አዲስ ምልከታ🌍


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


+ አዲስ የሳይንስ እይታ
+ አዲስ አስተሳሰብ
+ አዲስ እውቀት
+ ሃይማኖት
+ ፖለቲካ
+ ኢኮኖሚ
+ ሙዚቃ
# የኢትዮጵያ ትንሳኤ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: አዲስ ምልከታ🌍
The fact that the globe-universe-heliocentric model is based on unproven claims and explanations, meant that over time there was more and more evidence against it, and the so called scientists continued more and more "plausible" contrived explanations for them. This meant that they created lies upon lies, and that led to a point in the history of science, where only few, bright-minded people could understand it. When in reality, it should have been the opposite, anyone should be able to understand, and challenge these theories. But now they have gotten so complicated and non-common-sensical that it is simply impossible for the average person to engage with them.

Here is one example
- simple lies like newton's gravity, led to the problem of "singularity"
- this meant that the universe should come collapsing together
- but also the observations indicated that it was not the case
- so they created new concepts like dark matter and dark energy, this invisible, un-detectable mysterious thing that keeps the world from collapsing together. But there is no way to prove that it even exists

Another example
- there was a claim that earth moves through space
- but Michelson-morley experiment proved that that is wrong
- So they created new theories "length contraction", "time dilation" etc to explain away why Michelson-Morley experiment was wrong
- Not only is this non-sensical, there was no evidence for it and it was even disproven by the Sagnac Experiment
- On the other hand, Albert Einstein and others claimed that the aether, a form of matter believed to exist above earth, did not exist at all
- This created a big problem. If light is a wave, and it travels through space, then what is the medium
- And here, they created one more false theory: the "wave-particle duality". Now light is both a wave and a stream of particle, so it can move through empty space
- But now which one is it really? Wave or particle? Well it's both, kind of
- well then if it's a wave, how is it's speed constant?

There is just no answer to this. Just more and more nonsense answers that we have to just accept, because brilliant minded scientists told us.

But this is exactly what they were criticizing in religion -- that we were following the words of religious leaders, and trusting their word.

So how is this not hypocrisy?


We reject the premise. And thus the conclusion as well.

The premise is that earth is a spinning ball, flying in empty space, in a random corner of the universe, created by billion years of random events.

The conclusion is that there is no God that intentionally created and designed the world.

We reject the wrong premise, and we prove that it is wrong as well. Therefore we also reject its conclusion and show that it is wrong.

People who accept the premise are pushed/forced to slowly accept the conclusion. And that creates atheists/agnostics/deists over time. Therefore we see an epidemic of Godlessness in our world.

Why do we reject the premise? because we have proofs and evidence against it:
https://t.me/hasabochhh/6683
https://t.me/hasabochhh/6374
https://t.me/hasabochhh/6349
https://t.me/hasabochhh/6350
https://t.me/hasabochhh/6352


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የሜዲቺ ቤተሰብ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


አበው ስለ እመቤታችን ዕረፍት እንዲህ አሉ

‹ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

‹‹ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት የተለያየ ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ›› ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Homily on the Dormition)


በተረፈ ግን፣ እንኳን ለአስተርእዮ ማርያም በዐል በሰላም አደረሳችሁ!!!


ስለዚህ ጉዳይ እንዲብራራ በጠየቃችሁት መሰረት ነገሩን ይበልጥ ለማብራራት እና ረዘም ባለ ጽሁፍም ለማቅረብ ስሞክር ነበር፣ እና የደረስኩበት ነገር ቢኖር ጉዳዩ የተወሳሰበ መሆኑን ነው። በዚህ ቻናልም በኩል ርዕሱን በማስረዳት በኩል ስህተት ተፈጥሯል ስለዚህም ይቅርታ ለመጠየቅ እወዳለሁ።

