ባለ አራት ረከዓ ሶላቶችን ማሳጠር
1️⃣ ሰላትን የማሳጠር ሸሪዓዊ ብይን፦
መንገደኛ ባለ አራት ረከዓ ሶላቶችን ወደ ሁለት ማሳጠር እንደሚፈቀድለት ቁርዓን ሀዲስና የዑለማዎች ስምምነት ያስረዳሉ፡፡
ከቁርአን፡-
﴿وَإِذا ضَرَبتُم فِي الأَرضِ فَلَيسَ عَلَيكُم جُناحٌ أَن تَقصُروا مِنَ الصَّلاةِ إِن خِفتُم أَن يَفتِنَكُمُ الَّذينَ كَفَروا إِنَّ الكافِرينَ كانوا لَكُم عَدُوًّا مُبينًا﴾ النساء: ١٠١
‹‹በምድርም ላይ በተጓዛችሁ ጊዜ እነዚያ የካዱት ያውኩናል ብላችሁ ብትፈሩ ከሶላት (ባለ አራት ረከዓት የኾኑትን) ብታሳጥሩ በናንተ ላይ ኀጢአት የለም፡፡›› ኒሳእ 101
ከላይ የተጠቀሰው አንቀፅ እንደሚጠቁመው ሰላትን ለማሳጠር ፍራቻ መኖር ግድ አይደለም:: ይልቁንም ነብዩ ه ሰላም ሰፍኖ ሳለ ሰላትን ለምን እንደሚያጥር ተጠይቀው ‹‹አላህ እናንተ ላይ የመፀወተው ስጦታ ነውና ስጦታውን ተቀበሉ›› ብለዋል፡፡ሙስሊም 686
ነብዩም ه ሆኑ የርሳቸው ምትክ ዘወትር ጉዞ ላይ ሰላትን ያሣጥሩ ነበር፡፡ ኢብኑ ዑመር እንዲህ ብለዋል ከነብዩ ه ጋር አብሬ ጉዞ ወጥቻለሁ፡፡ ሆኖም ከሁለት ረከዓ በላይ ሰግደው አያውቁም ከአቡ በከርም ጋር ተጉዣለሁ ከሁለት በላይ አልጨመሩም፡፡ሙስሊም 689 ስለ ዑመርና ኡስማንም ተናገሩ፡፡
ኢማም አህመድ ከኢብኑ ዑመር ባስተላለፉትም ሐዲስ ነብዩ ه እንዲህ ብለዋል ‹‹ አላህ ኃጢአት ሲፈፀም እንደሚጠላ ሁሉ እርሱ ያግራራው ነገር ሲፈፀም ደግሞ ይወዳል››አህመድ 5832
ሶላትን ማሣጠር ዑለማዎች የተስማሙበትና ከሀይማኖት እውቀቶችም በግልፅ የሚታወቅ ጉዳይ በመሆኑ ጉዞ ላይ ሙሉ ሰላት ከመስገድ ይልቅ አሳጥሮ መስገድ ይበልጥ ተፈላጊ ነው፡፡
እንዲያውም አንዳንድ ዑለማዎች ነብዩ ه እና ሶሃቦቻቸው ዘወትር ጉዞ ላይ ሲሆኑ ሰላትን አሳጥረው የሚሰግዱ ስለሆነ ጉዞ ላይ ያለ ሰው ሙሉውን ረከዓ መስገዱ የተጠላ ተግባር ነው ይላሉ፡፡
2️⃣ ሊያጥሩ የሚችሉ ሰላቶች፦
ወደ ሁለት ረከዓ በማሳጠር ሊሰገዱ የሚችሉ ሶላቶች ባለ አራት ረከዓ ሶላቶች ማለትም ዙህር ዓስርና ዒሻ ናቸው፡፡
🛑በሁሉም ዑለማዎች ሰምምነት መግሪብና ሱብሂ ሶላቶችን ማሳጠር አይፈቀድም::
3️⃣ ሰላትን ማጠር የሚፈቀድበት የጉዞ መጠንና ዓይነት፡-
አንዳንድ ዑለማዎች እንደሚሉት ሰላትን ማሳጠር የሚቻልበት የጉዞ ርቀት ሰማንያ ኪሎ ሜትር ሲሆን ይህ ማለት በእግር ጉዞ ሁለት ቀን የሚፈጅ ሲሆን ነብዩም ه አንድ ቀን ከነሌሊቱ የሚደረግን ጉዞ ሰፈር (ጉዞ) ብለው ሰይመውታል፡፡ (“በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምን ሴት የአንድ ቀን ከነሌሊቱ ጉዞን ከቤተሰቦቿ ተነጥላ (ብቻዋን ወይም ከባዕድ ጋር) መጓዝ አይፈቀድላትም” ብለዋል::)
እንዲሁም ኢብኑ ዓባስና ኢብን ዑመር ሰማንያ ኪሎ ሜትር የሚሆን መንገድ ከተጓዙ ሰላትን ያሳጥሩና ፆምንም ይፈቱ ነበር:: (ይህ የአንዳንድ ዑለማዎች አቋም ሲሆን ሌሎች ደግሞ ገደብ ሳያስፈልግ በተለምዶ ጉዞ የሚባል ርቀት ጉዞ ላይ ሰላትን ማሳጠር ይፈቀዳል ይላሉ:: በዚህ ርዕስ ላይ የጉዞውን ልክ የወሰነ ሀዲስ ባለመኖሩ ይህኛው የተሻለ አቋም ነው፡፡)
ሰላትን ማሣጠር የሚፈቀድበት የጉዞ ዓይነት ደግሞ ሀላል የሆነ ጉዞ መሆን አለበት:: የተፈቀደ ጉዞ ለምሳሌ፡- ለንግድ ወይም ለመዝናናት፤ ግዴታ የሆነ ጉዞ ፡- ለምሳሌ ለሐጅ ወይም ለጂሐድ፤ ሱና የሆነ ጉዞ ለምሳሌ ለጥየቃ ወይም ለሁለተኛ ሀጅ የሚደረጉ ጉዞዎች ናቸው፡፡ በዚህ መሠረት የማይፈቀድ ሀራም የሆነ ጉዞ ላይ ሰላትን ማሣጠር እንደ አብዛኞቹ ዑለማዎች አቋም አይፈቀድም፡፡
♦️ፊቅህ አል ሙየሰር
✅ ፊቅህን በቀላል አቀራረብ ማቅረብ፡፡
✅ ቁርዓን እና ሱነን መሰረት ባደረገ መልኩ ከኡለማዎች አቋሞች ለመረጃ የቀረበዉን መለየት፡፡
አድራሻችን ፡-
ፌስ ቡክ www.fb.com/easyfiqh
ቴሌ ግራም https://t.me/easyfiqh
ብሎገር www.easyfiqh.blogspot.com