ተአምረ ማርያም ✤የእመቤታችን ተአምር የሚነገርበት✤ የቅዱሳን ህይወት የሚተረክበት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


... መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡›› (መዝ.86 ፥ 1) 
----------------✤✤✤---------------
"እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት
ይሉኛል፤ "የሉቃስ ወንጌል ፩:፵፰
-----------------✤✤✤-------------
ስለእመቤታችን ተዓምሯን አማላጅነቷን እና በአምላክ ዘንድ መመረጧን የሚነገርበት
አስታየት መልዕክት ካለ @Thsion21 ይላኩልን፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




#ጌታን_በልብህ_ውደደው!

ጌታ ክርስቶስን በእጁ ያቀፈው ሰው በግድ ካልሆነ በቀር ወዶ ላንዱ አይሰጠውም ነበር በክንዱ ያቀፈው ሰው ሁሌም መዓዛው ከልብሱ ተዋህዳ ትኖራለች ልብሱ ተቆራርጦ እስኪወድቅ ድረስ ፤ በፍቅር ይዞት የሚተወው አልነበረም ፡ እንዲሁ ሁሉ ጌታን ክርስቶስን በህሊናችሁ ከማፍቀር ፡ መዕዛውን ከማሽተት አትስነፉ፡፡

የህፃኑን ቃል ሰምቶ ልቡ እንደእሳት ያልተቃጠለ ማነው? እሱን ባገኘበት ቦታ ሁሉ ነገሩን ሰምቶ ደስ ያላለው አይቶትም በፍቅሩ ያልተቃጠለ ማነው? እሽኮኮ ብለህ ወደግብፅ ይዘኸው የሄድክ ዮሴፍ ሆይ ንዑድ ክቡር ነህ ፡ የሚሽከሙትን የሚሽከም ጌታን መሽከም ከባድ አይደለምና፤ ጌታ ክርስቶስን አይቶ ደስ ያላለው የልቡናውን ሐዘን ያልዘነጋ ማነው? ከእሱ ጋር መገናኘት ሐዘንን ያዘነጋል መልኩንም ማየት መከራን ያርቃል ቃሉንም መስማት ሃጢአትን ከልብ ነቃቅሎ ያጠፋል፡፡

የዮሴፍ ልጅ ያእቆብ በጌታ ፍቅር ይቃጠል ነበር  በትከሻው እሽኮኮ ብሎ ካንዱ ወዳንዱ ቦታ ይወስደው ነበር መልኩን አይቶ ይጠግበው ዘንድ ዮሴፍም ወደሚጠርብበት ቦታ ይዞት ይሄድ ነበር ከእርሱ ተለይቶ መቆየት አይቻለውምና ያዩት ሰወች ሁሉ በመልኩ ደስ ይላቸው ነበር ተዓምራትን የሚያደርግ ልጅነትን የሚሰጥ ያለዘር የተፀነሰ በፍፁም ድንግልና የተወለደ ወልድን ያደንቁት ነበር፡፡ ሐዘንን አርቆ ደስ የሚያሰኝ እሱን ባየነው እያሉ ይመኙት ነበር ፡ ልደቱ ድንቅ የሚሆን ጌታን ይወዱት ነበር እንዲህም አንተ ሳታቋርጥ ጌታን በልብህ ውደደው ፤ ደስ የሚያሰኝ ሕፃን ጌታ ያዩትን ሁሉ የሚያስደንቅ ሆነ ደስ የሚያሰኝ ሕፃን ጌታን አውቀው ወደዱት ሕፃናትም ባዩት ጊዜ በፍቅሩ እሳት ይቃጠሉ ነበር ጎልማሶችም ቀርበው ባዩት ጊዜ በእርሱ ደስታ ያድርባቸው ነበር ደናግልም እሱን አይተው ንፅህናን ያገኙ ነበር (አንድም የንፅህና ፅናት ይሆናቸው ነበር) ፡ ባልቴቶችም እሱን ባዩት ጊዜ እመቤታችንን ይህን የወለደች ማሕፀን እፁብ እያሉ ያመሰግኗት ነበር ህፃናት ወጣቶች ደናግላን ጎልማሶች ሁሉ የጌታን ፊቱን አይተው ደስ ይላቸው ነበር፡፡

