📚ለኢየሱስ እና ለጸጋው እሺ በል
📖1 ቆሮንቶስ 1 (1 Corinthians)
30-31፤ ነገር ግን፡— የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።
♦️ኢየሱስ ራሱ➡️ ጥበብህ ➡️ ጽድቅህ እንዲሁም➡️ ቅድስናህ ነው!
..✍እዚህ ጋ "ቅድስና" የተፈለጸው የግሪክ ቃል "ሀጊያስሞስ" የሚል ሲሆን መቀደስ ፥በረከት ለሚለው የተጠቀመው አንድ አይነት የግሪክ ቃል ነው።
👉ያ ማለት ቅድስናችን ወይም በረከታችን የተገኘው በኢየሱስ ነው። ስለዚህ ሃጥያትን እንድታደርግ የሚገፋፋህ ፥ የሚፈትንህ ንጹህ ያልሆኑ ሃሳቦች ሲኖሩህ ቆም በልና ወደኢየሱስ ወደ መስቀሉ ተመልከት።
☑እርሱ ለእርሷ ያለውን ፍቅሩን፥ምህረቱንና ጸጋውን ስተመለከት ፥ እርሱ በእያንዳንዱ ፈተና ፥ ሱስና እስራት ላይ ያንተ ድል መሆኑን ትገነዘባለህ!
✔ፈተና ሲገጥምህ ማድረግ ያለብህ ፈተናውን በቃ ማለት ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎች አሉ።ነገር ግን ይህን ለማድረግ የፈቃድ ሃይልህ ከሀጥያት ጋር ስለማይመጣጠን በራስህ ጥረት እምቢ ለማለት ስትሞክር የባሰ ይሆናል። ይህ አይነት ችግር የገጠመው ሐዋርያው ጳውሎስ ራሱ ትግሉን 📖" ሮሜ 7፥19" ገልጾታል።
✍ስለዚህ የሚፈታተንህን እምቢ ለማለት መደገፍ ያለብህ በራስህ የፈቃድ ሃይል ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ጸጋ ላይ ነው። ስለዚህ በትግልህና በፈተናህ መካከል ለኢየሱስ እሺ በል።
🗣 "ጌታ ኢየሱስ፣ ጽድቄ፣ ቅድስናዬና ቤዛዬ ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ " በል። እያንዳንዱ ፈተና ጳውሎስ እንዳደረገው ኢየሱስን ለመመልከትና ለማክበር አድርገህ ለውጠው!
📖በሮሜ 7 (Romans)
24፤ እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?
25፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። እንግዲያስ እኔ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ፥ በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ እገዛለሁ።
👉በሃጥያት ላይ ድል ስለማግኘት የጳውሎስ ጥያቄ "ማን ያድነኛል?" እንጂ "የትኛው ህግ ያድነኛል" አልነበረም።
☑የሃጥያት ነጻነት የሚገኘው በኢየሱስ ነው።እርሱ ጽድቅህ እና ቅድስናህ ነው።
🗣እሺ በለው!ድክመት እንዳለብህ በሚሰማህ ቦታዎች ላይ እንደሚገባ ፍቀድለትና የእርሱ ጸጋ ከውስጥ ወደውጭ ይለውጥህ።
==========================
@Ewunetawu@ewunetawu