️️️️️𝗙𝗔𝗡𝗔 𝗧𝗩 (ፋና) 🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


This is FANA Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit
https://t.me/fana_televisions
#ሼር 🙏 #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን
ሀሳብ ወይም መረጃ ለማቀበል @FANA_TV_BOT
https://t.me/joinchat/WC9-gid0rxB-S4Ac

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


"ሀገር በቀል ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን ሲያመርቱ መመልከት በእጅጉ ያበረታታል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***

ሀገር በቀል
ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን እና መለዋወጫዎችን ሲያመርቱ መመልከት በእጅጉ ያበረታታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ የኤሌትሪክ ገመዶችን እና የኤሌትሪክ ማማዎችን ለኤሌክትሪክ ብሎም ለቴሌኮም ዘርፎች በሀገር ውስጥ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ የብረት ምርትን ማሳደግ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲያችን አካል ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የተሽከርካሪዎችን እና የመለዋወጫዎችን የምርት ሥራ በመመልከቴ ተደስቻለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሀገር በቀል ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን እና መለዋወጫዎችን ሲያመርቱ መመልከትም በእጅጉ ያበረታታል ብለዋል።
አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


ኢትዮጵያ ከፍተኛ የተባለ የኮሌራ ወረርሽኝ እያስተናገደች መሆኗን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ‼️
ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ የተባለ የኮሌራ ወረርሽኝ እያስተናገደች እንደምትገኝ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ለሚያካሂደው ሥራ አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገውም ገልጿል።

የድርጅቱ ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሐኖም ድጋፉ የማይገኝ ከሆነ ድርጅታቸው በሀገሪቷ የሚያከናውነውን ከጤና ጋር የተገናኝ ሥራ ለመቀጠል እንደሚቸገር ተናግረዋል።

ዶክተር ቴድሮስ የተስፋፋ ድርቅና በሽታ በሚሊየን የሚቆጠሩ አትዮጵያውያንን ሕይወት አደጋ ላይ መጣሉንም አስረድተዋል።

በተለይም በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ሌሎች አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭት እና ጦርነት የከፋ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት።

በርካታ የጤና ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመት መከሰቱን አስታውሰው የተለያዩ ወረርሽኞች መከሰታቸውንም ጠቅሰዋል።


የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ በሥምንት ክልሎች 41 ሺህ ሰዎች በኮሌራ በሽታ መያዛቸውንም ገልጿል።

በሽታው በዚህ ልክ በኢትዮጵያ ሲከሰት በታሪኳ ከፍተኛው እንደሆነም ነው ድርጅቱ የገለጸው።

ወባና ኩፍኝም ሌሎቹ ወረርሽኞች መሆናቸውን የጠቀሰው ድርጅቱ፥ በኢትዮጵያ ለሚያከናውነው የበሽታ መከላከልና ጤና አጠባበቅ ሥራ አፋጣኝ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ አቅርቧል።


አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ኬሚሴ አቅራቢያ ተረፍ በሚባል አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ እንዳለ የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዋል።
ሰሞኑን በአንፆኪያ ገምዛ መኮይ ዙሪያ እንዲሁም በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ በርግቢ በሚባል አካባቢ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ያደረሰ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ከአካባቢው መውጣታቸውን ተከትሎ የፋኖ ሀይሎች መኮይ ከተማ የገቡ ሲሆን ዛሬ ወደ ከሚሴ ለመግባት በሚል ልዩ ስሙ "ተረፍ" በሚባል ቦታ ላይ በዚህ ሰዓት ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ሰለመሆኑ ያነጋገርኳቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልኛል[አዩዘሀበሻ]።

አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


የውጭ ባለሀብቶች #በጅምላ እና #ችርቻሮ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ‼️
ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ ተደረገ፡፡  

በዚህም መሰረት የውጭ ባለሀብቶች በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡ 

#የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
 
በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው፤ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያሟሉ የውጭ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ነዳጅ በስተቀር በሁሉም የገቢ ንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት ይችላሉ፡፡

