ኢትዮ - ኮን ሬድዮ ፕሮግራም/Ethio con radio perogram/


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Музыка


በግንባታው ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሳምንታዊ የባለሙያዎች ፕሮግራም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአሀዱ ሬድዮ 94.3 ትብብር
ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2፡30-3፡30 ሰዓት የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Музыка
Статистика
Фильтр публикаций


👉 ኢትዮ ኮን የዛሬ ምሽት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችን

🚧 👷♀🏢የሬድዮ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመንቀስ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የተለያዩ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን በመጋበዝ ዘርፉ ላይ ያላቸውን የሙያ ክህሎታቸውና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ነው፡፡

⭕️ ወቅታዊ ፕሮግራም

🔻 ኢትዮጵያውያን የዘርፉ ተዋናዮችና ባለድርሻ አካላት የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ምህንድስና ቀንና የአለም የሴቶች ቀን በድምቀት ተከብሯል፡፡ ክብረ በአሉን አስመልክቶ ወደ እናንተ የምናደርሰው ፕሮግራም ይኖረናል፡፡

⭕️ የእንግዳ ሰዓት

🔻 ለግንባታው ዘርፍ ጠቃሚ ነገር አለን ይሉናል የዛሬ እንግዳችን ፡፡ ማናቸው ʔ ምንድን ነው ጠቃሚው ነገርʔ የሚለውንና ሌሎችንም ጥያቄዎች የሚነሱበትን ፕሮግራም ጠብቃችሁ ትከታታሉ ዘንድ ከወዲሁ በአክብሮት ነው ምጋብዘው፡፡

✍️📞☎️ የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ጋር ይሁን!


🔵 ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ7 ሚሊየን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቀረበ

🔷 የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን 7 ሚሊየን ኩንታል ሲሚንቶ ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

🔷 ፋብሪካው የገበያ ተደራሽነቱን ለማስፋትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያለውን ተቀራርቦ የመስራት ባሕል ለማሳደግ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል፡፡

🔷 በዚህ ወቅትም የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የሲሚንቶ ምርት እጥረትና የሥርጭት ችግር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስና ዋጋ በማረጋጋት ቀዳሚ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

🔷 አሁን ላይም በቀን 100 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ እያመረተ ሲሆን÷በዚህም በኢትዮጵያ 33 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሲሚንቶ አቅርቦት መሸፈን መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

🔷 ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በ2017 በጀት ዓመት የጥንካሬ ደረጃዎችን ካሳኩ አቻ ኢትዮጵያዊያን ምርቶች በጥራት ተሸላሚ መሆን መቻሉም ተመላክቷል፡፡

🔷 በቅርቡ ወደ ሥራ የገባው ፋብሪካው ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ እና ቋሚ የሥራ እድል መፍጠሩ ተጠቅሷል፡፡

🔷 በቀጣይም በመላ ሀገሪቱ ያለውን የሲሚንቶ ተደራሽነት ለማስፋፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

(ኤፍቢሲ)


🔵 "በህይወት ማዉጣት ተችሏል"

🔷 ትላንት የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 7 ቤለር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በደረሰ የኮንስትራክሽን የስራ ላይ አደጋ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

አደጋዉ የደረሰዉ የመንገድ ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ለመቅበር በቁፋሮ ስራ ላይ በነበሩ ሁለት ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ መጠን ያለዉ አፈር ተንዶባቸዉ ነዉ።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ባለሞያዎች አምስት ሜትር ገደማ ጥልቀት ካለዉ ጠባብ ጉድጓድ ዉስጥ አፈር ተጭኗቸዉ የነበሩትን ሁለቱን ሰራተኞች 1:20 ሰዓት በፈጀ ጥረት በኋላ በህይወት ማዉጣት ችለዋል።

በህይወት የወጡት ሁለቱ ወጣቶች እድሜያቸው 27 እና 29 ዓመት የተገመተ ሲሆን በአደጋው ምክኒያት ጉዳት የደረሰባቸው በመሆኑ በኮሚሽኑ አምቡላንስ እየተረዱ ወደ ዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተገቢዉን የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቆ ባለመስራት መሰል አደጋዎች በተደጋጋሚ እያጋጠሙ በመሆኑ በተለይም አሰሪዎች የሰራተኞቻቸዉን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታቸዉን እንዲወጡም ኮሚሽን መ/ቤቱ ያሳስባል።

(እአሰኮ)


