Ethiopian Digital Library


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


በዚህ ቻናል ስለ
👉ትምህርት፣
👉ሥራ እና
👉ማህበራዊ ጉዳይ
መረጃ ያገኛሉ!
Contact: @ethiodlbot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


ከCGPA በላይ Exit Exam ውጤት ተመራጭ እየሆነ ነው

Exit Exam ማለፍ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ውጤት ማምጣት ለቅጥር ተመራጭ እየሆነ ነው ።

የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ አንዳንድ ቀጣሪዎች CGPAን ትተው የExit Examን ውጤት ሰራተኛ ለመቅጠር እያዩ ነው ።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


🌟 Exciting News, GLOBEDOCK ACADEMY Family! 🌟

We are thrilled to announce that GlobeDock Academy has been selected for the Legacy Builders Award at the Great Rift Valley Innovation Summit! 🎉

This recognition is a testament to the power of education and the incredible learning community we’ve built together. But now, we need your support to win!

🗳 Vote for GlobeDock Academy and help us make history!

👉 Click here to vote : https://vote.grvsummit.com/dashboard


📢 Spread the word! Share this with your friends, classmates, and family so we can achieve this milestone together.

Thank you for being part of our journey! Let’s keep shaping the future of education! ✨




በሜታ ወልቂጤ በአንዲት ታዳጊ ህጻን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ አንዲት ህጻን ከቤት ተወስዳ ከተደፈረች በኋላ ተገድላ መገኘቷ ቁጣ ቀስቅሷል። “በኛ የደረሰ በማንም አይድረስ” የሚሉት የተጎጂ ቤተሰብ በታዳጊ ልጃቸው ላይ ለደረሰው ቀሰቃቂ ወንጀል ፍትህ እንሻለለን ብለዋል።

ሲምቦ ብርሃኑ ትባላለች፡፡ የስምንት ዓመት ታዳጊ ህጻን ናት፡፡ የአንደኛ ክፍል ተማሪ፡፡ በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንት ባለፈ ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ተመልሳ ምሳ እንደበላች ከመኖሪያ ቤቷ የደረሰችበት ሳይታወቅ ቀርቷል ፡፡ በዕለቱ ፍለጋ የወጣው ቤተሰብ ታዳጊዋን ከነሙሉ ጤንነትና በህይወት ለማግኘት ግን አልታደሉም፡፡

ሮጣ ያልጠገበች ታዳጊዋ ለአዕምሮም በሚከብድ ሁኔታ ከተደፈረች በኋላ “እንዳትናገር በሚል” ከመኖሪያ ቤታቸው ጀርባ በቅርብ ርቀት ላይ ህይወቷ አልፎ መገኘቱን አንድ የቤተሰቧ አባል ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። ታዳጊዋ ከተገደለች በኋላ ተሰቅላ መገኘቷን የገለጹት የቤተሰብ አባሉ “ጫማዋን ያወለቁባትና የሰቀሏት ቦታ አንድ አይደለም የ50 ሜትር ገደማ ርቀት አለው” ብለዋል።

በወረዳው የኤላ ከተማ በታዳጊዋ ላይ የተፈጸመው ጥቃት አባት የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸው እና በስራ ቦታ መሆናቸው እንዲሁም እናት የ2 ወር እመጫት በመሆናቸው አጋጣሚውን በመጠቀም እንደነበር የቤተሰቡ አባል ተናግረዋል።

የተጎጂ ቤተሰብ አባል የሆኑት አስተያየት ሰጪ ቀጥለው፤ “የታዳጊዋ ቤተሰብ ቤት በፊት ለፊት በኩል ሆቴል በመሆኑ የሚገባውና የሚወታው ብዙ ነው፡፡ በጓሮ በኩል ፑል መጫወቻም አለ፡፡

ደፋሪዎችም በዚያው በጀርባ በር እንደወሰዷት ነው የቤተሰብ ስጋት” ያሉን አስተያየት ሰጪው፤ 2009 ዓ.ም. የተወለደችው ታዳጊዋ ሲምቦ ገና በ8 ዓመቷ ለዚህ ለአሰቃቂው ድርጊት ሰለባ መሆኗን በቁጪት ተናግረዋል፡፡

“ባለሙያዎች በሰውነቷ ላይ የታየውን ፈሳሽ በመውሰድ ምርመራ እያደረጉ ነው” ያሉን የቤተሰብ አባል እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ ተጠርጣሪ አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት ተኩል የተገኘው የታዳጊዋ አስክሬን በትናንትናው እለት ስርዓተ ቀብሩ መፈጸሙን የአዲስ አበባው ወኪላችን ስዩም ጌቱ ዘግቧል።

