አ.አ ነገ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች!!
116ኛውን የኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በዚህም መሠረት፦
👉 ከ22 አደባባይ ወደ ወደ ቅዱስ ዑራኤል -መስቀል አደባባይ
👉 ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ
👉 ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
👉 ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ
👉 ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ ጋዜቦ አደባባይ (መስቀል ፍላዎር አደባባይ ላይ )
👉 ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኤግዚብሽን ውስጥ ለውስጥ ወደ ፊላሚንጎ
👉 ከቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ወደ ለገሃር መብራት
👉 ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ
👉ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር መብራት
👉ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ )
👉ከጥይት ቤት ወደ ቅዱስ ገብርኤል
ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ
👉ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ ላይ) ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።
በተጨማሪም፦
👉 ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም
👉 ከብሔራዊ ቤተጰመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ማለትም ከ25/08/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ ሲሆን እንዲሁም ለዚሁ ፕሮግራም ሲባል ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በመስመሮቹ ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