ግጥም ብቻ 📘


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha
@leul_mekonnen1

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🤫🤫ዝምታ🤐🤐

🚫🧠ካላዋቂ ወሬ

🚫💶ከሌለበት ፍሬ፣

🚫🕐ጊዜን ከሚገድለው፣

🚫📚እውቀት ከማይሰጠው፣

🤥🗣ከውሸት ጋጋታ፣

👍🤐 ይበልጣል ዝምታ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem


▪️▪️የውሸት ብርሀን🔸🔸

ዙሪያክ ገደል ቢሆን መሄጃው መንገዱ

ያመንካቸው ሰዎች አንተኑ ቢከዱ

ተንዶ ቢከስም የነበረክ ተስፋ

ያካበትከው ሀብትህ በሙሉ ቢጠፋ

አዝነህ እየተከፋ

ድቅድቁ ጨለማ ዙሪያህን ሲከበው

መውጫ ቀዳዳህን ጨንቆህ ስትፈልገው

ድንገት ምታያቸው

ብርሀኖች ሁሉ

እንዳያታልሉክ ተስፋ እየመሰሉ: :

ምክኒያቱም

ካላየኸው በቀር በጥሩ እይታ

የጅቦችም አይን ያበራል በማታ::


  📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem


💗❤️ወድሻለው💗❤️

- ወደኔ ተራምደሽ ቆመሽ ካጠገቤ

- ድንገት አይኔ አይቶሽ ሲደነግጥ ልቤ

- ሻል እንዳለኝ ወዲያው ከጎንሽ እንዳለው

- ለመናገር ሀቁን አይንሽን እያየው

- ውስጤን አሳወኩሽ ብዬ ወድሻለው።
         :
         :
🎈 ወንዶች ለምትወዷት ሴት ላኩላት

  📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@gete
m
@getem


💗❤️ወድሀለው💗❤️

- ወደኔ ተራምደህ ቆመህ ካጠገቤ

- ድንገት አይኔ አይቶህ ሲደነግጥ ልቤ

- ሀሳቤን ሰብስቤ ከጎንህ እንዳለው

- ለመናገር ሀቁን አይንህን እያየው

- ውስጤን አሳወኩህ ብዬ ወድሀለው።
         :
         :
🎈 ሴቶች ለምትወዱት ወንድ ላኩለት
  
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️
@BEGITIMENAWGA

@getem
@gete
m
@getem


..........ፍቅር እንደ Icarus.......

ካልጠፋ ከዋክብት ካልጠፋ
ጨረቃ ፀሐይን መዉደዴ
ፍቅርሽ አሸንፎኝ ተፈጥሮን
ስታገል ላውልሽ ከክንዴ
ስቀርብሽ ብቃጠል ስጠጋሽ ብነድድ
ፍቅር ሆነበትና ቢችልልኝ ሆዴ
ተቃጥዬም ቢሆን ከእቅፍሽ ልደር
አትከልክይኝ ዉዴ
ህልሜ አንቺን ማቀፍ ነው
ሞቼም ቢሆን ነይ ልሳምሽ አንዴ

                   ዘረ-ሠናይ
           @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@getem


🤰ውዷ እናቴ🤰

ሲከፋኝ ሚከፋሽ ስስቅ የምትስቂ

ስሳሳት ምትመክሪኝ አንቺ የኔ አዋቂ

የአምላክ ስጦታ ለአንዷ ህይወቴ

ምን ይውጠኝ ነበር ያላንቺ እናቴ
:
:
ጓደኛ ወዳጄ ከኔ ማትርቂ

ጉዳዬን ማዋይሽ ሚስጥሬን ጠባቂ

በማንም በምንም መተኪያ የሌለሽ

በደስታ ኑሪልኝ ሳለሽ በህይወትሽ

ሁሌም ወድሻለው እኔ ያንቺ ልጅሽ::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem


ሞት
.
ያ....ክፉ ነጣቂ፤
ከሥጋ ለይቶ እስትንፋስ ፈልቃቂ፤

ወሳጅ መልአከ ሞት በሰዎች ጀርባ ላይ፤
ተንጠልጥሎ ሚኖር በእድሜ ገደብ ጣይ፤

ቀናትና ወራት በቀመር ሲለኩ፤
ወራትና አመታት ፈጥነዉ ሲተካኩ፤

የሰዉ ልጅ ማለፊያዉ፤
የእስትንፋሱ ማብቂያው ፤

ከአይን ጥቅሻ እጅጉን ይቀርባል፤
ከአፈር እንደመጣ ከአፈር ይከተታል።
.....................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem


..       💗ድንቅ💗

በትርምስ መሀል ባለበት ጫጫታ

ትኩረቴን ሰብስቤ ስሄድ በዝግታ

የንፋስ ሽውታ

ያንቺን ስም አምጥቶ ከጆሮዬ ቢያደርስ
            ወዲያው ልቤ መታ
:
:

እንደበነራ ፋኖስ በድቅድቅ ጨለማ

ሀሴት ይሞላኛል ስምሽን ስሰማ

አሁን አሁንማ

ሳወድስ ሳሞካሽ ያንቺን መልክ ደም ግባት

ካምሮዬ አጣው ሚሆንሽን ቃላት
:
:
መልካሙ ልብሽን

ትሁት መሆንሽን

ምገልፅበት ነገር አስሼ ስፈልግ
         ከቃላቱ ደሴት

አንድ ድምፅ ሰማሁ ሳያቋርጥ እያለ
         ድንቅ ነሽ አንቺ ሴት::

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

           ✍️ @BegitimEnawga

@getem
@getem
@getem


የትናንቱ ትናንት

ትናንት ትዝታ አቃጠለኝ ናፍቆትሽ ገደለኝ ብዬ የፃፍኩልሽ

የትናንቱ ትናንት ፈፅሞ እንዳይመስልሽ

ትናንት አፈቀርኩሽ ሞትኩኝ አበድኩልሽ

ልሰበር ልቀንጠስ ገለመሌ ያልኩሽ

ይህ ያለፈው ትናንት ጭራሽ እንዳይመስልሽ

እወድሻለሁ ያልኩሽ አንዴ አይንሽን ልየው

ቶሎ ደርሰሽልኝ ከንፈርሽን ልሳመው

ናፍቆኝ የዋለውን ጠረንሽን ልማገው

ሙት ሚያስነሳውን ድምፅሽንም ልስማው

ብዬ ያልኩት ትናንት የትናንቱ ትናንት አይደለም ፈፅሞ

በፍቅር በናፍቆት በትናንቱ ትናንት ዉል አትይም ከርሞ

በድሮው ዛሬዬ ትናንት ብዬ ያልኩሽ

ትናንት የሆነ ዛሬ ስንት አለ መሰለሽ

                   ዘረ-ሠናይ
           @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@paappii


ከርግቦች ትራስ ስር
(አሌክስ አብርሃም)

የላባን መከዳ አምነህ አትመቻች
ቂም በቀል ነው ከታች!
የመስዋዕት አንገት አግኝቶ እስኪመዘዝ
አንዳች የሚወገር አንዳች የሚወገዝ
"ከርግቦች" ትራስ ስር የዛገ ሰይፍ አለ
በፍቅር እየማለ!
ማነህ ባለሳምንት ማነህ ባለዝክር
ተሰልፏል ከሳሽ ተሰብቋል ምስክር
ብቻ እጣ ይውጣብህ ልክም ሁን ስህተት
አንተን ሞረድ አርጎ የተረሳው ሁሉ ይነቃል ከዝገት!

