ESAT (ኢሳት🇪🇹)®


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በጥላቻ ንግግር ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ‼️

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

ኢትዮጵያ ብዝሃ ሀይማኖት የሆነች ሀገር እንደ መሆኗ የተለያየ እምነት ተከታዬች ለዘመናት ተፈቃቅደውና ተከባብረው ኖረውባታል። እየኖሩባትም ይገኛሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ይህንን በጎ እሴት በመሸርሸር ውዝግብና ግጭት ለመፍጠር የሚሰሩ አካላት እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡

በተለይም የእስልምናን መልካም እሴቶች እና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር በመዳፈር ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጡ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እየተሰራጩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተረድቷል።

ጠቅላይ ም/ቤቱ እነዚህ አካላት ከዛሬ ነገ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ከጥፋታቸው ይታረማሉ በሚል ቀና እሳቤ ጉዳዩን በትዕግስት ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ም/ቤቱ ችግሩን ከዚህ በላይ በትዕግስት መመልከት ውጤቱ የከፋ በመሆኑ የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነኩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከየትኛው አይነት ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡ የጥላቻ ንግግር በየትኛውም ወገን ቢሰነዘር ጠቅላይ ም/ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንደሚሰራም ማወቅ ይገባል፡፡

በመሆኑም በተደጋጋሚ ተከስቶ በቸልታ እየታለፈ ያለው የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብርየሚነካ የጥላቻ ንግግር ያደረጉ ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፍትህ፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት የህግ ተጠያቂነትን ለማምጣትና መሰል ጥፋቶች እንዳይደገሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ም/ቤቱ ያሳስባል።

በመሆኑም፡-
1. የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳዩ ከዚህ በላይ ከመክረሩ በፊት የጋራ አቋም በመያዝ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲወስን።

2. ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤

3. የሰሞኑ የጥላቻ ንግግር ምንጩ የተራ ግለሰብ ቢመስልም ከጀርባ የአጀንዳና የሃሳብ ተጋሪዎች ያሉት በመሆኑ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀሱ በፊት የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በመቆም ትንኮሳውን እንዲያወግዙ፤ እንዲሁም

4. ወቅቱ በሙስሊሞች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የፆም ወቅት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ከሀይማኖትና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጡ የጥላቻ ንግግሮች የሚገሰፁበትና የሚታረሙበት የፅሞና ወቅት እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ጠቅላይ ም/ቤቱ የእስልምና አንኳር እሴቶችን በተለይም የፈጣሪያችንን አሏህ፣ የነቢያትን፣ የመለኮታዊ መፃህፍትንና የደጋግ ተከታዮችን ክብር የሚያጎድፉ ማንኛውም አይነት የጥላቻ ትንኮሳና ድርጊት በህግ አግባብ እንዲታረሙ ተቋማዊ ኃላፊነቱን የሚወጣም ይሆናል፡፡

ለእውነተኛ ሰላምና አብሮነት የሚቆረቆሩ አካላት ሁሉ ድርጊቱን እንዲያወግዙና ለፍትህ እንዲሰሩም ጠቅላይ ም/ቤቱ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

@Esat_tv1
@Esat_tv1




" ከነፍሳችን በላይ አብልጠን በምንወዳቸው ውዱ ነብያችን ክብር የማንደራደር መሆኑን ሁሉም ሊያውቅ ይገባል"‼️

🗣ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሀላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ከሰሞኑ በውዱ ነብያችን ላይ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ድምበር የሚያልፉ ግለሰቦችን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የፉሪ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ከኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የዳዕዋ መድረክ በርካታ ሙስሊሞች በተገኙበት መልዕክት ያስተላለፉት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ "ከነፍሳችን በላይ አብልጠን በምንወዳቸው ውዱ ነብያችን ክብር የማንደራደር መሆኑን ሁሉም ሊያውቅ ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል።

እኛ እምነታችን በምናስተምርበት ወቅት ፈፅሞ የሰዎች እምነት ላይ ድንበር አናልፍም እስልምናም ይህን አያዘንም ያሉ ሲሆን ሌሎች የእምነት ተቋማትም ድንበር የሚያልፍ ግለሰቦችን ተው ሊሉ ይገባል ብለዋል።

