TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
ፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ

20 Jul 2019, 10:15

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

"የልደቴ ቀን"

✍ደራሲ፦ ህብረቃል ሳሙኤል(ፓፒ)

ክፍል ሁለት

ዛሬ ልደቴ ነው ከዛሬ ጀምሮ ለእስካሁኑ ጥሩ ያልሆኑና መኖር ፈልጌ ስላልኖርኳቸው ሂወቶች አዲስ ጅማሬን መጀመር የምችልበት አዲስ ቀን ለዚች ቀን ስለደረስኩ እንኳን ደስ አለኝ።
በጠዋት ተነስቼ ስለራሴ አሰብኩ....እስከ ዛሬ 23 አመት ልደቴን አክብሬያለው ታዲያ በ23ቱም አስቤ የማላውቀውን ነገር ዛሬ በ24ኛው አሰብኩኝ። ህይወቴ እንዴት ነው? እራሴን ጠየኩት መልሱ ህይወቴ አላማ የሌለው አንድ የሚጨበጥ ነገር ላይ ለመድረስ የማይታሰብበት ከንቱ እሩጫ ነው።የነቃሁ መሰለኝ...! ከዚህ በኀላ ሱሰኝነት በቃኝ..የሆነ ነገር በውስጤ እንዲህ አለ። እኔም አመንኩ ከዚህ በኀላ በቃኝ እስከመቼ እንዲህ እኖራለው ዛሬ ልደቴ ነው 1 ብዬ ህይወቴን መጀመር አለብኝ! ወስኛለው....! ወደኀላ የሚመልሰኝ ምንም ነገር አይኖርም። ደስ አለኝ። ሶፋው ላይ የደስታ ፍልስስ ብዬ ተኛው። የሆነ ደስ ደስ የሚል ነገር እየተሰማኝ ነው።
እዛው ሶፋ ላይ እንቅልፍ ሸለብ አረገኝ።ከቀኑ 8 ሰአት ስልኬ ጮኸ የሱስ ጓደኞቼ ነበሩ አነሳሁት..... አንድ ላይ ተሰብስበው ይንጫጫሉ ....መልካም ልደት ለበረከት እያሉ ይዘምራሉ አሳቁኝ...እንድመጣ ነገሩኝ...ቆፍጠን ብዬ አልመጣም ከዚህ በኀላ ምነም ነገር እንደማልጠቀምና እነሱ ከፈለጉ ቤት እንዲመጡ ነገርኳቸው። 30 ደቂቃም አልፈጀባቸውም ቤት መጡ ለብዙ ሰአት ነዝንዘው ካልወጣን አሉኝ። ጭንቅላቴ ውስጥ አንድ ሀሳብ አቃጨለ "ሰውኮ ምንም ነገሩን ሲተው መሰናበትና ለመጨረሻ ጊዜ አብሮ ማሳለፍ አለበት ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ ሁሉንም ነገር አርጌ ልሰናበት በደንብ ልጠጣ ፣ በደንብ ልቃም፣ በደንብ ላጭስ ከነገ ጀምሮ ሁሉንም እተዋለው"።
ተያይዘን ወጣን ከሌላው ቀን በላይ ሁሉንም እየተጠቀምኩ ነው በነበርንበት ቤት እኔን ቢበዛ በ25 አመት የምትበልጠኝ ወጣት መሰል አሮጊት ከኛ ፊት ለፊት ባለ ሶፋ ብቻዋን ተቀምጣለች። ተነሳሁና ሄድኩ..... አጠገቧ ተቀመጥኩ...ፈገግ...አለች ጊዜ አልወሰድኩም ምንም ሳላወራ እጄን የለበሰችው አጭር ቀሚስ ባልሸፈነው ጭና ላይ አሳረፍኩት...... ፈገግታዋ አላቆመም ያኔ ባለትዳሮቹ በገንዘብ የሚገዟቸው ኮረዳዎች ላይ እንደሚሰዱት ሁሉ እኔም በአንዲት በእድሜ እጅግ በምትበልጠኝ ሴት ጭን ላይ እጄን አሳረፍኩ.....አጇን ይዣት አነሳኀት ምንም አላቅማማችም ተነሳችልኝ ወደ መፀዳጃ ቤቱ መሄጃ ጋ ባለው ኮሪደር ላይ አስደገፍኳትና እስማት ጀመር እሷም ትስመኛለች......ከዛ በኀላ የተፈጠረውን አላውቅም.....ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ እርቃኔን በዛች ሴትዮ ክንድ ውስጥ ሆኜ እራሴን አገኘውት። ቀስ ብዬ ተነስቼ ልብሴን ለብሼ ሹልክ ብዬ ወጣው።
ለራሴ ቃል እንደገባውት ከዛን ቀን ጀምሮ ከሱስ እራሴን አገለልኩ።ስራዬ ላይ ሆነ ትኩረቴ። ወደ ውጪ ሄጄ አንዳንድ እቃዎችን ለማስጫን ፕሮሰስ ጀመርኩ.....የጤና ምርመራ አምጣ.... ተባልኩ ያኔ ነው ታዲያ በልደቴ ቀን ህይወቴን ለማስተካከል እንዳረፈድኩ ያወኩት...........ደም ሰጠው..............በብዥታዬ ውስጥ የሚታወሰኝ ሀኪሟ እኔን ለማጠንከር ትነግረኝ የነበረው ምክር ብቻ ነው....ውጤት....ኤች አይቪ Postive........

ይቀጥላል......

@getinback
@hebreges
@getinback
@hebreges

1.1k 0 6
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot