*አዳም የት ተፈጠረ?
*የምጽፈው መራራ ሃቅ ነው።ትናት ስለ ኖኅ ጽፈናል።ዛሬ ደግሞ አዳም የት ተፈጠረ? የሚለውን እንጽፋለን።
*የአዳም አባት መሬት ነው ከአፈር ተፈጥሯልና።
አዳም የተፈጠረው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።የተፈጠረበት አፈር "ስውሩ አፈር" ይባላል።አዳም በምድር ላይ የኖረው 930 ዓመት ነው።አዳም የሚለው ቃል አደመ፥ አማረ፣ተዋበ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ነው፡፡ስለዚህ የመጀመሪያው ፍጡር አዳም የስሙ ስያሜ የመጣው ከግእዝ ነው።
አዳም የተፈጠረው ከአራት ባህርያተ ሥጋ ማለትም፦ከነፋስ፣ከእሳት ፣ከውሀ፣ከመሬት
እንዲሁም ከሶስቱ ባህርያተ ነፍስ ማለትም ከልብ ፣ከቃል፣ከእስትፋስ ሲሆን የተፈጠረበት ቀን እለተ አርብ 3 ሰዓት ላይ ነው።ሲፈጠር የ30 አመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጠረ።
የተፈጠረበት ቦታ "ኤልዳ" ትባላለች።መጽሐፈ ሔኖክ አዳም የተፈጠረበትን ቦታ "ኤልዳ" ነው ይለዋል።አስገራሚ ነገር አሁንም ጎጃም ውስጥ አስሌዳውያን ( ኤልዳውያን) የሚባል ቦታ አለ።ኤልዳ ከግዮን አትርቅም።
ግዮን ደግሞ የኤደን ገነት የሚያጠጣ ወንዝ ነው። አዳም ኤልዳ ከሚገኝ አፈር ተፈጥሮ በ40ኛ ቀኑ የግዮን ወንዝ ወደሚያጠጣት የኤደን ገነት አስገባው።አዳም ለሰባት አመታት የኖረው የአዴንን ገነት በሚያጠጠው ግዮን (አባይ) ዙሪያ ነው።በዘፍጥረት ምዕራፍ ሁለት ከቁጥር 13 ግዮን የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።የሚያበራ ዕንቁና የሚያብረቀርቅ ዕንቁም ይገኝበታል።የግዮን ምንጭ ደግሞ ጎጃም ሰከላ ውስጥ ነው።
*በሳይንሳዊ ምርምር እንደተረጋገጠው በጎጃም በስተምዕራብ ፋዞግሊ የሚባል የወርቅ ማውጫ ቦታ ነበረ።ንጉሥ ድግናዣን በጎጃም በስተምዕራብ የሚገኘውን ፋዞግሊ የተሰኘውን የወርቅ ማምረቻ ለመቆጣጠር
መቶ ሺህ የሚያህል ሠራዊት ይዞ በበጌምድር በኩል ሲዘምት በአሸዋ ተውጦ ቀረ።ፋዞግሊ የወርቅ ማውጫን ዐፄ ካሌብ በአገዎች ያስጠብቀው ነበር።በደቡብ እየገነነ የመጣው የዳሞት መንግሥትም ይህንን የወርቅ ማውጫና የወርቅ ጎዳና ለመቆጣጠር ወደ ሰሜን ተጉዞ ነበረ።የዛግዌ መሥራች መራ ተክለ ሃይማኖትም በዚህ የወርቅ ጎዳና ጥበቃ ላይ ከተሠማሩት ኃያላን የጦር አዛዦች መካከል አንዱ ነበረ።ከላይ በጠቀስነው መረጃ አግባብ በግዮን ዙሪያ የሚያበራውና የሚያብረቀርቀው ዕንቁ ከታዋቂው የወርቅ ማውጫ ብዙም አይርቅም።
*አዳም በምድር ላይ የኖረው 930 ዓመት ነው። የተቀበረው ኮሬብ በሚባል ቦታ ነው።ኮሬብ የሚባል ቦታም በአምሓራ ሳይንት ይገኛል።ክሬብ የዮቶር ርስት ነው።ሙሴ በግ የሚጠብቅበት የነበረ ተራራ ነው።
*አራራት ተራራ የሚገኘው ጎጃም ዘጌ ነው
*የኖኅ ሚስት መቃብር የሚገኘው ጭልጋ አይከል ነው።
*የኖኅ መቃብር የሚገኘው ጎንደር ፋሲለደስ ግንብ ከተገነባበት ቦታ ላይ ነው።
*ግማደ መስቀሉ የሚገኘዎ ቤተ አምሓራ ግሼን ማርያም ነው።
*የቃልኪዳን ታቦቱ የሚገኘው አኩስም ነው።
*ቅዱስ ኡራኤል የክርስቶስን ደም የረጨበት ቅድስ ጽዋ ተሰውሮ የሚገኘው መንዝ-እመጓ ቆጵሮስ ተራራ ላይ ነው።
*በዚህ ጉዳይ ጥንታዊ ሰነዶች፣የተለያዩ መረጃዎች አሉኝ። አሠናድቸ በረድፍ በረድፍ የምጽፈው ይሆናል።እንዲያውም ከሺህ ዓመታት በፊት በግእዝ ቋንቋ የተጻፈ ጥንታዊ ሰነድ በአንድ አርሶአደር ጎጃም ውስጥ በአንድ ዋሻ ተገኝቷል።የጊዜና የገንዘብ ጉዳይ ሆኖ ነው እንጂ ይፋ ለማድረግ አስበናል።ቀርቦ ከሚያግዘን ይልቅ ዘርፎን ለመሄድ የሚያስበው ብዙ ስለሆነ በምስጢር ተይዟል።ይኼ ክቡር ጥንታዊ ሰነድ አነጋገሪ መሆኑ አይቀርም።ያልተገለጡትን ይገልጣቸዋል ብለን እናስባለን።የተሰወሩ ቦታዎችን፣ታሪኮችን፣ማዕድኖችን፣ፒራሚዶችን፣ቤተ መንግሥቶችን፣ቤተ መቅደሶችን ይጠቁማል ብለን እናስባለን።እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሆናል።
*አዲሱን የYou tube ቻናል subscribe በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ።YouTube ላይ ዘፈንና ቀልድ የምታዮትን ያህል ለጭንቅላታችሁ ደግሞ እውቀት ያስፈልገዋል።በቅርቡ አዳዲስ መረጃዎችን የምንለቅ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UC6m-V3zA2xrlwPPWtXLJ33A