Ethio Today


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ፈጣን አዳዲስ እና የተረጋገጠ መረጃ በእየለቱ ያግኙ።
YouTube :- https://www.youtube.com/channel/UCM0oGovoseqStaFWh2wIi4g

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ኢራን እስራኤልን አስጠነቀቀች‼️

የኢራኑ የውጪ ጉድይ ሚኒስትር፤ እስራኤል የጋዛን ጥቃት የማታቆም ከሆነ፣ ከ“ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ” ጋር ባመሳሰሉት ጥቃት ትመታልች ሲሉ ቤሩት ላይ በሰጡት መግለጫ አስጠንቅቀዋል።

ሁሴን አሚራብዶላሂያን በሰጡት ማስጠንቀቂያ፣ እስራኤል ጥቃቷን የማታቆም ከሆነ እና ሄዝቦላ ውጊያውን ከተቀላቀለ፣ ግጭቱ ወደ ቀጠናው ሌሎች ሀገራት ይስፋፋል ብለዋል።

ቤሩት ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የኢራኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የሌባኖሱ ሄዝቦላ ሁሉንም የጦርነት ሁኔታዎች እየገመገመ መሆኑን እና እስራኤል በአስቸኳይ በጋዛ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ጠይቀዋል።

እስራኤል ሄዝቦላን ዋና ጠላት አድርጋ የምትመለከት ሲሆን፣ ሄዝቦላ 150ሺሕ ሮኬቶች እና ሚሳኤሎች፣ እንዲሁም በእስራኤል ማንኛውንም ቦታ በትክክል ሊመቱ የሚችሉ ሚሳኤሎች እንዳለው ይገመታል። በ12 ዓመቱ የሶሪያ ጦርነት የተሳተፉ ልምድ ያላቸው በሺሕ የሚቆጠሩ ተዋጊዎች እና ለየት ያለ ወታደራዊ ድሮንም እንዳለው ይነገራል።

የኢራኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስት በቤሩት በስደት የሚገኙትን ከፍተኛ የሐማስ ባለስልጣን ማግኘታቸውም ታውቋል።


እስራኤል ከሰሜን ጋዛ ለሚሸሹ አንደኛውን መንገድ ለሶስት ሰዓታት ከኢላማ ውጭ እንደምታደርገው አስታወቀች!

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምታደርገውን የምድር ላይ ጥቃት ከመጀመሯ በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ከሰሜን ጋዛ እየሸሹ ይገኛሉ።

በሰሜን ጋዛ ያሉ ሰላማዊ ሰዎች በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ አንድ ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ድረስ ወጥተው ወደ ደቡባዊ ጋዛ ማምራት እንዳለባቸው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አዲስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ነዋሪዎች ከቤይት ሃኑን ወደ ክሃን ዩንስ የሚወስደውን መስመር ብቻ መጠቀም እንዳለባቸው ጠቅሶ በእነዚያ ሰዓታት ውስጥ መንገዱ ከኢላማ ውጭም እንደሚሆንም አስፍሯል።

እስራኤል በሰሜን ጋዛ ለሚኖሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሄዱ ማስጠንቀቂያ ሰጥታ የነበረ ሲሆን በዚህ ወቅትም ሁለት መንገዶችን መጠቀም አለባቸው ብላ ነበር።

በሰሜን ጋዛ ያሉ ሆስፒታሎችም አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የእስራኤልን ውጡ ማስጠንቀቂያ በሆስፒታል ያሉ ህሙማንን አስገድዶ ማስወጣት "የሞት ፍርድ ነው" ሲል አውግዞታል።

[BBC]


አሜሪካ ለእስራዔል ድጋፍ 2ኛውን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ላከች‼️

ዋሽንግተን ቀደም ሲል “ጀራልድ ፎርድ” የተሰኘውን የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ወደ ሜዲትራኒያን በመላክ ለእስራዔል ድጋፏ ማሳየቷ ይታወሳል፡፡
በሁለቱም ወገን ጦርነቱ ተባብሶ መቀጠሉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