ወደሱ መጥተው በውጭ ለቆሙ ሁሉ እሱን ማየት ስንቅ ደስታ ይሆንላቸው ነበር እንዲሁ አንተም እሱን በማሰብ ከዚህ አለም ሃጥያት መሽሻ ስንቅን ያዝ ተዓምራትን የሚያደርግ ልጅነትን የሚሰጥ ጌታ ክርስቶስ በሰው ሁሉ ዘንድ የሚደነቅ ሆነ እሱን አይቶ ልቡ እሱን ከማየት የሰለቸ ማነው? መዓዛውን ያሽተተ እሱን ለማያዝ ቸኩሎ ደረቱን ያልደቃ ማነው? እኔስ እንኳን እሱን የዮሴፍ የቤቱን ግድግዳ አደንቃለሁ በእግሩ የረገጣትንም መሬት አደንቃለሁ፡፡
ጌታን የሚወዱት እነዚያ ግን የአምላክን ሰው መሆን ሳያውቁ ያከብሩት ነበር ሳያውቁት ሳይረዱት ልእልናውን ይናገሩ ነበር አምላክነቱን ሳያውቁ ይመኩበት ነበር ሐዘንን የሚያርቅ እሱ እንደሆነ ሳያውቁት በልባቸው ይወዱት ነበር የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ እንደሆነ ሳያውቁት በፍቅሩ እሳት ይቃጠሉ ነበር ሙታንን የሚያነሳ እሱ እንደሆነ ሳያውቁ ከእሱ ጋር በተገናኙ ጊዜ በሞቱባቸው ዘመዶቻቸው የሚያዝኑት ሐዘናቸውን ይዘነጉ ነበር ከእሱ የምትገኝ ሕይወትን የምታስገኝ መዓዛውን በአንድ ሆነው ያደንቁ ነበር ሐብት ምስጢር ከእሱ እንዲገኝ ሳያውቁ እሱን ለማየት ይሳሱ ነበር በሕፃናት ባሕርይ የተሰወረ አካላዊ ቃል እንደሆነ ሳያውቁ አንድ ሁነው መዓዛውን ያደንቁ ነበር ከሰማይ የመጣ ሙሽራ እሱ እንደሆነ ሳያውቁ በፍቅሩ ተጠልፈው በፍቅሩ ተስበው ዚህን አለም መከራውን የዚህን አለም ደስታውን ይዘነጉ ነበር አንተ ግን ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር አካላዊ ቃል መድህን አለም እንደሆነ አውቀሃልና በሚበልጥ ፍቅር በተደሞ ጌታ ክርስቶስን ውደደው የዚህን አለም ደስታ የሚያስንቀውንም ጌታ ክርስቶስን እየወደድህ እያደነቅህ ይህንን አለም ግን ጥላው ናቀው፡፡

ከሄሮድስ የኮበለለ የሕፃን የክርስቶስ መልክ በግብፃውያን ዘንድ ተወደደ የግብፅ ቆነጃጅት በየጊዜው ይሰበሰቡ ነበር እሱንም በማየት ደስ ይላቸው ነበር ያለዘር የተፀነሰ በድንግልና የተወለደ ብዙ ተአምራትን የሚያደርግ ጌታን ኑ እንየው እያሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር፤ እንዲሁም አንተ ከልቦናህ ጋር ጌታህን ክርስቶስ በፀሎት በተዘክሮ ታየው ዘንድ እለት እለት ተማከር
ያዩት ሁሉ ከበረከቱ ጠግበዋልና
ያዩት ሁሉ የውበትን መጨረሻ አይተዋልና
ያዩት ሁሉ ፍቅሩ በልባቸው ተነድፎ ቀርቶላቸዋልና
ያዩት ሁሉ ከዚች ሃላፊ ብርቅርቅ አለም መለየትን አግኝተዋልና...
አንተም፦ ጌታን ታየው ዘንድ ወደጌታ ሂድ በእግረ ንስሃ ወደ ልብህ መቅደስ ተመለስ፡፡

(#አረጋዊ_መንፈሳዊ)

