Ministry of Education Ethiopia


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


የትምህርት ሚኒስትሩ በነገሶ ጊዳዳ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ተማሪዎችን አበረታቱ።
--------------------------------------------------------

የትምህርት ሚኒሰቴርና የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ የሚገኘውን የነጋሶ ጊዳዳ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመጎብኘት ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተማሪዎች ኩረጃና ስርቆት የሚጠየፉ፣ በራሳቸው የሚሰሩና ጊዜያቸውን በአግባቡ የሚጠቀሙ ጠንካራ ተማሪዎች እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ትምህርት ሰውን ሰው ያደረገ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ተማሪዎች ወደፊት የሚገጥማችሁ አለም ትልቅ እውቀት የሚፈልግ መሆኑን አውቃችሁ ለዛ መዘጋጀት ይጠበቅባችኃል ብለዋል።

እንደ ሀገር ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲማሩ ሀገራቸውን ከሌላው አለም ማወዳደር የሚችሉ ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን ለማፍራት በትምህርት ሚኒስቴር ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተገነቡ እንደሚገኝም አንስተዋል።

ተማሪዎች ጠንክረው በመማር ወደፊት ሀገራቸው ራሷን የቻለች፤ ለሌላ ሀገር የምትተርፍ እንድትሆን እንደሚያደርጓት እምነት እንዳላቸው በመግለፅ ይህን እንዲወጡ አደራ በማለት መልዕክታቸው አስተላልፈዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤
https://www.facebook.com/share/p/163sKpcEtq/


ዩኒቨርሲቲዎች ነፃ ምሁራዊ ውይይት የሚካሄድባቸው የሀገር የሀሳብና የእውቀት መሪ ሊሆኑ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ አሳሰቡ።
-----------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ አመራሮችና ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች ተልዕኳቸውን በሚገባ እንዲወጡ ከመንደር አስተሳሰብና ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በነፃነት እውነተኛ ምሁራዊ ውይይት የሚደረግባቸው የዚች ሀገር እውቀት መሪ ሊሆኑ ይገባል፤ ወደዛ እንዲሄዱም እንፈልጋለን ያሉ ሲሆን፤

ዩኒቨርሲቲዎች ትክክልና ስህተትን የሚለዩ ጥሩ ሥነ-ምግባር የተላበሱ ምሩቃንን የሚያፈሩ እንዲሁም ሙስናን የሚቃወሙና የሚከላከሉ ሊሆኑም እንደሚገባም አሳስበዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ሪሶርስ በአግባቡ ለመጠቀም የቅድሚያ ትኩረት ጉዳዮችን ለይተው በመስራት ችግሮችን ደረጃ በደረጃ መፍታት ይጠበቅባቸዋል ፤ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/12FGDNEuLcL/


በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓትን ወጥና ዲጂታላይዝድ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ።

-------------------------------------------------

(የካቲት 28/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የክልልና ከተማ መስተዳድር የትምህርት መረጃ አስተዳደር ባለሙያዎች፣ ስራ ሀላፊዎችና ሌሎች ቤለድርሻ አካላት ጋር እየተሠሩ ባሉ ስራዎች ላይ ምክክር አድርጓል።

በምክክር መድረኩ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ይበልጣል አያሌው የትምህርት ዘርፉን የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ለማዘመንና ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በማያያዝም በመከናወን ላይ ያሉ ጅምር ስራዎችን በሚገባው ፍጥነት በማጠናቀቅ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የመረጃ አስተዳደር ስርዓቱን ማዘመንና ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1DoRVfgfVp/


በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ግምቢ ከተማ ለሚገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መሠረት ድጋይ ተቀመጠ።
----------------------------------

(የካቲት 27/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ከተማ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መሠረት ድጋይ አስቀምጠዋል።

ሚኒስትሩ የግንባታውን ማስጀመሪያ መሠረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅትም የኢትዮጵያን ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል መሆኑን ተናግረዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ዛሬ የግንባታ ማስጀመሪያ መሠረት ድንጋይ የተቀመጠው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታም በአጭር ጊዜ ተጠናቆ የመማር ማስተማር ስራውን እንዲጀምር ይደረጋልም ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው ደረጃቸው የተሻሻሉና መሠረተ ልማታቸው የተሟላላቸው ትምህርት ቤቶችን መገንባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።

የዞኑ አመራሮች በበኩላቸው የትምህርት ቤቱ ግንባታ በመጀመሩ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

ከዚም በተጨማሪ ሚኒስትሩና አመራሮቹ በጊንቢ ከተማ በሚገኙት ቢፍቱ ግምቢ እና ሴና ግምቢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።


የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነቱን ለማረጋገጥ የሚካሄዱ ስራዎች የሁሉንም የልማት አጋሮችና ባለድርሻዎች የጋራ ተሳትፎና ርብርብ እንደሚጠይቁ ተጠቆመ፤
የሂዩማን ካፒታል (Human Capital) ፕሮጀክት መክፈቻና ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

------------------------------------------------------
(የካቲት 27/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስትር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ መርሃ ግብሩን ሲከፍቱ እንደገለጹት የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነቱን ለማረጋገጥ የሁሉንም የልማት አጋሮችና ባለድርሻዎች ቅንጅት ፣ ተሳትፎና ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ትምህርትን ለማዳረስ በተሰሩ ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አኳያ አሁንም ሰፊ ክፍተት መኖሩን ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል።፡

በትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሳደግ፣ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማትና ሌሎችም አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ስፋትና ጥልቀት ማሳደግ እንደሚገባም ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/12FfRxCiTBt/


የትምህርት ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ።
-------------------------------------------------
(የካቲት 27/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በመጎብኘት ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በጉብኝታቸውም ገተማ ሁለተኛ ደረጃ እና የነጌሶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትን ተመልክተዋል።

በዚሁ ጊዜ ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች አሁን ያሉበት ደረጃ የቀጣይ ህይወታቸው የሚወሰንበት በመሆኑ ጠንክራችሁ መማር ይጠበቅባችኋል፤ በፍፁም በጊዜ መቀለድ የለባችሁም ሲሉም አሳስበዋል።

ይህ ሀገር እንዲቀጥል የወደፊቱ ሀገር ተረካቢዎች እናንተ በመሆናችሁ በቀለም ብቻ ሳይሆን በስነ-ምግባርም የተመሰገናችሁ ልትሆኑ ይገባል ብለዋል።

አክለውም የሚቀጥለውን ትውልድ በመቅረፅ ረገድ ትልቁ ድርሻ የመምህሩ መሆኑን በማንሳት መምህራን የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሚገባ እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው ተማሪዎች የዓመቱ ትምህርት በአግባቡ ስለማይሸፈንላቸውና ስታንዳርዱን የጠበቀ የክፍል ፈተና ስለማይወስዱ መጨረሻ እየተቸገሩ መሆኑን ጠቅሰው መምህራን በዚህ ረገድ ትኩረት ሰጥተው መስራትና ተማሪዎች ተገቢውን እውቀት ይዘው ከክፍል ክፍል እንዲዛወሩ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አመራሮቹ በትምህርት ቤቶቹ በነበራቸው ጉብኝት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ እየተከናወነ እንደሆነና ተማሪዎችም ተረጋግተው እየተማሩ መሆኑን መመልከት መቻላቸውን ገልፀዋል።


ዩኒቨርሲቲዎች እውነተኛ የመማሪያ፣ የማስተማሪያ እንዲሁም ጥናትና ምርምሮች የሚሰሩባቸው ትክክለኛ የእውቀት መፈለጊያ ሰላማዊ ቦታዎች ሊሆኑ ይገባል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
-------------------------------------

(የካቲት 27/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በወለጋ ዩኒቨርስቲ በመገኘት ከዩኒቨርስቲው አመራሮችና ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል ።

በዚሁ ወቅት ዩኒቨርሲቲዎች እውነተኛ የመማሪያ፣ የማስተማሪያ እንዲሁም ጥናትና ምርምሮች የሚሰሩባቸው ትክክለኛ የእውቀት መፈለጊያ ሰላማዊ ቦታዎች ሊሆኑ ይገባል፤ ለዚህም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎሮም ሥራዎች አላማ ይህን ለማሳካት መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም የዩኒቨርሲቲዎችን አስተዳደር፣ አስተሳሰብና አጠቃላይ ባህል መቀየር አስፈላጊ በመሆኑ የዩኒቨርቲውን አመራር የመቀየር ሥራ መሰራቱን ጠቅሰዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የአካባቢያቸውን ፀጋ በመለየት ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ የህብረተሰቡን ህይወት መቀየር እና ለሀገራቸው ችግር መፍትሔ መፈለግ ይገባቸዋል ያሉ ሲሆን በዚህ ረገድ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1YPrspy2UE/


ማስታወቂያ
የሶስተኛው ዙር የ2017 ዓ.ም የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ እና የፈተና ጊዜን ስለማሳወቅ

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ በ https://ngat.ethernet.edu.et/registration የመመዝገቢያሊንክ በኩል ይከናወናል፡፡
ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።

የመፈተኛ ' USER NAME ' እና " PASSWORD ' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል፡፡

ማሳሰቢያ
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን በቀጣይ የምናሳውቅ ሆኖ በፈተና ወቅት የተሰጣችሁን User Name and Password፣ እና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታዋቂያ ይዛችሁ መቅረብ ይጠበቃባችኋል።

የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር

Показано 8 последних публикаций.