Ethiopian Electric Utility


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Карьера


EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Карьера
Статистика
Фильтр публикаций


በአዲስ አበባ ከተማ የመልሶ ግንባታ ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን አካባቢዎችን ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-
http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/power-interruption?lang=am


ከብልሹ አሰራር የፀዳና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት ሊሠራ ይገባል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከብልሹ አሰራር የፀዳና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንደሚገባው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት በተቋሙ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አድርገዋል፡፡

ለአዲሱ ዋና ስራ አስፈፃሚና ለተቋሙ አመራሮች የስራ መመሪያ የሰጡት ዶ/ር ብሩክ ተቋሙ ሃገራዊ ኢኮኖሚው እንዲሳለጥ እና እየጨመረ የመጣውን የሃይል ፍላጎት መልስ ሊሰጥ የሚችል ስራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

አዲሱ ዋና ስራ አስፈፃሚ በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ይቀርፋሉ የሚል እምነት እንዳላቸው የገለፁት ዶ/ር ብሩክ ተቋሙ ለሚያከናውናቸው ስራዎች መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመው በበኩላቸው ተቋሙን ለመምራት እድል በማግኘታቸው አመስግነው እስከታች ያለውን አመራርና ሠራተኛ በማስተባበር ተቋሙን ለመለወጥ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት ተመልሷል

መንዲ -ጊዳሚ- አሶሳ በተዘረጋው 132 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኃይል አስተላለፊ መስመር ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት በጊዳሚ፣ ቤጊ ቆንዳላ፣ በአሶሳ ከተማ ፣ በባምባሲ፣ በኡራ፣ በአብራሃሞ፣ በሸርቆሌ፣ በመንጌ፣ በኩርሙክ፣ በሆሞሻ፣ በቶንጎ ፣ በኡንዱሉ፣ በብልድግሉ ወረዳዎችና አካባቢዎቻቸው ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት ተመልሷል።

በተመሳሳይ ለቡሌ ሆራ፣ ለያቤሎ እና ሞያሌ ሰብስቴሽኖች የኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰጠው የ132 ኪ.ቮ መሰመር በመውደቁ ምክንያት በተጠቀሱት አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት ተመልሷል።

የጥገና ስራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁን ክቡራን ደንበኞቻችን ከልብ እናመሰግናለን ።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ መስመር ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል

ለቡሌ ሆራ፣ ለያቤሎ እና ሞያሌ ሰብስቴሽኖች የኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰጠው የ132 ኬቪ መሰመር በመውደቁ ምክንያት በተጠቀሱት አካባቢዎች የሃይል አቅረቦት ተቋርጧል፡፡

በከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ መስመሩ ላይ ያጋጠመው ችግር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ተፈትቶ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትእግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የትራንስፎርመር ጥገና ለማከናወን ሲባል የሚቋረጥ የሃይል አቅርቦት


በአዲስአበባ እና በጎንደር ከተማ የመልሶ ግንባታ ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-

http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1211?lang=am


ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተመደቡ

ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙን በዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩትን ሽፈራው ተሊላ (ኢ/ር) በመተካት ተቋሙን በዋና ስራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ተመድበዋል፡፡

ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) በተቋሙ የተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ላይ ለረጅም አመታት ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

6.6k 0 121 29 83

በከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ መስመር ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

መንዲ ወደ ጊዳሚና እና አሶሳ በተዘረጋው 132 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኃይል አስተላለፊ መስመር ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት ከዛሬ 8፡22 ጀምሮ በጊዳሚ፣ ቤጊ ቆንዳላ፣ በአሶሳ ከተማ ፣ በባምባሲ፣ በኡራ፣ በአብራሃሞ፣ በሸርቆሌ፣ በመንጌ፣ በኩርሙክ፣ በሆሞሻ፣ በቶንጎ ፣ በኡንዱሉ፣ በብልድግሉ ወረዳዎችና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል፡፡

በከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ መስመሩ ላይ ያጋጠመው ችግር ተፈትቶ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትእግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


የግብዓት አቅርቦት ማሻሻያ ለአገልግሎት ቅልጥፍና

ተቋማችን ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ሰፊ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በዚህም ለኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች አስተማማኝ የሃይል አቅርቦት ተደራሽ ከማድረግ ጎን ለጎን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ በያዝነው በጀት ዓመት በሰፊው አቅዶ እየሰራ ነው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት መገንባት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ ሲሆን፤ ተቋማችንም ለመሰረተ-ልማት ዝርጋታ የሚውሉ ጥራታቸውን የጠበቁ ግብዓቶችን ለሀገር ውስጥ አቅራቢዎች ቅድሚያ በመስጠት የጎደለውን ከሃገር ውጪ በማቅረብ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም ተቋሙ የአገር ውስጥ አምራቾችን በማበረታታት ጥራት ያለው ግብዓት እንዲያቀርቡ በማድረግ ከውጭ ለሚገቡ እቃዎች የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት በማቃለል አስተማማኝ አቅርቦትን በማረጋገጥ ደረጃ ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ አምራቾችም ከተቋሙ ጋር ውል በመዋዋል የግብዓቶች ጥራትም እየተረጋገጠ እያቀረቡ ይገኛሉ፤የአቅርቦት መሻሻልም እየታዬ ነው፡፡

