እያደር ነገሩን እና ሊያደርስ የሚችለውን የጉዳት መጠን እየተረዳነው፣ የመከላከል እንቅስቃሴዎች እየተሻሻሉ እና እየተጠናከሩ፣ ክፉ ቀንን ለማሳለፍ ሁሉም በሚችለው እየተረባረበ፣ መንግስትም ለአገር በቀል የመድኃኒት እውቀት ቦታ ሰጥቶ መምከር ጀምረዋል። ሁሉም የሚደነቁ ይበሉ! የሚባሉ ናቸው።
ትክክለኛ መረጃዎች በማካፈል ለመከላከል ለምትወተውቱ ዜጎች፣ ህንጻዎቻችሁን ለአደጋ ዝግጁነት የሰጣችሁ ባለሀብቶች፣ ለራሳችሁ አስቤዛ ስትገዙ ለጎረቤታችሁም ባአቅማችሁ የገዛችሁ መካከለኛ ኑሮ ላይ ያላችሁ ሰዎች፣ ከምትጎርሱት ከጎናችሁ ላለው ለምታጎርሱ፣ ከጥሬው ቆንጥራችሁ ለምታቀምሱ ደሀዎች፣ እንዲሁም በየሰው አገሩ ሥራ ፈቶ አቅም ላጣው ግሮሰሪ ለምታደርጉ ሰዎች... በሙሉ እጅ እንነሳለን!
ይኼ የጋራ ጦርነት ነው። እጅ ያለው በእጁ ይተባበር። ይሰብስበው። ይታጠበው። ሰው አይንከበት። ለቸገረውም ይዘርጋው። እግር ያለውም በእግሩ ይተባበር። ሰው ከሚበዛበት ይራቅበት። ቤት ይዋልበት።
#Covid19Ethiopia