🔵 𝟮𝟱 𝗯𝗮𝘀𝗶𝗰 𝗲𝗹𝗲𝗺𝗲𝗻𝘁𝘀 𝗼𝗳 𝘁𝗵𝗲 𝗯𝘂𝗶𝗹𝗱𝗶𝗻𝗴 𝗲𝘃𝗲𝗿𝘆 𝗲𝗻𝗴𝗶𝗻𝗲𝗲𝗿 𝗺𝘂𝘀𝘁 𝗸𝗻𝗼𝘄

𝟭. 𝗖𝗼𝗽𝗶𝗻𝗴
𝟮. 𝗣𝗮𝗿𝗮𝗽𝗲𝘁 𝗪𝗮𝗹𝗹
𝟯. 𝗪𝗲𝗮𝘁𝗵𝗲𝗿𝗶𝗻𝗴 𝗖𝗼𝘂𝗿𝘀𝗲
𝟰. 𝗥𝗼𝗼𝗳 𝗦𝗹𝗮𝗯 (𝗥𝗖𝗖)
𝟱. 𝗕𝗿𝗶𝗰𝗸 𝗪𝗮𝗹𝗹
𝟲. 𝗦𝘂𝗻𝘀𝗵𝗮𝗱𝗲 (𝗖𝗵𝗮𝗷𝗷𝗮)
𝟳. 𝗟𝗶𝗻𝘁𝗲𝗹
𝟴. 𝗪𝗶𝗻𝗱𝗼𝘄
𝟵. 𝗪𝗶𝗻𝗱𝗼𝘄 𝗦𝗶𝗹𝗹 𝗟𝗲𝘃𝗲𝗹
𝟭𝟬. 𝗗𝗼𝗼𝗿
𝟭𝟭. 𝗙𝗹𝗼𝗼𝗿𝗶𝗻𝗴
𝟭𝟮. 𝗗𝗣𝗖 (𝗗𝗮𝗺𝗽 𝗣𝗿𝗼𝗼𝗳 𝗖𝗼𝘂𝗿𝘀𝗲)
𝟭𝟯. 𝗚𝗟 (𝗚𝗿𝗼𝘂𝗻𝗱 𝗟𝗲𝘃𝗲𝗹)
𝟭𝟰. 𝗦𝗮𝗻𝗱 𝗙𝗶𝗹𝗹𝗶𝗻𝗴
𝟭𝟱. 𝗖𝗼𝗻𝗰𝗿𝗲𝘁𝗲 𝗕𝗮𝘀𝗲 (𝗣𝗖𝗖)
𝟭𝟲. 𝗙𝗼𝗼𝘁𝗶𝗻𝗴/𝗙𝗼𝘂𝗻𝗱𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻
𝟭𝟳. 𝗘𝗻𝘁𝗿𝘆𝘄𝗮𝘆 𝗦𝘁𝗲𝗽𝘀
𝟭𝟴. 𝗣𝗹𝗶𝗻𝘁𝗵 𝗟𝗲𝘃𝗲𝗹
𝟭𝟵. 𝗦𝗸𝗶𝗿𝘁𝗶𝗻𝗴
𝟮𝟬. 𝗖𝗼𝗹𝘂𝗺𝗻
𝟮𝟭. 𝗕𝗲𝗮𝗺
𝟮𝟮. 𝗖𝗲𝗶𝗹𝗶𝗻𝗴
𝟮𝟯. 𝗦𝘂𝗽𝗲𝗿𝘀𝘁𝗿𝘂𝗰𝘁𝘂𝗿𝗲
𝟮𝟰. 𝗦𝘂𝗯𝘀𝘁𝗿𝘂𝗰𝘁𝘂𝗿𝗲
𝟮𝟱. 𝗕𝗲𝗱 𝗟𝗲𝘃𝗲𝗹 𝗼𝗳 𝗙𝗼𝘂𝗻𝗱𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻

***


👉 ኢትዮ ኮን የዛሬ ምሽት የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችን

🚧 👷♀🏢የሬድዮ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመንቀስ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የተለያዩ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን በመጋበዝ ዘርፉ ላይ ያላቸውን የሙያ ክህሎታቸውና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ነው፡፡

🔵 ወቅታዊ ፕሮግራም

🔷በሪል ስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግምታ አዋጅን በተመለከተ ከሪል ስቴት አልሚዎች የተዘጋጀውን የግንዛቤ መስጨበጫ መድረክ በዛሬው ወቅታዊ ፕሮግራማችን የምንመለከተው ጉዳይ ይሆናል፡፡

✍️📞☎️ የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ጋር ይሁን!


**ማስታወቂያ*

🔵በአዲስ አበባ ከተማ ለምትገኙ የሪል እስቴት አልሚዎች በሙሉ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሪል እስቴት ልማት ስራ ላይ የተሰማራችሁ አልሚዎች በሪል አስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅ እንዲሁም ይህንን ለማስፈጸም በወጣው ረቂቅ ደንብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ስለሚካሄድ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባምቢስ አጠገብ በሚገኘው በዲል ኦፖል ሆቴል ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት ጀምሮ ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪል የሆናችሁ ሁሉ በመገኘት የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪ እናሰተላልፋለን፡፡ 

🔷የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ


👉 ኢትዮ ኮን የዛሬ ምሽት የየካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችን

🚧 👷♀🏢የሬድዮ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመንቀስ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የተለያዩ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን በመጋበዝ ዘርፉ ላይ ያላቸውን የሙያ ክህሎታቸውና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ነው፡፡

⭕️ ወቅታዊ ፕሮግራም

🔻 የጀርመን የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ፌደሬሽን በተመለከተ እንግዳ ጋብዘን ቆይታ እናደርጋለን፡፡ ፌደሬሽኑ ከኮንስትራክሽን ከማህበራት ጋር ስለሚሰራው ስራ በተጨማሪም ጀርመን ሀገር ወስዶ ኮንስትራክሽን ምህንድስናው ዘርፍ ስለሚሰለጥኑትን ወጣቶች በተመለከተ  የምንወያይበት ጉዳይ ይሆናል፡፡

🔻የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ቃሊቲ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ፓራዳይዝ መሰብሰቢያ አዳራሽ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ዙርያ የተካሄደውን ውይይት አስመልክቶ ከኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር የተደረገ ቆይታ ይኖረናል፡፡

✍️📞☎️ የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ጋር ይሁን!


🔷በስካይ ላይት የተካሄደው ፕሮግራም በፎቶ







Показано 11 последних публикаций.