በገነቷም ምድር
""""""""""""""""""''
ስንቱ አፍሪቃዊ
ሆኖ ያንቺ ተገዥ ሆኖ ያንቺ አፍቃሪ
ነፍስ እየማገደ
ሄደ ተራመደ
ሃሳቡን ገመደ
ያሰበበት ሳይደርስ በጥይት ነደደ
ስንቱ አፍሪቃዊ
ሆኖ ያንቺ ወዳጅ ሆኖ ያንቺ አፍቃሪ
በረሀ አስቀረው
ባህር ዓሳ በላው
ሀሳብ ቢያሻግረው
ያ ቀቢፀ ተስፋ ዓይኑን ቢያሳውረው
ስንቱ አፍሪቃዊ
ሆኖ ያንቺ ባርያ ሆኖ ያንቺ አፍቃሪ
ስላንቺ እሚያስበው
የሚያሰላስለው
ምድራዊ ገነትን
ይደነቀች ምድርን
ወርቅ መረገጫ ገንዘብ መንተራሻ
ሁሉም እሱን ሲሻ
ሀገሩን ሲረግም ሌላን ማወደሻ
ሌላውን ሲያወድስ ሀገር ማንቋሸሻ
ስንቱ አፍሪቃዊ
ሆነሽበት ናፍቆት ሆኖ ያንቺ አፍቃሪ
ፈጣሪን ሲለምን
በቃል ሲያወድሰው
ባህሩን ልሻገር ሰው አርገኝ እንደሰው
ነፍሴን ማግዳለሁ
ግድየለም ግድየለም ከዛው እደርሳለሁ
አንተ ሁነኝ ስንቄ
ልታይ በሀገሬ ከሰው ሁሉ ልቄ
እያለ እያለ ፈጣሪን ለመነ
አምላክን ጠየቀ ሁሌ እየተጫነ
አምላክም አየና
የሰዎች ባህሪ እያደር ቢገርመው
ቸነፈር አምጥቶ
የጉጉቷን ምድር እንደወርቅ ፈተነው
አሳየ ፈጣሪ
የሌለው እንዳለው ያለው እንደሌለው!
አሁን ሰው ጉድ ይላል ባነገሳት ምድር
መከራ ሲያንኳኳ በሽታ ሲያስቸግር...
ፈላጭ ቆራጭ ሀገር
ለደዌ በሽታ ህዝቦቹዋን ስትገብር
ወድቃ ስታጣጥር
ጉድ ትበል አፍሪቃ
ይህን ጊዜ ትንቃ!
በደውሉ ጩኸት በቃጭሉ ዋይታ ሀገር ስትደቃ።
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@habeshatube3 @jona7
""""""""""""""""""''
ስንቱ አፍሪቃዊ
ሆኖ ያንቺ ተገዥ ሆኖ ያንቺ አፍቃሪ
ነፍስ እየማገደ
ሄደ ተራመደ
ሃሳቡን ገመደ
ያሰበበት ሳይደርስ በጥይት ነደደ
ስንቱ አፍሪቃዊ
ሆኖ ያንቺ ወዳጅ ሆኖ ያንቺ አፍቃሪ
በረሀ አስቀረው
ባህር ዓሳ በላው
ሀሳብ ቢያሻግረው
ያ ቀቢፀ ተስፋ ዓይኑን ቢያሳውረው
ስንቱ አፍሪቃዊ
ሆኖ ያንቺ ባርያ ሆኖ ያንቺ አፍቃሪ
ስላንቺ እሚያስበው
የሚያሰላስለው
ምድራዊ ገነትን
ይደነቀች ምድርን
ወርቅ መረገጫ ገንዘብ መንተራሻ
ሁሉም እሱን ሲሻ
ሀገሩን ሲረግም ሌላን ማወደሻ
ሌላውን ሲያወድስ ሀገር ማንቋሸሻ
ስንቱ አፍሪቃዊ
ሆነሽበት ናፍቆት ሆኖ ያንቺ አፍቃሪ
ፈጣሪን ሲለምን
በቃል ሲያወድሰው
ባህሩን ልሻገር ሰው አርገኝ እንደሰው
ነፍሴን ማግዳለሁ
ግድየለም ግድየለም ከዛው እደርሳለሁ
አንተ ሁነኝ ስንቄ
ልታይ በሀገሬ ከሰው ሁሉ ልቄ
እያለ እያለ ፈጣሪን ለመነ
አምላክን ጠየቀ ሁሌ እየተጫነ
አምላክም አየና
የሰዎች ባህሪ እያደር ቢገርመው
ቸነፈር አምጥቶ
የጉጉቷን ምድር እንደወርቅ ፈተነው
አሳየ ፈጣሪ
የሌለው እንዳለው ያለው እንደሌለው!
አሁን ሰው ጉድ ይላል ባነገሳት ምድር
መከራ ሲያንኳኳ በሽታ ሲያስቸግር...
ፈላጭ ቆራጭ ሀገር
ለደዌ በሽታ ህዝቦቹዋን ስትገብር
ወድቃ ስታጣጥር
ጉድ ትበል አፍሪቃ
ይህን ጊዜ ትንቃ!
በደውሉ ጩኸት በቃጭሉ ዋይታ ሀገር ስትደቃ።
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@habeshatube3 @jona7