Фильтр публикаций


በትናንትናው እለት በ100 አመታቸው ያረፉት የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ

የካርተር ማዕከል (The Carter Center) እንደ ትራኮማ፣ የጊኒ ትል በሽታ፣ ወባ እና ወዘተ ያሉ በሽታዎችን ከመከላከል እስከ የምግብ ምርት ማሳደግ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ከምርጫ ታዛቢነት እስከ እርቅ ማፈላለግ ባሉ ስራዎች ላይ በሀገራችን በስፋት ተሳትፋል።

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ምናልባትም የጂሚ ካርተር ተቋም በአለም ዙርያ ካሉት ስራዎቹ ሁሉ ትልቁን ያከናወነው በኢትዮጵያ ነው፣ በዚህም በአብዛኛው የሀገራችን የገጠራማ አካባቢዎች ነዋሪ ተጠቃሚ ሆኗል።

ብዙዎች የካርተር ማዕከልን የሚያስታውሱት ምርጫ 97'ን ተከትሎ የተገደሉ ንፁሁንን በማውገዙ እና ምርጫው ላይ የታዩ ጉድለቶችን በግልፅ በማሳወቁ ነበር። ደርግ ሊወድቅ ሰሞን ደግሞ በኮሎኔል መንግስቱ እና በህወሓት እንዲሁም የኤርትራ ሀይሎች መሀል የሰላም ንግግር ናይሮቢ ላይ አስጀምረው ነበር።

የአሜሪካ ተንታኞች ጂሚ ካርተርን ከቀደሙት መሪዎች ሁሉ ከስልጣን ከወረዱ በሗላ ከፍተኛ ተፅእኖ የፈጠሩት ናቸው ይሏቸዋል፣ ሀገራችንም አንዷ ተጠቃሚ ነበረች።

እናመሰግናለን፣ ነፍስ ይማር!

@EliasMeseret


በሲዳማ ክልል በቦና ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችን ቁጥር 71 መድረሱ ታውቋል

እጅግ ያሳዝናል፣ ነፍስ ይማር!

@EliasMeseret


በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ዳር አበባ እና ሳር ለማጠጣት የሚውለው የመጠጥ ውሀ በመሆኑ ህዝቡ መቸገሩ ታወቀ

(መሠረት ሚድያ)- በአዲስ አበባ ከተማ በተለይ በቅርብ ግዜያት ከተሰሩ የኮሪደር ልማቶች ጋር ተያይዞ ለተተከሉ የመንገድ ዳር አትክልትና ሳር ለማጠጣት የሚውለው ውሀ ለነዋሪዎች መጠጥ ከሚያገለግል የውሀ መስመር በመሆኑ ህዝቡ ውሀ መቸገሩ ታወቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://t.me/meseretmedia/736

Via @MeseretMedia
@EliasMeseret


የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ መንግስት ራሱ በምንጭነት የሚጠቅሳቸው ተቋማት ደግሞ ከ120 ሚልዮን ህዝባችን ውስጥ 86 ሚልዮኑ በድህነት ውስጥ እንደሚገኝ እየነገሩን ነው

የህዝቡን ምሬት፣ እሮሮ እና ስቃይ ደግሞ እለት ከእለት በግልፅ እያየነው ነው። ኢኮኖሚያችንን ፕላን የሚያረጉልን ደግሞ ስሌታቸው ስክሪንሾቱ ላይ ያለውን እያሳያቸው ነው።

ችግር ሲያጋጥም ጭንቅላትን ብቻ ለይቶ አሸዋ ውስጥ መቅበር ማለት ይህ ነው። 

@EliasMeseret


Journalism is not just about speaking to those in power; it is about speaking truth to power ✊️

#Journalism

@EliasMeseret




"ጠንካራ ዲፕሎማሲ... " ብሎ ለኮመተ ክፍያ ተጀመረ እንዴ?

አንዳንዴ እኮ አንሰማም፣ የሰማችሁ አሳውቁን።

#የሚድያሰራዊት

Via Inbox

@EliasMeseret


#መልካምዜና ሚያንማር ውስጥ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለማውጣት እንቅስቃሴ ተጀምሯል

በቅርቡ ያጋራሁትን ይህን ከታች የሚታይ ካርታ መነሻ በማድረግ ምርመራ እንደተደረገ እና በቻይና ጋንግ ቡድን ታግተው የሚገኙትን 1,300 ገደማ ዜጎች ለማውጣት የውጭ ጉዳይ አንድ ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚጓዝ ታውቋል።

ይሁንና እኔ ካጋራሁት ቦታ በተጨማሪ ሌሎች ስፍራዎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ። በእነሱ ዙርያ ምንም እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ አሳውቀውኛል ስለዚህ ለክትትል እንዲመች ቦታዎቹን ከታች አስቀምጣቸዋለሁ።

@EliasMeseret


"ጡጦ የምልበት አቅም የለኝም። ጡቴን ብቻ ነው ሳጠባቸው የከረምኩት። የጡት ወተት አሁን አነሳቸው፤ እንዴት ይድረሳቸው?. . . የተገኘው ምግብም አልሆናቸው አለ፤ አልስማማቸው አለ።"

ይህ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ዛሬ ላይ ያለው ሁኔታ ነው... መቸስ አይናችን እያየ ከሚረግፉ ህዝብ ያለውን አሰባስቦ ቢረዳስ?

