ኢትዮጵያ ከነፋስ ኃይል 1 ነጥብ 35 ሚሊዮን ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ማመንጨት የሚያስችል አቅም አላት
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከነፋስ ኃይል 1 ነጥብ 35 ሚሊዮን ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ማመንጨት የሚያስችል አቅም እንዳላት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። ዘርፉን ባለሀብቶች እንዲያለሙ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገለጸ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍሰሃ ጌታቸው በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከነፋስ ኃይል ብቻ 1 ነጥብ 35 ሚሊዮን ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ማመንጨት የሚያስችል አቅም አላት። በአሁኑ ሰዓት ከዚህ ዘርፍ ማመንጨት የተቻለው ከ400 ሜጋ ዋት የማይበልጥ ነው።
ሀገሪቱ በዘርፉ ካላት ሀብት አንጻር እስከ አሁን የተመረተው ኢምንት እንደሆነ የገለጹት አቶ ፍሰሃ፤ ከንፋስ የሚገኘውን ኃይል ለማሳደግ መንግሥት ከሚሠራው ሥራ በተጨማሪ የግሉ ዘርፍ ቢሰማራ የኃይል አቅርቦት መጠንን.....
https://press.et/?p=144090