እንዲሁም ከላይ ሼር የተደረገው ቪድዮ ላይ ያለው ጥንተ አብሶ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ አይደለም የሚለው ሙሉ በሙሉ ትክክል አይደለም። ጥንተ አብሶ ማለት በአጭሩ የቀደመው በደል፣ አዳም እና ሄዋን የሰሩት ሃጢአት ነው። ነገር ግን በነሱ ሃጢአት ምክንያት እኛ ልጆቻቸው የሃጢአቱን ፍዳ ወረስን ወይስ ሃጢአቱንም ጭምር ወረስን የሚለው ጋ ነው ልዩነቱ። በዚህም ካቶሊኮች ሃጢአቱንም ጭምር በውርስ እንደተቀበልን ያስተምራሉ። ይህን አስተምህሮአቸውን ዋና አነሳሽ የሆነው ደግሞ አውግስጢኖስ ነው። ነገር ግን ከአውግስጢኖስ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ወይም ከርሱ በፊት የነበሩት እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ ቄርሎስ እና ቅዱስ ጎርጎርዮስን ስንመለከት የቀደመው የአዳም ሃጢአት እኛን የወደቀ የተዋረደ ባህሪ እንድንላበስ አደረገን ይላሉ እንጂ የአዳም ሃጢአት እኛም እንዳለብን ወይም እኛ እንደሰራነው ይቆጠራል፣ ወይም እኛም እንጠየቅበታለን አይሉም።

የኛ ቤተክርስቲያን እና የኢርትራ ቤትክርስቲያን አባቶች ስለ ጉዳዩ ምን ይላሉ የሚለውን የተለያዩ ጽሁፎች እንዳየሁት የሚሉት በአዳም እና ሄዋን ሃጢአት ምክንያት እኛ የሃጢአታቸው መዘዝ የሆነው ሞት፣ እና ለሃጢአት የሚያደላው የወደቀው ባህሪ ወረስን የሚለውን አቋም ነው የሚይዙት። ስለዚህ ያ ነው ከካቶሊኮች የሚለየን። ጉዳዩን ይበልጥ ከመዘዝነው ሌላም ብዙ ነገር አብሮት ይነሳል። ለምሳሌ immaculate conception የሚባለው ድንግል ማርያም ያለዚህ የውርስ ሃጢአት ነው የተወለደችው የሚለውን ያነሳሉ።

ነገር ግን ይህ አስተምህሮ በኛ ቤትክርስቲያን ስነ መለኮታዊ አስተምህሮ ውስጥ የሚገኝ አይሆንም። ምክንያቱም መጀመርያም እኛ የአዳምን ሃጢአት ወርሰናል ብለን አናምንም። ይልቁንም ስለ ድንግል ማርያም መወለድ የምናምነው ነገር ቢኖር እኛ ያለንን የጎሰቆለ ባህርይ ይዛ አልተወለደችም፣ እንዲሁም በህግ እና በስርአት፣ ያለ ዝሙት ወይም ስጋ ፈቃድ ተወለደች እንጂ።


ኦሪጂናል ሲን ወይም ጥንተ አብሶ የሚባለው የካቶሊኮች አስተምህሮ ሲሆን የሰው ልጆች በሙሉ የአዳምን እና የሄዋንን ሃጢአት ወርሰናል የሚል ነው። በዚህም ምክንያት ሁላችንም የውርስ ሃጢአት አለብን ይላል። ነገር ግን ይህ አስተምህሮ የካቶሊኮች አስተምህሮ እና የኛ ቤትክርስቲያንም ሆነ የምስራቅ ኦርቶዶክሶች የማያምኑበት የተሳሳተ አስተምህሮ ነው። ይህንን አስተምህሮ ከጀመሩት ውስጥ ደግሞ አውግስጢኖስ አንዱ ነው።

የኛ ቤትክርስቲያን የምታስተምረው አዳም እና ሄዋን በበደሉ ጊዜ ሰውነታቸው መዋቲ፣ ለሃጢአት የተጋለጠ ወይም ሃጢአት ለመስራት ቅርብ የሆነ የተጋለጠ ባህሪን ያዝን የሚለው ነው። ታዲያ ጌታችን ሲወለድ ይህንን የወደቀ ለሃጢአት የተጋለጠ ባህሪ አልያዘም፣ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያምም ለዚህ ለሃጢአት የተጋለጠ ባህሪ አልነበራትም ብለን ነው የምናምነው። ለዚህም ነው እመቤታችን ሃሳቧ ሁሉ ስለ እግዚአብሔር የሆነ፣ በስጋም በህሊና(ሃሳብም) ድንግል የሆነች ብለን የምንገልጻት።

ነገር ግን ሰዎች ይህንን አስተምህሮ ያዩና ከጥንተ አብሶ ጋር ያምታቱታል። ነገር ግን ያ ስህተት ነው። ጥንተ አብሶ የሚባለው መጽሃፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምህሮ ነው።


ምንድነው original sin?