@getem
@getem
@paappii


ናፍቀሽኛል

ጊዜ ይሮጣል አሉ

ጊዜ ይበራል አሉ

አንደዚ በማለት ሚያወራ ሰው ሁሉ

ምናለ ቢያስረዱኝ ይህንን ከቻሉ
:
:
ለኔ ጊዜው አይሮጥም

በፍፁም አይበርም

እንደው ይባስ ብሎ መቁጠሩንም ትቷል

ካንቺ ከራቅኩ ወዲህ ቀኑ አመት ሆኗል

እናም ርዝማኔው አሁንስ ከብዶኛል

የውነቴን ነው ምልሽ በጣም ናፍቀሽኛል
:
:
ሀልጊዜም ቢሆን አንቺን ነው ማስብሽ

ከራሴ በላይ ነው እኔ የምወድሽ

በደስታ ቆዪልኝ በአካል እስካገኝሽ::


፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

           ✍️ @BegitimEnawga

@getem
@getem
@getem


ቤት ማንም ሳይኖር ብቻዬን ሳለሁኝ
ስራ ጨራርሼ ፋታ እንዳገኘሁኝ
ትንሽ መለስ ብዬ ትናንቴን ለማየት
ያለፈው ዘመኔን ጥቂት ለመጎብኘት
የትዝታን መዝገብ ጀመርኩኝ መቃኘት።

እልፍ ደስታ ንፁህ ፍቅር 
ሀሜት የለ እዛው ንግር
የጨዋታው ለዛ ጥርስ የማያስከድን
ልጅነት ይመስገን ያ መልካም ዘመን።

ደሞ እሱ አልፎ ታድጎ ተጎርምሶ
በንፁ ልቤ ላይ አለማወቅ ነግሶ
መልካም ስሜ ሆኖ ከግብሬ ወርጄ
ይሉኝታን ገድዬ ንቀትን ወልጄ
ታዘብኩት እራሴን ወደኋላ ሂጄ።

By ሳምሪ የዝኑ ልጅ

@getem
@getem
@paappii


#ለፈገግታ 😂

😍አፍቃሪው😘

ሚበላ በገንዘብ መግዛቱ ሲከብደኝ
           ኑሮ ጣራ ነክቶ

ባፌ እንደዚህ አልኩ ልቤ አንድ ነገር
          ድንገት ተመኝቶ።

'' ምናለ እንደድል

ባገኝ እንደነሱ የኔ ማቶንን ሴት
       የማፍቀሩን እድል

እሷን ካላገባው እህል ባፌ አይዞርም
     ከቶ አልበለም እንድል
።''

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem


.....ስድስት እና ስድስት

ተገጣጠሙና ወርና አመታት
ስድስት የጥላቻ ስድስቱ የናፍቆት
ማልቀስ ሳይቀር ማንባት
መቁሰል ነበር መድማት
እነዛን አመታት
ዛሬ ተቀይሮ አመታት በወር ላይ
አልውልም ትላለህ አይኖችሽን ሳላይ
የልቤ ደረሰ አንተን ሰጠኝ ከላይ
ወደድከኝ አለሜ ህይወትን ሠጠኸኝ
እሠየው አበጀህ እንካን አፈቀርከኝ
ስድስቱን አመታት በስድስት ወር ካስከኝ

4/8/2016
By
@Hanipia

@getem
@Hanipiagetem
@getem


አንቺን እንዲያስረሳኝ እግዜርን ለመንኩኝ
ፍቅርሽ እንዲተወኝ ከአላህ ተማፀንኩኝ
እጣኑን ዘቢቡን ልሰዋ ከሰሙኝ
ለዓመት ደጁ ላልቀር ድባቡን ተሳልኩኝ

ግን እያደር ሳየው ናፍቆት ሆድ ሲያስብሰኝ
እግዜር እና አላህን መጠበቅ ሲሳነኝ
የ መርሳት ጉጉቴ ሆድ ሆዴን ቢያባባኝ
በአምላኮች መንገድ ተስፋዬን ቆረጥኩኝ
የእነሱን ቻይነት ሳልጠረጥር ባምንም
የእኔን ስለማውቀው ሚሆን አይመስለኝም

እና የአምላክ ነገር አልሳካ ቢለኝ
ተዋረስኩ ከአጋንንት ትዝታሽ ቢለቀኝ
አንቺን ከረሳሁኝ እንዳሻው እንዲያደርገኝ
ስጋዬን በቀብድ ለሰይጣን አስያዝኩኝ
ይቺ ብኩን ነፍሴን ሲዖል ወረወርኩኝ
ሠይጣን በዓለም እንጂ በፍቅር መች ይፈርዳል ይህም አልሆነልኝ