እንደ ተቋም በህግ መሄድ እስካለብን ጥግ ድረስ እንሄዳለን ያሉ ሲሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብ በተለይ ወጣቱ በሰላማዊ መንገድ እምነቱን ማስከበር አለበት ሲሉ ገልፀዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


የአውሮፓ መሪዎች ለአረብ ሀገራት የጋዛ መልሶ ግንባታ እቅድ ድጋፍ ሰጡ‼️

ግብፅ ያቀረበችውና 53 ቢሊየን ዶላር የሚያስፈልገው የጋዛ መልሶ ግንባታ እቅድ በአረብ ሀገራት መሪዎች ባሳለፍነው ሳምንት መጽደቁ ይታወሳል።

የጋዛ መልሶ ግንባታ እቅድ በአረብ ሀገራት ከጸደቀ በኋላ የተለያዩ የዓለም ሀገራት በእቅዱ ላይ አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ።

የፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ኢጣሊያ እና ጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር መስሪያ ቤቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ በ53 ቢሊየን ዶለር ጋዛን መልሶ ለመገንባት ለቀረበው እቅድ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


#ቴምር ሪልስቴት

⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
       ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል

ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
 ☎️📞👇👇👇👇👇👇

0901168027

0901179577

    


የኤሌክትሪክ ታሪፍ ድጋሚ የዋጋ ጭማሪ ሊደረግበት  ነው‼️

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ በመኖሪያ ቤት ታሪፍ ላይ 0.50 ኪሎ ዋት ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞች የፍጆታ ታሪፍ 0.60 ሳንቲም እንዲከፍሉ የሚደረግ ሲሆን፣

የአገልግሎት ክፍያ ተመንን በተመለከተ ለድኅረ ክፍያ አሥር ብር ከ95 ሳንቲም ሲከፍሉ፣ ለቅድመ ክፍያ አራት ብር ከ18 ሳንቲም እንደሚከፍሉ ሪፖርተር ያገኘው ሰነድ ያሳያል፡፡

የመኖሪያ ቤት ታሪፍን በተመለከተ ከ51 እስከ 100 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ ደንበኞች አንድ ብር ከ49 ሳንቲም፣ ከ101 እስከ 200 ኪሎ ዋት ሁለት ብር ከ67 ሳንቲም፣ ከ201 እስከ 300 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ ደንበኞች ሦስት ብር ከ84 ሳንቲም እንደሚከፍሉና በየኪሎ ዋቱ መጠን ክፍያው የሚለያይ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


ኢትዮጵያ ድሮን ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም ገንብቻለሁ አለች‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) የሚያመርተውን የስካይ ዊን ኢንዱስትሪን መርቀው በከፈቱበት እንዳስታወቁት ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸው ድሮኖች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን የመጠበቅ አቅሟን ይበልጥ ያሳድጋል ፡፡

ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸው ድሮኖች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን የመጠበቅ አቅሟን ይበልጥ የሚያሳድጉ ናቸው ተብሏል፡፡ድሮኖቹ በከፍተኛ መልካዓ-ምድር ላይ በብቃት አገልግሎት የሚሰጡና ጸረ-ድሮን ጭምር የታጠቁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡ኢንዱስትሪው ድሮኖችን ከኢትዮጵያ ባሻገር ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም አለው ብለዋል ፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1


"መለኮታዊ ጉብኝት በኢትዮጵያ" የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው‼️

መለኮታዊ ጉብኝት በኢትዮጵያ" የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር በርካታ የወንጌል አማኞች በተገኙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አቢያተ ክርስቲያናት እና በቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ ማህበር ቅንጅት በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር ላይ ፤ የቄስ ቢሊ ግራሃም ልጅ ፍራንክሊን ቢሊ ግራሃም ለስብከት የተገኙ ሲሆን የጸሎትና እና የዝማሬ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወኑም ተገልጿል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1


የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ70ኛ ዙር እጩ መኮንኖችን አስመረቀ‼️

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የሚጠበቅባቸውን ሥልጠና ወስደው ያጠናቀቁ የ70ኛ ዙር ቃኘው ኮርስ እጩ መኮንኖችን በዲግሪ መርሃ ግብር አስመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ጄኔራል መኮንኖች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ወታደራዊ አታሼዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1


