#MINISTRY_OF_EDUCATION
ጉዳዩ የተከለሰ የሪሜዲያል ሲለበስ ስለመላክ፤
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የሪሜዲያል ፕሮግራም ስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል። በዚሁ መሠረትም የማስፈጸሚያ ሲለበስ የሁለተኛ ደረጃ ሥርዓተ-ትምህርት ተዘጋጅቶ በተላከው መሰረት የመማር ማስተማር ሥራው ሲካሄድ ቆይቷል። ሆኖም የሁለተኛ ደረጃ ሥርዓተ-ትምህርት በመቀየሩ ሲለበሶቹን መቀየር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሠረት ስለበሶቹ ተከልሰው የተከለሰ ሲለበሶች በተፈጥሮ ሳይንስ ለፊዝክስ፣ ለኬምስትሪ ለሒሳብ፣ለባዮሎጂ እና እንግሊዝኛ እንዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ለጅኦግራፊ፤ ለታሪክ፤ሒሳብ (ለተፈጥሮ ሳይንስ ከተዘጋጀው ጋር ተመሳሳይነ እና ለአንግሊዝኛ (ከተፈጥሮ ሳይንስ ጋር ተመሳሳይ) ለሁሉም ተቋማት ተልከዋል፡፡ በመሆኑም የተላኩ ሲሰበሶች ላይ ለአፈጻጸም ያመች ዘንድ የሚከተሉትን ጉዳዮች ለተቋማት ግልፅ ማድረግ አስፈልጓል፡፡
1ኛ. በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የሪሜዲያል ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም አስራ ሁለተኛ ክፍል ላይ ብቻ በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት የተማሩ በመሆኑ 12ኛ ክፍል የሚመለከቱ ርዕሶች ብቻ በአዲሱ ሲለበስ የሚማሩ ይሆናል፡፡ እነዚህ ተማሪዎች የ9ኛ፣ 10ኛ፣ እና የ11ኛ ክፍል ትምህርታቸውን በነባሩ : ስርዓተ-ትምህርት ስለተማሩ ትምህርቱም የሚሰጠው በነባሩ
የሪሜዲያል ሲለበስ ይሆናል፡፡
2ኛ. በተላከው አዲሱ ሲለበስ ላይ እንደገለፀ ምዘናን በተመለከተ 50% የተከታታይ ምዘና 50 ደግሞ የማጠቃለያ ፈተና እና 100% ከማዕከል የሚሰጥ ፈተና እንዳለ ያሳያል፡፡ ይህ ማለት ተቋማት በተከታታይ ምዘና እና በማጠቃለያ ፈተና የየራሳቸውን ተማሪዎች የሚገመግሙት እንደተጠበቀ ሆኖ ከማዕክል 100% ተማሪዎቹ የሚፈተኑ መሆኑን ለማመላከት ነው፡፡
ኦ ሚጀና (ዶ/ር) የአካዳሚክ ጉዳዮች ም ኣስፈፃሚ
ሳራ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር
FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA MINISTRY OF EDUCATION
J. 13671 EEA HIP እዲስ አርማ ኢትዮጵያ
PO, ARADA BUDG ARABA, ETIOPIA
DATE
CHEF NO:
በየተቋማቱ የሚስጡ የተከታታይና የማጠቃለያ ፈተናዎች ውጤት በቀጣይ በሚላከው ቅፅ መሠረት ለትምህርት ሚኒስቴር ይላካል፤ በማዕከል የሚስጠው ፈተና የተማሪዎቹን የመቀጠልና ያለመቀጠል የሚወሰን ይሆናል፡
3ኛ, የዘንድሮው በማዕከል የሪዲያል ፈተና ከግንቦት 26-30/2017 ዓም የሚሰጥ መሆኑ ታውቆ ከወዲሁ ተገቢው ሁሉ ዝግጅት እንዲደረግ እናሳውቃለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
■ የኢትዮጵያ
ግልባጭ፡-
4 ለከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ጽ/ቤት + ለአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ
ትምህርት ሚኒስቴር
አባ ሚጀና ዶር) የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ
@ethiofreshman201