እስራዔል ጋዛ ላይ በወሰደችው የዓየር ጥቃት እስካሁን ከ2 ሺህ 329 በላይ ፍልስጤማውያን ሕይወት አልፏል፡፡
ከ9 ሺህ 700 በላይ ፍልስጤማውያንም ቆስለዋል ነው የተባለው፡፡

በአንጻሩ ሃማስ በደቡባዊ እስራዔል ባደረሰው ጥቃት እስካሁን ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ÷ ከ3 ሺህ 400 በላይ በሚሆኑት ጉዳት አድርሷል፡፡


በወልቄጤ የቀጠለውን ግጭት ተከትሎ በከተማው እግድ ተጣለ።

በቀን 02/02/2016 ዓም በወልቂጤ ከተማ ተቀሰቀሰው አመጽ እንዲበርድ የጸጥታ ኃይላት በሆደ ሰፊነት ግጭቱ እንዲበርድ እና የሚደርሰው ቁሳዊና ሰብዓዊ ጉዳት ለመቀነስ በኃላፊነት ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዜጎች ላይ የሚደርሰው አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ለመቀነስ የዞኑ ኮማንድ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲጣል ወስኗል።

በመሆኑም ከዛሬ ጥቅምት 03/2016 ጀምሮ በተሽከርካሪዎች እና በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ የሰዓት ገደብ ተጥሏል።

በዚህ መሰረት የትኛው ተሽከርካሪ ማለትም ሞተር ሳይክል፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ)፣ አነስተኛም ሆነ ከፍተኛ የህዝብ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሰዎች ከ11:00 እስከ ጠዋት 1:00 ድረስ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።


«ኢትዮጵያ የባህር በር የግድ ያስፈልጋታል» ጠ/ሚ አብይ አህመድ

«የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ ስለሆነ ኢትዮጵያ አሁን የግድ የባህር በር ያስፈልጋታል፣ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ የባህር በር እንደነበራት ታሪክ ይናገራል ስለዚህ እነዚህን የባህር በሮች በንግግር እና ውይይት ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ አለብን፣ ይህ ብቻ አይደለም በሰጥቶ መቀበል ከህዳሴ ግድብ፣ ከአየር መንገድ፣ ከቴሌ ድርሻ በመስጠት የባህር በር ድርሻ መውሰድን የመሳሰሉ አማራጮችን መጠቀም አለብን፣ በፍፁም ግን በጉልበት በጦርነት የባህር በር ይኑረን ብለን ጦር አንመዝም» ሲሉ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከጠብታ ውኃ እስከ ባህር ውኃ በተሰኘ ለፓርላማ አባላት በሰጡት ማብራሪያ የተናገሩት


የትግራይ ክልል በሁለቱ ዓመት ጦርነት የሞቱትን የቀድሞ ታጋዮች ቤተሰቦችን ማርዳት ተጀመረ!

በጦርነቱ በትግራይ ወገን እየተፋለሙ የሞቱት ስንት መሆናቸው አሁንም በግልፅ ባይነገርም፥በየአካባቢው እየተደረጉ ካሉ የመርዶ ስነ-ስነርዓቶች መታዘብ እንደሚቻለው፥ ጥቂት የማይባሉ ዕድሜያቸው በአስራዎቹ መጨረሻ፣ በሃያዎቹ መጀመርያ እና አጋማሽ የነበሩ ወጣቶች፣ ከጦርነቱ በፊት በተለያየ ሥራ አልያም ትምህርት የነበሩ፣ መሆናቸውን መረዳት ይቻላል።

ከነገ ጀምሮ ደግሞ በመላው ትግራይ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን እንደሚታወጅም የክልሉ አስተዳደር አስታውቋል። በጦርነቱ ልጆቻቸውን እና ሌሎች ዘመዶቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች ከመርዶ በኃላ ሐዘን ተቀምጠዋል። በትግራይ ክልል ከጦርነቱ ማብቃት አንድ ዓመት ገደማ በኃላ፥ በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ ኃይሎች ጋር  ሆነው ሲዋጉ ያለፉት የቀድሞ ታጋዮች የማሰብ፣ መርዶ ለቤተሰቦች የመንገር እና የማፅናናት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስነስርዓቶች በሁሉም አካባቢ እየተከወነ ይገኛል።