በዚህ ዙርያ ለማስተባበር የምትችሉ እንነጋገር፣ ይህም ስም ካልተሰጠው እና ካልተከለከለ ማለት ነው።

Quote via BBC Amharic

@EliasMeseret


1. "30 አመት ውጪ ሀገር ታክሲ እየሰራህ እዚህ መጮህ አይቻልም..."

2. "ዛሬ የአሜሪካንን ድሪም ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ችለናል..."

... አለ አፍሪካን የሚወክል ሚድያ አዲስ አበባ ላይ ላቋቁም ነው ብሎ ከመንግስት በተሰጠው ሁለት ሰፋፊ ቦታ ከባድ ጆካ የተጫወተው ወንድማችን... አሜሪካን ሀገር Seattle ከተማ ላይ ደግሞ የገዛውን ጭውቴ እናውቃለን።

#የዛሬይቱኢትዮጵያ 

በሰፊው እመለስበታለሁ...

@EliasMeseret


የቀድሞው ምክትል ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮንን አፍሪካ ውስጥ ያሉ ህፃናትን መቀንጨር የሚከላከል ድርጅት እንዳቋቋሙ ዛሬ ሰማን

ድርጅታቸው ለግዜው አፍሪካን ትቶ እሳቸው የወጡበት የአማራ ክልል ውስጥ እንዲህ በርሀብ እየተጎዱ ያሉ ህፃናት ላይ ትኩረት ቢያደርግ እላለሁ።

ይህ የ1977 ድርቅ ሳይሆን አሁን ላይ የኢትዮጵያ ህፃናት ምንም በማያውቁት እያለፉበት ያለ ስቃይ ነው፣ አንዳንዱ ህዝባችን ደግሞ "ጦርነት አቁሙ በሏቸው፣ ወይም ርሀቡ ይቀጥላል" እያለ በህፃናቱ መሳለቅ ይዟል።

እንደ ህዝብ መጨረሻችን ይህ መሆኑ ያሳዝናል።

Photo: Belay Manaye

@EliasMeseret




#MyOpinion በዚህ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ የዛሬ 11 ወር ገደማ ከሶማሊላንድ ጋር የፈረመችው ስምምነት ከዚህ በኋላ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው መረዳት ይቻላል።

በሌላ በኩል "የሶማሊላንዱ ስምምነት በስም ተጠቅሶ ተሰርዟል ካልተባለ ለስምምነት አንቀመጥም" ሲሉ የነበሩት የሶማልያ መሪዎች የፈለጉትን ሳያገኙ ቀርተዋል።

በዋናነት ግን ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ የባህር በር የማግኘት አካሄዷን በሞቃዲሾ በኩል ለማድረግ መስማማቷ ሶማሌዎችን ዋናው የስምምነቱ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል። ሲቀጥል ስምምነቱ የግብፅ ጦር ከሶማልያ እንዲወጣ የሚል ነጥብ አልተካተተበትም። 

ለዲፕሎማሲያችን ትልቅ፣ ትልቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ክስተት ሆኖ ማለፉ ግልፅ ነው... ግን ቢያንስ ጦርነት ማስቀረት መቻሉ ትልቁ ትርፍ ነው።

"ይሄ አካሄድ ግን ያስኬዳል?" ብለን በወቅቱ የጠየቅን የተለያየ ስም ሲሰጠን ነበር። የሆነው ይሁን... ከዚህ ክስተት መማር ከቻልን መልካም፣ ካልሆነ ግን የሀገርን ዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን ታሪክ እና ጥቅም በእጅጉ የሚጎዳ መሆኑ ግልፅ ነው።

@EliasMeseret


አስታራቂ አይጥፋ!

Peace is what we need.

@EliasMeseret


በአዲስ አበባ የሚሰማው ተኩስ ምንድን ነው?

- በተኩሱ አንድ ሴት መገናኛ አካባቢ ተመትታ ህይወቷ አልፏል

ሙሉ ዜናው ⤵️
https://t.me/meseretmedia/683

@EliasMeseret


ከሰሞኑ የሰማነው የተወሰኑ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለው) አባላት ሰላም መምረጥ ተስፋ ይሰጣል

አካሄዱ ላይ ግን ጥንቃቄ ካልተደረገበት ውጤቱ ከታሰበው በተቃራኒ እንዳይሆን ያሰጋል።

ዛሬ ጠዋት ስልኬን ስከፍት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ልብስን የለበሱት ጃል ሰኚ ነጋሳ መግለጫ ሲሰጡ ተመለከትኩ። "በምን አግባብ?" የሚለው ትልቁ ጥያቄዬ ነበር፣ ምክንያቱም የሰራዊቱ አባል ያልሆነ ሰው ልብሱን ለብሶ ከተገኘ እንደ ከፍተኛ ወንጀል ስለሚቆጠር።

