*ሰባት ቁጥር የዓለም መጨረሻ...#share
*ሰባት ቁጥር ፍጹም ነው።6 ቁጥር ከ7 ተቀንሶ የሚገኝ በመሆኑ (7-1=6) ፍጹምነት የጎደለው ነገር ለመግለጥ ይውላል።666 የሚለው ምሳሌም
"ጎደሎ፣ጎደሎ፣ጎደሎ-ፍጹም ጎደሎ"መሆኑን ያመለክታል።
1.ሰባቱ ቀንዶች
2.ሰባት ሺው ሰማዕታት
3.ሰባቱ ራሶች
4.ሰባቱ ዘውዶች
5.ሰባቱ መለከቶች
6.ሰባቱ መቅሰፍቶች
*ሰባቱ ቀንዶች፦ዮሐንስ በራእዩ በዙፋኑ ላይ ያየው በግ ሰባት ቀንዶች ነበሩት።ቀንድ የኃይል፥የክብር እና የሥልጣን ምሳሌ ነው።(ራእይ.5፥6)
*ሰባት ሺው ሰማዕታት፦ሁለቱ ነቢያት ኤልያስ እና ሄኖክ የሚሰጡትን ምስክርነት ሰምተው በማመናቸው በሐሳዊው መሲሕ የሚሠውት ሰማዕታት ናቸው።(ራእይ.11፥13)
*ሰባቱ ራሶች፦ምእመናንን ለማረድ ቤተ ክርስቲያንንም ለማጥፋት የተነሣው አውሬ ሰባት ራሶች ነበሩት።ይህም ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ያለ የሌለ ዐቅሙን እንደሚጠቀም፤ከዚያ በፊት ታይቶ ተሰምቶ የማያውቅ ፍጹም አሰቃቂ የሆነን መከራ እንደሚያደርስ ያመለክታል።
( ራእይ.12፥3)
*ሰባቱ ዘውዶች፦ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት የተነሣው አውሬ ሰባት ዘውዶች ነበሩት።ይህም በየዘመናቱ የሚነሡ ባለሥልጣናትን፣ነገሥታትን እና መሪዎችን የሚጠቀም በእነርሱም የሚነግሥባቸው መሆኑን ያሳያል። (ራእይ.12፥3)
*ሰባቱ መለከቶች፦በእግዚአብሔር ልጆች ላይ መከራ እና ስደት ለሚያመጡት የተሰጠ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ማሳያ ነው።(ራእይ.8፥1፤11፥9)
*ሰባቱ መቅሰፍቶች እና ሰባቱ ጽዋዎች፦ለእግዚአብሔር ለአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ማስጠንቀቂያ በመስጠት (በመለከት) ብቻ አያቆምም ስለማይመለሱ እና ክፋታቸውን ስለማያቆሙ ወደ መቅሰፍት ይሸጋገራል።
(ራእይ.15፥1፤16፥21)
*ለአዳዲስ መረጃ፣ለታሪክ፣ለዶክመንተሪ፣ለ application፣ለፖለቲካ፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ግእዝ ለማወቅ ለወደፊቱ በቪዲዮ የታገዘ መረጃ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን subscribe አድርጉ።
https://www.youtube.com/channel/UC6m-V3zA2xrlwPPWtXLJ33A