የጅምላ ንግድን በተመለከተ ከማዳበሪያ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላል ተብሏል፡፡ 

በተጨማሪም የውጭ ባለሀብቶች ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያሟሉ ለአገር ውስጥ ባለሃብት በተከለሉ ሁሉም የችርቻሮ ንግድ ስራዎች መሳተፍ እንዲችሉ መፈቀዱም ተጠቅሷል።  

በጉዳዩ ላይ በባለድርሻ አካላት የተካሄዱ ዝርዝር ጥናቶች ላይ በመመርኮዝ መሠረታዊ የፖሊሲ ለውጥ ያደረገው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድም አዲስ የአፈፃፀም መመሪያ ማጽደቁን ከኢቲቪ የተገኘው መረጃ ያሳያል።


አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


በአማራ ክልል ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር በሚያደርገዉ ዉጊያ ላይ የባህር ሀይል ወታደሮች እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ

የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ባለው ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል። ዳጉ ጆርናል ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንደተመለከተው"የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ተሰማርቷል" ብሏል።

ተቋሙ የባህር ሀይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አድሚራል ናስር አባዲጋን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶዎች በሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች ግዳጃቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ብሏል።

ማሪን ኮማንዶ በመርከብ ላይ በባህር ከሚሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ ግዳጁን የሚወጣ ሀይል መሆኑንም ሬር አድሚራል ናስር አባድጋ መናገራቸውን የሀገር መከላከያ ስራዊት ገልጿል።

ማሪን ኮማንዶ ከአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በወሰዳቸው እርምጃዎች የክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንም በዚሁ ዘገባ ላይ ተጠቅሷል።

የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን "መልሼ አደራጃለሁ" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው። ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁም አይዘነጋም።

#ዳጉ_ጆርናል


ሊቅ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን መጠኑ ከፍተኛ የኾነ ገንዘብ ወደ ግል ሒሳባቸው ሊያስገቡ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ ተባለ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የኾኑት ሊቅ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዋዜማ ከታማኝ ምንጮች ሰምታለች።

ምክትል ሥራ አስኪያጁ ትላንት ማክሰኞ ሚያዚያ 9 ቀን በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ አፍሪካ ኅብረት ዋና መስሪያ ቤት አካባቢ በሚገኝ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መጠኑ ከፍተኛ የኾነ ገንዘብ ወደ ግል ሒሳባቸው ሊያስገቡ ሲሉ መሆኑን ምንጮች ለዋዜማ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባዉ ተመልክቷል። ሊቀ አዕላፍ በላይ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ልደታ ወደሚገኘው አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች።

ሊቀ አዕላፍ በላይ ከዓመታት በፊት ከቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ልዩነት ከፈጠሩ በኋላ፣ በእርቅ ወደ ቤተክህነት ተመልሰው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኾነው እንደተሾሙ ይታወሳል።

Via ዋዜማ
#ዳጉ_ጆርናል


በስለት የተወጉት የኦርቶዶክስ ጳጳስ ጥቃት አድራሹን “ይቅርታ ብያለሁ” አሉ

ባለፈው ሰኞ በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በቀጥታ በሚተላለፍ ሰብከት ላይ ሳሉ በስለት ጥቃት የደረሰባቸው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በፍጥነት እያገገሙ እንደሆነ ገልጸው ጥቃቱን እንዳደረሰ ለተጠረጠረው ግለሰብም ይቅርታ እንዳደረጉ ተናግረዋል።

ጳጳሱ በተቀረጸ ድምጽ ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰቡ እንዲረጋጋም ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ሳምንት በተፈጸመው ጥቃት አራት ሰዎች ተጎድተዋል። ፖሊስ ጥቃቱ ሃይማኖታዊ መነሻ ያለው የሽብር ድርጊት ነው ብሏል።

