ኢትዮ መረጃ - NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@B_promotor

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ወሊሶ በደረሠ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ወረዳ በደረሠ  የተሽከርካሪ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ ፣3-83143 ኢቲ የጭነት ተሽከርካሪ ሴኖትራክ ተሽከርካሪ ከጐሮ ወደወሊሶ ሲጓዝ ከወሊሶ ወደ ወልቂጤ አስራ ሰባት ሰው አሣፍሮ  ሲጓዝ ከነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ጋር በመጋጨቱ  የሚኒባሱ ሹፌሩን ጨምሮ ወዲያው አራት ሠዎች ህይወት አልፏል።

በሆስፒታል ደግሞ ሑለት ሰው በአጠቃላይ ስድስት ሠው ሲሞት አስራ አንድ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። አደጋው ዛሬ ንጋት ላይ የደረሠ ሲሆ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወሊሶ ቅዱስ ሉቃስ ሆስፒታል በህክምና ድጋፍ ላይ እንደሚገኙ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሠ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

#ዳጉ_ጆርናል

@sheger_press
@sheger_press


❖ የሚዲያ ንቅናቄ ዘመቻውም እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም ከቤተ-ክርስቲያን የሚዲያ አካላት ጋር በመነጋገርም ዶክሜንተሪዎችን እንዲሰሩና ምዕመኑ ገዳማዊያኑ ያሉባቸውን ችግሮች በመረዳት ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማስቻል ስራዎች የሚሰሩ ይሆናል፡፡

‹ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሄር ያበድራል፣በጎነቱንም መልሶ ይክፍለዋል› እንዲል ጠቢቡ ሰለሞን፣ ለዓለሙ ሰላም፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ድህነት ዘወትር የሚማጸኑት እነዚህ ገዳማዊያን፣ ያሉባቸው ችግሮች ተፈተውላቸው፣ ዓለሙን ትተው የሄዱበትን ፈጣሪን መማጸን ላይ ብቻ እንዲያደርጉ፣ ሁሉም ምዕመን ድጋፍ እንዲያደርግ በልዑል እግዚአብሄር ስም ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444


🙏🙏🙏❤️❤️❤️

ተመስገን.........

በሶሻል ሚዲያ ንቅናቄ ከ 12,000,000 ብር በላይ የተሰባሰበ ቢሆንም አሁንም ገዳሙ ድጋፍ ይፈልጋል"

በማዕከላዊ ጎንደር ሐገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሚገኘው ይህ ገዳም፣ ከዘጠና በላይ መነኮሳትና በመቶ የሚቆጠሩ ፀበልተኞች የሚገኙበት እጅግ ድንቅ ተዓምር ያለበት ታሪካዊ የአንድነት ገዳም ቢሆንም መነኮሳቱ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ችግር ተጋርጦባቸው ይገኛሉ።

በአንድ በኩል አካባቢው በርሃማ በመሆኑ በበጋ ወቅት ለከፍተኛ ድርቅ ይጋለጣል፣በዚህም ምክንያት ምንም ዓይነት አዝዕርት አይበቅልበትም፣ይህን ተከትሎ ቀደም ሲል ድጋፍ ያደርጉ የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ሳይቀር ለገዳሙ ምንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ተቸግረዋል።

ገዳማዊያኑ የሚቀምሱት እህል፣የሚለብሱት ልብስ በመጠኑ የተሟላላቸው ቢሆንም ከጾም፣ ጸሎት መልስ ስጋቸውን የሚያሳርፉበት በዓት (ቤት) የላቸውም። በአንድ ደሳሳ ጎጆ በዓት ውስጥ ለሶስት ለአራት የሚያድሩበት በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ዉስጥ ይገኛሉ።

በዚህ ገዳም የሚገኙ ገዳማዊያን ዛሬም ከጸሃይ፣ ከብርድ፣ ከዝናብ የሚከላከል መጠለያ አጥተው በከፍተኛ ችግር እየተፈተኑ የሚገኙ በመሆኑ፣ ገዳማዊያኑን ከነዚህ ችግሮች እንዲወጡና በቀጣይም ገዳሙ ራሱን እንዲችል ለማድረግ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት እውቅና እና በሐገረ ስብከቱ ፍቃድ ገዳሙ ብቻ የሚጠቀመው በገዳሙ ስም የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ይፋ ተደርገው፣ በሕዝበ ክርስቲያኑ በሚደረገው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፣ ገዳሙም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በወረዳ ቤተ-ክህነት፣በሐገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጸድቆ በሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬና የቅርብ ክትትል እየተደረገበት በመሰራት ላይ ይገኛል።

