EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Медицина


ETHIOPIAN FOOD AND DRUG AUTHORITY /EFDA/
This is EFDA'S official Telegram Channel
For more updates please visit
Free call 8482
join the Channel
t.me/ethiopianfoodanddrugauthority

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Медицина
Статистика
Фильтр публикаций




ከደረጃ በታችና የተጭበረበሩ መድኃኒቶችን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

በአዳማ ከተማ በተካሄደው የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ምግብን መድኃኒት ባለስልጣን የመድኃኒት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ እንደተናገሩት የአለም ጤና ድርጅት በ2017 ባወጣው ጥናት መሰረት በታዳጊ ሀገራት ከ10 መድኃኒቶች አንዱ ከደረጃ በታችና የተጭበረበሩ እንደሆኑ ገልፀው ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ የሆነ አለም አቀፋዊ ትብብር፣ የግንዛቤ ማስጨበጫና ያላሰለሰ ስራ  እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

ባለስልጣኑ ከደረጃ በታችና የተጭበረበሩ መድኃኒቶች ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የድርጊት መርኃ ግብር ማዘጋጀቱን ገልፀው ጉዳይ የተወሰኑ ተቋማትን ትብብር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካላትና አለም አቀፋዊ ትብብርን የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀው ባለስልጣኑ ለሁሉም መድኃኒቶች ልዩ መለያ ኮድ ለመጠቀም ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተዘጋጀው የድርጊት መርኃ ግብር ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ኢንተርፖል፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣  የሙያ ማህበራት፣ የፍትህ አካላት፣ የመድኃኒት አምራቾችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ውይይት ውጤታማ ያደረጉ ሲሆን ከተሳታፊዎች በተነሱ አስተያየቶች መሰረት የተዘጋጀው የድርጊት መርኃ ግብር የባለድርሻ አካላትን አስተያየት መሰረት አድርጎ በቅርቡ ወደስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።


የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር ዘርፍ ተናቦና ተቀናጅቶ በመስራት የህብረተሰብን ጤና በመጠበቅ ረገድ አበረታች የሚባል ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ።

የካቲት 19/2017 ዓ.ም የምግብና የጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ከፌደራል እስከ ክልል ድረስ የሚሰሩ የጤና ቁጥጥር ስራዎች የአሠራር ስርዓትና ደረጃዎችን ጠብቀው እንዲፈፀሙ የመከታተል ተግባር የአመራሩ የአንበሳ ድርሻ ሊሆን ይገባል፡፡
የጤና ቁጥጥር ዘርፍ ተናቦና ተቀናጅቶ በመስራት የህብረተሰብን ጤና በመጠበቅ ረገድ አበረታች የሚባል ውጤት አስመዝግቧል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ውጤቱን በማስቀጠል በኩል  በአጠቃላይ የቁጥጥር ሴክተሩን ለማጠናከር በበጀት፣ በሰው ኃይልና በአሠራር እንዲሁም ጉዳዩን አጃንዳ በማድረግ ረገድ የአመራሩ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም የሕገወጥ የመድኃኒት ቁጥጥርን በቴክኖሎጂ በማጠናከር የቁጥጥር ስራውን ማስፋት፤ በመውጫና መግቢያ ኬላዎች በመድኃኒትና ምግብ የፈጣን የጥራት ምርመራ ማካሄድ የሚያስችል ስራዎች መስራትና፤የምግብ አምራቾች ደረጃ ማዘጋጀት በቀጣይነት በትኩረት ከሚሰሩ ተግባራት መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በባለስልጣኑ የምግብ ቁጥጥር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ በበኩላቸው  ሕገወጦችን በወንጀል ጭምር የመጠየቅ ስራ አጠናክሮ በመቀጠል  ሕብረተሰቡን ከሕገወጥ የምግብና የመድኃኒት ግብዓቶች የመጠበቅ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ነው ያሉት፡፡
የምግብ  ምርቶችን ያልተመዘገቡትን እንዲመዘገቡ፤አስገዳደጅ ምልዕክት ያለጠፉ ምርቶችን ወደ ገበያ ሲገቡ እርምጃ የመውሰድ ስራ ተቆጣጣሪዎች እንዲሰሩ አሳስበዋል


ከምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት እቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ጎን ለጎን በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ አውደ ርዕይ  ተካሂዷል።


ከምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት እቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ጎን ለጎን በተካሄደው አውደ ርዕይ ላይ እንደተገለፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ጨምሮ በ12ቱ ክልሎችና በ2ቱ ከተማ መስተዳድሮች ስር በሚገኙ የምግብና የጤና ግብዓቶች ተቆጣጣሪ አካላት በተሰሩ ስራዎች የምርት ጊዜያቸው ያለፈባቸው፣ የጥራት ጉድለት የተገኘባቸውና ተመሳስለው በተሰሩ የምግብና የጤና ግብዓቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ታውቋል።


ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀውና 12ቱ ክልሎችና 2ቱ ከተማ መስተዳድሮች የተሳተፉበት የተቆጣጣሪ አካላት አውደ ርዕይን ጥሪ የተደረገላቸው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጤና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርትጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የባለድርሻ አካላት፣ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮች የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ተገኝተው ጉብኝት አካሂደዋል።

Показано 4 последних публикаций.