እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?
===============
ከትዳር አጋሬ ጋር ከመጋባታችን አስቀድሞ አንድ ዓመት በፍቅር ቆይተናል፤ ከኔ ጋር የፍቅር ግንኙነት ከመመስረታችን በፊት ሌላ ትዳር ነበራት።
ከቀድሞ ትዳሯም አንድ ልጅ አፍርታለች፤ በወቅቱ ሁለታችንም ፍቅር ላይ ስለነበርን እና በምንኖርበት ሀገር ተጋብተን ለመኖር አመቺ ስላልነበር እኔ ያለኝን ንብረት ሸጬ ከምኖርበት ከተማ ቀይሬ ሄድኩ፡፡
ፍቅረኛዬም ነርስ ሆና ትሰራ ስለነበር ለፍቅር ብላ ስራዋን ጥላ ተከተለችኝ።
ያለሁበት መጥታ ተጋብተን አብረን መኖር ጀመርን፤ በወቅቱ ቶሎ ልጅ መውለድ ብንፈልግም አልቻልንም፤ ችግሩ ከኔ ይሆን ብዬ ስለሰጋሁ እና ባለቤቴም ከቀድሞ ትዳሯ ልጅ እንደነበራት ስለማውቅ የቅርብ የስራ ጓደኛዬን ሳማክር ምርመራ እንዳደርግ መከረችኝ፤ ስመረመር መውለድ አለመቻሌ ተነገረኝ።
በሁኔታው በጣም ተደናገጥኩ፤ ችግሩን እንዳወኩ ለባለቤቴ እንዴት እንደምነግራት ሳሰላስል ግዜያት አለፉ።
በመሀል ያልጠበኩትን ዱብዳ ከባለቤቴ ሰማሁ፤ ባለቤቴ አረገዝኩ አለችኝ፤ እንዴት ሊሆን ይችላል ብዬ ባስብም ባለቤቴ ካለን ፍቅር እና መተማመን የተነሳ በላዬ ላይ ትሄዳለች ብዬ ለማመን በፍፁም ተቸገርኩ።
በምርመራ መውልድ አለመቻሌን እያወኩ ባለቤቴ ከኔ ስለማርገዟ የነገረችኝን ጉዳይ እንዴት አምኜ ተቀብዬ ልቀጥል? በህክምና እኔ መውለድ አለመቻሌን ማወቄ እና ልጁ የማን ነው ብዬ እንዳልጠይቃት ትዳራችን ተናግቶ የምወዳት ፍቅሬን እና ብዙ መስዋትነት ከፍዬ የመሰረትኩት ትዳር ፈርሶ የማጣት ይመስለኛል፤ እናንተ በኔ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?
Share https://t.me/fkeradis
የሚቀርብ ታሪክ ካላችሁ ላኩልኝ 👉 @eyobreta