በዑስማን (ረ.ዓ) የኺላፋ ዘመን ነበር ይህ የተከሰተውን። በዛ ሙስሊሞች በበላይነት ከጫፍ ጫፍ በሚገዙበት ብርቅዬ ዘመን የበግ ለምድ ለብሶ የተቀላቀለው የሁዲ - ኢብን ሰበእ በዑስማን አገዛዝ ላይ አቃቂር እያወጣ ግልብ ወጣቶችን ያነሳሳ ገባ።
እናም በአንዲት ቀን እነዚህ ግልብ ወጣቶች በኢብን ሰበእ የተሞሉትን ጥላቻ ተሸክመው መዲና ተገኙ የዑስማንንም ቤት ከበቡ። ያ ከአፍሪካ እስከ ህንድ የሚገዛ ኸሊፋ ቤቱ ቢከበብም የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ነገሩንም ለማብረድ አስቦ ጦሩም ሆነ ሶሐቦች ከቤታቸው እንዳይወጡ አስጠነቀቀ።
ዑስማን ወጣቶቹን በእርጋታ ያወያያቸው ገባ ግና ግልፍተኞቹ እጅግ ስለጋሉ ከአዕምሮአቸው ይልቅ ስሜታቸውን ማስቀደም መረጡ። በቤቱ ቁርአን በመቅራት ላይ ሳለ ገብተው በሰይፍ መቱት። ልትከላከልለት እጇን የዘረጋችውን ባለቤቱን ጣትም አረገፉ።
ያንን መላኢካዎች እንኳ የሚያፍሩትን የነብዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምርጥ ሶሐባ ዙኑረይንን ገደሉ። ይህንን ተከትሎ ደም አፋሳሽ የታሪክ ጠባሳ ተከሰተ።
ያኔ ያ ከንቱ መንጋ በዑስማን ላይ የጣለው ሰይፍ እስካሁን ከኡማው ላይ አልተነሳም።
ሞብ/Mob ይኸው ነው። ከኋላ የሚቆሰቁስ ይኖራል፤ መነሻው እዚህ ግባ የማይባል እንደውም ውሸት ሊሆን ይችላል። ግና በጩኸት እና ግርግር አዕምሮ ይታፈንና ማስተዋል ቀርቶ ስሜት ይነግሳል። ይህኔ የማያገናዝቡ መንጋዎች በሁከት ተደግፈው ጉዳት ያስከትላሉ። ያስከተሉት ጉዳት ግን በቀላሉ የሚሽር አይሆንም።
ሞብ/Mobን ረብሻ፣ ብጥብጥ ወይም ሁከት የሚሉት ቃላት ብቻቸውን አይፈቱትም። ትርጉሙም ጉዳቱም ከነሱ ይልቃል።
በአንዳች ሰበብ የተነሳሳ፣ የእዝ ሰንሰለት የሌለውና ከቁጥጥር የወጣ፤ ሌሎችን ለማጥቃት የሚጣደፍ የሰዎች መንጋ ብንለው ይሻላል።
ባለፈው ሳምንት በሀዋሳ ያየነው ይኸው ነው። ብድግ ብሎ መረበሽ፣ ዱላ ይዞ መሮጥ፣ ህፃን አዋቂ ሴት አዛውንት ሳይመርጡ ያገኙትን መደብደብ፣ መግደል፣ ማቃጠል ማውደም።
እጅግ አሳፋሪ እና ፈፃሚዎቹ መልሰው ቢያስተውሉት የሚያሸማቅቃቸው አስነዋሪ ድርጊት። በሶዶ እና በወልቂጤ የሆነውም ይኸው ነው።
አንድ አመት ወደ ኋላ ስንመለስ ደግሞ የሱማሊ ክልል ልዩ ፓሊስ ጥቃት አድርሷል በሚል የተቆጣ መንጋ በአወዳይ ከሰላሳ የማያንሱ ተጋብተው ተዋልደው እዛው የኖሩ ወንድሞቹን ገደለ።
ሬሳቸው ጅጅጋ ሲደርስ ግን ሌላ ጣጣ ጠራ። በዛም የተቆጣ መንጋ ደግሞ የተለያየ ቦታ ከአንድ ሚልየን የማያንስ እዛው የተወለደ፣ ያደገ፣ የኖረ ወንድሙን ከክልሌ ውጣ ብሎ አባረረ። ብዙዎችን ደበደበ፣ ዘርፈ ብሎም ገደለ።
በምላሹ በኦሮምያም ከተለያየ ቦታ ሱማሌዎች ተፈናቀሉ፣ ተሳደዱ ተገደሉ። አብረው በጀመዓ የሚሰግዱ ወንድማማቾች እንዳውም ተጋብተው የተዋለዱ የተዛመዱ ተላለቁ።
በጎንደር፣ ወልዲያና ቆቦ የሆነውም ይኸው ነው። በአሶሳ፣ ጌዲዮና ጉጂም እንዲሁ። በተቆጣ ለማገናዘብ ለማሰብ እድል በሌለው ስሜታዊና ግልብልብ መንጋ!