ከክስተቱ በኋላ ጳጳሱ በሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ሁከት ተፈጥሯል። ጥቃቱን እንዳደረሰ የተጠረጠረ እና ራሱም የተጎዳው የ 16 ዓመት ታዳጊ በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም እስካሁን ክስ አልተመሰረተበትም። ባለስልጣናት የታዳጊውን እምነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ታዳጊው በአረብኛ ሲጮህ እና “ነብዩ” የሚልበትን ቪዲዮ የሀገሪቱ የስለላ ቢሮ እየመረመረው እንደሆነ የተቋሙ ኃላፊ ተናግረዋል። አራት ደቂቃ ርዝማኔ ባለው እና በቤተክርስትያኑ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው ድምጽ ላይ ጳጳሱ “ማንም ይሁን ማን” ይህንን ላደረገው ግለሰብ ይቅርታ አድርጌያለሁ ሲሉ ይደመጣሉ።

“እናም ለአንተ ሁልጊዜ እጸልያለሁ። ይህንን እንድታደርግ የላኩህ ማንም ይሁኑ ማን በኃያሉ ኢየሱስ ስም ይቅርታ አድርጌላቸዋለሁ” ብለዋል። “የክርስቶስን ተግባር እንድትፈጽሙ እፈልጋለሁ። ጌታችን ክርስቶስ እንድንጣላ በፍጹም አላስተማረንም። መጥፎ ስራ እንድንሰራ አላስተማረንም” ብለዋል።

#ዳጉ_ጆርናል


አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት የኢድ አል ፈጥር እና መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ658 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።

በዚህም፦

🟢 በሙሉ ይቅርታ ወንድ 637 ፤ሴት 11 ፤

🟢 በልዩ ሁኔታ ወንድ 3 ሴት 3

በጠቅላላው 654 ታራሚዎች ሲሆኑ ለ 4 ወንዶች ደግሞ የእስራት ቅናሽ ተደርጎላቸዋል።

በክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ስር ባሉ #ሰባት ማረሚያ ተቋማት ውስጥ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች በ2016 በጀት ዓመት ይቅርታ ሲደረግ ይህ ለ2ኛ ዙር ነው።

አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል?

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ በርካቶች ጥያቄ አድርሰውናል።

12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን አስታወቀ‼️

የኢትዯጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታውቋል።ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺህ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለፁ ይታወሳል።

ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺህ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺህ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ባንኩ ገልጿል።

አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


አንድ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ይዞ ለመሰወር ሲሞክር በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የኢትዮ ቴሌኮም አሶሳ ቅሪንጫፍ የሽያጭ ሰራተኛ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ይዞ ለመሰወር ሲሞክር ነው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው።

ግለሰቡ ገንዘቡን ይዞ ከተሰወረ ከአንድ ሳምንት በኋላ በፖሊስ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የአሶሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃ ያመለክታል።

👉"ባለቴሌብሩ ኢትዮ ቴሌኮም ሚሊየን ብሮችን በአንድ ሰራተኛ በካሽ ይሰበስባል?" የሚለው ጥያቄ ይመዝገብልን😳

አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


የራያ አላማጣ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ትናንት ከቆቦ ከተማ 15 ኪሜ ርቀት ላይ በድንገት በተከፈተበት ተኩስ ህይወቱ ማለፉን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየተሰሙ ቢሆንም በግድያውን ዙሪያ እስካሁን የተረጋገጠና ትክክለኛ መረጃ አልተገኘም።
አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ጋር ተወያዩ
****

የአዲስ
አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ከሆኑት ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገለፁ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ በመዲናዋ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ስራዎች፣ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም አዲስ አበባ ከአሜሪካ ከተሞች ጋር ያላትን የእህትማማችነት ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያም ተወያይተናል ብለዋል።

አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የፓርላማው ድብድብ‼

የጆርጂያ ሕግ አውጭዎች ሰኞ ዕለት በተሰበሰበው ፓርላማ ውስጥ ተደባድበዋል።

የፓርላማ አባላቱ አወዛጋቢ በሆነው የውጭ ወኪሎች ረቂቅ ህግ ላይ በፓርላማ በተካሄደው ክርክር ወቅት የተቃዋሚው ፓርላማ አባል አሌኮ ኤሊሳሽቪሊ የገዥውን የጆርጂያ ድሪም ፓርቲ መሪ ማሙካ ምዲናራዜን በንግግራቸው ፊት ለፊት በቡጢ ከመቱ በኋላ ነው።

በውጭ አገር ገንዘቦችን የሚቀበሉ ድርጅቶች እንደ የውጭ ወኪልነት እንዲመዘገቡ ወይም ሊቀጡ የሚችሉበት ሂሳቡ፣ ጆርጂያን ፖላራይዝድ አድርጓል እና በ2023 መጀመሪያ ላይ የጅምላ ሰልፎችን አድርጓል።
=አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ጳጳሱ በጩቤ ተወጉ
(NB ምስሉ ሊረብሽ ይችላል)
ታዋቂው  የኤሲሪያን  (አሶራውያን) ኦርቶዶክስ ቄስ ብጹዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል (ቢሾፕ ማር ማሪ) ሲድኒ ውስጥ በዘውትራዊውና የተመለደው ቀጥታ የሚሰራጭ  የስብከት መርሃ ግብራቸው ላይ ሳሉ ማንም ባልገመተው ሁኔታ አንድ ሰው በፍጥነት ተጠግቶ በጩቤ ፊትና አንገታቸው ላይ ወግቷቸዋል።

የጉባኤው አባላት ጳጳሱን ለመርዳት ሲጮሁ እና ሲጣደፉ ይሰማሉ።

አንድ ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉን የኒው ሳውዝ ዌልስ ፖሊስ አስታውቋል።

በጥቃቱ አራት ሰዎች ቆስለዋል ሲል ኒው ሳውዝ ዌልስ ዘግቧል።
በፅኑ ህሙማን መርጃ ውስጥ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


የዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ
አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions


በጂቡቲ ሰነድ አልባ ሆነው የሚኖሩ ዜጎች ያለባቸውን ችግር ለመፍታት በተለየ መልኩ ይሰራል፡- የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት
****

በጂቡቲ ሰነድ አልባ ሆነው የሚኖሩ ዜጎች ያለባቸውን ችግር በተሻለ መልኩ ለመፍታት እና የድንበር ኬላ ትብብርን ለማጠናከር በተለየ መልኩ እንደሚሰራ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ።

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በሆኑት ሰላማዊት ዳዊት የተመራ የልዑካን ቡድን በጂቡቲ ከተለያዩ አካላት ጋር ምክክር አድርጓል።

ምክክሩም በጅቡቲ የሚኖሩ እና ሀገሪቱን እንደመሸጋገሪያ በመጠቀም ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚሄዱ ሰነድ አልባ ዜጎች ያለባቸውን ችግር ለመቅረፍ እና ከኬላ ቁጥጥር ላይ ያለ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ልዑኩ በቆይታው በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የጂቡቲ ኃላፊ እና በጂቡቲ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በዘርፉ ባሉ ችግሮች እና በሚወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ዙርያ ጠቃሚ ውይይት ማካሄዱ ተገልጿል።

በጅቡቲ ኢምባሲ በተደረገ ውይይት፤ኢትዮጵያውያን በአግባቡ በመለየትና ሰነዳቸውን በማጣራት የጉዞ ሰነድ እንዲዘጋጅላቸው በማድረግ ወደ ሀገር በማስመለስ ስራ ያለው ክፍተት እንዲስተካከል ማስቻልና ይህንንም ወጥ በሆነ መንገድ ለመምራት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል።

አስተያየት መረጃ  ካሎት @FANA_TV_BOT 👈ያድርሱን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 
@fana_televisions
@fana_televisions

Показано 17 последних публикаций.