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


2 Peter 3 (አማ) - 2 ጴጥሮስ
9: ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


Репост из: ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
+ ዕረፍታ ለቅድስት አርሴማ +

ሴቶች እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ
(ዕብ 1፥35)

ቅድሰት አርሴማ ሰማዕቷ ። በአርመንያ ታኅሣሥ 6 ቀን ሐሙስ ዕለት ተወለደች ። አባቷ ቴዎድሮስ አትናስያ ይባላሉ ። የነበረችበት ዘመን ዘመነ ሰማዕታት በመባል ይተወቃል ። ዲዮቅልጥያኖስ ቆንጆ ሴት ፈልጋችሁ አምጡልኝ ብሎ ሠራዊቱን በየሀገሩ ላከ አምጡልኝ ሲላቸው አርሴማ በተራራ ተቀምጣ ነበር ፤ እርሷም የእግዚአብሔር መንፈስ ተገልጦላት ወደ አርመንያ ሄደች ። ይህንን ሰምቶ ለንጉሡ ለድርጣድስ አሰፈልገህ ላክልኝ ብሎ ላከበት አስፈልጎ አገኛት እርሷም መልከ መልካም ሴት መሆኗን አይቶ ይህችንስ ለማንም አሳልፌ አልሰጥም ብሎ ዶርታንን ለምኚልኝ አላት ለመንግሥተ ሰማያት የታጨሽ ነሽና ይህ አላዊ እንዳያረክስሽ አለቻት መልኳን አይቶ በስሜት ተሸንፎ ዘሎ ያዛት ከእግዚአብሔር ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷልና ጎትታ ከመሬት ጣለችው ። በሰይፍ መስከረም 29 ቀን አሰቆረጣት በ27 ዓመቷ በሰማዕትነት በዚህ ዕለት አረፈች ። ( ፍኖተ ስብከት ሊቀ ስዮማን አዲሱ ላቀው ገጽ_37 )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


አንዲት ክፉ ቃል መልካሙን ሰው እንኳ ክፉ ታደርገዋለች፤ አንዲት መልካም ቃል ግን ክፉውን ሰው መልካም ታደርገዋለች፡፡
አባ መቃርዮስ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 46)
----------
1፤ አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።

2፤ ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።

@Ewunetgna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


“ወዳጄ ሆይ!
የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርሃል፡፡

የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮሃልን? ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለህ፡፡

የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮሃልን? እንኪያስ ወደ ሰማያዊው መዓድ ቅረብ፤ ምህረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡

ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ልል ዘሊል ብትሆን ይህን መንፈሳዊ መዓድ ተመገብና ብርቱ ትሆናለህ፡፡

ቆሽሸሃልን? እንኪያስ ወደዚሁ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርሃለሁ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡”

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


"እኔ በስምሽ አምናለሁ፥ አንቺም ስለእኔ ትማልጃለሽ፥ ልጅሽም ስለአንቺ የልመናዬን ዋጋ ይሰጠኛል።"
— ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ




ብዙኃን ማርያም


በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡

በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን::


በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡

ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡

በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡

ንጉሡ ሊቃውንቱን ‹‹ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ›› ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ መካከል ፫፻፲፰ (ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው ‹‹ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው›› ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም ‹‹ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን›› ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡


፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት ‹‹ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን›› የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡

ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት ‹‹ብዙኃን ማርያም›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡


በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው ‹‹የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል›› አሏቸው፡፡

ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር ‹‹የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ›› የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ ‹‹ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት›› ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡


ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡

መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡


መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ›› የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡

ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ›› ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡

ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡


ምንጭ፡- መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ መ/ር አፈወርቅ ተክሌ፤ ፳፻፭ ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ ገጽ ፫፶፬-፫፶፮፡፡

የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የክርስቶስ የመስቀሉ ኃይል፣ የአባቶቻችን ሊቃውንትና ነገሥታት በረከት አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡


የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@ewuntegna
@ewuntegna


ዕንባቆም ፩፥፩-፫

እግዚአብሔር ሆይ፤ ለርዳታ እየተጣራሁ፣
አንተ የማትሰማው እስከ መቼ ነው?
“ግፍ በዛ” ብዬ እየጮኽሁ፣
አንተ የማታድነው እስከ መቼ ነው?
3 ስለ ምን በደልን እንዳይ አደረግኸኝ?
እንዴትስ ግፍ ሲፈጸም ትታገሣለህ?
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