ተቋማችን ከደንበኞች ለሚቀርቡለት የኤሌክትሪክ ኃይል ጥያቄ በፍጥነት አገልግሎት እንዳይሰጥ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ አስቀድሞ የግብዓት አቅርቦት አለመኖሩ መሆኑ ተለይቷል፡፡ በመሆኑም አዲስ እየተተገበረ በሚገኘው የተቋም ሪፎርም መሰረት ለደንበኞች ግብዓት ለማቅረብ የሚወስድባቸውን ጊዜ ለመቀነስ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ተቋሙ የግብዓት አቅርቦት እጥረቱን ለመፍታትና የደንበኞችን እንግልት ለመቀነስ ግብዓት በራሳቸው ገዝተው እንዲያቀርቡ ሲደረግ የቆየ ቢሆንም አገልግሎቱን ለማግኘት የሚወስድባቸውን ጊዜ በእጅጉ የሚያጓትት ከመሆኑም በላይ ገዝተው የሚያመጡት ግብዓት ወደ ተቋሙ ኔትወርክ ከመግባቱ በፊት ጥራት ማረጋገጥ አስገዳጅ በመሆኑ በዚህ የሚፈጠረው ሂደት ለደንበኞች አላስፈላጊ ወጪ፣ ቢሮክራሲና ቅሬታ የሚፈጥር ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በተጨማሪም አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የአገር ውስጥ አምራቾች ለተቋማችን እያቀረቡት ያለው ግብዓት ለደንበኞቻችን ጥያቄ በቂ ምላሽ እንድንሰጥ እያስቻለን በመሆኑ በተቋም ደረጃ አሰራሩን ወጥነት እንዲኖረው በማድረግ በሁሉም የተቋሙ አገልግሎት ማዕከላት ደንበኞች ከተቋማችን ግብዓቶችን እንዲያገኙ እየተደረገ ነው፡፡ይህም ጊዜና ጉልበት እዳይባክን የአገልግሎት ቅልጥፍናና የግብዓት ጥራት አስተማማኝነትን ለማሳደግ እያገዘ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ እንደሁልጊዜው ተቋማችን የትራንስፎርመርና ሌሎች ግብዓት ከሚያመርቱ የሃገር ውስጥ አምራቾች ጋር ውል በመያዝ በተቀመጠው የጥራት መስፈርት መሰረት ለሚያቀርቡ ሁሉ በፍትሃዊነት ግዥ በመፈፀም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡




የጨረታ ማስታወቂያ


በአዲስአበባ ከተማ የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1210?lang=am


አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ነው

አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ የኃይል መቆራረጥ ችግር የሚታይባቸዉ መስመሮችን በመለየት የመልሶ ግንባታ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የደብረ-ብርሃን ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ ገለጹ፡፡

ሀገረ ማርያም 33 ኬ.ቪ፣ እነዋሪ 33 ኬ.ቪ፣ አጣዬ 15 ኬ.ቪ እና አረርቲ 33 ኬ.ቪ መስመሮች የኃይል መቆራረጥ የሚስተዋልባቸው ከፍተኛ መስመሮች መሆናቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ የእንዋሪ 33 ኬ.ቪ መስመር 42 ሳታላይቶችን እና የእንዋሪ ከተማ መጋቢ መስመር በሸክላ ሲኒ የተዘረጋ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ሪጅኑ ባከናወነው መስመር ፍተሻ ስራ ከደብረ ብርሃን እስከ እንዋ ሪ የተዘረጋው 67 ኪ.ሜ መስመር፤ ከደነባ-አንጭቆረር 12.5 ኪ.ሜ እና ከደነባ - ሲያ ደብር 16 ኪ.ሜ በአጠቃላይ 95.5 ኪ.ሜ መስመር ላይ ያሉት 6000 የሸክላ ሲኒዎች ሙሉ በሙሉ የማያገለግሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሪጅኑና ማዕከላቱ በጋራ ባከናወኑት ሥራ ከደብረ ብርሃን እስከ እንዋሪ አና ከደነባ እስከ አንጭቆረር የተዘረጉ 3,300 ሸክላ ሲኒዎችን ወደ ፕላስቲክ ሲኒ የመቀየር ስራ እንዲሁም የረገቡ መስመሮችን የመወጠር ስራ መከናወኑን አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ዳይሬክተሩ በ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪጅኑ በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን የመለየት እና የቅድመ ጥገና ሥራዎችን በስፋት ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በግማሽ ዓመቱ 1365.4 ኪ.ሜ መካከለኛ መስመር ላይ ያሉ ችግሮችን የመለየት ሥራ በማከናወን 251.5 ኪ.ሜ የቅድመ ጥገና እና 1785 ቁጥር ያለው አስቸኳይ ጥገና ስራ መሠራቱን ገልጸዋል፡፡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ኤሌክትሪክ እና የመስኖ ልማት!!