ፈፃሚዎቹ ግን ረጋ ብለው ቢያስተውሉ እንኳን ሊያደርጉት ሊያስቡት ይሰቀጥጣቸው ነበር። ግና ተንኮል የሸረበ ሁሉ ስስ ጎናቸውን እየነካካ ከቆሰቆሰ በኋላ በሚንቀለቀለው ቁጣቸው ላይ ላምባ እያርከፈከፈ ለጥፋት ዳረጋቸው።
ማን ነው ያነሳሳችሁ ቢባሉ እንኳ ለመጠቆም እስከማይችሉ ድረስ ለማስተዋል ግዜ አልነበራቸውም። ጥፋት ላይ ሲሰማሩ ምን ይፈይደናል? ብለው እንኳ ከራሳቸው ጋር አልተማከሩም።
ሲደበደብ ያገኙትን ይደበድባሉ፣ ሲዘረፍ ከደረሱበት ይዘርፋሉ፣ ሲቃጠል ካዩበት ያቃጥላሉ። በቃ ይኸው ነው መንጋ!
Mob ለምን እንድትል ግዜ አይሰጥህም። በስሜታዊነት የተሸበበ ነው። ከጀመዓው ጋር ትጮሀለህ ከጀመዓው ጋር ትሮጣለህ። ጀመዓው የሰራውን ትሰራለህ። አዕምሮህን ሳይሆን ስሜትህን ትታዘዛለህ።
ለምን እንደምትደበድብ፣ ለምን እንደምትገድል፣ ለምን እንደምታቃጥል አታውቅም። በርግጥ ይህ የቂያማ ምልክትም ነው። ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ...
"ገዳይ ለምን እንደገደለ፤ ሟችም ለምን እንደተገደለ የማያውቅበት ግዜ ሳይመጣ ቂያማ አትቆምም" አሉ። ሙስሊም ዘግበውታል
በሌላ ሐዲሳቸው ላይ የዚህ መንስኤው የዕውቀት መጥፋት፣ ውሸትና መገዳደል እንደሆነ ጠቅሰው ሰው ዘመዶቹን ሳይቀር እንደሚፈጅ ተናግረው ነበር።
ግርርም ያለኝ ሰልጥኛለሁ ከተሜ ነኝ ያለው እንኳ ሳይቀር በተራ የኳስ ጨዋታ ድጋፍ በየስታዲየሙ ሲከሳከስ ማየቴ ነው። በስሜት ስለከነፉ ምን እየሰሩ እንዳሉ እንኳ አያስተውሉም።
ይሳደባሉ፣ ይዝታሉ ሞቅ ሲላቸው መጎሻሸምና ድንጋይ መወራወር ይጀምራሉ። ከዛ በኋላማ የሚሆነውን እነርሱም አያውቁትም። ወይ ሟች ናቸው ወይም ገዳይ ... ከንቱ!
ከሰሞኑ የሀዋሳውን ሁከት ሲተች የነበረውን አዲስ አበቤ ሰኔ 16 ታዘብነው። ቦንብ ወርውረዋል ያላቸውን ሰዎች ሲደበድብ፣ ሲያሰቃይ የሚያሳዩ ቪድዮዎችን አየን።
ይህን ያደረጉት ምን ፋይዳ ይገኛል ብለው ነው?