Job 34 (አማ) - ኢዮብ
4: ቅን የሆነውን ነገር እንምረጥ፤
መልካሙንም ነገር በመካከላችን እንወቅ።

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


Psalms 22 (አማ) - መዝሙር
1: አምላኬ፡ አምላኬ፡ ለምን ተውኸኝ?
እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ።
2: አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጠራለሁ፥ አልመለስህልኝም፤
በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም።


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!


"በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ"። ቆላ.1÷20

       መስቀል ማለት የተመሳቀለ "ተ" ፊደል ቅርጽ ያለው ማለት ነው። በፊት መስቀል የተረገሙ የተወገዙ የሆኑ የዘራፊዎች  የወንበዴዎች መቅጫ  ነበረ። ይሄንንም ተግባር በመስቀል ላይ ወንበዴዎችን መቅጣት የተጀመረው በፋርስ ሀገር ነው። ይኸውም የፋርስ ሰዎች ጣኦት አምላኪዎች ነበሩና ቅጣቱ በመሬት ላይ ከሆነ የመሬት አምላክ "አርሙዝድ" የሚሉት እንዳይቆጣን በማለት ሰዎችን ከመሬት ከፍ አድርገው ይሰቅላሉ።
      በመስቀል ላይ ወንበዴዎችን መቅጣት ይህ አድራጎት  በሮማ ግዛት እንደ ልምድ ሕግ ሆነ።
ሎቱ ስብሐት ንጹሐ ባሕሪ ጌታችን መድኃኔአለም ክርስቶስም እንደ ወንበዴ ተቆጥሮ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ተሰቀለ።

      የርጉማን፣ የወንበዴዎች፣የኃጢተኞች፣የቀማኞች መሰቀያ የነበረው እንጨት፥
ንጹሕ ጌታ ተሰቀለበት።
የረከሰ ደም ይፈስበት የነበረ እንጨት፥
የጌታ ክቡር ንጹሕ ደም ፈሰሰበት፣ የአማኑኤል ቅዱስ ስጋ ተቆረሰበት።

           አዳም በዕጽ/በእንጨት/ ትዛዝ ማፍረስ ምክንያት ከፈጣሪው ተጣልቶ ወደ ምድር ተሰዶ በኋላም በሲኦል ወድቆ ሲኖር ነበረ፥
        መድኃኒታችን ክርስቶስ በዕጽ/በመስቀል/ ተሰቅሎ ከተፈረደበት መርገም ከወደቀበት ሲኦል ከሰይጣን ባርነት ቀንበር ነጻ አውጥቶ ልጅነትን ሰጥቶ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ርስቱ ወደ ገነት አስገባው።

         አዳም ዕጽዋ ላይ ያለውን ፍሬ በልቶ የሞት ሞት አገኝቶት ከእግዚአብሔር የነበረውን ኅብረት ሲያጣ፥
            መድኃኔአለም ክርስቶስ በዕጸ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ቅዱስ ስጋውን፡ክቡር ደሙን ሰጥቶ ዘለአለማዊ ሕይወትን፡ ኅብረቱን አደለን። ዮሐ.6÷53

በዕጸ በለስ መርገም፣ ኩነኔ ፣ ጉስቁልና ሲሆን፥
በዕጸ መስቀል ሰላም ፍቅር አዲስ ሕይወት ተሰጠን።

   " በመስቀሉ ደም ሰላም አደረገ" የአምላካችን ንጹሕ ደም አለምን ሁሉ ቀደሰ ፣ ከኃጢአትም ሁሉ አነጻን።
“ደሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያነጽሐነ እም ኩሉ ኃጣውኢነ፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።”
      1ኛ ዮሐንስ 1፥7
  ቅዱስ ደሙን መላእክት በአለሙ ሁሉ ረጭተውታል። "ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ፤ ምድር ጸዳች ሐሴት አደረገች በክርስቶስ ደም ስለ ታጠበች"

  ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በመስቀል ነው። "መስቀል ብርሃን መሰረተ ቤተርስቲያን" ደሙ በነጠበበት ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ትታነጻለች።

       ክብር ይግባውና ቅዱስ አምላካችን አማኑኤል በመስቀል ላይ ሆኖ ሳለ የመጨረሻ የሰውን ልጅ የማዳንን ስራ "ተፈጸመ" አለ ድኅነታችን የተፈጸመው በመስቀል ነው። በመስቀሉ ሳለ ጥንተ ጠላታችንን ዲያብሎስን በአራቱ ማዕዘን በነፋስ አውታር አሰሮ እንደቀጠቀጠው ሁሉ እኛም ቅዱስ መስቀሉን ጋሻ አድርጎ ስለሰጠን መስቀሉን ይዘን ሰይጣንን እንዋጋበታለን ድል እናደርገውማለን።

    መስቀሉን በአንገታችን አስረን ስናየው፡ በመስቀሉ ስናማትብ፡ መስቀሉን ስንሳለም፥ የመስቀልን በዓል ስናከብር ሁል ጊዜ ትዝ የሚለን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ብሎ በመስቀል ላይ የከፈለውን ውለታ እናስታውሳለን።

መስቀል የጌታን የእለተ አርብ ውሎ የምናይበት መስታዎት ነው።

በመስቀሉ ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን ተሰጠን!
በመስቀሉ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ተሰጠችን!
መስቀል የእግዚአብሔር ኃይል የጠላት ጋሻ ሆኖ ተሰጠን!
በመስቀሉ ረድኤት ፍቅር ሰላም አንድነት ሰፈነልን!

ሞገሰ መስቀሉ ወሀብተ ረድኤቱ ይድር በላዕሌነ የሀሎ ምስሌነ አሜን!!!

"መልካም የመስቀል በዓል"
ዲ/ን ደሳለኝ ወርቄ

@ewuntegna
@ewuntegna


ንግሥት እሌኒን እናወድሳት ዘንድ ይገባል፡፡ ክብር የሚገባውን የአምላካችንን የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኝ እንደሆነ ብላ በእምነት ለመፈለግ ተግታለችና፡፡

የጌታችን መስቀል ቅዱስ ስጋው የተቆረሰበት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት ከሁሉ የተለየ ከሁሉ የተቀደሰ ሁሉንም የሚቀድስ እንደሆነ አስቀድማ ተገንዝባለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

ንግሥትነቷን በዓለማዊ ቅምጥልናና ምቾት ታሳልፈው ዘንድ አልወደደችም፤ ይልቁንስ የተወደደውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ በመንፈስ ብርቱ ሆና በስጋ ደከማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

እጅግ የከበረውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ ስትጀምር በራሷ መታመን አልታበየችም ይልቁንስ ሁሉን ስለክርስቶስ ትቶ የወጣ ባህታዊ ኪራኮስን ታማክር ዘንድ ወዳለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

በተዋህዶ የከበረ የአብ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ይዞ እንዳላስቀረው ሞትንም ድል አድርጎ እንደተነሳ ሁሉ ክቡር መስቀሉም ተቀብሮ ለዘላለም እንደማይኖርና ከተቀበረበትም እንደሚወጣ አምናለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

ከጌታችን መስቀል ጋር የተቀበሩት መስቀሎች ብዙ ናቸው የጌታየን እንዴት እለየዋለሁ? ብላ ሳትጨነቅ የክርስቶስ መስቀል ክብሩን ራሱ እንደሚገልፅ በልቧ ተማምና እስክታገኝው ደክማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

@ewuntegna


 ​
“ “ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና”

