(✍ GOSPEL TALK ✍)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


ክርስትና ማለት ክርስቶስ ነው ክርስትያን ነኝ ካሉ መኖር ነው ክርስቶስ ለኛ ሲል ከሞተ እኛ ለሱ ስንል መኖር ነው
አቤል ግዛው ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየቶች ካሏቹ በ @abel_gizaw አናግሩን

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5

መልካም በአል የተወደዳችሁ ❤
























የበረከት ተስፋዬ 'መምህሩ' full album


ማስታወቂያ | #GOSPEL TALK

_______
💐ተወዳጁ ቻናላች
ን በነዚህ ዘርፎች አብራችሁ ለመስራት የምትፈልጉን በሙሉ ይጋብዛል። በመረጣችሁት ዘርፍ መመዝገብ ጀምረናል።

💐በስነፅሁፍ  |በግል ወይም በቡድን

💐በዝማሬ | በግል ወይም በቡድን

💐በድምፅ | በአቅራቢ ወይም በትረካ

💐በፕሮግራም መሪነት | ድምፅ

💐በቃል |በድምፅ ወይም በፅሁፍ

💻በtechnology |graphics design, audition editing, video editing, camera man



የምትፈልጉትን በመምረጥ በ @abel_gizaw ስማችሁንና የመረጣችሁትን ዘርፍ ላኩልን።
መንግስቱን አብረን እናገልግል

Share guys🤗


እሺ እንዴት አመሻችሁ 😁

እስኪ ዛሬ ደሞ online ያለን እናውራ ወደ ተለያየ university በdegree ፕሮግራም እንዲሁም በremedeal ፕሮግራም የተቀላቀላችሁ

እንወያይ

-University ለእኔ ምኔ ነው?

-ስለገባቹበት ዩኒቨርሲቲ ያላችሁ እይታ?

-በቆይታዬ ዋና ትኩረቴ ምንድነው?

-የምማርበት ምክንያት ምንድነው?

-ከወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት ምን ትጠብቃላችሁ የኛስ ድርሻ ምንድነው?


...... ወዘተ ሃሳባችሁን ግለፁልን እስኪ

@abel_gizaw ወይም @gospeltalkdiscussion

Share it ❤❤❤


ሰላም ሰላም ውድ የ GOSPEL TALK ተከታታዮች እንደምን አላችሁ እኔ ጌታ ይመስገን ደህና ነኝ በተለያዩ የግል ምክንያቶች እንደጠፋን ይታወቃል እናም ይህንን ነገር ለማስተካከል ጥረት እያረግን ነው 🤗 ለዚህም እንዲያግዘን በድሬዳዋ ከተማ የምትኖሩና universityዋ ውስጥ የምትማሩ ከኛ ጋር ማገልገል የምትፈልጉ ወንድምና እህቶች እንጋዛቹሃለን ተያይዘን ለመንግስቱ ለመስራት ያበቃን ዘንድ 😁

ለሌሎቻችሁ ደሞ በሌላ ከተማ ለምትገኙም ሰዎችን እየመደብን ስለሆነ በቅርቡም በሆሣና በአዲስ አበባ ባህርዳር ላይ ይኖሩናል ለአሁኑ ግን በድሬ ላይ ያላችሁ ማገልገል ምትፈልጉ እንዲሁም በድሬ ጉአደኞች ያላችሁ ጠቁሟቸው

ስልክ ቁጥር -0988055119 abel creator
-0919688864 buze admin

Tg account @abel_gizaw


Репост из: ናዝራዊ Tube
ስለ ዮሃንስ ወንጌል እግዚአብሔር ይመስገን

የዮሃንስ ወንጌል ልክ እንደ ሌሎቹ ሦስት ወንጌሎች ኢየሱስን በአመዛኙ ከታሪክ ጋር አጋብቶ ብቻ ሳይሆን የሚነግረን “አሁን” በአማኝ ወይም በቤተክርስትያን ሕይወት ውስጥ ያለውን ፋይዳ በጥልቀት በማውሳትም ነው፡ በሌላ አባባል ታሪካዊ / historical ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን የሚያስተዋውቀን አሁናዊ / existential ክርስቶስንም ነው።

