Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Путешествия


ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Путешествия
Статистика
Фильтр публикаций


በስኬት የደመቀ የስራ ሳምንት ይሁንልዎ!!!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ


የፅናት፣ የአንድነት እና የኩራት ምልክት፤ ዓድዋ!
እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ዓድዋ


አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት የመሪነት ድርሻውን በብቃት እየተወጣ የሚገኝ የስታር አሊያንስ አባል አየር መንገድ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርቱጋልዋ ፖርቶ ከተማ ከሀምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት አራት ቀን የበረራ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን ለውድ ደንበኞቹ በደስታ ያበስራል። ይህ አዲስ በራራ ወደ አውሮፓ ለሚጓዙ መንገደኞቻችን የተቀላጠፈ አገልግሎት እና ምቹ የበረራ አማራጭ ከመሆኑ ባሻገር አየር መንገዳችን በአውሮፓ ሀገራት ያለውን የበረራ አድማስም ያሳድጋል።
ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-to-commence-new-flight-service-to-porto-in-portugal
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፖርቶ


ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሞዴል ምን ይመስልዎታል?
Опрос
  •   ሀ-ቦይንግ 787
  •   ለ-ኤርባስ A350
  •   ሐ-ቦይንግ 777
  •   መ-ቦይንግ 767
686 голосов






የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ እና አጠቃላይ በካርጎ አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን የአፍሪካ ምርጥ የፋርማ እቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Air Cargo Pharma Service of the Year, Africa) እና የአፍሪካ ምርጥ የዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Cargo Airline of the Year, Africa) በመባል ሁለት ሽልማቶች ከ “Aviation Achievement Awards” (AAA) የተበረከተለት መሆኑን ሲገልጽ በደስታ ነው።
እነዚህ ሽልማቶች አየር መንገዳችን ለልህቀት፣ ፈጠራ እና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለደንበኞች ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክቱ ሲሆን አየር መንገዳችን ዓለም አቀፍ የዕቃ ጭነት በረራ አድማሱን እያሰፋ መሄዱን ተከትሎ በዓለም ደረጃ ያለውን ተፎካካሪነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ያስችለዋል።
አሸናፊዎች እንድንሆን ላበቁን የምንጊዜም አጋሮቻችን እና ታታሪ ሰራተኞቻችን ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን። የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መዳረሻዎቹንና አገልግሎቶቹን በማስፋፋት የመሪነት ሚናውን ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያካርጎ


ቀደም ባሉት ግዜያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሀገር ውስጥ በረራ ይጠቀምበት የነበረውና እስከ 62 መንገደኛ የመያዝ አቅም የነበረው ፎከር 50 (Fokker 50) አውሮፕላን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ


የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @Matebu Yenehun ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ በሚገኙ መዳረሻዎቹ 32 ሳምንታዊ በረራዎች እንደሚያደርግ ያውቃሉ? ትኬትዎን በድረገፃችን www.ethiopianairlines.com አሊያም በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያችን https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app ገዝተው ባመችዎ የበረራ አማራጭ እና በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይብረሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ


ምርጫዎን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ


በክብር ልንቀበልዎ ተዘጋጅተናል፤ ይምጡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ


በልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ አስደሳች የበረራ ግዜ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያሳልፉ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ







Показано 17 последних публикаций.