እነዚህን የታቀዱ ለገዳሙ አስፈላጊ እና መሰረታዊ የሆኑትን የልማት ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ገቢ ለማሰባሰብ የሚረዱ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን ለመጠቀም ጥረት ተደርጓል።

ከነዚህም ውስጥ፦ ገዳሙ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የሚገልጹ እና የሚያሳዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እንዲሁም ትሁፊት በጠበቀ መልኩ፡

❖ በቴሌቪዥንና ራዲዮን ማስታወቂያዎችን በማስተላለፍ ሕብረተሰቡ መረጃዉ ኖሮት የተቻለውን ድጋፍ እንዲያደርግ

❖ በማሕበራዊ ሚዲያ ማለትም፡ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ፣ በቲክቶክ፣ በቴሌግራም፣ በኢንስታግራምና ሌሎችንም በመጠቀም ለታቀዱት የልማት ሥራዎች የሚያስፈልገውን ገቢ ለማሰባሰብ ጥረት ተደርጓል።

በዚህም እስካሁን 11,000,000.00 (አስራ አንድ ሚሊዮን) ብር የሚያህል የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም 1,200,000.00(አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር የሚሆን የአይነት ድጋፍ ማሰባሰብ ተችሏል።

ፕሮጀክቱ ከተጀመረ 11(አስራ አንድ) ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን በነዚህ ጊዚያት በመጀመሪያው ምዕራፍ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።

ከተሰሩ ስራዎች መካከል ፡-

❖ የእናቶች በዓት ወይም ቤት በጥሩ ሁኔታ ተሰርቷል።

❖ 170 ሜትር ተራራ ተቦርቡሮ ለእናቶችም ለአባቶችም ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበረው ቦታ በአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት ለገዳማዊያን እንቅስቃሴ ምቹ እንዲሆን ተደርጓል።

❖ በአካባቢው ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት ያልነበረ ሲሆን አሁን የሶላር መብራት ተሟልቶ የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ ተችሏል።

❖ ቤተ-እግዚአብሔር ወይም ማዕድ ቤት ተሰርቷል፤ የሚያስፈልጉ ሙሉ ቁሳቁሶችም ተሟልተዋል።

❖ ገዳማዊያኑ በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸውን የምግብ አቅርቦት ችግር እና የአቅም ውስንነት በዘላቂነት ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

❖ ለገዳማዊያኑ የእደ-ጥበባት ውጤቶችን ማምረቻ ሼድ ግንባታ ተከናውኗል እንዲሁም የሸማ ስራ ሙያ እንዲሰለጥኑ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፣ ለስራው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች እና የጥሬ እቃ ግብዓቶችም ተሟልተዋል።

❖ የሻማ እና የጧፍ መስሪያ ማሽን ግዢ ተከናውኗል።

❖ አካባቢው በተደጋጋሚ በድርቅ የሚጠቃ በመሆኑ ለገዳማዊያኑ የተሻለ ለማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

❖ ወደ ገዳሙ የሚያደርስ 8 (ስምንት) ኪሎ ሜትር ደረጃ አንድ የጠጠር መንገድ ሥራ ተሰርቷል።

❖ የእናቶች የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ተከናውኗል።

❖ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል የሲምንቶ ማቡኪያ ማሽን፣የብረታ ብረትና የእንጨት መስሪያ ማሽነሪ ግዥ ተፈጽሟል።

❖ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የገዳሙ ይዞታ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ያልነበረው በመሆኑ የገዳሙ ህጋዊ ይዞታው እንዲረጋገጥለት ተደርጓል።

❖ ገዳማዊያኑ እየሰሩ ቀጣይነት ያለው ገቢ እንዲያመነጩ ለማድረግ በማሰብ በሃሙሲት ከተማ የሸቀጣ ሸቀጥ እና የንዋያተ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ተከፍቶ ወደ ስራ ተገብቷል።

❖ ለግንባታ የሚውል በሃሙሲት ከተማ 30 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከመንግስት በሊዝ በመውሰድ በዚህም የአብነት ት/ቤት ፣ አለማዊ ት/ቤት እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ በተጨማሪም ሌሎችም ለገዳማዊያኑ አስፈላጊ የሆኑ የልማት ስራዎች የሚሰሩበት ይሆናል።