ዶቼ ቬለ በታዳጊዋ ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ድርጊት እና ቀጣይ እርምጃዎች ለመጠየቅ ለወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ አጀማ በእጅ ስልካቸው ላይ ቢደወልም ስልካቸው ስለማይነሳ አስተያየታቸውን በዚህ ዘገባ ማካተት አልተቻለም፡፡
ምስል ፤ ከቤተሰብ አባል የተገኘ
#DW #ዶቼ_ቬለ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


GlobeDock Academy is honored to be recognized at the Great Rift Valley Innovation Summit! 🎉 Now, we need your support to win the People’s Choice Award! 🏆

📚 Support GlobeDock at the GRV Summit and help us continue transforming education in Ethiopia.

🗳 Cast your VOTE NOW! 👇
🔗 https://vote.grvsummit.com/dashboard


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library








Mekdela Amba University Vacancy

Experience: 0 year

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የቻይና ሲሆን ደህንነት ምናምን ይላሉ...አይ አለም

ጣሊያን ከሰሞኑ መነጋገሪያ የነበረውን የAi app Deepseek ን ከደህንነት ስጋት ጋር በተገናኘ ምክንያት አግዳለች::

ያም ሆነ ይህ ቻይና አሜሪካን መገዳደር ጀምራለች::

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


🔴 በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 6 እና 7/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። https://tinyurl.com/dbu-rcp-2017 ሊንክ ላይ በመግባትና የአድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት የተመደባችሁበትን ግቢ ማወቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

🔴 በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 28 እና 29/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ
✔️የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-H የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ
✔️የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-E የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ
✔️ሌሎቻችሁ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


አዲሱ የትራንፕ አስተዳደር የግብረሰዶማዊያን ምልክት በየትኛውም የአሜሪካ ግዛት እንዳይያዝ ከልክለዋል። ሰውየው ከመጽሃፍ ቅዱስ ውጪ አሻፈረኝ ብለዋል። በተጨማሪም ይህንን መመሪያ የጣሱ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ መባረርን ጨምሮ የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ትእዛዝ ሰጥተዋል::

The new Trump administration has banned the display of gay symbols in any US state. He refused to do so outside of the Bible.
He also ordered that government employees who violate this directive could face disciplinary action, including dismissal. Trump admin tells U.S. embassies they can't fly pride flag on flagpoles

www.nbcnews.com

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library




የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ - ትምህርት ሚኒስቴር

ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ አሳስቧል፡፡በሚኒስቴሩ የመምህራን ትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት የተጻፈው ደብዳቤ፥ " በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ለመሸጋገር የትምህርት ማሻሻያ ስልጠና የሚከታተሉ መምህራን፣ ስልጠና ሳያጠናቅቁ መረጃ እየተሰጠ እንደሆነ ደርሼበታለሁ " ብሏል፡፡

በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ለማሻሻል ስልጠና እየወሰዱ ያሉ መምህራን፣ የማስተማር ሙያ (PGDT) መውሰድና የመውጫ ምዘና ማጠናቀቅ እንዳለባቸው በመስከረም 2017 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁን በደብዳቤው ገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ክልሎች ከዚህ በተለየ የማስተማር ሙያ ስልጠናም ሆነ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን፣ የደረጃ ዕድገት እየሰጡ መሆኑናቸውን መረዳቱን አሳውቋል፡፡

ማንኛውም ሠልጣኝ የትምህርት ማስረጃ ማግኘት የሚችለው የትምህርት ምዘና ወስዶ ማለፍ ሲችል መሆኑ እየታወቀ፣ የዲግሪ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ በማድረግ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያና የደረጃ ዕድገት የሚሰጡ አንዳንድ ተቋማት መኖራቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው መሪ ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ወጪያቸውን በመሸፈን የሚያስተምረው የበቁ መምህራንን ለማፍራት ነው ያሉት ኃላፊው፤ ማንኛውም ተቋም የመውጫ ምዘና ወስደው ላላለፉ ዕጩ መምህራን ምንም ዓይነት ማስረጃ እንዳይሰጥ በደብዳቤ ማሳወቁን አስረድተዋል፡፡ #ሪፖርተር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከመጭው አመት ጀምሮ የዩንቨርስቲ ምርጫ ውስጥ ሊገባ ነው