  — ፊልጵስዩስ 3፥18
👉 በአምላኩ ደም የተቀደሰ ከፈጣሪው ጐን በወጣ ውሃም የተጠመቀ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
👉 ለገነት ዛፎች አክሊል፤ ለገዳም ዛፎችም ክብር የኾናቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
👉 ለአሸናፊ የእግዚአብሔር በግ መሠዊያ የኾነው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
👉 ለእስራኤል አምላክ የፋሲካው መሠዊያ የኾነ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
👉 የጎልጎታዊዉ የምስጢር ወይን መፍለቂያ የኾነ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
👉 ከርሱ ምእመናንን ለማተም የሚኾን የሕግንና የሥርዐት ደምን ያንጠባጠበ ዕፅ ምን ዐይነት ነው!
👉 ቡሩካን በጎችን ለማጠቢያ የሚኾን ምንጭን ያወጣ ዕፅ ምን ዐይነት ነው!
👉 ምድርን የቀደሳት ሰማይንም ያማተበበት፤ ዓለምንም ኹሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ በረከት የባረከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
👉 ሰማያውያንን ከምድራውያን ያስተባበራቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው! አዳምን ከስሕተት ያዳነው ሔዋንንም ከሞት ጻዕረኛነት ነጻ ያወጣት ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
👉 ስለ ርሱ በኦሪትና በነቢያት የተነገረ በሐዋርያትም በገሐድ የተሰበከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
👉 የተከሉትን የበተናቸው ያመኑትንም የሰበሰባቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
👉 ቤተ ክርስቲያንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ላይ የመሠረታት ዕፅ እንደምን ያለ ነው!"
(አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)
"እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ" 

@ewuntegna
@ewuntegna


#ቅዱስ_መስቀል

#ቤተ_ክርስቲያን_ከመሠረቷ_እስከ_ጉልላቷ_ያጌጠችው_በመስቀል_ነው

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከማኅሌት እስከ መቅደሱ የመስቀል አገልግሎት እጅግ ብዙ ነው ማኅሌቱን ስንመለከት ሊቃውንቱ ገና ስቡሕ ብለው የሚጀምሩት በመስቀል ሲሆን እንዲሁም የመስቀልን ክብር በሚያወሳ ጣዕመ ዝማሬ በየዚቁ መሐል በማቅረብ ነው ።

በመቀጠልም ዲያቆኑ የምልጣን ምስባክ በሚሰብክበት ሰዓት መስቀልን ይዞ ነው እስመ ለዓለሙና አንገርጋሪው የሚቃኘው ስለዚህ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን #መስቀል_የማኅሌቱ_ጌጥ_ነው ።

በቅድስት ውስጥ በሚቀርበው አገልግሎት ውስጥ ስንመለከት ደግሞ መልክአ ሥዕሉ የሚጀመረው በመስቀል ነው ተአምረ ማርያም የሚነበበው በመስቀል ነው ኪዳን የሚደረሰው በመስቀል ነው ።

ወደ መቅደሱ ውስጥ ስንገባ ደግሞ ቅዳሴው የሚጀመረው በመስቀል ነው ገና ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት የመቀደሻ ንዋያተ ቅድሳት መጀመሪያ በመስቀል ተባርከው ነው ለአገልግሎት የሚውሉት ለምሳሌ ጻሕሉ ፣ ጽዋው ፣ ዕርፈ መስቀሉ ፣ ሙዳዩ ፣ መሶበ ወርቁ ፣ ዕጣኑ ፣ ልብሰ ተክህኖው ፣ መጎናጸፊያው ፣ ማኀፈዱ ወዘተ በመስቀል ይባረካሉ ።

ቅዳሴው ሲጀመር ደግሞ ረቡዕ ዓርብና ቅዳሜ ሲሆን ገና መግቢያው የሚታወጀው በመስቀል ዜማ ነው ይኸውም « መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ እምኵሉሰ ፀሐየ አርአየ ። መሰቀል አበራ ከሁሉ ይልቅ ፀሐይን አሳየ #ለፀሐይ_ፀሐይዋ_ሆነ » የሚለውን ዜማ እያዜሙ ወደ መቅደስ ይገባሉ ።

ከዚያም ዲያቆናቱ የመጾር መስቀል ካህናቱ የእጅ መስቀል ይዘው ቅዳሴውን ያከናውናሉ በእያንዳንዱ የጸሎት አንጓ የመስቀል ቡራኬ አለ መልእክት ከመነበቡ በፊት ዲያቆናቱ መስቀል ይሳለማሉ ።