በአዲስ አበባ እና ሐረር ከተሞች የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ ኃይል የሚቋረጥባቸውን ቦታዎችለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1208?lang=am


በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ታወር ላይ በተፈፀመ ስርቆት ምክንያት የሃይል አቅርቦት ተቋርጧል

ከላሊበላ - አላማጣ በተዘረጋ 66 ኪ.ቮልት ትራንስሚሽን መስመር ታወር ላይ በተፈፀመ ስርቆት ምክንያት በሽምሽሀ፣ በብልባላ፣ በላልኪው፣ በአዲስ አምባ፣ በገለሶት፣ በገ/ማሪያምና ነአኩቶለአብ ሳተላይት ጣቢያዎች፣ በብርኮ፣ በቅዱስ ሀርቤ፣ በአይና ሚካኤል እና ዳሪያ ሳተላይት ጣቢያዎች፣ በኩልመስክ፣ በወንዳች፣ በደንሳና ጠረወንዝና ሳተላይት ጣቢያዎች አቅርቦት ተቋርጧል።

ስለሆነም በኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ በተፈፀመው ስርቆት ምክንያት የተፈጠረው ችግር ተፈትቶ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ለመልሶ ግንባታና አቅም ማሰደግ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው

ለመካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታ እና አቅም ማሳደግ ሥራዎች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የወላይታ ሪጅን የኔትወርክና ኢንፍራስትራክችር ኃላፊ አቶ ገረሱ ቴጋ ገልፀዋል፡፡

የመልሶ ግባታ ስራው እየተከናወነ የሚገኘው በስድስቱ ከተሞች ያልተካተቱ እና የኃይል መቆራረጥ በሚስተዋልባቸው የገሡባ፣ የበቁሎሠኞ፣ የቦዲቲ፣ ሻንቶ እና የኮሙቡጠበላ ወረዳዎችን ያቀፈ መሆኑን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

በመልሶ ግንባታ ስራው 420 ምሰሶዎች ተከላ እና 49 ነጥብ 5 ኪ.ሜ መካከለኛ መስመር ዝርጋታ መከናወኑን የገለፁት አቶ ገረሱ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የመልሶ ግንባታ ስራው 95 በመቶ መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቱን ለመገንባት ከ63 ሚሊየን 621 ሺህ ብር በላይ በጀት ተመድቦለት ወደሥራ መገባቱን ጨምረው ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ኃላፊው ለጨለለቅቱ አንድ ባለ 1250 ኪ.ቮ.አ፣ ለቦረዳ ባለ 630 ኪ.ቮ.አ አዲስ ትራንስፎርመር የተከለ ሲሆን ቦምቤ፣ ቦዲቲ እና ወናጎ ላይ የተተከሉ ትራንስፎርመሮች አቅም ከ100 ኪ.ቮ.አ ወደ 200 ኪ.ቮ.አ እንዲያድጉ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የመካከለኛ መስመር አቅም ግንባታ ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በዝቅተኛ መስመሮች ላይ ደግሞ የቅደመ መከላከል ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመልሶ ግንባታ እና አቅም ማሰደግ ሥራዎች አዲስ የኃይል ተጠቀሚን ለማፍራት፣ ጥራት ያለውና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ የሚያግዝ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የገጠር ከተሞችን በአማራጭ የሃይል ምንጭ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወኑ ለሚገኙ እንቅስቃሴዎች ማሳያ !!


በኃይል አስተላለፊያ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅረቦት

ከኮሶበር -ቻግኒ በተዘረጋው 66 ኪ.ቮልት ኃይል አስተላለፊያ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ቻግኒን ጨምሮ በመተከል ዞን፣ በግ/በለስ ከተማ፣ በማንዱራ፣ በፖዌ፣ በዲባጠ፣ በቡለን፣ በደ/ዘይት፣ በዳንጉርና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም በኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ የተፈጠረው ብልሽት ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሳለጠና የተቀናጀ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመስጠት 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 46ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረገው አስተዋፆ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እውቅና ሰጥቶታል፡፡

6.8k 0 12 10 29
Показано 20 последних публикаций.