በመቐለ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ሰሞኑን መታዘብ እንደሚቻለው የዘመዶቻቸው የህልፈት ዜና የተነገራቸው በርካታ ቤተሰቦች ሐዘን ተቀምጠዋል። በየአብያተ ክርስትያኑ እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ የቀጠለ የሞቱትን የማሰብ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስነስርዓቶች እየተከወኑ ነው።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በጦርነቱ ወቅት ያለፉ የቀድሞ ታጋዮች ለማሰብ ከነገ ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኞ የሚዘልቅ የሶስት ቀናት ብሔራዊ ሐዘን መታወጁ ያስታወቀ ሲሆን በእነዚህ ቀናት ሰማእታት ይታሰባሉ፣ ለቤተሰቦቻቸው መንግስት ይፋዊ መርዶ ይነግራል እንዲሁም እውቅና ይሰጣል ተብሏል።(#DW)


1.1 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን በ 24 ሰዓታት ዉስጥ ሰሜናዊ ጋዛን እንዲለቅቁ እስራኤል አሳሰበች!!

ሰባተኛ ቀኑን በያዘዉ የ ፍልስጤም - እስራኤል ጦርነት እስራኤል ከፍተኛ አጸፋዊ እርምጃን በፍልስጥኤም ላይ በመዉሰድ ላይ ትገኛለች።

እስራኤል በሀገሪቱ ላይ ከምታዘንበዉ ጥይት ጎን ለጎን የዉሃ ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የምግብ አቅርቦትን በጋዛ በማቋረጥ 2.5 ሚሊዮን ሰዎችን አደጋ ላይ ጥላለች።

እስራኤል አወጣች በተባለዉ ማሳሰቢያ በሰሜናዊ ጋዛ የሚኖሩ 1.1 ሚሊዮን ሰዎች በአፋጣኝ ወደ ደቡባዊ የጋዛ ክፍል በ 24 ሰዓታት ዉስጥ ለቅቀዉ እንዲጓዙ አዝዛለች ተብሏል። ይህም እስራኤል እወስደዋለሁ ባለችዉ የእግረኛ ወታደሮች ዘመቻ ጉዳት እንዳይደርስባችሁ ነዉ ብላለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ ይህን መሰል የጅምላ ዝዉዉር የማይቻል ሲል የጠቀሰዉ ሲሆን ሐማስ ሀሰተኛ የእስራኤል ማስጠንቀቂያ በመጠቀም የዉሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነዉ ብሎታል።

የኢራን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቤሩት በነበራቸው ቆይታቸዉ እንደተናገሩት ፤ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ያለችዉ የአየር ጥቃት ከቀለ በሌላ ግንባር ዉጊያ ሊከፈት እንደሚችል ጠቁመዋል። ይህም ጦርነቱ በአጎራባች ሀገራት ተሳትፎ ሊቀጥል እንደሚችል አመላክቷል።እስካሁን እስራኤል በፈጸመችዉ ጥቃት 1 ሺህ 537 ፍልስጤማውያን መገደላቸው የተዘገበ ሲሆን 6 ሺህ 6 መቶ በላይ የሆኑ ሰዎችም ቆስለዋል ተብሏል። በእስራኤል በኩልም ሐማስ በፈጸመዉ ጥቃት 1 ሺህ 300 ሰዎች መገደላቸዉ ተዘግቧል።


ሀናን ናጂ አህመድ👏

በኢትዮጵያ ደረጃ የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ናት።

ተማሪ ሀናን ናጂ አህመድ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ከዘንድሮ ተፈታኞች በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡

ተማሪ ሀናን ናጂ ባስመዘገበችው ውጤት በጣም ደስተኛ መሆኗን ገልጻለች።

በቀጣይም ለበለጠ ውጤት እንደመትተጋ ተናግራለች፡፡

የክሩዝ ሁተኛ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ነው፡፡


ሀማስ ከእስራኤል ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ አለ

በእስራኤል ድንገተኛ ጥቃት ያደረሰው ሀማስ "ለሁሉም የፖለቲካ ንግግሮች" በሬ ክፍት ነው ብሏል
የሀማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ቡድኑ “ዓላማውን በማሳካቱ" ከእስራኤል ጋር ለስምምነት ለመወያየት በሩ ክፍት ነው ብለዋል።

ሙሳ አቡ ማርዙክ ሀማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመወያየት ፈቃደኛ ነው ወይ ተብለው ሲጠየቁ "ለሁሉም የፖለቲካ ንግግሮች" በሩ ክፍት ነው ብለዋል።
ቅዳሜ ዕለት ሀማስ እስራኤል ላይ በአየር፣ በባህርና በምድር ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ እስራኤል ጦርነት አውጃለች።

በእስራኤል-ፍልስጤም ጦርነት የሟቾች ቁጥር ከአንድ ሽህ 100 በላይ ደርሷል። 
ጥቃቱን ተከትሎ በጎ ፈቃደኞች አስከሬንና የተጎዱ ሰዎችን ለመፈለግ ሲዘዋወሩ ታይተዋል።

ሆኖም የሙዚቃ ፌስቲቫል እየተካሄደ ባለበት ቦታ ቢያንስ 260 አስከሬኖች መገኘታቸው አስደንጋጭ ግኝት ሆኖ ተመዝግቧል። 

የእስራኤል የነፍስ አድን አገልግሎት በጋዛ አቅራቢያ በሚገኘው ኪቡትዝ ሬኢም በመቶዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖችን ማግኘቱን ተናግሯል።

ሀገሪቱ በጋዛ ሰርጥ አቅራቢያ በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በጅምላ አሰባስባ ከአሜሪካው 9/11 ጋር ተመሳሳይ ነው ለተባው ጥቃት ምላሽ እየሰጠች ነው።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የጋዛ ሲቪሎች ከሀማስ ቦታዎች እንዲርቁ በማስጠንቀቅ አካባቢውን ዶግ አመድ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።


ውጤት ነጌ ይለቀቃል ‼️

" ነገ ጥዋት 12 ሰዓት ላይ በዌብሳይት እና በSMS ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይቻላሉ። " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ


የ2015 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ያመጡት 3 በመቶዎቹ ብቻ ናቸዉ ተባለ!

የ2015 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡በዚህም በ2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 3.2 በመቶ ብቻ ከ50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሰጡት መግለጫ አሁንም በከተማ እና ገጠር ትምህርት ቤቶች መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ ሆኖ መታየቱን አመልክተዋል፡፡


እስራኤል ጦር እና በሐማስ ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች በደቡባዊ እስራኤል መቀጠላቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የእስራኤል ጦር በርካታ የደቡባዊ አካባቢዎችን መልሶ መቆጣጠሩን ሃሬትዝ የተሰኘው ሚዲያ የእስራኤልን ጦር ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ነገር ግን ቤይሪ እና ስዴሮት የተባሉ ግዛቶችን ጨምሮ በጋዛ ድንበር አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ውጊያዎች ቀጥለዋል ብሏል።በደቡባዊ እስራኤል እና በጋዛ ሰርጥ ከ400 በላይ የፍልስጥኤም ታጣቂዎች መገደላቸውን እንዲሁም በርካቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይን ዋቢ አድርጎ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።

የእስራኤል ባለስልጣናት ሃገሪቱ "አሁንም በጦርነት ላይ ነች። የእስራኤልን ግዛት እና ማህበረሰቦችን ከሃማስ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት በማጠናቀቅ ላይ ናት" ብለዋል። ዩናይትድ ኪንግደም ጄክ ማርሎዌ የተሰኘ ዜጋዋ መጥፋቱን እስራኤል በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል አስታውቃለች።