ዮሃንስ በወንጌሉ ከሚገልጻቸው አሁናዊ እውነቶች መካከል አንደኛው አንድነት / unity ነው፡ ይህንን የአንድነት ክቡር እውነት በዋነኛነት በምእራፍ 17 ላይ አጽንኦት በመስጠት ያቀርብልናል።

ክፍሉ የሚጀምረው፦

“ኢየሱስም . . . ወደ ሰማይ አይኖቹን አነሳና እንዲህ አለ”
ብሎ ነው።

ይሄም የሚያሳየን እውነት በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታችን የሚናገረው ነገር በሙሉ በአብ ፊት እንደ ጸሎት የቀረበ ምልጃ መሆኑን ነው። በዚህ የምልጃ ምእራፍ ውስጥ ነው እንግዲህ ጌታችን በሚገርምና እጅግ ደስ በሚል መልኩ በአብ፣ በወልድና፣ በአማኞች መካከል ያለውን አንድነት ጸሎታዊ በሆነ ቅርጽ ለአባቱ የሚያቀርበው።

#አንድ
የአማኞች የእርስ በርስ አንድነት

ክርስቶስ በዚህ ምእራፍ ቁጥር አሥራ አንድ ላይ እንዲህ ብሎ ይጸልያል፦

“ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው”

መቼም ይህን ቁጥር በጥድፊያ ካላነበብነው በስተቀር ወሳኝ የሆነውን አሳብ የምናልፈው አይመስለኝም፡ ክርስቶስ በዋነኛነት አማኞች እርስ በርስ በአንድ የሰመረ ሕብረት እንዲሆኑ ወይም ብዙዎች ቢሆኑም ነገር ግን አንድ እንዲሆኑ አባቱን ይለምንላቸዋል፡ ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ አማኞች አንድ እንዲሆኑ ለማነጻጸሪያ የተጠቀመበት እውነት ነው፡ እንዲህ ይላል፦

“እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ”

የአንድነቱ ንጽረት አባትና ልጅ ናቸው፡ ታዲያ ይሄ አይገርምም!
በዚሁ ወንጌል ውስጥ ጌታችን “እኔና አብ አንድ ነን - We are in one accord” ብሎ እንደተናገረ እናነባለን፣ ይሄንኑ አንድነት ወይም የአሳብና የልብ ስምረት አማኞች እርስ በርሳቸው እንዲለማመዱት ይጸልይላቸዋል፡ እውነት ግን እስኪ አስቡት፣ አብና ወልድ አንድ እንደሆኑት እኛ አንድ እንድንሆን እኮ ነው የሚጸልየው፡ በምድር ላይ የአማኞችን አንድነት ለማነጻጸር የሚመጥን አንድ እውነት ያለው በአብና በኢየሱስ መካከል ያለው አንድነት ብቻ ነው፡ ይሄ አንድነት ደግሞ እኛ #የምንጀምረው ሳይሆን #የምንገባበት ነው፣ ምክንያቱም አስቀድሞ በአባትና በኢየሱስ መካከል የተመሰረተ ነው። አንድነታችን የዘር፣ የቋንቋ፣ የአጥቢያ ቤተክርስትያን፣ የጓደኝነት፣ ወይም የቲፎዞ ሳይሆን የእግዚአብሔርና የኢየሱስ ነው፡ ከዚህ ያነሰ አንድነት በሰው፣ ከሰውና፣ ለሰው የሆነ ነው።

#ሁለት
የአብ፣ የወልድና፣ የአማኞች አንድነት


አማኞች እርስ በርስ ሊኖራቸው ከሚገባቸው አንድነት ወይም ሕብረት በዘለለ መልኩ ጌታችን፣ እርሱ፣ አብና፣ አማኞች ደግሞ በአንድ አንድ እንዲሆኑ ሲጸልይ እናነባለን ቁጥር 21 - 22

