Fetan Sport ⚽️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ፈጣን ስፖርት የአውሮፓን ከፍተኛ የእግር ኳስ ሊጎች የሚሸፍን የኢትዮጵያ የዜና ቻናል ነው። ይዘቱም የቡድን ዜናዎችን፣ የጨዋታ ውጤቶችን፣ የተጫዋቾች ዝውውሮችን እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያካትታል።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


🏆 ሳላህ: "ዛሬ ነበር ማሸነፍ የፈለኩት"

የሊቨርፑል ኮከብ መሐመድ ሳላህ ማክሰኞ ምሽት የሪድስ የሊግ ዋንጫ አሸናፊነት ዛሬ በአንፊልድ በደጋፊዎች ፊት እንዲረጋገጥ እንደፈለገ ገልጿል።

"አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ ባደረጉት ጨዋታ ተሰባስበን ስንጠብቅ ነበር፣ ነገር ግን በዚህ መንገድ እንድናረጋግጥ አልፈለኩም ነበር" ብሎ አብራርቷል።

ስሜቱን በመግለጽ "ዛሬ በአንፊልድ በደጋፊው ፊት የዋንጫ አሸናፊነታችን እንዲረጋገጥ ፈልጌ ነበር፣ ተሳክቶልኛል" ሲል፣ "ከእነዚህ ደጋፊዎች ጋር ሊጉን ማሸነፍ የማይታመን ስሜት አለው" ብሏል።


🏆 ማድሪድ ተጫዋቾች ከባድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል!

የሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች በትላንቱ የኮፓ ዴላሬ ፍፃሜ ጨዋታ ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ ምክንያት ከባድ የጨዋታ እገዳ ይጠብቃቸዋል።

"ዘ አትሌቲክ" እንደዘገበው፣ አንቶኒዮ ሩዲገር ከ4 እስከ 12 ጨዋታዎች ሊታገድ ሲችል፣ ጁድ ቤሊንግሀም በሚቀጥለው ዓመት ሁለት የኮፓ ዴላሬ ጨዋታዎች እገዳ ሊጣልበት ይችላል።

እንዲሁም፣ ሉካስ ቫስኩዌስም የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተገልጿል።

ለማስታወስ ያህል፣ ከፍፃሜ ጨዋታው በኋላ ቤሊንግሀም እና ቫስኩዌስ ቀይ ካርድ ተሰጥቷቸው ነበር።


🔥 ሻምፒዮንነቱን ለማረጋገጥ አንድ ነጥብ የሚያስፈልገው ሊቨርፑል ዛሬ ወሳኙን ጨዋታ ከቶተንሀም ጋር ያደርጋል።

❔ ማን ያሸንፋል ❔


⚪️ ሩዲገር ለዳኛው ይቅርታ አቀረበ!

የሪያል ማድሪድ ተከላካይ አንቶኒዮ ሩዲገር በትላንት ምሽት ጨዋታ ላይ ላሳየው ባህሪ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይቅርታ ጠይቋል። "ላሳየሁት ባህሪ የማቀርበው ምክንያት የለኝም። ለተፈጠረው ነገር ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ሲል ገልጿል።

"ተቀይሬ ከወጣሁ በኋላ ቡድኔን መርዳት ባለመቻሌ ጨዋታው ከመጠናቀቁ በፊት ስህተት ሰርቻለሁ" በማለት፣ በተለይም "የጨዋታውን ዳኛ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ሲል ለባህሪው ኃላፊነት ወስዷል።

የጀርመኑ ተጫዋች ከ4 ጨዋታዎች በላይ ሊታገድ እንደሚችል ዘገባዎች ይጠቁማሉ።


🏆 የአርሰናል እና ፒኤስጂ ጨዋታ በስሎቬኒያዊ ዳኛ ይመራል!

በፊታችን ማክሰኞ በኤምሬትስ ስታዲየም የሚደረገው የሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በ42 ዓመቱ ስሎቬኒያዊ ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺክ የሚመራ ይሆናል።

ይህ ተሞክሮ ያለው ዳኛ በዚህ ዓመት አርሰናል ፒኤስጂን በኤምሬትስ 2-0 ያሸነፈበትን የሊግ ክፍለ ጊዜ ጨዋታም መርቷል። ሳስኛሉ ፍንጮች ነው!

በተጨማሪም፣ አርሰናል እስካሁን በስላቭኮ ቪንቺክ ዳኝነት ስር ባደረጋቸው ጨዋታዎች አንድም ጊዜ አልተሸነፈም።

እናንተስ ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ብላችሁ ትገምታላችሁ?