ስንቱን ልጥቀስልሽ አንዱ እንኳ አልቀረኝ
ሰንደሌን ለኩሼ ጠንቋይም አልተውኩኝ
እንዲያስረሳኝ ብዬ ስንቱን ዶሮ አረድኩኝ
እልፍ አዕላፍ ኡቃቤ ባንቺ ተማፀንኩኝ
ውቅያኖስ ናፍቆትሽን ከጠብታ አርቅቀው
ዓለም ትዝታሽን ከሀገር አሳንሰው
ያንቺን መውደድ ክብደት አቅለው ቢያሳዩኝ
እኔም እውነት መስሎኝ "አሜን" ልርሳት አልጉኝ

ወራት ቢቆጠሩ ቀናቶች ቢነጉዱ ፈገግ ስል ቢያዩኝ
"ከራማችን ፈርዷል ስለትህን አስገባ ረስተሃታል" አሉኝ
የናፍቆትሽን ፀባይ የፍቅርሽን አመል እኔ መች አጣሁኝ
ይኸው ትናንትና ድምፅሽን ብሰማ ዳግም ተነሣብኝ

                   ዘረ-ሠናይ
           @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@paappii


/ይቀጥላል ፍቅር/
ሳላገኝሽ በፊት ሳትሆኚ በቅርቤ
በገሃድም ሳይሆን ሳለሽ በአሳቤ፤
የዛኔ የሆንኩት አንቺን ላገኝ ብዬ
ሙሾ ያስወረደኝ ያስባለኝ እዬዬ፤
ያ ፍቅርሽ ብዙ ጉድ ያሳየኝ
ጊዜው ደርሶ ዛሬ ካንቺ ቢያቆራኘኝ፤
አጣጥሜ በቅጡ ሳልቀምሰው
ልኖር ካንቺ ቤቴን ሳልቀልሰው፤
በጅምሩ በፍቅራችን ንጋት
የመውደድን ፅዋ አብረን ሳንጋት፤
" ዛሬላይ"
እስክረሳው ያንቺ ወደኔ መምጣት
እስክል ድረስ ለምን አፈቀርኳት፤
አርጎኝ የነበረው ላንቺ እንድረታ
ሰከን ያላረገኝ እንዳላስብ ላፍታ፤
የከለለኝ እሱ እንዳላይ ጋርዶብኝ
ፍቅርሽ አይደለም ሆይ ያረገኝ ባንቺሞኝ፤
ግን የሚገርመው የኔ ፅኑ አቋም
ይቀጥላል ፍቅር እንዴት ባንቺ ሊቆም:
#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@getem


...ንገረኝ በሞቴ

ንገረኝ በሞቴ ምንህ ይሻለኛል
ዘንድሮን በጠና ሆድ ሆዴን በልቶኛል
ስለዚ ንገረኝ ምንህ ይሻለኛል
እህትህም መሆን ዛሬ አሰኝቶኛል
ፍቅረኛህ እንድሆን ደሞ ተሰምቶኛል
ብቻ እንዳታረገኝ ምስኪኖ እናትህን
በስስት ምታይህ የምትሞትልህን
አንተን ቀና ብለህ ያጎነበሰችን
ውስጣን እየከፋት የሳቀችልህን
ብቻ እንዳታረገኝ ምስኪኖ እናትህን

By
@Hanipia

@getem
@getem
@Hanipiagetem


🔥🔥እሳትና ውሀ🌊🌊

የታፈነ ውሀ በብረት ድስት ገብቶ

በጭቆና ሲኖር ነፃነቱን አጥቶ

     ስንት ስቃይ አይቶ
      ታጋሽ ሆኖ ሳለ

አንድ ጉልበተኛ እሳት የተባለ

ብረት ድስቱን ሊያግል እየተቀጣጠለ

ነበልባል ተላብሶ ድንገት ከተፍ አለ::
:
:
ቃጠሎ ንዳዱ ውሀው ሲበዛበት

የስቃዩ ማብቂያ ጊዜው ሲረዝምበት

ትግስቱ ተሟጦ የሚገነፍል ለት

        የእሳቱ ግለት
     ምን ያክል ቢከፋ

የታፈነው ውሀ በምሬት ሲደፋ

ሀያሉም ነበልባል አብሮት ነው ሚጠፋ::


