ebstv worldwide📡️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Welcome to EBS TV WORLDWIDE Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates. Don’t forget to share it with your friends.
@ebstvworldwidebot
@EbswhatsnewBot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


























የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም የምሽት 1፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና  ዜናዎች፡_

🇪🇹የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር የነበሩት ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው በመሾም በዛሬው እለት ቃለ መሃላ ፈጸሙ፡፡

❇️ለሶስት ቀናት የሚካሄደው የገዥው ብልፅግና ፓርቲ 2ተኛ መደበኛ ጉባዔ በዛሬው እለት  እየተካሄደ ይገኛል፡፡

🔽የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኦዲቶችን መርምሮ የሚያረጋግጥ አዲስ ክፍል ማደራጀቱን ገለጸ፡፡

🚝የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በግማሽ ዓመቱ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ቶን ዕቃ በባሕር ላይ አጓጉዣለሁ አለ፡፡

👉ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በግማሽ ዓመቱ 454 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ መሰብሰቡን የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ አሳወቀ።

“ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው!"

ቆንጆ ቀን ተመኘንላችሁ!

ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም የእኩለ ቀን 7፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፡_

🇱🇾በሊቢያ "ለባርነት ጨረታ" ቀርባ የነበረችው ኢትዮጵያዊት 700 ሺህ ብር ተከፍሎ ነጻ መውጣቷን ቢቢሲ አማረኛ አስነበበ፡፡

🇪🇹የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ሱዳን ፣ በህንድና አሜሪካ በተከሰተው ድንገተኛ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ፡፡

🔴በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሽሮሜዳ ታቦት ማደርያ አካባቢ የ13 ዓመት ታዳጊ ዋና ለመዋኘት ገብቶ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀ፡፡

❇️በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 6 ወራት 125 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 111 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ፡፡

⚡️በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ 300 ሚሊዮን አፍሪካውያን የኤሌትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ፡፡

❇️85ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ምስረታ በዓል በተለያዩ መርሐ ግብሮች በእንጅባራ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

❇️የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት 74 አመራርና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ አለ፡፡

“ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው!"

ቆንጆ ቀን ተመኘንላችሁ !

ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews


የጥር 23/2017 ዓ.ም የረፋድ ዓበይት የዓለም  ዜናዎች !

🇺🇸 በአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ትናንት  ከወታደራዊ ሄሊኮፕተር ጋር የተጋጨው  አውሮፕላን ጥቁር ሳጥኖች መገኘታቸው ሲነገር በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ መቀጠሉ ተሰምቷል።

🇵🇸🇮🇱 የፍልስጤሙ የሀማስ ቡድን  ከ አንድ አመት በላይ አግቶ ይዟቸው የነበሩ 8 እስራኤላዊያን ታጋቶችን ዛሬ መልቀቁን አስታወቀ ። 

🇮🇱🇵🇱🇺🇦 እስራኤል በ አውሮፓዊቷ ፖላንድ በኩል ለዩክሬን የ ሚሳኤል የጦር መሣሪያ ድጋፍ ማድረጓ ተነገረ ።

🇨🇩 በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ  ክፍል የምትገኘውን የጎማ ከተማን የተቆጣጠረው የ ኤም 23 አማፂ ቡድን መሪ ጥቃታቸውን በመቀጠል ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ እናቀናለን ሲሉ ዛቱ ::

ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN




ኢትዮጵያ በአለማቀፍ ደረጃ 2ኛዋ ቡና ላኪ ሀገር ለመሆን እየሰራች እንደሆነና : ሶስተኛ የቡና አምራች ሀገር መሆን መቻሏን ጨምሮ : የኢትዮጵያን ቡና በብዛት የሚገዙት ሀገራት እነማናቸው ? የሚሉትን ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበናል።

ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይከተሉ።
https://youtu.be/pQ-tv99FA2I


ኢትዮጵያ በአለማቀፍ ደረጃ 2ኛዋ ቡና ላኪ ሀገር ለመሆን እየሰራች እንደሆነ እና ሶስተኛ የቡና አምራች ሀገር መሆን መቻሏን ጨምሮ የኢትዮጵያን ቡና በብዛት የሚገዙት ሀገራት እነማናቸው ? የሚሉትን ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበናል።

ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይከተሉ።
https://youtu.be/7EytuXgDL_Y




የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም የምሽት 1፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና  ዜናዎች፡_

🇺🇸አሜሪካ ለኤች አይ ቪ ቫይረስ ህክምና የምትሰጠውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ገለፀች፡፡

❇️የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በህገወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በነበሩና ያለደረሰኝ ሲገበያዩ ነበር ባላቸው ከ1ሺ 700 በላይ በሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገለጸ፡፡

❇️በቋንቋ ጉዳይ ከህገመንግስቱ ጋር ይጋጫል የተባለው የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፀደቀ፡፡

🇪🇹🛩ዘ አፍሪካ ሪፖርት ይዞት በወጣው መረጃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2024 ከአፍሪካ ብቸኛው የቦይንግ ምርት በመግዛት ድርጅቱ ከደረሰበት ኪሳራ እየታደገው እንደሆነ ገለጸ፡፡

👨‍⚕️👩‍⚕️በሐኪሞች ላይ እየተፈጸሙ ናቸው የተባሉ ችግሮች ላይ የሚመክር ጉባኤ በመጭው ወር የካቲት ያካሄዳል ተባለ፡፡

👉በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ  ገለጸ፡፡

“ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው!"

ያማረ ምሽት ተመኘንላችሁ !

ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews

Показано 20 последних публикаций.