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል።

ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ላሉ ሥራዎች በጥናት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ እንደሚያደርግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል። ከቀጣይ ዓመት ጀምሮም የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲም እንደ አንድ አማራጭ እንደሚካተት ተጠቁሟል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የአጠቃላይ ትምህርት ፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው ከፍተኛ የትምህርት አቀባበል ያላቸው ተማሪዎች የሚገኙበትን የትምህርት ክፍል ሳያጠናቅቁ ወደ ቀጣዩ ክፍል መሸጋገር የሚያስችል የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል። የአዋጁ መፅደቅ ብቁ የትምህርት ባለሙያ፣ አመራርና አደረጃጀት ለመፍጠር የሚያስችል ነው ተብሏል።

የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ለምክርቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት፣ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍን መሠረት አድርገው ከተቀረጹ መርሐግብሮችና ዕቅዶች አንጻር ትምህርትን ለመምራት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ዘርፉን በሚፈለገው ደረጃ አላደገም።

ይህንን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት አዲስ አዋጅ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል። አዋጁ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚደረገውን ሪፎርም ያግዛል። በአዋጁ ከፍተኛ የትምህርት አቀባበል ያላቸው ተማሪዎች የሚገኙበትን የትምህርት ክፍል ሳያጠናቅቁ ወደ ቀጣይ ክፍል መሸጋገር እንዲችሉ ተደርጎ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል።

አዋጁ ብቁ የትምህርት ባለሙያ፣ አመራርና አደረጃጀት ለመፍጠር ይረዳል ያሉት ሰብሳቢው፣ በመላው ሀገሪቱ ሁሉም የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት የሚከናወነው የመማር ማስተማር ሂደት የሀገሪቱን እሴት ጠብቆ እንዲካሄድ ግልጽ አቅጣጫ የሚሰጥ ስለመሆኑ አስረድተዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


መምህራንና ተማሪዎች ዕገታ

በጎጃም አካባቢዎች በመምህራንና ተማሪዎች ዕገታ ምክንያት ዘንድሮ ማስተማር ጀምረው ያቆሙ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውንና በርካታ ተማሪዎች በወላጆች ላይ በሚደርስባቸው ማስፈራሪያ ሳቢያ ትምህርት እያቋረጡ መኾኑን ዋዜማ ተረድታለች።

በርካታ የገጠር ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና የትምህርት ተቆጣጣሪዎች በየጊዜው በፋኖ ታጣቂዎች እንደሚታገቱ ዋዜማ ተገንዝባለች።

ባንዳንድ አካባቢዎች ዕገታውን በመፍራት ወደ ትምህርት ቤት የማይገቡ መምህራን ደሞ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንደሚታሠሩ ምንጮች ገልጸዋል።

በክልሉ የዚህ ዓመት የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ድረስ መራዘሙን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ትናንት አስታውቋል። #Wazema

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


🛑 በዚህ ዘመን ተፈላጊ የሆነውን የቪድዮ ኤዲቲንግ  ሙያ  በስልካችሁ ብቻ መማር ትፍልጋላችሁ ?

📌 ማንኛውም ጀማሪ የሆነ ሰው ሊማርበት የሚችል እና ወደ መካከለኛ ቪድዮ ኤዲተርነት ከፍ የሚልበት በዝርዝር ያስረዳውበት ሙሉ የ 2 ሰዓት ኮርስ ነው።

📌 አሁን ላይ በቪድዮ ኤዲተርነት Upwork ላይ ከ    International Client  ጋር እየሰራሁ እገኛለሁ!

📌እናንተም አሁኑኑ ይህንን ሙያ ለመማር እና በዶላር ተከፋይ ለመሆን ከፈለጋችሁ ይህ ቪድዮ ለእናንተ ነው።

ቪድዮውን በዝርዝር ለማየት
👇 👇👇
https://youtu.be/a5ST4u9b-Dc


መቄዶንያ በመላው ኢትዮጵያ 44 ቅርንጫፎች ያሉት ከወደቁበት የተነሡ ሰዎች ወደ አእምሮአቸው ሲመለሱ ወደ ሥራ የሚገቡበት ብዙ ሥልጠና ያለው በሆስፒታል ደረጃም ብዙ ቁጥር የሚያስተናግድ ሥፍራ ነው::

በመሥራት ላይ ያሉትና የፊታችን የካቲት 1 2017 ዓ.ም. በሰይፉ ኢቢኤስ ዩቲዩብ ቻናል በሚደረግ የገቢ ማሰባሰቢያ ይጠናቀቃል::

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Показано 20 последних публикаций.