🔴 አሞሪም: "ዩናይትድን በመረከቤ አልፀፀትም"

የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቀያዮቹን ሴጣኖችን መረከባቸው እንደማይፀፀታቸው በግልፅ አስታውቀዋል። "አልፀፀትም" ያሉት አሰልጣኙ፣ ክለቡን መምራት ከፍተኛ ፈተና እንደሆነ ቢገልጹም፣ ተሞክሮውን ለሚቀጥለው ዓመት እንደ ዝግጅት እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል።

"ብዙ ተበሳጭተናል፣ ብዙም ተሰቃይተናል፣ ነገር ግን ይህንን ራሳችንን ለሚቀጥለው አመት በደንብ ለማዘጋጀት እንጠቀምበታለን" ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የደጋፊዎችን ድጋፍ እያደነቁ፣ "ድጋፉ ልዩ ነው፣ አመስጋኝ ነኝ፣ ነገር ግን ውጤት ካላመጣን እንደሚቆም አውቃለሁ" ሲሉ አክለው ተናግረዋል።


🔴 የሊቨርፑል ትኬቶች በአስገራሚ ሁኔታ ተናሩ!

ሊቨርፑል ዛሬ በአንፊልድ ከቶተንሀም ጋር በሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ፣ ሊጉን ማሸነፉን ሊያረጋግጥ ይችላል። ይህ ታሪካዊ ጨዋታ፣ ሬድስ ከ35 አመታት በኋላ የሊግ ዋንጫን በራሳቸው ሜዳ ለማንሳት የሚያስችላቸው ሲሆን፣ ለመታደም ከፍተኛ ፍላጎት ተፈጥሯል።

በኦንላይን መገበያያ ድረገጾች ላይ የሚገኙ ትኬቶች ዋጋ በአስደናቂ ሁኔታ ናሯል። በመጀመሪያ በ61 ፓውንድ የተሸጡ ትኬቶች አሁን ከ3,000 ፓውንድ በላይ እየተሸጡ ነው!

ክለቡ ደጋፊዎችን ሀሰተኛ ትኬቶች ከሚሸጡ ህጋዊ ካልሆኑ ቦታዎች እንዳይገዙ አሳስቧል።

ለተጨማሪ የስፖርት ዜናዎች ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+zWR077nMKsk4OTY0


የስራ ኣማራጭ ለማግኘት የሚቸገሩ ኢትዮጵያዊያን ሆይ፣ ጥሩ ዜና ኣለኝ ለእናንተ!

ምርጥ የሆኑ ከፍተኛ ክፍያ ያላቸው የNGO ስራዎችን በኢትዮጵያ ውስጥ በቀላሉ ማግኘት ይፈልጋሉ? የእኛን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።

በእኛ ቻናል ላይ የምታገኙት፡
• የዕለት ተዕለት የስራ ማስታወቂያዎች
• ከNGOዎች ጋር ለመስራት የሚጠቅሙ ጠቃሚ ምክሮች
• ኤክስፐርቶች ስለ ኢንተርቪው ዝግጅት የሚያካፍሏቸው ጠቃሚ ሀሳቦች
• የህይወት ታሪኮች - ስኬታማ የሆኑ ግለሰቦች ያካፍሉናል

ዛሬውኑ ይቀላቀሉ! ካልተቀላቀሉ የሚያመልጥዎ ብዙ ነገር ነው።

👉 https://t.me/+uwLJGsxjDekzZDQ0

#NGOjobs #EthiopiaJobs #CareerOpportunities #ስራ #ኢትዮጵያ


🔴 ዩናይትድ እና ኩንሀ - ዝውውር በጥሩ ሁኔታ እየተጓዘ ነው!

ማንችስተር ዩናይትድ የዎልቭሳምፕተን ኃይል ተጫዋች ማቲውስ ኩንሀን ለማስፈረም ንግግር መጀመሩ ታውቋል። ቀያዮቹ ሴጣኖች ይህን ዝውውር በተቻለ ፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰሩ ነው።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ኩንሀን ለማፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ሲገለጽ፣ ተጫዋቹም ዩናይትድን ለመቀላቀል ዝግጁ መሆኑ ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት ዝውውሩ በትክክለኛው አቅጣጫ እየተጓዘ እንደሆነ ምንጮች ይጠቁማሉ።


⚪️ ካማቪንጋ ከአመቱ ውድድሮች ሙሉ በሙሉ ይርቃል

የሪያል ማድሪድ አማካይ ኤድዋርዶ ካማቪንጋ ትላንት ምሽት ሄታፌን ባሸነፈበት ጨዋታ በግራ እግሩ ላይ ከባድ ጉዳት አጋጥሞታል። በዚህም ምክንያት ተቀይሮ ሜዳውን ለቆ ወጥቷል።

ይህን ተከትሎ ካማቪንጋ ከቅዳሜው የካፓ ዴላሬ ፍፃሜ እና ከመላው የውድድር አመቱ ጨዋታዎች ውጪ እንደሚሆን ተሰምቷል።

የክለቡ አመራሮች ተጫዋቹ ከሚቀጥለው የአለም ክለቦች ዋንጫም ውጪ እንደሚሆን ስጋት እንዳላቸው ታውቋል።


#PremierLeague

🏆 ሊቨርፑል ለ20ኛ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አንድ ነጥብ ብቻ ይፈልጋል!

አርሰናል ዛሬ ከክሪስታል ፓላስ ጋር አቻ መለያየቱን ተከትሎ፣ ሊቨርፑል በቀጣይ ከቶተንሀም ጋር በሚያደርገው ጨዋታ አሸናፊ ከሆነ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ያረጋግጣል።

ሬድስ ዋንጫውን ካገኙ ከቼልሲ፣ አርሰናል እና ሌሎች ቀሪ ተጋጣሚዎች የክብር አቀባበል ይጠብቃቸዋል።

ይህ ታላቅ ጨዋታ እሁድ መሽቱ 12:30 ላይ በአንፊልድ ይካሄዳል።


🔴 ማውንት: "ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ መድረስ እንፈልጋለን"

የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሜሰን ማውንት በቀሪው የውድድር ጊዜ ሙሉ ግልጋሎት መስጠት እንደሚፈልግ ገለፀ። "በሁሉም ጨዋታዎች መኖር እፈልጋለሁ" ያለው ማውንት፣ ቡድኑ በዩሮፓ ሊግ እስከ ፍፃሜ እንደሚጓዝ ተስፋ አለው።

ለተጨማሪ የሰፖርት ዜናዎች ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+zWR077nMKsk4OTY0


"ሜሲ ለብቻው ለውጥ የማምጣት አቅም አለው" - ቤቤቶ

የቀድሞው ታሪካዊ የብራዚል ኮከብ ቤቤቶ የአሜሪካ ሊግ ለውጥ ላይ እንደሆነ ገልጿል።

ቤቤቶ በሰጠው አስተያየት "የአሜሪካ ሊግ ባለፉት አመታት ተለውጧል፣ እንደ ሊዮኔል ሜሲ ያሉ ታላላቅ ተጫዋቾች ለለውጡ ትልቅ አቅም አላቸው" ሲል ተናግሯል።

"ሜሲ የትኛውንም ጨዋታ የመቀየር አቅም አለው" ያለው ቤቤቶ፣ በአለም የክለቦች ዋንጫ ላይ ተሳታፊ መሆኑ ትኩረትን እንደሚስብ አክሏል።

ቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+-Tnh-aUH3CIzMzg0


"ቶተንሃም የአካዳሚ ቡድን ነው የሚመስለው!" - ካራገር 🗣️
የቀድሞ የሊቨርፑል ኮከብ ጄሚ ካራገር የአንሄ ፖስቴኮግሉን አካሄድ ነቅፏል። 😠
"አንሄ ስለ ችግሩ ደጋግሞ ይናገራል እንጂ መፍትሄ እየሰጠ አይደለም" ሲል ካራገር ተናግሯል። 🤨
"የቶተንሃም የተከላካይ ክፍል በጣም ደካማ ነው፤ ቡድኑ የአካዳሚ ቡድን ይመስላል" ብሏል። 🤯
ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+-Tnh-aUH3CIzMzg0


ዩናይትድ የኩንሀን ዝውውር ንግግር ጀመሩ!

ማንችስተር ዩናይትድ የዎልቭሱን ኮከብ ማቲውስ ኩንሀ ለማስፈረም ወደ ንግግር መግባታቸው ተገልጿል።

ዘ አትሌቲክ እንደዘገበው ቀያይ ሴጣኖቹ ከዎልቭስ ጋር ፍሬያማ ውይይት እያደረጉ ነው።

ዎልቭስ የተጫዋቹን ኮንትራት ማፍረሻ 62.5 ሚልዮን ፓውንድ እንዲከፈል እየጠየቁ ሲሆን፣ ክፍያው ለረጅም ጊዜ ተከፋፍሎ እንደሚፈፀም ተነግሯል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ተጫዋቹን ለአስር ቁጥር ቦታ እንደሚፈልጉት ታውቋል።

ቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+-Tnh-aUH3CIzMzg0


"ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ድል አሳክቷል!"

