እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ ?
በፍቅር ብዙ ጊዜያትን አብረን አሳልፈናል ። የተገናኘንበት አጋጣሚ በጣም ድንቅ ነበር ። ለፍቅር እመኘው የነበረ አይነት ሰው ነው፡፡ በዚህም ፈጣሪዬን አብዝቼ አመሰግነው ነበረ ።
በቀደመው ህይወቴ ለጓደኞቼም ለቤተሰቦቼም ስለ ፍቅር ጓደኛ ማውራትም ማስተዋወቅም አልደፍርም ነበር ። አሁን ግን ደፈርኩ በኩራት አስተዋወቅሁ ።
የምንጋባበትን ቀን ለመቁረጥ አሰብንና እኔ ቶሎ እንዲሆን መወትወት ጀመርኩ ። ቆይ ዛሬ ቆይ ነገ ሲል ብዙ ጊዜያት ቆየን ። የምንቆይበት ሁኔታ ምክንያቱ አላጠግብ ሲለኝ እኔም ውትወታዬን አላቋርጥ ስለው አምጦ አምጦ አንድ ጉድ ነገረኝ ፤ ባለትዳር መሆኑን ፣ ግን ለመፍታት በዝግጅት ላይ መሆኑን ፣ ሁኔታዎቹ ሲጠናቀቁ ሊነግረኝ እንደነበረ አስረዳኝ ።
በማመንና ባለማመን መሀል ሆኜ ወደ ኋላ ብዙ ነገሮችን ለማስተዋል ሞከርኩ ᎓ ማታ ማታ ስደውል በተደጋጋሚ ስልክ አያነሳም ፤ በማግስቱ በጠዋት ደውሎ ስራ ላይ እንደነበረ ብቻ ይነግረኝ ነበር ። ምንም አጉድሎብኝ ስለማያውቅ ተጠራጥሬ አላውቅም ።
ዝምታን አልመረጥኩምና ለምን ፣ እንዴት ፣ አልኩ ከባለቤቱ ጋር በትዳር 4 አመታቸው ነው ፤ልጅ አልወለዱም ልጅ አለመውለዳቸው ግን ላለመግባባታቸው ምክንያት እንዳልሆነ ነግሮኛል ከዚያ ይልቅ ብዙ ከባለቤቱ ጋር አላኖር ያላቸውን ምክንያቶችን ደረደረልኝ ። ለማመንም ላለማመንም የማጣራበት መንገድ የለኝም ።
በሰው ህይወት እገባለሁ ብዬ ሰጋሁና አመነታሁ ። እኔም ሴት ነኝ የባለቤቱ ፅዋ በኔ እንደማይደርስ ማረጋገጥ አልችልም ።ግፍ እንዳይሆንብኝ ፈራሁ ። እሱ ግን በጭራሽ በኔ ምክንያት እንዳልሆነና እኔ እንኳን ፈቃደኛ ባልሆን መፍታቱ እንደማይቀር ምሎ ተገዝቶ ነገረኝ።
ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ልጅ ነኝ በቶሎ እንዳገባ ከመጓጓታቸው የተነሳ ገና እንዳስተዋወኳቸው ወዳጅነታቸው ጠንቷል ። ሲሰሙ ምን እንደሚፈጠር አሁን ማወቅ አልችልም ።
እኔ ይቅርብኝ ብዬ ከሱ ጋር ያለኝን ግንኙነት ባቆም ፤ እሱም ትዳሩን ፈቶ ሌላ ቢያገባ እፀፀታለሁ ። እስከመቼ እንደሆነ ባላውቅም ብታገሰውና ባገባው የነገረኝ ሁሉ ምክንያቶች እውነት ባይሆንስ ብዬም እጠራጠራለሁ፡፡ ሁሉም ነገር ዝብርቅርቅ ብሎብኝ ለመወሰን ተቸገርኩ፡፡