▪️ ነገሮችን በትግዕስት ማለፍ ተገቢ ነው ግን ሁሉም ነገር ገደብ አለው። ይሄ ግጥም ገደብ እንዳለው ላልተረዱ ይድረስልኝ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem


አይ ገላ አባ ወረት

በምናብ ሸራ ላይ ፥ በሐሳቤ ሰሌዳ
በምኞቴ ጓዳ ፥ በፍትወቴ ሜዳ
ውብ ሰውነትሽን፥ አየሁ ተቀይዳ
በስጋ እሳት ላንቃ ፥ በቁም እስር ርዳ።

የአይኖችሽን ጨረር ፥ የከንፈርሽን ማር
የአንገትሽን መርዘም ፥ የእግሮችሽን ማማር
የዳሌሽን ደጀን ፥የሽንጥሽን ጅረት
በስጋዬ አሰስኩት ፥በገላ ዳበስኩት
አወይ ገላ ግፉ፥ አይ ስጋ አባ ወረት

የጉንጭሽ ላይ ስንቡክ ፥ የአንገትሽ ስር ከርቤ
ቀመስኩት ሁሉንም ፥ መች ቀረሁ ተርቤ
የቤትኾቨን ኖታ ፥ የሞዛርት ሙዚቃ
መች ይስተካከላል ፥ ከአንደበትሽ ሲቃ
አወይ ገላ ግፉ ፥ አይ ስጋ አባ ወረት
ይገኝ ይመስለዋል ፥ ለነብስ ህመም ደዌ
አንድ የስጋ መድኅን ፥ አንድ የስጋ ሽረት።

አይጥመኝ ሐር ልብ ፥ ለስላሳ የተባለ
ከሐር ጠጉርሽ በቀር ፥  ከአለንጋ ጣቶችሽ
አላውቅም በአለም ፥ ላይ የተስተካከለ።

ይፈሳል እንደ አዋሽ ፥ ሳቅሽ እንደ መልካው
እጅ እግር አጠረኝ ፥ ነብስሽን በየት ልንካው
ሁሉን ስዳስሰው ፥ ጠጉርሽን ስለብሰው
እንደ ጠበል ጠዲቅ ፥ ከንፈርሽን ስቀምሰው
ጣፋጭ እሳትሽን፥  እንደ ኩዳድ ሳርሰው
ገላን በገላ አቅም ፥ ስትጠግቢኝ ስጠግብሽ
ንገሪኝ አንችዬ ፣
ለዚህ ጥያቄዬ ፥ ምን መለሰ ልብሽ?

አወይ ገላ ግፉ፥ አይ ገላ አባ ወረት
ምኞት ሙሉ ሜዳ ፥ ምኞት ሙሉ በረት

በአፍ እንደወደድሽኝ ፥በአይን እንደዳበሽኝ
መአት ረግረግሽ ውስጥ ፥ያኔ እንዳሰጠምሽኝ
መዘንጋት የማያውቅ ፥ ፍቅሬ እሱን ለግሽኝ
ገል አፈሩ ይቅርብኝ ፥
ገል አፈሩ ይብቃኝ፣
ነብስሽና ነብሴ ሁለቱ ይጣመሩ፥
ፍቅር እንደዚያ እንዲቃኝ።

By ©እስራኤል
(@isrik)

@getem
@getem
@getem


ማስታወቂያ
..................
📲Iphone 15promax

💾Internal Storage:256GB
🔋battery:100%
👌Brand New

💲PRICE-149,999birr

📩 DM @paappii

📞 0922303747

Показано 20 последних публикаций.