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
Original Sin ከግኖስቲኮች የመጣ አስተምህሮ ይሆን? አውግስጢኖስ በርግጥም ክርስትናን ሳይቀበል በፊት ግኖስቲክ ነበር። ያ ስለ ጥንተ አብሶ ያመጣውን እምነት ምክንያቱ ነበር ልንል እንችላለን?


To explain this shortly, a three body, or N body system where n > 2, creates a system of equations where there are more unknown variables than the number of equations. And this creates a problem that cannot be solved "analytically". The equations create a system of differential equations, and they become unsolvable. And the mathematicians say they can solve it through numerical methods, but those are just "approximations" of the system and not the real solutions, and as one of the scientists have described it, it is a "blind" solution and people only resort to numerical if they couldn't find the proper analytical solutions.


Репост из: አዲስ ምልከታ🌍
Three Body Problem
The Three Body Problem is a four hundred year old problem of mathematics which has its roots in the unsuccessful attempts to simulate a heliocentric Sun-Earth-Moon system.
Due to the nature of gravity, a three body system inherently prefers to be a two body orbit and will attempt to kick out the smallest body from the system—often causing the system to be destroyed altogether.[1] There are a limited range of scenarios in which three body orbits may exist.[2] It is seen that those configurations require at least two of the three bodies to be of the same mass, can only exist with specific magnitudes in specific, sensitive, and highly symmetrical configurations, and exhibit odd loopy orbits that look quite different than the systems of astronomy proposed by Copernicus. The slightest imperfection, such as with bodies of different masses, non-symmetrical spacing, or the effect of a gravitational influence external to the system, causes a chain reaction of random chaos which compels the entire system to fall apart.[3]
A typical response to this is to claim that there are numerical solutions. However, these are approximations which do not fully simulate the situation. See the page Numerical Solutions. We are taught that it should be possible for a star to have a planet which has a moon, yet the greatest mathematicians of human history have been unable to get it to work.
  “ Describing the motion of any planetary system (including purely imaginary ones that exist only on paper) is the subject of a branch of mathematics called celestial mechanics. Its problems are extremely difficult and have eluded the greatest mathematicians in history. ”


ኀዲጎ ተስዓ ወተሳዕተ ነገደ
ቆመ ማዕከለ ባሕር


ዘጠና ዘጠኙን የመላእክት ነገድ ትቶ አንዱን አዳም ሊፈልግ ወደ ምድር መጣ። በዮርዳኖስ ባሕር መካከልም ቆመ። በፍጡሩ እጅ ተጠምቆም ጥምቀት እንደሚገባ አስተማረን።  በዮርዳኖስ የተሠወረውን የአዳምን የእዳ ደብዳቤም ደመሰሰ።

በዚያም አብ ድምፁን ከሰማይ አሰማ። መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወረደ። እግዚአብሔርም የመለኮቱን ምስጢር ገለጠልን። ከብሉይክ ዘመን ጀምሮ ከሰዎች ተሰውሮ የነበረው የእግዚአብሔር ባሕርይ፣ የአንድነቱና ሶስትነቱ ምስጢር፤ አባቶቻችን ለዘመናት ሽተው ያላዩት የመለኮት ምስጢር በዚች ቀን ተገለጠ። እግዚአብሔር አብ ከሰማይ በድምጹ፣ እግዚአብሔር ወልድ በዮርዳኖስ መካከል በሥጋ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ተገልጠው አንድነታቸውን ሶስትነታቸውን አሳዩን። ስለዚህም አባቶቻችን የዚህችን ቀን ስም "አስተርእዮ" ወይም የመገለጥ በዓል አሏት።

እንኳን አደረሳችሁ!!