ማንችስተር ሲቲ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከኤቨርተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሲቲው ግቦች በኒኮ ኦሬሊና ማቲኦ ኮቫቺች አማካኝነት የተመዘገቡ ሲሆን፣ ኦሬሊ በ2025 ባደረጋቸው አስር ጨዋታዎች አምስት ጎሎችን አስቆጥሮ ሁለት አምቻችቶ አቀብሏል። በሌሎች ጨዋታዎች፣ ዌስትሀም ዩናይትድ ከሳውዝሀፕተን 1ለ1 ተጣጥሟል፣ ክሪስታል ፓልስና በርንማውዝ 0ለ0 ተለያይተዋል፣ እንዲሁም ብሬንትፎርድ ብራይተንን 4ለ2 አሸንፏል። በሊግ ደረጃም፣ ማንችስተር ሲቲ በ4ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ 58 ነጥብ አለው፣ ኤቨርተን ደግሞ በ13ኛ ደረጃ ላይ ሆኖ 38 ነጥብ አለው።

ተጨማሪ እና ተሳታፊ ለመሆን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/+zWR077nMKsk4OTY0


"ራምሴይ ካርዲፍ ሲቲን በአሰልጣኝነት ይመራል!"

የቀድሞው የአርሰናልና ጁቬንቱስ አማካይ አሮን ራምሴ በሚቀጥሉት ሶስት ጨዋታዎች ካርዲፍ ሲቲን በአሰልጣኝነት እንዲመራ ተሾሟል። በልጅነቱ ካርዲፍ ሲቲን የተጫወተው ራምሴ፣ ክለቡ አሰልጣኙን ማሰናበቱን ተከትሎ ፣ አሁን እያገለገለ ያለውን ቡድን እንዲመራ ተመርጧል። በአሁኑ ሰዓት በጉዳት ምክንያት ከጨዋታ ውጪ የሚገኘው ራምሴ፣ በሻምፒዮንሺፕ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ያለውን ቡድን ከወረዳ የመታደግ ሀላፊነት ተሰጥቶታል።

ተጨማሪ እና ተሳታፊ ለመሆን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/+zWR077nMKsk4OTY0


"ከክለቡ ጋር የተፈጠረ ችግር የለም" - አንቾሎቲ

የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከክለቡ ጋር አለመግባባት ውስጥ መግባታቸው "ሀሰተኛ" መሆኑን አረጋግጠዋል። "የክለቡ ውጤት ሁላችንንም ነው የጎዳን" ያሉት አንቾሎቲ፣ ምንም አለመግባባት እንደሌለና ሁሉም አንድ አላማ እንዳላቸው ገልጸዋል። ከፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ጋር ችግር እንዳለ የሚናፈሰው ወሬ "የሀሰት ዜና" መሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኙ፣ ፔሬዝ "በጥሩ ጊዜያት በበለጠ ድጋፍ እና ፍቅር" እያሳዩት እንደሆነ አመልክተዋል። "አሁንም ለዋንጫ እየተፎካከርን ነው" ያሉት አንቾሎቲ፣ ስለወደፊት ቆይታቸው በአመቱ መጨረሻ ከክለቡ ጋር እንደሚነጋገሩ ተናግረዋል።

ተጨማሪ እና ተሳታፊ ለመሆን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/+zWR077nMKsk4OTY0


"ሌዊስ ስኬሊ ውሉን ሊያራዝም ነው!"

የአርሰናል ወጣት የመስመር ተጨዋች ሌዊስ ስኬሊ በክለቡ አዲስ ኮንትራት ለመፈረም እየተቃረበ ነው። 18 ዓመት ዕድሜ ያለው እንግሊዛዊው ተጨዋች ውሉን ማራዘሙ "የጊዜ ጉዳይ ብቻ" እንደሆነ ተዘግቧል። የውል ማራዘሙ ሂደት አዲሱ የክለቡ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሬ ቤርታ እንደሚመሩት ተነግሯል።

ተጨማሪ እና ተሳታፊ ለመሆን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/+zWR077nMKsk4OTY0


"በጋርዲዮላ መሰልጠን ሁለተኛ ዲግሪ ነው" - ሜሲ

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስር መሰልጠኑን "በእግርኳስ ሁለተኛ ዲግሪ ያገኘሁ ያህል" ሲል ገልጿል። "ጋርዲዮላ ልዩ አሰልጣኝ ነው" ያለው ሜሲ፣ አሰልጣኙ ነገሮችን በሚያይበት መንገድ ማንም እንደማያይና በእግርኳስ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር መቻሉን ተናግሯል።

ተጨማሪ እና ተሳታፊ ለመሆን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/+zWR077nMKsk4OTY0

Показано 20 последних публикаций.