ሊጠቅማችሁ ስለሚችል አንብቡት 👇
ጌታን በትጋት የሚያገለግሉ ስወች ምክርና ምክርነት መስማት በጣም እወዳለሁ ምክኒያትም ያለፉበትን ስለሚያስተምሩ ይጠቅማልና ።
በቅርቡ ወደ ጌታ የሔዱት #ወንጌላዊ #ገብሩ እንዲህ ብለው መከሩን
1/ ለታመሙ ስወች ሁሉ ጸልይ እግዚአብሔር ይፈውሳል ያልተፈወስውን ስው ስታይ እኔ እምነት የሌኝ ሆኖ ስውየው እምነት የለው ሆኖ አትበል እግዚአብሔር የሚፈውስውን ይፈውሳል ያልተፈወሱትን ለምን እንዳልፈወስ እግዚአብሔር ያውቃል
2/ ወንጌል ለመመስከር ስትወጡ 2 ሁኑ አንዱ ይመስክር አንዱ በልቡ ይፀልይ
3/ እየስራችሁ ማንንም ሳትንቁ በስራችሁ ጌታን አሳዩ
ለሚስሩት ስወች መስክሩ ከሁሉ በላይ በህይወታችሁ ጌታን ይይዩት ታማኞች ሁኑ ።
4/ ለመመስከር ስትወጡ ስወች ጋር አትከራከሩ መስክራችሁ እለፉ እናተ መስክራችሁለታል ደንዳና ልቡን አነቃንቃችሁለታልና ሌላ ስው ደግሞ ሲመስክርለት ያምናል ።
6/ ስወችን እንደ ሁኔታቸው ቅርቡ ከምስጊኑም ጋር እንደ ስውየው ሁኔታ ቅርቡት
7/ የምትፈልጉትን ጌታን በትጋት ጠይቁት
8/ ለዲያቢኖስ ምንም ክፍተት አትስጡት
9/ አገልጋዮች ከሌሎች አገልጋዮች ተማሩ ከመፅሃፍ ቅዱስ ውጭ የሚጠቅማችሁን መፅሃፍ በብዛት አንብቡ
10/ የምታገለግሉትን ህዝብ ምንም ባይረዳችሁም ውደዱት
11/ ከሁሉ በላይ ትሁትና የፍቅር ስወች ሁኑ በዚህ ህይወት ነው ጌታ የሚስራው
12/ ስራ ቦታችሁን እና ስራችሁን ለወንጌል አድርጉት ታማኞች ሁኑ ፣ እየስራችሁ ድሆችን እርዱ
13/ ለምታገለግሉት አገልግሎት የሚረዳችሁን ጸጋ ለምኑ
14/ ምንም ስወቹን ባታውቁም ባትግባቡም ለቅሶ ቤት ሒዱ ህዝቡን በእግዚአብሔር ቃል አፅናኑ እግዚአብሔር በዛ ይስራል
15/ ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት ሁሌ ጸልዩ
የጸጋ ስጦታ አጠቃቀሞችን በደንብ ተማሩ
16/ ስነፎች አትሁኑ ትጋት ይኑራችሁ
17/ የማካፈል ህይወት ይኑራችሁ
18/ እግዚአብሔር ሲናገር ጫፍ ይዛችሁ አትሩጡ እግዚአብሔር ተናግሮ መጨረሻ ላይ ምን አለ ? ንስሃ ግቡ አለ ? እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ አለ ? እፈውሳለሁ አለ ? ተዘጋጅ ልወስድህ ነው አለ ? የመጨረሻዋን ቃሉን በደንብ ስሙ ስምታችሁ ታዘዙ
19/ ከበሽታ እግዚአብሔር ፈውሳችኋል ይተባላችሁ ስወች ህመሙ አለባችሁ ያላችሁ ሃኪም ነውና ሔዳችሁ አርጋግጣችሁ ነው መዲሃኒት መጣልና ምስክርነት መስጠት ያለባችሁ ።
20/ ስውን በፍፁም በፍፁም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ
21/ በአስተምሮ የሳቱትን ወገኖች ምከሩ አስተምሩ እንጂ ስውየውን በፍፁም አትሳደቡ አትናቁትም