የልማት ስራዎች ከተጀመሩ አጭር ጊዜ በመሆኑ እስካሁን የተሰሩ ስራዎች አበረታች ቢሆኑም ከዚህ በተሻለ ፍጥነት መስራት እንዳይቻል የተለያዩ ተግዳሮቶች አጋጥመዋል፡፡

❖ በገዳሙ ውስጥ ስራ የሚሰራባቸው ቀናት ውስን መሆን፤ ማለትም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ገዳማዊያኑም የሚያከብሯቸው በዓላት ሲጨማመሩ በወር ውስጥ የሚሰራባቸው ቀናት ከ 4 (አራት) – 14 (አስራ አራት) የሚሆኑ ቀናት ብቻ ናቸው።

❖ በግንባታ እቃዎች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚስተዋል የዋጋ ልዩነትም አንዱ ችግር ነው።

❖ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ተጠቃሽ ሲሆኑ

❖ ከሚዲያው አካባቢ በተለይም ቲክቶክ አንዳንድ ቲክቶከሮች ፣ የገዳሙ አባቶችን ሆነ የቤተክርስቲያን መዋቅር ምንም አይነት መረጃ ሳይጠይቁና ያለ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ በይመስለኛል ብቻ፣ የገዳሙንም የተከታዮቻቸውንም ክብር በማይመጥን መልኩ ተገቢና ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን ማሰራጨት የሚሉት ከብዙዎቹ ተግዳሮቶች ጥቂቶቹ እነዚህ ናቸው።

እስካሁን የተከናወኑ ስራዎች በተለይም የእናቶችን ችግር በመቅረፍ ደረጃ ጥሩና አስደሳች ቢሆንም በአባቶች በኩል ገና ብዙ ስራዎች ይቀራሉ፡፡በመሆኑም በቀጣይ በትኩረት ከሚሰሩ ስራዎች መካከል፡-

❖ የአባቶች በዓት ግንባታ ሥራ

❖ የአባቶች ቤተ እግዚአብሔር ግንባታ ሥራ

❖ የአባቶች የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ
❖ የእንጨት እና የብረታብረት ውጤቶችን ማምረቻ ሼድ ግንባታ ሥራ፣
❖ የእህል መጋዘን ግንባታ ሥራ

❖የቅዱስ ሚካኤል ህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ ሥራ

❖ የአብነት ት/ቤት ፣ ዓለማዊ ት/ቤት እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ ግንባታ ሥራ

❖ የጸበልተኞች ማረፊያ ቤት ግንባታ ሥራ እንዲሁም

❖ የውሃ እና መብራት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ በቀጣይ ከሚሰሩት ስራዎች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በቀጣይ ለሚሰሩት የልማት ሥራዎች ማከናወኛ የሚሆን ድጋፍን ለማሰባሰብ በቀጣይም የተለያዩ መርሀ-ግብሮች የሚከናወኑ ይሆናል።

ለአብነትም፡-

❖ ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ምዕመኑ ከገዳሙ በረከት እንዲያገኙ እንዲሁም ገዳሙን እንዲጎበኙ የጉዞ መርሃግብር ተዘጋጅቷል።

❖ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ-ግብር በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የሚከናወን ይሆናል።

❖ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያ በተገኙበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ጉባኤ ይኖራል፤


በትግራይ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ 20 ሰዎች መቁሰላቸው ተነገረ

በትግራይ ክልል መዲና መቀለ አቅራቢያ በምትገኘው ሰሐርቲ ወረዳ፣ ረቡዕ፣ የካቲት 12/ 2017 ዓ.ም ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ 20 ሰዎች መቁሰላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሰሐርቲ ወረዳ፣ አዲስ አለም ቀበሌ አጽገብታ መንደር የተፈጸመውን ይህንን ጥቃት አውግዞ፣ ፖለቲካዊ አላማ እንዳለው በመግለጽ፤ አንዳንድ የትግራይ ሰራዊት አዛዦችን በድርጊቱ ከሷቸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ

#Ethiopia | የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡

የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው። ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው፡፡

በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ አሉ፡፡

በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የፈተና ዝግጅቱ፡-
1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣
2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።

ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ ይሆናል።

በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

ስለሆነም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት!
የካቲት 2017 ዓ.ም

@sheger_press
@sheger_press


ለሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም 11 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለፀ
I በማዕከላዊ ጎንደር ሐገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንደነት ገዳም፣ ከዘጠና በላይ መነኮሳትና በመቶ የሚቆጠሩ ፀበልተኞች የሚገኙበት ታሪካዊ የአንድነት ገዳም ቢሆንም መነኮሳቱ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ችግር ተጋርጦባቸው እንደሚገኝ ተነግሯል።
ገዳማዊያኑ የሚቀምሱት እህል፣ የሚለብሱት ልብስ በመጠኑ የተሟላላቸው ቢሆንም ከጾም፣ ጸሎት መልስ ስጋቸውን የሚያሳርፉበት ቤት የላቸውም፣ በአንድ ደሳሳ ጎጆ ቤት ውስጥ ለሶስት ለአራት የሚያድሩበት በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ዉስጥ እንደሚገኙ ነው የተገለፀው።
ገዳማዊያኑን ከነዚህ ችግሮች እንዲወጡና በቀጣይም ገዳሙ ራሱን እንዲችል ለማድረግ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት እውቅና እና በሐገረ ስብከቱ ፍቃድ ገዳሙ ብቻ የሚጠቀመው በገዳሙ ስም የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ይፋ ተደርገው፣ በሕዝበ ክርስቲያኑ በሚደረገው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፣ ገዳሙም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በወረዳ ቤተ-ክህነት፣ በሐገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጸድቆ በሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬና የቅርብ ክትትል እየተደረገበት በመሰራት ላይ ይገኛል ተብሏል።
ገዳሙ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የሚገልጹ እና የሚያሳዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እንዲሁም ትሁፊት በጠበቀ መልኩ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎችን በማስተላለፍ ሕብረተሰቡ መረጃዉ ኖሮት የተቻለውን ድጋፍ እንዲያደርግ ተደርጎ በዚህም እስካሁን 11,000,000 (አስራ አንድ ሚሊዮን) ብር የሚያህል የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም 1,200,000 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር የሚሆን የአይነት ድጋፍ ማሰባሰብ እንደተቻለ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ ከተጀመረ 11 (አስራ አንድ) ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን በነዚህ ጊዜያት በመጀመሪያው ምዕራፍ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።
ከተሰሩ ስራዎች መካከል ፡-
❖ የእናቶች በዓት ወይም ቤት በጥሩ ሁኔታ ተሰርቷል።
❖ 170 ሜትር ተራራ ተቦርቡሮ ለእናቶችም ለአባቶችም ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበረው ቦታ በአርማታ ደረጃ ተሰርቶለት ለገዳማዊያን እንቅስቃሴ ምቹ እንዲሆን ተደርጓል።
❖ በአካባቢው ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት ያልነበረ ሲሆን አሁን የሶላር መብራት ተሟልቶ የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ ተችሏል።
❖ ቤተ-እግዚአብሔር ወይም ማዕድ ቤት ተሰርቷል፤ የሚያስፈልጉ ሙሉ ቁሳቁሶችም ተሟልቷል።
❖ ገዳማዊያኑ በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸውን የምግብ አቅርቦት ችግር እና የአቅም ውስንነት በዘላቂነት ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
❖ ለገዳማዊያኑ የእደ-ጥበባት ውጤቶችን ማምረቻ ሼድ ግንባታ ተከናውኗል እንዲሁም የሸማ ስራ ሙያ እንዲሰለጥኑ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፣ ለስራው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች እና የጥሬ እቃ ግብዓቶችም ተሟልተዋል።
❖ የሻማ እና የጧፍ መስሪያ ማሽን ግዢ ተከናውኗል።
❖ አካባቢው በተደጋጋሚ በድርቅ የሚጠቃ በመሆኑ ለገዳማዊያኑ የተሻለ ለማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
❖ ወደ ገዳሙ የሚያደርስ 8 (ስምንት) ኪሎ ሜትር ደረጃ አንድ የጠጠር መንገድ ሥራ ተሰርቷል።
❖ የእናቶች የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ተከናውኗል