እንዲሁም በንዋየ ቅድሳቱ ላይ መስቀል ይሳላል ፤ ይቀረጻል ፤ ይጠለፋል ለምሳሌ በካህናት ልብሰ ተክህኖ ላይ በጽዋው ክዳን ላይ በዕርፈ መስቀሉ ጫፍ ላይ ፤ በማኅፈዱ ላይ በመሶበ ወርቁ ላይ ፣ በጽናው ላይ በአጎበሩ ላይ ፤ በመጻሕፍት ድጉሰት ላይ መስቀል ይደረጋል ።

ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጥምቀት የምትፈጽመው በ40ና በ80 ቀን ሀብተ ወልድ ስመ ክርሰትና የምታድለው ፤ ልጅነት የምታጎናጽፈው በመስቀል ነው ሥርዓተ ጋብቻ ሲፈጸም ሙሽራውና ሙሽሪት እጆቻቸውን በመስቀሉ ላይ አነባብረው ቃለ መሐላ የሚፈጽሙት ቃል ኪዳናቸውን የሚያረጋግጡት በመስቀል ነው ።

ምእመናን የእንግድነታቸውን ኑሮ ጨርሰው በሞት ከዚህ ዓለም ሲለዩ ቤተ ክርስቲያን ክብርት ነፍሳቸው ለፈጣሪያቸው ክቡር ሰውነታቸውን ለመቃብር የምታረካክበው በመስቀል ባርካ ነው የምትሸኘው ።

አባቶቻችን የመስቀልን ክብር በብዙ መንገድ እንዲገለጥ አድርገዋል ዓመታዊና ወርኃዊ በዓል ሰይመውለታል መልክ ደርሰውለታል #መልክአ_ሕማማት ጽላት ቀርጸውለታል ፤ ቤተ ክርስቲያን አንጸውለታል መስተብቁዕ ደርሰውለታል #መስተብቁዕ_ዘመስቀል
ውዳሴ ደርሰውለታል ፤ ድርሳን ጽፈውለታል #ድርሳነ_መስቀል ክርስቲያኖች በስሙ እንዲጠሩ አድርገዋል ለምሳሌ ብርሃነ መስቀል ፣ ገብረ መስቀል ፣ ወለተ መስቀል፣ ኀይለ መስቀል ፤ወልደ መስቀል ፤ መስቀል ክብራ ወዘተ እያሉ ስመ ክርስትና ተሰይሞለታል ።

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ከመሠረቷ እስከ ጉልላቷ  ያጌጠችው በመስቀል ነው

#እንኳን_ለብርሃነ_መስቀሉ_በሰላም_አደረሰን_አደረሳችሁ

@ewuntegna


አንተ ሐሳብህን ልትመራዉ እንጂ፤ ሐሳብህ አንተን ሊመራ ቦታ አትስጠዉ፥ እዉነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራዉ ሳይሆን ስሜቱን የሚመራ ነዉ።
        አቡነ ሸኖዳ ሣልሳዊ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


Репост из: Smart ፕሮፋይል Pictures🌼™
‼️አሰቸኳይ የ እርዳታ ጥሪ‼️

ይህቺ ልጅ ሜሮን ካፒታ ትባላለች የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ ስትሆን የሶስተኛ አመት የፊርማሲ ተማሪ ነበረች አሁን ካይ ግን የኩላሊት ታማሚ ሆና በአልጋ ካይ ትገኛለች። በአዲስአበባ ታዝማ የዉስጥ ደዌ የህከምና ማአከል ዉስጥ የምትገኝ ሲሆን ሁለቱም ኩላሊቷ መስራት ስላቆሙ በአጥበት ካይ ትገኛከች።
አናም ይሀ እጥበት ብቻ በቂ ባለመሆኑ ወደ ህንድ በመሄድ የኩላሊት ንቅለ ተከካ አንድታደርግ ተብላለች።
ቤተሰቦቿም የተጠየቁትን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻካቸው ለእርዳታ አጃቸዉን ዘርግተዋል አናንተም የተቻላችሁን አንድታደርጉ በፈጣሪ ስም አንጠይቃቹሃለው

አህታችን ሜሮንን አናድናት።

JOIN US 👉 @wendi_officiall🌼
https://t.me/+J0ynCyKIZu85N2Y0


‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር››
   ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

Показано 20 последних публикаций.