በድብደባው ተጠርጣሪዎቹ ቢሞቱ ማን እንደላካቸው ተዳፍኖ ቀረ ማለት አይደለምን?በMob ውስጥ ግን ይህን ለማሰብ አይቻልም።
እንደው ሰዎቹ የተያዙት በስህተት ቢሆንስ? እስኪ አስቡት ... ምን ያክል ዘግናኝ እንደሆነ!
ለድጋፍ የወጣን ሰው በስህተት እንደ ጠላት ደብድቦ .... ይቅርታ ቢጠየቅስ እንዴት ሆዱ ይሽራል? ቢሞትስ??? ቤተሰቦቹ የዘላለም ቁርሾ በሆዳቸው ተቀመጠ ማለት አይደለም???
ደሞስ ያንን ግሪሳ ማን ቀጪ አደረገው? እውነት አጥፊ ቢሆን እንኳ ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ማን ስልጣን ሰጠው?
ለመሆኑ የአፈንጂዎቹ ተባባሪ ጓዶቹን ለማስመለጥ ንፁህ ሰው ላይ ጠቁሞ ቢሆንስ? መንጋ እኮ ከሚሰራለት ቀለበት አሻግሮ መመልከት የማይችል ነው!
በቅርብ ቀናት እየሆነ ያለው ደግሞ ይበልጥ ያሳምማል። በየቦታው ቆሸሽ ያለ ልብስ የለበሱትን ሁሉ እየያዙ ዘርን መሰረት ባደረገ ጥርጣሬ ማንገላታትና መደብደብ። ይሄ በጣም ደባሪ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነውረኛ ተግባር ነው።
ቦምብ ይዘዋል እየተባሉ ወደ ጣቢያ ከተነዱ አስር ሰዎች አንዳቸውም ቦምብ አልያዙም። የተሰራው ግፍ ግን በፌስቡክ ተሰራጭቷል። ይህ ግፍ ሌሎችን እንደሚያስከፋ ለበቀልም እንደሚዳርግ ማስተዋል ተስኖናል።
በህዝባቸው መነገድ ለሚፈልጉ ሴረኞች ደግሞ እኛም -በዝምታ ተመልካቾች- ሳንቀር ጥሩ ወጥመድ እየገባንላቸው ነው። የማወራው እንደ ህዝብ ነው።
ፓለቲከኛ ይመጣል ይሄዳል። ነገ አብረነው ከምንኖረው ህዝብ ጋር የሚያቃቅር ነገር ሰርተን እንዴት ነው ሰላምን የምንሽተው??
ለመሆኑ ከኤርትራ ጋር እዚህ ድረስ ያዳረሰን ምን እንደሆነ ተዘነጋን እንዴ? ፈገግ የሚያሰኘኝ ያን ሁሉ እልቂት ረስተን ስለ ኤርትራ እርቅ እያሰብን ከዛ የሚቀርበንን በአይነቁራኛ ማየታችን ነው። ቀቢፀተስፋ¡
በቅድሙ ሐዲስ ላይ ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) "ገዳይም ሟችም የእሳት ናቸው" ብለው ነበር። ይህ ሁለቱም ወገንተኝነት/ ዘረኝነት ቆስቁሷቸው የገጠሙ እንደሆነ ነው ይላሉ ኢማሙ ነወዊ።
እስኪ ወደቀልባችን እንመለስ እና እናስተውል። ለመሆኑ ከሰማያት በላይ ጌታችን እያየን መሆኑን ዘነጋን እንዴ? ሰዎችን መስደብ፣ ማነወር፣ ማንገላታት፣ መደብደብ ጌታችን ይወድልናል እንዴ? አላህ ጋር አያስጠይቀንም ወይ? ጀሐነም አይዶለንም ወይ?
ያ በአጅር ተጥለቅልቆ ሲያበቃ የሰራውን ሁሉ ለበደላቸው አከፋፍሎ ጀሀነም እንደወደቀው መሆን አለብን ወይ?
እኛ ባንሳተፍ እንኳ በዳዮችን ተው ማለት እንዴት ይሳነናል። በዝምታችን እየተባበርናቸው እኮ ነው። ስንቶቻችንስ በየቤታችን ሁነን 'እሰይ' የምንል አለን? የ