ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ; ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት እየተከናወነ ነው።
ዘጋቢ መ/ር አቤል አሰፋ
(#EOTCTV ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም አዲስ አበባ)
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በኢትዮጵያ አስተናጋጀነት በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል በይፋ ተጀምሯል።
በኮንፈረንሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤ የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ; ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቦርድ ሰብሳቢ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ; ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ; ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤጠቅላይ ጸሐፊ; የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነትና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ኮንፈረንሱ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ የሚገኘው የመሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሂዩማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር " መቻቻል አብሮነትና ሰላም" በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው ።
በኮንፈረንሱ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ብናልፍ አንዱዓለም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
መድረኩን የከፈቱት ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከመላው ዓለም የመጡ የጉባኤውን ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የሃይማኖት ተቋማት መቻቻልን አብሮነትና ሰላምን በማምጣት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው በመግለጽ ለጉባኤው አሰናጅ ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል ።
በኮንፈረንሱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት በብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቦርድ ሰብሳቢ ለጉባኤው በንባብ ቀርቧል።
ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው በዓለም በሩሲያና ዩክሬን በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሌሎችም የዓለም ክፍሎች ያለው ጦርነት በሰዎች ኑሮ ላይ አሉታዊ ጥላ ማጥላቱን በመግለጽ ሰላም በመላው ዓለም እንዲሰፍን መልዕክት በማስተላለፍ ለዚህም የሃይማኖት ተቋማት ድርሻ ከፍ ያለ መሆኑን አስገንዝበዋል ።
በጉባኤው ጥናታዊ ጽሑፎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚሁ ጎን ለጎን በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማትን የእርስ በእርስ መልካም ግንኙነት እንዲሁም ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያከናወኗቸውን ተግባራት የሚያሳይ የፎቶ ዐውደርዕይ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ተከፍቷል።
በዓለም አቀፍ ጉባኤው ከውጪ ሀገራት ቻንስለር ዶ/ር ኸሊፋ የሚመራ የዩናይትድ አረብ ኤምሬት፣ ሊባኖስ፣ዮርዳኖስ፣ አሜሪካ እና የሳዑዲ አረቢያ ተሳታፊዎች ታድመውበታል።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅትን
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000165122406
ዓባይ ባንክ 1462319237132015
በመጠቀም የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ።
☎️ ለበለጠ መረጃ 👉 +251985585858
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo 🇪🇹 "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 🇪🇹
📡 የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት 🎥
📱 የዲጂታል ሚዲያ ገጾች💻
ለመረጃ 📞 +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=