ትንቢት በሐዋርያት ዘመን ለአጨዳ /ለፍሬ/ መድረሱን መናገሩ ነው፡፡ ስለሆነም «ማዕረረ ትንቢት፤ የትንቢት መካተቻ» ማርያም አላት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ ክርስቶስን ያስገኘችና «ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች» እየተባለ የተነገረላት በመሆንዋ በአበባ ትመሰላለች፡፡

ስለዚህ እመቤታችን በመከር ወራት የምትገኝ አበባ ናት፡፡ በመከር ጊዜ የአበባ መገኘት ያልተለመደ ስለሆነ «ወዘመነ ጽጌ እንግዳ፤ እንግዳ የሆነ አበባ» አላት፡፡

ከዚህ በኋላ
«ብኪ ተአምረ ዘይቤ ነቢየ ኤልዳ፣
ያንጸፍጽፍ እም አድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ፣
ፀቃውዓ መዐር ጥዑም ወሀሊብ ፀዓዳ. . .» በማለት ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረውን ትንቢት አፈጻጸም ይናገራል፡፡

ነቢዩ ኢዩኤል በዘመኑ ጽኑ ረኀብ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን በምሕረት እንደሚጎበኛቸውና ረሀቡ እንደሚጠፋ ይነግራቸው ነበር፡፡ «ብዙ መብል ትበላላችሁ.ትጠግቡማላችሁ ከዚህ በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ተራሮች በተሃ ጠጅ ያንጠበጥባሉ.ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ.በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጎርፋሉ » /ኢዩ.3.18፤ 2.26/፡፡

«ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ፤ያንጸፍጽፍ እምአድባሪሁ ወእምእግሪሁ ለይሁዳ ፀቃውዐ መዓር ወሀሊብ ፀዓዳ»፡፡ ይህም ማለት ነቢዩ ኢዩኤል ከይሁዳ ተራሮችና ኮረብቶች ጣፋጭ ሣርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ይመነጫል ያለው በአንቺ ተፈጸመ ማለት ነው፡፡ ይህም እመቤታችን ክርስቶስን በወለደች ዕለት መሪሩ ጣፍጦ፣ ይቡሱ ለምልሞ ተገኝቷል፡፡ ይህ ለጊዜው ሲሆን ፍጻሜው ደግሞ ከእርሷ በነሣው ሥጋና ደም ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ፣ ከልጅነት ተራቁቶ፣ በረሀበ ነፍስና በጽምዓ ነፍስ ተይዞ የነበረውን የሰው ልጅ ከጎኑ ውኃን ለጥምቀት፤ ሥጋውንና ደሙን ምግበ ነፍስ አድርጎ የአምስት ሺህ አምስት መቶውን ዘመነ ረሀብ እንዳስወገደልን ያስረዳል፡፡

ድንግል ሆይ፤  ክብር የክብር ክብር ካለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ስርጉት በቅድስና ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።

      
#ድምፀተዋህዶ ✨
                                           
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
         👇👇👇
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW


ዘኪዎስ አጭር ባይሆን

ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት::
የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::
እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኪዎስን ጠራው::
ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኪዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ልይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኪዎስ ቤት መዳን ሆነለት::
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር::
ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር::
ዘኪዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኪዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኪዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር::በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኪዎስ ዘኪዎስ አጭር በመሆኑ ነው::
ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ:: እንደ ዘኪዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::
ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው:: ይሄ ይጎድልብኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር:: እጥረትህ መከበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::
እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያት ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኪዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም:: ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::
እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ነበር::
ግንቦት 23 2014 ዓ ም
ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ

#ድምፀ_ተዋህዶ

           YouTube channel
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️ ናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4

Показано 20 последних публикаций.