የረመዳን ፆም የመጀመርያው የጁምዓ ፀሎት ምክንያት በማድረግ በአል-አቅሳ መስጊድ ከ 13 - 55 እድሜ ያሉ ወጣቶች እንዳይሰግዱ ገደብ ተጣለ‼️

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት መንግስታቸው ከዌስት ባንክ ወደ አል-አቅሳ መስጊድ መግባት የሚችሉ አማኞች የቁጥር ገደብ መጣሉን ይፋ አድርጓል።

በአዲሱ ገደብ መሰረትም ከ55 ዓመት በላይ የሆናቸው ወንዶችና ከ50 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ብቻ በአል-አቅሳ መስጊድ የሚደረገውን የረመዳን ፆም የመጀመርያው ዓርብ የፀሎት መርሀግብር ላይ ለመሳተፍ ይችላሉ።

እንዲም ሆኖ ግን በአዲሱ መመርያ መሰረት ወደ መስጊዱ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ሰዎች ጥብቅ የሚባሉ የደህንነትና የፍተሻ ስርዓቶችን ማለፍ ግድ እንደሚላቸው ተነግሯል።

ውሳኔው በተከበረው የረመዳን ወር ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ሰፋሪዎች ወደ አል-አቅሳ መስጊድ ግቢ ከሚያደርጉት ዕለታዊ ወረራ እና ወደ ዌስት ባንክ በሚጓዙ ፍልስጤማውያን ላይ የሚጣሉ ገደቦችን እየጨመሩ ባሉበት ወቅት የተላለፈ ነው።

የአል-አቅሳ መስጊድ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ሶስተኛው ቅዱስ ስፍራ ሲሆን አይሁዶች በበኩላቸው ቴምፕል ማውንት ሲሉ የሚጠሩት የመጀመርያውና ሁለተኛው የአይሁድ ቤተ መቅደሶች የነበሩበት ቦታ ነው ብለው ያምናሉ። መስጊዱ በጥንቷ እየሩሳሌም ከተማ የሚገኝ ሲሆን የዓለም ቅርስ ተብሎም በዩኔስኮ የተመዘገበ ነው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


የደቡብ ኮሪያ አየር ኃይል በስህተት የሀገሪቱን ዜጎች በቦምብ ደበደበ‼️

ከኬ.ኤፍ 16 ተዋጊ ጄት በልምምድ ወቅት 8 ቦምቦች ንጹሃን ላይ መጣሉ ተነግሯል።

የቦምብ ጥቃቱ ከሰሜን ኮሪያ በ25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ቡቸን ከተማ ላይ ነው የተፈጸመው።

የደቡብ ኮሪያ አየር ኃይል በዛሬው እለት እንዳታወቀው ከሆነ፤ በልምምድ ላይ የነበረው የጦር ጄት በስህተት በንጹሃን መኖሪያ መንደር ላይ ስምንት ቦምቦችን ጥሏል።

አየር ኃይሉ በመግጫው ከኬ.ኤፍ 16 (KF-16) ተዋጊ ጄት የስልጠና ተልእኮ በማካሄድ ላይ እያለ ባልተለመደ ሁኔታ “Mk 82” የተባሉ ቦምቦች በመኖሪያ መንደር ላይ መጣሉን አረጋግጧል።

የአየር ድብደባው ከሰሜን ኮሪያ በ25 ሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቡቸን ከተማ ላይ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ እንደተፈጸመ ጦሩ አስታውቋል።

በስህተት በተፈጸመው የአየር ጥቃት በንጹሃን ላይ ጉዳት መድረሱን ያስታወቀው አየር ኃይሉ፤ ምን ያክል ሰው እንደተጎዳ እና የጉዳታቸው መጠን ምን ያክል ነው የሚለውን ግን ከመግለጽ ተቆጠቧል።

ከስፍራው የወጡ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርች እንደሚያሳዩት ከሆነ በአየር ጥቃቱ በ4 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስ በ3 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ ትዕዛዝ ተላለፈ‼️

ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለፀ፡፡

የግብር ዕዳ ያለባቸውና በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግላቸውም ዕዳቸውን ለመክፈል ፈቃደኛ ያልሆኑ 62 ግለሰቦችን በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 44 ንዑስ አንቀፅ ከ1-3 ለተቋሙ በተሰጠ ስልጣን መሰረት ከሀገር እንዳይወጡ ለፌዴራል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዝርዝራቸውን ማስተላለፉን ተገልጿል፡፡

ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የግብር ዕዳቸውን በአግባቡ ሳይወጡ የሚሰወሩ ግብር ከፋዮችን በአግባቡ በመከታተል ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የዕዳ ክትትልና አስተዳደር የስራ ክፍልን በአዲስ መልክ በማደራጀት ወደ ተግባር ገብቷል::

በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ከ6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡

ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ቢሮው ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1


በግልጽ በማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ሲገለገሉ በነበሩ ከ1ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ አስታወቀ‼️

በተደመሰሰ፣ በታጠፈ፣ በተፋፋቀ፣ በደበዘዘ እና በማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር ሲገለገሉ በተገኙ 1 ሺህ 587 ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አግባብነት ካለው አካል የተሰጠን የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር በሚታይና ግልፅ በሆነ መልኩ በተሽከርካሪው አካል ላይ መለጠፍ እንደሚገባ በአዋጅ መደንገጉን የገለጸው ፖሊስ፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አሽከርካሪዎች ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን በመጠቀም ደምብ ሲተላለፉ ቆይተዋል ብሏል፡፡

አንዳንዶቹም ደምብ መተላለፉን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ወንጀል ሲፈፅሙ የተገኙ ተይዘው ምርመራ እየተጠራባቸው መሆኑንም ፖሊስ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በሁሉም ክፍለ ከተሞች በቀንንና በማታ ባደረገው ቁጥጥር የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥርን ያለ አግባብ ሲገለገሉ በተገኙ 1 ሺህ 587 ደንብ ተላላፊዎች ላይ በትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ መሰረት እርምጃ መውሰዱን ነው የገለጸው፡፡

ፖሊስ በደንብ ተላላፊዎች ላይ እያደረገ ያለውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ፤ የተሽከርካሪ ባለ ንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች በተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር አጠቃቀም ዙሪያ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1


የአረብ ሀገራት ጉባዔ የግብጽን የጋዛ መልሶ ግንባታ እቅድ አጸደቅ‼️

በካይሮ የተካሄደው የአረብ ሀገራት አስቸኳይ ጉባዔ ግብጽ ጋዛን መልሶ ለመገንት ያቀረበችውን እቅድ ተቀብሎ አጸደቀ።

53 ቢሊየን ዶላር የሚያስፈልገው እቅዱ ጋዛን በ5 ዓመታት ውስጥ መልሶ መገንባት የሚያስችል ነው ።

በእቅዱ መሰረት በመልሶ ግንባታው ፍሊስጤማውያንን ከመሬታቸው ሳያፈናቅል የሚካሄድ ነው የተባለ ሲሆን፤ ጋዛን ከሃማስ ውጪ ሌላ ገለልተኛ ኮሚቴ እንዲያስተዳድር ይደረጋል ተብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ማስጠንቀቂያ‼️

የአዲስ አበባ መጅሊስ ከዚህ በኋላ በመስጂዶች ጉዳይ አይታገስም።

1446ኛው ታላቁ የረመዳን ወር መስጂዶች ደምቀውና ተውበው ህዝበ ሙሊሙን በተገቢው መንገድ በመቀበል እያሰተናገዱ ነወ።
በአብዛኛዎቹ መስጂዶች ህዝበ ሙሰሊሙ እምነቱ በሚያዘው መሠረት ዒባዳውን እያከናወነ ሲሆን በጣት በሚቆጠሩ መስጂዶች ሁከት ለማስነሣት የተደረጉ ሙከራዎችን በየመሰጂዱ የሚገኙ ኮሚቴዎች፣ ሀዲሞችና ህብረተሰቡ ባደረገው ጥረት በቁጥጥር ሰር ሊውሉ ችሏል።
    
