FBC (Fana Broadcasting Corporate)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


This is FBC's official Telegram channel.
For more updates please visit www.fanabc.com

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሚደግፍ የፕሮጀክት ስምምነት ከጃይካ ጋር ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሚደግፍ የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረሙ። የፕሮጀክት ስምምነቱ ለአራት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴን ተግባራዊ በማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪን ተወዳዳሪነት ማሳደግ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተጠቁሟል። በዚህም የቴክኒካል፣ የፖሊሲ እና የአቅም ግንባታ ድጋፎች ይደረጋሉ ተብሏል። ስምምነቱን የተፈራረሙት…

https://www.fanabc.com/archives/243072


በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በሸገር ከተማ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በሸገር ከተማ በሰበታ ክላስተር የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱ አቶ ሽመልስን ጨምሮ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/243067


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሐዋሳ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለሥራ ጉዳይ ሐዋሳ ገብተዋል፡፡ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች÷ ሐዋሳ ሲገቡ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞና የክልሉ የሥራ ሀላፊዎች በሐዋሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው…

https://www.fanabc.com/archives/243064


አየር መንገዱ ወደ ፖላንድ ዋርሶው በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው 4 ሳምንታዊ በረራዎችን ማድረግ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡ ዋርሶው በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) የተመዘገቡ ቅርሶች መገኛ፣ የድንቅ ኪነ ሕንፃዎች ማዕከል እና ታሪክንና ዘመናዊነትን አጣምራ የያዘች በዓለም በቱሪስት መዳረሻነታቸው ከሚጠቀሱ ቀዳሚ ከተሞች አንዷ ነች። አየር መንገዱ…

https://www.fanabc.com/archives/243050


ኤምባሲው በፓኪስታን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፓኪስታኑ የዘላቂ ልማት ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን አስጀመረ፡፡

ኤምባሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው÷በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ይፋ የተደረገው በኢስላማባድ በተካሄደው የኢትዮ-ፓኪስታን ወዳጅነት ሴሚናር ላይ ነው፡፡

፡፡ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር…

https://www.fanabc.com/archives/243043


የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር አፈጻጸም ላይ ያተኮረ መድረክ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ለውጦች ላይ ያተኮረ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ነገ በሃዋሳ ከተማ ይካሄዳል። በምክክር መድረኩ ለመሳተፍ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል፡፡ በእንስሳትና አሣ ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ የተቀረጸው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ…

https://www.fanabc.com/archives/243045


የጉራጌ ህዝብ ስለ አንድነት ያስተማረ፣አንድነት ሃይል ነው ብሎ የሚያምን ህዝብ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉራጌ ህዝብ ስለ አንድነት ያስተማረ ፣ አንድነት ሃይል ነው ብሎ የሚያምን ፣በአንድት የሚገኘውን ፀጋ በልምድ ፣በሕይወቱ የተገነዘበ ነው ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ የተገኙት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ÷ጉራጌ “ጎጎት”በተባለ…

https://www.fanabc.com/archives/243039


የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫን አስመልክቶ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫን አስመልክቶ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡ ነገ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገውና የአዲስ አበባን ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልለው የ2016 የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ሩጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት…

https://www.fanabc.com/archives/243032




የጉራጌ ህዝብ ሀገራዊ ለውጡ እውን እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል- አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉራጌ ህዝብ ሀገራዊ ለውጡ እውን እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ገለፁ፡፡ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ÷በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ምስረታ ከፍተኛ…

https://www.fanabc.com/archives/243029


በወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በድጋፍ ሰልፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል ፣የክልልና የዞን አመራሮች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡ በድጋፍ ሰልፉ የከተማው ነዋሪዎች ለውጡን የሚደግፉ የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

https://www.fanabc.com/archives/243024


በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ሀምበሪቾን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

ቀን 10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማን ለድል ያበቃውን ጎል የሀምበሪቾው ዲንክ ኪያር በራሱ ላይ አስቆጥሯል።

