አሳዛኝ ዜና
(ድምጻዊ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ አሳዬ ዘገየ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፉ ተሰማ።
በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ውስጥ ህክምናውን ሲከታተል የቆየው አሳዬ በኋላም "ዶክተሮቹ በህይወት የምትቆየው ከ 6 ወር እስከ አንድ ዓመት ነው ብለውኛል" በሚል ወደ ሃገር ቤት መሄዱ ይታወቃል። በሚኒሶታና በዋሽንግተን ዲሲም ወዳጆቹና የሙያ አጋሮቹ ሽኝት አድርገውለት ነበር።
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ላለፉት 47 ዓመታት ለበርካታ ድምፃዊያን ግጥምና ዜማ በመስጠት የሚታወቀዉ አርቲስት አሳየ ዘገየ፣ ከ37 ዓመት በኋላ ከወራት በፊት ወደ ሃገሩ መመለሱ የሚታወቅ ነው።
ክራር፣ ማሲንቆ፣ ዋሽን፥ አኮርዲዮንና ኪቦርድ የሚጫወተው አሳዬ ድምፃዊና የዜማ ግጥም ደራሲም ነበር።
t.me/Carotmusics