በርካቶች ይህን ሁኔታ አይተው "ቀድሞውም እኮ አንድ ነበሩ" እና "ቁስል እንኳን ሳይደርቅ እንዴት እንዲህ ይደረጋል?" የሚሉ አስተያየቶችን እየሰጡ እንደሆነ ታዘብኩ።

መንግስት ከጥቂት ሳምንታት እና ወራት በፊት በግድያ፣ በዝርፊያ፣ በእገታ እና በሽብር ሲከሰው ከነበረው አካል ጋር ስምምነት ሲፈፅም ረጋ ተብሎ እና በሰከነ ሁኔታ ካልተያዘ ጉዳት የደረሰባቸው እና በተለይ አሁን ድረስ ከታጣቂዎቹ ጋር በዱር በገደሉ ተፋጠው ላሉ የመንግስት ፀጥታ አካላት የሚያስተላልፈው መልዕክት ያሰጋል።

አለም አቀፍ ልምዶች እንደሚያሳዩት ከሁሉም በፊት የሚቀድመው የተሀድሶ ፕሮግራም ነው።

ሰላም ለሀገራችን።

@EliasMeseret


አቶ ታዬ ደንደአ እንኳን ለቤትዎ አበቃዎት!

ፍርድ ቤት የፈታውን ግለሰብ እስር ቤት በር ላይ ጠብቆ ማፈን ከኢህዴግ ግዜ ጀምሮ ተደጋግሞ የሚፈፀም ድራማ ሆኗል፣ ይህ በግልፅ ለፍትህ ስርዐቱ ያለ ቸልተኝነት ማሳያ ነው።

ወደፊትም የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ፍትህ ጠባቂዎች ጉዳያቸው በፍጥነት ታይቶ እንደሚፈቱ ተስፋ አደርጋለሁ።

ጋዜጠኞቹን "ሶስት አመት አቆዩዋቸው" የሚል ትእዛዝ ከበላይ መጥቷል የሚል መረጃ አለ፣ እውን የፍትህ ሚኒስቴር ይህን ያውቀው ይሆን?

@EliasMeseret


መንግስት 'ዋልታ' የተባለን ሚድያ ለማጠፍ መወሰኑ ይበል ያሰኛል፣ ጥቂት የሚባሉ መልካም ጋዜጠኞች ቢኖሩትም ከውልደቱ እስከ ሞቱ የፕሮፖጋንዳ እና ህዝብን የማጥቂያ መሳርያ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል 

ከአመት በፊት ፋና እና ዋልታ ሊዋሀዱ እንደሆነ አንድ መረጃ ባቀረብኩበት ወቅት የቀድሞው የዋልታ ስራ አስፈፃሚ መረጃው 'ሀሰት' እንደሆነ ተናግሮ ነበር።

ስራ አስፈፃሚው አክሎም "የቀረበው ሃሳብ ተራ አሉባልታ ከመሆኑም ባሻገር ከጀርባው ብዙ ሴራ ያዘለ ነው" ብሎት ነበር። ዛሬ ግን ራሳቸው በይፋ ተዋህደዋል እያሉን ነው።

ግዜ ደጉ...

@EliasMeseret


#ጥቆማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተታለው ሚያንማር እና ታይላንድ ድንበር ላይ በቻይና የወንጀለኞች/ጋንግ ቡድን ተይዘው እየተሰቃዩ ይገኛሉ

ውጭ ጉዳይ በቅርቡ ሲጠየቅ "የት እንዳሉ ለማወቅም አስቸጋሪ ሆኗል" ብሎ የሰጠውን ምላሽ አየሁ። አድራሻቸው ጠፍቶ ከሆነ እዚህ ይገኛሉ:

https://maps.app.goo.gl/CHHduoAGAVs4dx8J9

በነገራችን ላይ የስሪላንካ መንግስት ሙሉ በሙሉ ዜጎቹን ነፃ አስወጥቶ ወደ ሀገራቸው መልሷል፣ የእኛዎቹ ግን አሁን ድረስ በኤሌክትሪክ ሽቦ እየተገረፉ እና ካለ ክፍያ በቀን እስከ 16 ሰአት እንዲሰሩ እየተደረጉ ይገኛሉ።

@EliasMeseret


ከሰሞኑ ወጣቶች በብዛት ከየመንገዱ እየታፈሱ መጋዘን ውስጥ እየታጎሩ እንደሆነ መረጃ ስናቀርብ "ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት ነገር ፈፅሞ የለው" ብለው ነግረውን ነበር

አሁን ላይ ግን ውሸቱን መደበቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ "በፍቃደኝነት የተመለመሉ ወጣቶች ወደ ካምፕ ገቡ" ብለው ዜና ይሰሩባቸው ይዘዋል።

ዩኒቨርስቲ፣ ሙያ ማሰልጠኛ፣ እርሻ ወይም ኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ ሊሆኑ የሚገባቸውን ወጣቶች ወደ #እሳት!

@EliasMeseret

Показано 20 последних публикаций.