❖ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ማቡኪያ ማሽን፣ የብረታ ብረትና የእንጨት መስሪያ ማሽነሪ ግዥ ተፈጽሟል
❖ የገዳሙ ይዞታ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ያልነበረው በመሆኑ የገዳሙ ህጋዊ ይዞታ እንዲረጋገጥ ተደርጓል።
❖ ገዳማዊያኑ ቀጣይነት ያለው ገቢ እንዲያመነጩ በማሰብ በሃሙሲት ከተማ የሸቀጣ ሸቀጥ እና የንዋያት ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ተከፍቶ ወደ ስራ ተገብቷል።
❖ ለግንባታ የሚውል በሃሙሲት ከተማ 30ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከመንግስት በሊዝ በመውሰድ የአብነት ት/ቤት፣ አለማዊ ት/ቤት እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ በተጨማሪም ሌሎችም ገዳማዊያን አስፈላጊ የሆኑ የልማት ስራዎች የሚሰሩበት ይሆናል።
ከሚዲያው አካባቢ በተለይም ቲክቶክ አንዳንድ ቲክቶክሮች የገዳሙ አባቶችን ሆነ የቤተክርስቲያን መዋቅር ምንም አይነት መረጃ ሳይጠይቁና ያለ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ በይመስለኛል ብቻ፣ የገዳሙንም የተከታዮቻቸውንም ክብር በማይመጥን መልኩ ተገቢና ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን ማሰራጨት ተገቢ አይደለም ተብሏል።
በቀጣይ ለሚሰሩት የልማት ሥራዎች ማከናወኛ የሚሆን ድጋፍን ለማሰባሰብ በቀጣይም የተለያዩ መርህ-ግብሮች የሚከናወኑ ይሆናል።
ለአብነትም፡-
❖ ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ምዕመኑ ከገዳሙ በረከት እንዲያገኙ እንዲሁም ገዳሙን እንዲጎበኙ የጉዞ መርሃግብር ተዘጋጅቷል።
❖ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ ግብር በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የሚከናወን ይሆናል።
❖ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ሊቃውንት ቤተክርስቲያን በተገኙበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ጉባኤ ይኖረናል፤
❖ የሚዲያ ንቅናቄ ዘመቻውም እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም ከቤተ ክርስቲያን የሚዲያ አካላት ጋር በመነጋገርም ዶክሜንተሪዎችን እንዲሰሩና ምዕመኑ ገዳማዊያኑ ያሉባቸውን ችግሮች በመረዳት ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማስቻል ስራዎች የሚሰሩ ይሆናል፡፡


@sheger_press
@sheger_press


አዲሱ ፖስፖርት ዛሬ ይፋ ተደረገ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ዘርጋሁት ባለው የኢ-ፓስፖርት ሲስተም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሚስጥራዊ ህትመትና ቴክኖሎጂ ልምድ አለው ከተባለው የጃፓኑ ቶፓን ሴኩሪቲ ኢትዮጵያ አ.ማ አማካይነት ዘመኑ በደረሰበት የሚስጥራዊ ህትመት የታተመ አዲስ ፖስፖርት ዛሬ የካቲ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ይፋ እያደረገ ነው፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


Alert News ‼️

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር፣ የትግራይ ጸጥታ ኃይል አባላት በደቡባዊ ምሥራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ ዓለም በተባለ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር በነዋሪዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በማለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን አውግዟል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የተወሰኑ የክልሉ ጸጥታ ኃይል አመራሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩን መዋቅሮች ለማፍረስ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው በማለት ከሷል። ጸጥታ ኃይሉ የአንድ ቡድን የሥልጣን መወጣጫ መሳሪያ ሊኾን እንደማይችል የገለጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ኹኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ክልሉ ከባድ ቀውስ ሊገባ ይችላል በማለት አስጠንቅቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው፣ ትናንት የተወሰኑ የጸጥታ ኃይል አባላት የቀበሌ አስተዳደሩ ማኅተሙን እንዲያስረክቡ ባስገደዱበትና፣ በዚሁ ወቅት ድርጊቱን በተቃወሙ ነዋሪዎች ላይ የኃይል ርምጃ በወሰዱበት ወቅት እንደኾነ ተገልጧል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


ጥቆማ‼️

በሀገራችን እውቅ ጋዜጠኞች የተመሰረተና ታማኝ የዜና ምንጮችን የሚያገኙበት የቴሌግራም ቻናል ነው!

