ቻይና በግዳጅ ላይ እያለ እንቅልፍ ወስዶታል ያለችውን የጸረ ፈንጅ ውሻ ቀጣች
ውሻው ከዚህ በፊት ለየት ያሉ እና ያልተጠበቁ ስራዎችን ሰርቷል በሚል በርካታ ሽልማቶችን በማግኘት ዝናን ያተረፈ ነበር
ቻይና የጸረ ፈንጅ ውሻዋ በግዳጅ ላይ እያለ እንቅልፍ ወስዶታል በሚል ቅጣት አስተላለፈች።
የዓለማችን ቁጥር ሁለት ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና እንደ ፈንጅ፣ አደንዛዥ እጾች እና ሌሎች ረቀቅ ያሉ ወንጀሎችን ለመከላከል የሰለጠኑ ውሻዎችን ትጠቀማለች።
ልዩ ስልጠናዎችን ወስደው ቻይናዊያንን ከጥቃት እየጠበቁ ካሉ ውሾች መካከል "ፉ ዛይ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ውሻ አንዱ ነው።
የ18 ወራት እድሜ ያለው ይህ ውሻ ከአራት ወሩ ጀምሮ የተለያዩ ረቂቅ የፖሊስ ስልጠናዎችን ወስዷል።
ኮኬይን የተሰኘውን አደገኛ እጽ አነፍንፎ በመለየት የሚታወቀው ይህ ውሻ "ኮኬይን ኦፊሰር" የሚል ስያሜንም አግኝቷል።
በተለይም ፉዛይ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ውስጥ በተመደበበት ዌፋንግ የህዝብ ፖሊስ ክፍል ስር ላሳየው የላቀ አገልግሎት በርካታ ስጦታዎችን አግኝቶ ነበር።
ይሁንና ይህ ውሻ ከሰሞኑ በግዳጅ ላይ እያለ እንቅልፍ ወስዶት ተገኝቷል። ከዚህ በተጨማሪም አልጋው ላይ ሽንቱን ሸንቷል ተብሏል።
የቻይና ፖሊስ ኮሚሽን እንደገለጸው ውሻው ሀላፊነቱን በመዘንጋት የዲስፒሊን ግድፈት ፈጽሟል በሚል ቅጣት ተላልፎበታል።
በፉ ዛይ ላይ ከተጣሉበት ቅጣቶች መካከልም ከዚህ በፊት የተሰጡት ስጦታዎች እና ሽልማትን መቀማት፣ ዓመታዊ ቦነሱን ማስቀረት ዋነኞቹ ናቸው።
በልዩው የቻይና ፖሊስ ላይ ቅጣት እንደተጣለበት ከተገለጸ በኋላ በርካቶች አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ናቸው።
ዓመቱን ሙሉ ስኬታማ ሆኖ ለቆየ ፖሊስ አንድ ቀን ስህተት ሰርቷል በሚል ቅጣት መጣል የለበትም የሚለው አስተያየት የብዙዎች ሆኗል።
የፉዛይን እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በማሳየት የሚታወቀው የማህበራዊ ትስስር ገጽ በትንሽ ቀናት ውስጥ ከ340 ሺህ በላይ ተከታዮችን እንዳፈራም ተገልጿል።(አል አይን)
@Ethionews433 @Ethionews433