“አባት ሆይ በእኔ እንዳለህ፣ እኔም በአንተ፣ እነርሱም ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ . . . እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ . . . “

ደቀመዛሙርት በአብና በወልድ መካከል ባለ አንድነት እርስ በርሳቸው አንድ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን የተጸለየላቸው፣ እነርሱ ራሳቸው ከአብና ከወልድ ጋር በአንድ እንዲሰመሩም ጭምር ነው፡ አብ በወልድ ውስጥ፣ ወልድ ደግሞ በአብ ውስጥ፣ አማኞች ደግሞ በአብም በወልድም ውስጥ ሆነው በአንድ እንዲሆኑ፡ እውነት ከዚህ የሚበልጥ ጸሎት አለ? እውነት ከዚህ የሚበልጥ ክብር ወይም ሕይወት አለ? ከአብና ከወልድ ጋር አንድ መሆን!!

#ማሳረጊያ

የእርስ በርስ አንድነታችን ወይም ሕብረታችን በአብና በወልድ መካከል ባለው ሕብረት መቃኘቱ ሲገባን፣ እንዲሁም አንድነታችን የእርስ በእርስ ብቻ ሳይሆን ከአብና ከወልድም ጋር በአንድ መሆኑ ሲገባን፣ ለዚህ ክቡር እውነት ስንል የማንጥለው ነገር አይኖርም፡ ለዚህ ሕብረት ብለን የምንጥለው ነገር ሕብረቱ የገባንን ያህል ነው።

በዚህ አንድነት ውስጥ ያልተሰመረ ሁሉ፣ ፓስተር ይሁን ሐዋርያ፣ ወንጌላዊ ይሁን ነብይ፣ የሥነ-መለኮት ምሁር ይሁን ዓቃቤ-እምነት፣ ፈጽሞ የመለኮትን ሕይወት አይቋደስም - የመለኮት ሕይወት ከአብና ከወልድ ጋር እንዲሁም እርስ በርስ አንድ በመሆን ብቻ የሚገለጥ ነው።

ምን አይነት ክብር ነው!
ከአብም ከወልድም ጋር በአንድ መሰመር!


“ኅብረታችንም ከአባት ጋር ክልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው”

✍🏾Yilu danu
@nazrawi_tube
@nazrawi_tube


Relation ship #1 share ከተቀማችሁ 🥰🥰🥰
አቤል ነኝ ❤
Any comment or question @abelo_fisher

@gospel_talk
@gospel_talk


የተሠጠክ ምን ያክል #ትልቅ እንደሆነ ብታውቅ የጠየከው #ቀሊል እንደሆነ ይገባካል 💯

✅በነፃ የተሠጠህ #ክርስቶስ_ታላቅ ነው 💯

አንዳች ነገር አስፈልጎክ ወደ #ፀጋው_ዙፋን_ፊት ቀርበህ ስትጠይቅ፣ #በእምነት አድርገው እንጂ ላንተ ሠማይ የደመደልክ የጠየከው ያንተ እንዲሆን ያረጋገጠልክ #የኪዳን_ቋንቋ #እንዲያው✅ የሚል ነው ‼️

"ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ #ሁሉን ነገር #እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?"
ሮሜ 8:32
         
‼️ስለዚህ የሠማይ አባትክን #አምነክ ቅረበው፣በነፃ የሠጠክ #ልጁ ታላቅ #ከልኬትም_በላይ  በመሆኑ ሌላውን #ልጄ_ሆይ በነፃ ውሠድ ይልካል ✅

‼️ጌታን ከምጠይቀው ይልቅ እርሡ አስቦልኝ በነፃ የሠጠኝ ታላቅ ነውና ሌላውን ነገር #እንዲያው ይሠጠኛል የሚል ብቻ #አሜን ሲል መልክቱን ይቀበላል ✅

Share ✅share
Join ✅join

@gospel_talk


-sexual purity with tseba ministry👌
ለድምፁ ጥራት sorry😔
እንደምትማሩበት ተስፋ አለኝ 🥰

Показано 20 последних публикаций.

1 451

подписчиков
Статистика канала