በጋዛ ድንበር አቅራቢያ በነበረ የዳንስ ፌስቲቫል ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት የደህንነት ስራ እየሰራ ነበር ተብሏል።እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በፈጸመችው ተከታታይ የአየር ጥቃቶች ቢያንስ 313 መገደላቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።

እስካሁን ቢያንስ 700 እስራኤላውያን መገደላቸውን እንዲሁም በርካቶች መታገታቸውን የእስራኤልን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል።


የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል።

የትምህርት ሚኒስቴር
የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል። በዚህም ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።

ተማሪዎችም ትክክለኛውን መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ገፆች ላይ እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።


ሰበር ዜና!

እስራኤል በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ ጦርነት አዋጅ አወጀች!!

ሐማስ በአስራኤል ላይ የሮኬት ጥቃቶችን ፈፅሟል፣ ታጣቂዎቹም ወደ እስራኤል መግባታቸውም ተገልጿል!

በርካታ የእስላማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ታጣቂዎች ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝረው ወደ ደቡባዊ እስራኤል ክፍል ዘልቀው መግባታቸው ተዘገበ።

ከጥቃቱ ቀደም ብሎ በርካታ ሮኬቶች ወደ አስራኤል ግዛት የተተኮሱ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በመላዋ አገሪቱ የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደውሎች ተሰምተዋል።

እስራኤልም በበኩሏ በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ ኢላማዎች የአየር ጥቃት ማካሄድ ጀምራለች።

በሮኬት ጥቃቶቹ አስራኤል ውስጥ አንድ ሰው የተገደል ሲሆን፣ በቴላቪቭ አቅራቢያ እና በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ ፍንዳታዎች መሰማታቸው ተነግሯል።የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን የሆነው ሐማስ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ ሲሆን፣ በ20ደቂቃ ውስጥ 5ሺህ ሮኬቶችን ወደ አስራኤል መተኮሱን ገልጿል።

የእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለሕዝባቸው " የእስራኤል ህዝብ ሆይ ፤ ጦርነት ላይ ነን ፤ ይህን ጦርነትም እናሸንፋለን " ብለዋል።

የእስራኤል የመከላከያ ኃይል ባወጣው መግለጫ “ቡድኑ ሰፊ የሮኬት ጥቃቶችን ወደ እስራኤል ግዛት ከተኮሰ በኋላ” በተለያዩ አቅጣጫዎች ደግሞ ታጣቂዎቹ ወደ እስራኤል ግዛት መግባታቸውን አስታውቋል። መግለጫው አክሎም የእስራኤል ጦር ኃይል ጠቅላይ ማዘዣ በተከፈተው ጥቃት ዙሪያ “ሁኔታዎች ግምገማ” እያካሄደ መሆኑን ጠቅሶ ሐማስ ለተፈጸመው ጥቃት “ኃላፊነት እና የአጸፋ እርምጃ እንደሚከተለው” ገልጿል።

በተጨማሪም በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች ቤታቸው እንዲቆዩ የተጠየቁ ሲሆን፣ በደቡባዊና በማዕከላዊ የአገሪቱ አካባቢ ያሉ ሲቪል ሰዎች ደግሞ ከጥቃት መጠለያዎች አቅራቢያ እንዲቆዩ ተነግሯቸዋል።
Via BBC


አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ትናት ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።

አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል።

ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ።

አስፈላጊ #መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/

አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።


በካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ህንፃ በከባድ መሳሪያ ተመታ። ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል። ሁለቱም ጄኔራሎች አንደኛው ሌላኛውን ለጥቃቱ ተጠያቂ እያደረጉ ነው።


"በመጪው ጥቅምት ወር በትግራይ አጠቃላይ የሀዘን አዋጅ ይታወጃል።" ጀ/ል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሰሜኑ ጦርነት ለሞቱ የክልሉ ተዋጊዎች በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት የሃዘን ቀን እንደሚያውጅ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ጀኔራል ታደሠ ወረደ ትናንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ክልላዊውን የሃዘን ጊዜ የሚያውጀውና ለሟች ቤተሰቦች በይፋ መርዶ የሚያረዳው፣ ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደኾነ ጀኔራል ታደሠ ገልጸዋል።

ጀኔራል ታደሠ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሟች ተዋጊዎችን ለመለየት ሰፊ ሥራ ሲሰራ እንደቆየም ጠቅሰዋል።

በሌላ መረጃ ልጃቸው ለተሰውባቸው እናቶች መርዶውን ለመናገር አመራሮች ገንዘብ እየጠየቁ ነው መባሉን ተከትሎ ጀነራል ታደሰ ቀጣዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ልጅዋ ለተሰዋባት የትግራይ እናት መርዶ ለመንገር ብር የሚያስከፍሉ አመራር እንዳሉ እናቃለን” ሲሉ ታደሰ ወረደ ትላንት በሰጠው መግለጫ ገልፀዋል። በመጪው ጥቅምት ወር በትግራይ አጠቃላይ የሀዘን አዋጅ ይታወጃል ብለዋል።

ጄነራል ታደሰ የሃዘን ቀኑ ጥቅምት 2 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጠናቀቀ በኃላ #ከምሽት ጀምሮ ይከናወናል ብለዋል። ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የሃዘን ቀን የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ፣ የመንግስትና የግል ሚድያዎች ሰማዕታትን የተመለከቱ መልእክቶች እንደማያስተላልፉ ተነግሯል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተደር ይህን የሀዘን ሂደት የሚያውክ ማንኛውም ነገር የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ ነው ሲል አስጠንቅቋል።


ከእገታ ለመለቀቅ 60ሚልዮን ብር የተጠየቀባቸው ሰዎች!

ከሶስት ቀን በፊት ከባቱ (ዝዋይ) ከተማ 17 ኪሜ ገባ ብሎ ወደሚገኘው የአሉቶ ጂኦተርማል ፕሮጀክት ሲጓዙ የነበሩ ስድስት ሰራተኞች በታጣቂዎች ታግተው እንደተወሰዱ ማምሻውን የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል፣ ከታጋቾቹ መሀል አንድ ኬንያዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ይገኛል።

እነዚህን ታጋቾች ለመልቀቅ የተጠየቀው ገንዘብ 60 ሚልዮን ብር ነው (ለእያንዳንዱ 10 ሚልዮን ብር)።

"የፕሮጀክቱ ባለቤት መብራት ኃይል እስካሁን ምን ተፈጠረ ብሎ እንኳን አልጠየቀም፣ ሲደወልላቸው አውቀናል ግን ምንም ማድረግ አንችልም ይላሉ" ብሏል አንደኛው የመረጃ ምንጭ።

አክሎም "መንገድ ላይ ከV8 መኪና አስወጥተው ነው የወሰዷቸው። ሌላ ሪቮ መኪና ከኋላ የደረሰ ቢሆንም በሪቮ ውስጥም ካሉት ሁለቱን ወስደው የቀሩትን በእድሜ ገፋ ያሉትን፣ የሪቮ ሹፌሩን እና ምግብ አብሳይ የነበሩትን ብሎም አንዲት ሴት ኬንያዊትን የተወሰነ መንገድ ከወሰዷቸው በኋላ በፍጥነት ሊሄዱላቸው ስላልቻሉ ተመለሱ ብለው ለቀዋቸዋ። እነሱ ናቸው የሰራተኛ ካምፕ ተመልሰው መታገታቸውን የነገሩን" ብለው ጉዳዩን አስረድተውኛል።

"60 ሚሊዮን ቀርቶ 60 ሺህ ብር ማግኘት እንዴት እንደሚከብድ... ቤተሰብ በጣም ተጨንቋል... የስራ ባልደረቦቻችን ሁሉ ተረብሸዋል... እባካችሁ ድምፅ ሁኑን" ብለዋል።

Va :- Elias Meseret

Показано 18 последних публикаций.

3 319

подписчиков
Статистика канала