በተመሳሳይ ቀን 1:00 ላይ የተካሄደው የፋሲል ከነማ እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።


ከ1 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016/17 ምርት ዘመን 1 ሚሊየን 78 ሺህ 257 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡ እስከ አሁን ባለው መረጃም በ20 መርከቦች 1 ሚሊዮን 116 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ መድረሱ ተመላክቷል፡፡ ጂቡቲ ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ 96 ነጥብ 61 በመቶ የሚሆነው…

https://www.fanabc.com/archives/243018


ተመድ በመካከለኛው ምስራቅ የሚስተዋለው አደገኛ የበቀል አዙሪት እንዲቆም አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን አደገኛ የበቀል አዙሪት ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አስገንዝበዋል። የዋና ፀሐፊው ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በሰጡት መግለጫ፤ ዋና ፀሐፊው በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን አደገኛ የበቀል አዙሪት ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው ማለታቸውን አንስተዋል። ዋና ፀሐፊው ማንኛውንም የበቀል እርምጃ…

https://www.fanabc.com/archives/243009


ከ30 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ጉዳት በማድረስ ተደራራቢ ክስ የቀረበበት ግለሰብ በ4 ክሶች ነጻ ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ30 ቢሊየን ብር በላይ የግብር ጉዳት አድርሷል ተብሎ ተደራራቢ ክስ የቀረበበትን ግለሰብ በአራት ክሶች ነጻ በማለት በሁለት ክስ ብቻ እንዲከላከል ብይን ተሰጠ። የዐቃቤ ሕግ የምስክር ቃልና የሰነድ ማስረጃን መርምሮ ብይን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ነው። የፍትህ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት…

https://www.fanabc.com/archives/243007


የግብርና ሜካናይዜሽን የልህቀት ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሜካናይዜሽን የልህቀት ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀመጠ። በደቡብ ኮሪያ መንግስት ድጋፍ የሚገነባው ማዕከሉ የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂ ጥራት ለመፈተሽ፣ የአቅም ግንባታ ስራ እና ተያያዥ ተግባራትን ለማከናወን አገልግሎት እንደሚውል ተገልጿል። የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ጥረት የደቡብ ኮሪያ መንግስት እያደረገ ያለውን…

https://www.fanabc.com/archives/243002


የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም÷ የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ለ2ኛ ዙር የሚሰጠውን ይቅርታ ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 431 ወንድ እና ለ29 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል ብለዋል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/242990


በማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ እየተካሄደ ባለው የማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸንፋለች፡፡ በ60 ኪሎግራም የደቡብ አፍሪካ አቻዋን የገጠመችው ቦክሰኛዋ በውድድሩ ሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ባሰረፈችው ቡጢ በዳኛ ውሳኔ አማካኝነት በበቃኝ ማሸነፍ ችላለች። ማሸነፏን ተከትሎም ቦከሰኛዋ ወደ ቀጣይ ዙር…

https://www.fanabc.com/archives/242940


በአዲስ አበባ 150 የኤሌክትሪክ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች ርክክብ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃዉ ለሚገኙ ተቋማት የሚያገለግሉ 150 የኤሌክትሪክ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች (ሚኒባስ) ርክክብ አከናወነ።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎቹ ለ11ዱ ክፍለከተሞች እና ለማዕከል ተቋማት የተሰጡ ናቸው ተብሏል።የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎቹን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ለህዝብ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት ተሽከርካሪዎችን መግዛት ያስፈለገበት…

https://www.fanabc.com/archives/242973


የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ እያደረገ ነው – አቶ ፈቃዱ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተከናወነ የሚገኘው የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ እያደረገ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ገለፁ፡፡ በአቶ ፈቃዱ ተሰማ የተመራ ልዑክ በሰሜን ሸዋ ዞን ቅምቢቲ እና አቢቹኛኣ ወረዳዎች በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል፡፡ በዚህ ወቅትም አቶ ፈቃዱ…

https://www.fanabc.com/archives/242974

Показано 20 последних публикаций.