ሊንክ👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0


ኤርትራ በአዲስ አበባ ያለውን ኤምባሲዋን እየዘጋች መሆኑ ታወቀ

ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ግንኙነታቸው እየሻከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት የቃላት ጦርነት መጀመራቸውን ተከትሎ ኤርትራ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እየዘጋች መሆኑ ታውቋል።

የዛሬ ሰባት አመት ገደማ ግንኙነታቸውን ያደሱት ሁለቱ ሀገራት በትግራይ የተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ላይ በጋራ ቆመው ቢዋጉም የፕሪቶሪያው ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ግንኙነቱ መሻከር መጀመሩ ይታወሳል።

"ኤምባሲው ከዚህ በኋላ የአፍሪካ ህብረት ተወካዩን ይዞ ይቀጥላል፣ በኢትዮጵያ ያለውን የኤምባሲ ስታፍ ግን እያሰናበተ ነው" ያሉን አንድ የኤምባሲው ምንጫችን ሂደቱ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኤርትራ መንግስት የአፍሪካ ቀንድን የማተራመስ አላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው፣ በአስቸኳይ እንዲቆም መደረግ አለበት በማለት አልጀዚራ ላይ በቀረበ ፅሁፋቸው አስነብበው ነበር።

የኤርትራው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ለዚህ ምላሽ የሰጡ ሲሆን የፕሬዝደንቱን አስተያየት አጣጥለው የኢትዮጵያን መንግስት የቀጠናውን ሀገራት በመተንኮስ ከሰዋል።

የኤርትራ ኤምባሲ መዘጋት መጀመርን ተከትሎ በአስመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እጣ ፈንታ እስካሁን አልታወቀም። ላለፉት ጥቂት አመታት ኤምባሲው ክፍት ቢሆንም አምባሳደር ሳይመደብበት መቆየቱም ይታወሳል።
(MeseretMedia)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


በአዲስ አበባ በየቀኑ 7ሺህ አሽከርካሪዎች ይቀጣሉ ተባለ።

በአዲስ አበባ በየቀኑ በአማካይ 7,183 አሽከርካሪዎች በትራፊክ ደንብ መተላለፍ በትራፊክ ፖሊስ ብቻ ይቀጣሉ።

ይህ በሌሎች የትራፊክ ደንብ ታላፊዎችን የሚቀጡትን አይጨምርም።

ባለፉት በስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች ከአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ዘጠና ሦስት ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ ተቀጥተዋል፡፡

ይህም በየቀኑ 7183 አሽካርካሪዎች መቀጣታቸውን ያሳያል ሲል ሸገር ሬዲዮ ነው የዘገበው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news


መረጃ‼️

የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር፣ ለከተማዋ የኮሪደር ልማት ከመደበው 15 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚኾነውን ከከተማው ነዋሪዎች ለመሰብሰብ ማቀዱ ገልጿል።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ፣ የከተማ አስተዳደሩ ለኮሪደር ልማቱ ከትልልቅ ባለሃብቶች፣ ነጋዴዎች፣ ነዋሪዎችና ከመኖሪያ ቤትና የንግድ ድርጅቶች አከራዮች በደረሰኝ ገቢ እየሰበሰበ መኾኑንና በተያዘው ዓመት 1 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን ተናግረዋል።

የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋይ ነጋዴዎች 30 ሺሕ ብር፣ የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች 15 ሺሕ ብር፣ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋይ ነጋዴዎች 10 ሺሕ ብር፣ የመኖሪያ ቤት አከራዮች 2 ሺሕ ብር እና ነዋሪዎች 1 ሺሕ ብር እና ከዚያ በላይ እንዲከፍሉ እየተደረገ መኾኑን ዋዜማ ተረድታለች።

በኮሪደር ልማቱ ቀጥታ ተጠቃሚ የኾኑ ወይም መንገድ ዳር የሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት፣ የግል ድርጅቶችና ባለሃብቶች ለብቻ ተመን እንደወጣላቸው ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል።


#በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁአን ናቸው


ጌታችንን ያጠመቀው ቅዱስ ዮሐንስ፣ ሰማይን ዝናብ እንዳይሰጥ የዘጋው ነቢዩ ቅዱስ ኤልያስ የገዳማዊ ሕይወት ድንቅ ምሳሌዌች ናቸው።

