ዘመን ባንክ የሠራተኞች ሙያዊ እድገት ተምሳሌት!
****
ላለፉት 3 ቀናት በ CaFEC SC አማካይነት በIFRS 9 Financial instruments ላይ የተዘጋጀ ስልጠና ለ Zemen Bank S.C. ሠራተኞች ሰጥቼ አጠናቀቅሁ።
በስልጠናው ላይ በሰለጠነው ዓለም በእያንዳንዱ ሙያ ላይ ስለሚተገበረውና ቀጣይነት ስላለው የሙያዊ እድገት /Continuous Professional Development/ አስገዳጅነት ለሰልጣኞቹ ሳስረዳ...
"የእኛም ባንክ ለ LinkedIn ገንዘብ ከፍሎልን ስልጠና እንድንወስድ፣ ሙያችንን እንድናሳድግ እድል ሰጥቶናል፣ ስልጠና ከአመታዊ እና ከመንፈቃዊ የአፈጻጸም መለኪያ/performance evaluation ነጥቦች መካከል አንዱ ነው! ሰራተኞች በየመንፈቁ ሊማሩ ስለሚገባው ዝቅተኛ ሰዐት ተቀምጦ በእዛ እንለካለን"
ሲሉ ልቤን ያሞቀ ነገር ነገሩኝ።
ዘመን ባንክ የሠራተኞቹን ሙያዊ እድገት ለማረጋገጥ ያሳየው ቁርጠኝነት፣ በተለይ ደግሞ ስልጠናን ከአፈጻጸም መለኪያ ጋር ማያያዙ ለሌሎች ተቋማት ተምሳሌት ሊሆን የሚችልና ሊተገበር የሚገባው ነገር ሆኖ አግቼዋለሁ።
በሠራተኞች ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ለሠራተኞቹ ጥቅም ብቻ ሲባል የሚደረግ ሳይሆን ባንኩ በዘርፉ ላይ የሚኖረውን ተወዳዳሪነት የሚጨምርና በአጠቃላይ ለባንኪንግ ዘርፉ ስልጡንና ለለውጥ የተዘጋጀ የሰው ኃይልን የሚያበረክት መሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል ስል ጽሁፌን እደመድማለሁ።