በተለይም ጠሮ መስጂድ ፣ሎሚ ሜዳ(ዓሊ) መስጂድና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው ሀምዛ መሰጂድ የረመዳንን መግባት ተከትሎ በአንዳንድ  ሰውር አላማ ያላቸው ግለሰቦች ሁከትና ብጥብጥ በማሰነሣት ከፍተኛ ችግር ሲፈጥሩ የቆዩ አካላት መሸሸጊያ ሆኖ የቆየ ቢሆንም መጅሊስ ከዛሬ ነገ ይቀየራሉ ብሎ ሁኔታውን አባታዊ በሆነ ትዕግሰት ይዞት ቆይቷል።

መጅሊሰ በእነዚህ ጥቂት መስጂዶች የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶችን ቢያደርግም ዕድሉን ባለመጠቀም ቡድኑ መሰጂድ ሰብሮ በመግባት፣ ጄነሬተር በማጥፋት፣ ለደህንነት የተገጠመ ካሜራን በመሰባበር እና አማኞች የተረጋጋ ዒባዳ(የአምልኮ ስርዓት) እንዳይከውኑና የረመዳንን ወር የብጥብጥና የረብሻ አውድማ የማድረግ እንቅሰቃሴያቸውን ቀጥለውበታል።

ከወራት በፊት ማዕከላቸውንና የብጥብጥ መነሻቸውን ዓሊ መስጂድ በማድረግ ሴቶችና ህፃናትን ከፊት በማሰለፍና የተወሰኑ ግለሰቦችን በገንዘብ በመደለል የተጀመረው ውንብድና  ኢማሞችን ማይክ ቀምቶ በመደብደብ የተራዊ ሰላት እንዲቋረጥ እሰከ ማድረግ ደርሰዋል
     
ይህ በግልፅ በሚታወቁ ግለሰቦች የሚመራው ቡድን በተመረጡና ለማምለጥ ምቹ በሆኑ መስጂዶች ከተለያየ አካባቢ ተጠራርተው በመግባት አወል ሰፍን (የሰላቱን የመጀመሪያ ረድፍ) ለመሰጂድም ሆነ ለሸማግሌዎች ክብር የሌላቸው አሰቀድመው በመያዝ ረብሻ በማሰነሣት መሰጂዱን አውከዋል።

በየጊዜው በየመስጂዱ እየተዘዋወሩ ሁከት  የሚፈጥሩ አካላት በሚገባ የሚታወቁና መረጃ ያለን ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ለህዝብ እንደምናሳውቅ እየገለፅን መጅሊሱ ከዚህ በላይ እንደማይታገሰና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የፀሎት ቦታዎች ሠላማዊ እንዲሆኑ መስራቱን እንደሚቀጥል ለህዝበ ሙስሊሙ ያሣውቃል።
    
መጅሊሱ ካለበት ሀላፊነትና ተጠያቂነት አኳያ ጉዳዩን በትዕግሰት መያዙ አግባብ ቢሆንም በዚህ የሠላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመተዛዘን ወር በሁለቱ መስጂዶች በተፈጠረው አሳፋሪ ተግባር ክፉኛ ማዘኑን እየገለፀ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ዒባዳውን(የአምልኮ ሥርዐቱን) የሚፈፅምባቸው መስጂዶች ሠላማቸው እንዲጠበቅ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሠራ በድጋሚ ለመግለፅ ይወዳል።

የአ/አ/ከ/እ/ጉ/ከ/ም ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@Esat_tv1
@Esat_tv1




በሳዑዲ ዓረቢያና በኦማን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 470 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ‼️

በዚህ ሳምንት ውስጥ 180 ወንዶች፣ 109 ሴቶች እና 13 ጨቅላ ህፃናት በድምሩ 302 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 56 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

በተያያዘ ዜና በሳምንቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 157 ወንዶች 11 ሴቶች በድምሩ 168 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው የተመለሱ መሆኑ ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን 91 ሺህ 420 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


እስራኤል የሙስሊም ረመዳን እና የአይሁዶች የፋሲካ በዓል እስኪያልፍ ድረስ በሚል ለቀጣይ ስድስት ሳምንታት የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን በጊዜያዊነት ለማራዘም ወሰነች‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ይህንን ያስታወቀው ቀደም ሲል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ቅዳሜ እኩለ ሌሊት ላይ ካበቃ በኋላ ብዙም ሳይዘገይ ነበር።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል‼️

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጅ እና መመሪያ መሠረት መንግስታዊ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1


ዓድዋ! 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Показано 20 последних публикаций.