በበረሀ ሲኖሩ ጸጉራቸው የተንዠረገገ፣ ከሰው ርቀው በእግዚአብሔር ዓላማ የኖሩ ገዳማውያንም ናቸው።

በስጋዊው ዓለም ባላቸው ድርሻ ድሆች ሲሆኑ በመንግስተ ሰማያት ግን ከሁሉ የበለጡ ናቸው። እልጫውን ዓለምም አጣፍጠውታል።

ዛሬም ድርስ የእንርሱን እርእያነት የተከትሉ፣ ምንኩስናን የመረጡ፣ በገዳማዊ ሕይወት በጾምና በጸሎት የሚተጉ እናቶችና አባቶች በረከታቸው ለሀገርና ለወገን ተርፎ ይገኛል።

ታዲያ ገዳማቸውን በመደገፍ በዓታቸውን በማጽናት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን።


ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም
                        ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                        1000442598391
                        አቢሲኒያ ባንክ
                        141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


ኢትዮጵያ  የሚያስፈልጋት የኮንዶም መጠን ከአንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን በላይ ቢሆንም ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው 100 ሚሊዮን ብቻ መሆኑ ተነገረ

በኢትዮጵያ  ከፍተኛ  የሆነ የኮንዶም እጥረት መኖሩ ተመላክቷል።ኮንዶም የኤች አይ ኤቪ ኤድስ ስርጭትን ከመከላከል ባለፈ የአባላዘር እንዲሁም በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የመጣው የጉበት  በሽታን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ይታወቃል፡፡

በርካቶች  ለኮንዶም ያላቸው  ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑ በኤ ኤች ኤፍ የኤችአይቪ መከላከል እና ምርመራ አገልግሎት አድቮኬሲ ፕሮግራም ኃካፊ የሆኑት ቶሎሳ ኦላና በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

የኮንዶም አጠቃቀም ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆኑን ጥናቶች እንደሚያመላክቱ የተጠቆመ ሲሆን በኢትዮጵያ ኮንዶም በሶስት ዓይነት መንገድ  ከውጪ ይገባል። አንደኛው በነጻ  በበጎፍቃደኞች እና በመንግስት ሲገባ ሁለተኛው በዲኬቲ በኩል እንዲሁም ሶስተኛው በግዢ የሚገባ  መሆኑን  አንስተዋል፡፡ ይሁን እና በሶስቱም መልኩ  ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የኮንዶም መጠን ከመቶ ሚሊዮን የሚበልጥ አለመሆኑ ጠቅሰው ነገር ግን ኤችአይቪን ከመከላከል አንጻር የሚያስፈልገው ከአንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን በላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኤች አይቪ ኤድስ በትምህርት ቤት እና ከትምህትር ውጪ የመያዝ እድሉ  1.7 በመቶ  ጨምሯል የተባለ ሲሆን  በ2023 የተጠና ጥናት እንደሚያመላክተው በኤችአይ ቪ ኤድስ በደማችሁ ውስጥ ተገኝተዋል ከተባሉት አዲስ ታማሚዎች መካካል  ትልቁን ቁጥር  ማለትም 27 በመቶ የሚሆነው  የሚይዙት ዕድሜያቸው  ከ15 እስከ 24 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ናቸው፡፡ 

በተለያዩ ቦታዎች ኮንዶም መሸጥ በሌለበት ዋጋ እየተሸጠ ሲሆን  አግባብነት የሌለው መሆኑ ተመላክቷል። ካለው እጥረት አኳያ በተጋነነ ዋጋ እየተሸጠም ይገኛል፡፡ ኤ ኤች ኤፍ ኢትዮጵያ በየወሩ ከ60 ሺህ በላይ ኮንዶም በነጻ እየተሰጠ እንደሚገኝ እና በቅርቡ  ከ2ሚሊዮን በላይ ኮንዶም በመላው ሀገሪቱ የሚታደል እንደሆነ አቶ ቶሎሳ ኦላና ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

@sheger_press
@sheger_press

8k 0 11 2 30

ጥቆማ‼️

በሀገራችን እውቅ ጋዜጠኞች የተመሰረተና ታማኝ የዜና ምንጮችን የሚያገኙበት የቴሌግራም ቻናል ነው!

ሊንክ👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0


አንኳር ታሪክ❗️

ከአመታት በፊት ነው ። እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሪቻርድ ብሮንሰን ከፖርቶሪኮ ወደ ቨርጅን አይስላንድ ለመሄድ ፈልጎ በረራው ተሰርዞበት በጣም ተናደደ ።
ከዛ ወዲያው ወደ አንድ የግል  አውሮፕላን ማከራያ ድርጅት በመደወል መለስተኛ አውሮፕላን ተከራይቶ ፡ ልክ እንደሱ  በተመሳሳይ በረራ የተሰረዘባቸውን ሰወች ፡ ወደ ቨርጅን አይስላንድ ለመሄድ አውሮፕላን እንደተከራየና ፡ ከሱጋር መጓዝ ከፈለጉ 39 ዶላር ብቻ በመክፈል መሄድ እንደሚችሉ ነገራቸው ።

ሌሎች መንገደኞችን ለመሳብም ፡ በፓርከር ቨርጅን ኤርላይንስ የሚል ፅሁፍ በፓርከር ፅፎ ሰቀለ ።

ልክ እንደሱ ወደቨርጅን አይስላንድ ለመሄድ ፈልገው በረራ ተሰርዞባቸው የተጉላሉ ሰወች ፡ ሪቻርድ ብሮንሰንን ያቀረበላቸውን አማራጭ በመጠቀም 39 ዶላር እየከፈሉ በፓርከር ቨርጅን አይስላንድ የሚል ፅሁፍ በተጻፈበት አውሮፕላን ወደሚፈልጉበት ቦታ ተጓዙ ።

ሪቻርድ ብሮንሰን ከዚህ ጉዞ በኋላ ወዲያው ህዝብ ሳይጉላላ በአማራጭ ሊጓዝበት የሚችል አየር መንገድ ለማቋቋም ወሰኖ
አውሮፕላኖች በመግዛት  ፡ ወደቢዝነሱ ገባ ።

ከአመታት በኋላ ያ ፡ ሪቻርድ ብሮንሰን ተናዶ በተከራየው አውሮፕላን ላይ ቨርጅን ኤርዌይስ ብሎ በፓርከር በመጻፍ የተጀመረው ቢዝነስ ዛሬ ላይ አድጎ. ..
በዚህ አመት Airbus A330, Airbus A350 እና 787 Dreamliner 2  ን የመሳሰሉ ዘመናዊና ትላልቅ አውሮፕላኖችን ጨምሮ ከ45 በላይ አውሮፕላኖች ያሉት ግዙፍ አየር መንገድ ሆኗል ።
ሀብታም ጉዞ ተሰርዞበት ሲናደድ ....አየር መንገድ ነው የሚከፍተው  🤔
በነገራችን ላይ ይሄ ሰውዬ የሚገራርሙ ታሪኮች ያሉት ነው ሌላ ቀን እንመለስበታለን ።


#ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?


ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፤ ሚስቱም መካን ነበረች ልጅም አልወለደችም። የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ አንቺ መካን ነሽ፣ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ። እነሆ ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።

ሴቲቱም ለባልዋ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደ መጣ አልጠየቅሁትም ስሙንም አልነገረኝም። እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አሁን የወይን ጠጅ የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ ርኩስም ነገር አትብዪ አለኝ ብላ ተናገረች። ማኑሄም “ጌታ ሆይ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እባክህ እንደ ገና ወደኛ ይምጣ፤ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንድናደርግ ያስገንዝበን” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም። ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ለባልዋም “እነሆ በቀደም ዕለት ወደ እኔ የመጣው ሰው ደግሞ ተገለጠልኝ” ብላ ነገረችው።  


ማኑሄም ሚስቱን ተከትሎ መጥቶ “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን?” አለው። እርሱም፦ “እኔ ነኝ” አለ። ማኑሄም “ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? የምናደርግለትስ ምንድን ነው?” አለው። የእግዚአብሔር መልአክም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም “አንተ የግድ ብትለኝ መብልህን አልበላም፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበርና  “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” አለው። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።

መልአኩም ተአምራት አደረገ፣ ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ ሲወጣ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ በምድርም በግምባራቸው ተደፉ። እርሱም ዳግመኛ አልተገለጠላቸውም፤ ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ለሚስቱም “እግዚአብሔርን አይተናልና እንሞታለን” አላት። ሚስቱም “እግዚአብሔርስ ሊገድለን ቢወድድ ኖሮ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ከእጃችን ባልተቀበለን፣ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን፣ እንዲህ ያለ ነገርም በዚህ ጊዜ ባላስታወቀን ነበር” አለችው። ሴቲቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሶምሶን ብላ ጠራችው፤ ልጁም አደገ፤ እግዚአብሔርም ባረከው። የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444



Показано 19 последних публикаций.