🟢🟡🔴
ጥር 7 | #በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፥ በአካል፥ በግብር ሦስትነት፣ በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው። በዚህ ጊዜ ተገኙ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም። መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና።

ሩኅሩኀን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን። የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም። የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል።

በዚህች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው።

፩. ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው
፪. ቅዳሴ ቤታቸው ነው።

#ሕንጻ_ሰናዖር
በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ በነበረ ግዛት ከናምሩድ ክፋት በኋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ። ሰማይ ጠቀስ ሕንፃን ሠሩ። በክፋትም ሥላሴን ሊወጉ ተነሡ።

ርኅሩኀን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም። የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና። ይልቁኑ "ኑ እንውረድ ቋንቋቸውን እንደባልቀው" አሉ እንጂ።

ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቋንቋዎች ተፈጠሩ። እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ። ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት። ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል።

#ቅዳሴ_ቤት
አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮጵያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጎንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታ ተጠናቃለች።

በተሠራች በ16 ዓመቷ፣ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በኋላ ግን ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል። ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በዓፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው።

#ቅዱስ_ሶል_ጴጥሮስ ዕረፍቱ ነው፨

የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት፣ ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ፣ የኒቂያ ጉባኤ ሊቀመንበር ከነበሩና አርዮስን ካወገዙ አንዱ የሆነ፣ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ያጠመቀ ሊቅ ነው።


🟢🟡🔴
ጥር 6 | በዚህች ቀን፦

#የጌታችን_መድኃኔዓለም የግዝረቱ በዓል ነው፨

ይኸውም ከጌታችን 9ኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ሲሆን መድኃኔዓለም ሕግን ፈጻሚ ነውና በተወለደ በ8 ቀኑ እንደ ሥርዓቱ ግዝረት የፈጸመበት ነው።



#አባታችን_ጻድቁ_ኖኅ ዕረፍቱ ነው።

ጻድቁ ኖኅ በትዳር ሲኖር 3 ጊዜ ብቻ ዘርን ለመተካት ከእናታችን ሐይከል ጋር የተገናኘ፣ 500 ዓመት በድንግልና የኖረ ሲሆን፣ ዝናብና መርከብ ምን እንደሆነ በማይታወቅበት ጊዜ ከቁጣ ዝናብ ለመዳን በእምነት መርከብ የሠራ በምድር ላይ ብቻውን በጊዜው ጻድቅ ሆኖ የተገኘ አባት ነው።


🍀 ዕርገተ #ቅዱስ_ኤልያስ_ነቢይ ነው።

በቤ/ክናችን ከቅዱስ ሙሴ ቀጥሎ ትልቁ ነቢይ ቅዱስ ኤልያስ ነው።

በተለይ ደብረ ቀርሜሎስ ለእርሱ ቤቱ ነበር። በዚህ ሕይወቱም ከመልከ ጼዴቅ ቀጥሎ፦

፩. ለድንግልና (ድንግል ነበርና)
፪. ለብሕትውና (ብቸኛ ነበርና)
፫. ለምንኩስና (ተሐራሚ ነበርና) በብሉይ ኪዳን መሠረትን የጣለ ነቢይ ይባላል።

በብሉይ ኪዳን የቅዱስ ኤልያስን፣ በዘመነ ክርስቶስ የመጥምቁ ዮሐንስን፣ በዘመነ ሊቃውንት ደግሞ የአፈ ወርቅ ዮሐንስን ያህል ደፋርና መገሥጽ አስተማሪ አልነበረም።


#ቅድስት_አርሴማ ልደቷ ነው።

የቅድስት አርሴማ አባቷ ቴዎድሮስ ከሌዋውያንና ከኃያላን ነገሥታት ወገን ሲሆን እናቷ አትኖስያ ደግሞ ከጳጳሳት አለቆች ወገን ናት፡፡ ወላጆቿ በሃይማኖት በምግባር ያጌጡ በበጎ ትሩፋት የተመሰገኑ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡

በእርጅናቸው ዘመን ልጅ ስላልነበራቸው በስእለት ያገኟት ቅድስት ልጃቸው ነች።


#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሣርያ ዕረፍቱ ነው፨

🍀 ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ ነው። ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊንም ያስተማረው እርሱ ነው።

🍀 ቅዱስ ባስልዮስ ገዳማዊ ጻድቅ፣ ባለ ብዙ ምሥጢር ሊቅ፣ የብዙ ምዕመናን አባት፣ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት፣ ባለ ብዙ ተአምራትና ከመጨረሻው የቅድስና ማዕረግ ከዊነ እሳት (ከፍጹምነት) የደረሰ አባት ነው።

🍀 ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳያንን ሆስፒታል በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ያስገነባ እርሱ ነው።

በተቀደሱት ወላጆቻቸው ከ5 ጳጳሳት ወንድሞች እና ከ1 ቅድስት ገዳማዊት እኅት መካከል የተገኘ ቅዱስ ሊቅ ነው።


#አቡነ_ኢዮስያስ ልደታቸው ነው፨

እኚህ ቅዱስ ኢትዮጵያዊ የንጉሥ ዓምደ ጽዮን ልጅ ናቸው። መንግሥትን ትተው በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ መንኩሰው፣ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቆብ ደፉ።

ልክ እንደ ጥንቱ በጸለዩበት ወንዝ ነሐሴ 6 ዓሣ ከሰማይ ይዘንብበታል።

✨ ቃልኪዳናቸው፦
ወደ ገዳማቸው መጥቶ መካነ ዐፅማቸውን የተሳለመውን እስከ 14 ትውልድ ድረስ እንደሚምርላቸው ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ልጁን በስማቸው የሰየመ ቢኖር የሰይጣንን ፊት ፈጽሞ እንደማያይ ገድላቸው ይናገራል፡፡

የበዓሉ በረከት ይድረሰን፨


በካቶሊኮች ዘንድ ያለውን በገና ዋዜማ መዝሙር የመዘመር ስርአት ወይም "Christmas Carol" የሚሉትን እዚህ መተግበር ለምን አስፈለገ? ወጣቱን መሰብሰብ በሚል መልካም በሚመስል ሃሳብ ቀባብቶ ማቅረብስ ለምን?

ሲጀመር ዲያቆን ሄኖክ አውግስጢኖስ (Augustine) የሚባለውን ካቶሊኮች እንደ ቅዱስ የሚያዩትን መናፍቅ ሰው ማወደስ እና ስለሱ ደጋግሞ ማውራት ሲጀምር ነው መጠርጠር የነበረብን።


Репост из: ሴራ ታሪክ እና ምርምር
ሄኖክ በ2015 ቫቲካን  ሄደ..., በዓመቱ በ2016 ይሄ የአላፋት ዝማሬ ተጀመረ፣ በዚህ ዓመት ደግሞ በጣም ተዋወቀ፣ለሚቀጥለው ለሚሠሩት ሥራ መሠረት ተጣለ ማለት ነው

ከአላፋት ዝማሬ ወይም ጃንደረባ ትውልድ ጀርባ ያሉት እነማን ናቸው ... ማነው የሚመራው? ማነው የሚያቀነባብረው?  የገንዘብ ምንጩ ምንድንው? 

የካቶሊክ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ ያላትነት ጠላትነት ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ነው....   ሲጀመር ከካቶሊክ ጋር መጎበኛኘትን ምን አመጣው... በሃይማኖት አንድ አይደለን ፣ በዓላማ አንድ አይደልን... የምናመልከው አምላክ  የተለያየ ነው.... ከርስቶስን አንቀበልም ብለው ተወግዘው ከተለዩ ስንት ሺህ ዓመታት አለፉ... ታዲያ ምን ነገር ያገናኘናል?  ምንም።
ታዲያ ሄኖክ ምን ሊሠራ እዛ ሄደ፣ ከነዚህ ሰዎች ጋር ምን ሊወያይ ይችላል?

ደግሞ የሚያስቀው፣እነ ሄኖክ  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እየደረሰባት ያለውን መከራ ለጳጳሱ  ነገሩት ይላል...   ጳጳሱ  ራሱ አይደል እንዴ  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ መከራ እያደረሰባት ያለው።

ስለዚህ እንደዚህ እንደዚህ አይነት ነገሮች ስላሉ ነው... ትንሽ እናስተወል የምንለው...

ምክንያቱም በወጣቱ ዘንድ አንዴ የሆነ ተቀባይነትን እና እምነትን ካገኙ ቡሃላ... የሆነ ነገር ለወጥ ማድረግ ይጀምራሉ... ያ ደግሞ ትንሽ ወጣቱን ወደ ቤተክርስቲያን የሚያመጣ አስመስሎ ሙሉ ለሙሉ ሃይማኖቱን እና ኢትዮጵያዊነቱን  አስጥሎ ካቶሊክ የማድረግ ክፉ መዘዝ ይኖረዋል።


ኢንግሊዞች ዓለም አቀፍ ኢምፓነራቸውን ለማስፋፋት የረዷቸው ሁለት ነገሮች የባሕር ሃይላቸው እና የስለላ ድርጅታቸው ናቸው። የባሕር ሃይላቸው ዓለም አቀፍ ንግድን እንዲቆጣጠሩና በሀገራት ላይ ወረራቸውን እንዲያሳልጡ የረዳቸው ሲሆን የስለላ ድርጅታቸው ደግሞ ሀገራት ውስጥ ዘልቀው ገብተው ክፍፍልን ለመፍጠር፣ ጠንካራ ሀገራትን ለማዳከም፣ የነሱን ጥቅም የሚያሳልጡ ንቅናቄዎችን ለመመስረት ጠቅሟቸዋል።

ታዲያ ይህንን ካደረጉበት ውስጥ አንዱና በተደጋጋሚ የተፈጠረው በሀገራት ገብተው አዲስ ንቅናቄን ወይም ቡድኖችን መመስረት የተካኑበት ሲሆን ከነዚያም አንዱ የወሃቢዝም እንቅስቃሴ ነው። ይህንንም ያከናወነው ሰላያቸው አንድን ሙሃመድ አብድል ወሃብ የተሰኘ ወጣት በመጠቀም አዲስ የሱኒ እስልምና ክፋይ የሆነ አክራሪ እንቅስቃሴን በፈረንጆቹ 1744 መሠረተ። ይህም እንቅስቃሴ እስከ ዛሬ በኢንግሊዝ የሚደገፍ እና ለብዙ አክራሪ ቡድኖችም የሚመሩበት አይዲዮሎጂ ነው። ይህም እንደ አልቃይዳ፣ አልሸባብ፣ በሶርያ የነበረው ጀባት አል ኑስራ እንዲሁም አይ. ኤስ የዚህ አራማጆችና የአክራሪ ሽብርተኝነታቸው አንኳር የሆነ ነው።

እንዲያውም የአይ ኤስ መስራች የነበረው አንድ ኢንግሊዛዊ ግለሰብ እንደሆነ ሁሉ ይታወቃል። ዛሬ ላይ መካከለኛው ምስራቅ ላለበት የማያባራ ቀውስ እና ጦርነት የኢንግሊዝና ፈረንሳይ የእጅ ስራ ሲሆን ይህ አይዲዮሎጂም አንዱ የዛ ተግባራቸው አካል ነው።

ታዲያ ያንን ሲያደርጉ ከዛው ከአከባቢው ተወላጆች መልምለው ስለሚያሰማሩ እና ተመልማዮቹም ከውጪዎቹ ጋ ያላቸውን ግንኙነት በጣም በጥንቃቄ ስለሚደብቁ የአከባቢው ሰዎች የውጪ ተጽዕኖ ያለበት ንቅናቄ መሆኑን ባለመረዳት ይከተሏቸዋል።


የክርስቶስ ልደት በቅዱስ ኤፍሬም

እመቤታችን በቤተልሔም ርሱን እየደባበሰች ዘመረችለት ስትስመውም ርሷን ለማግኘት ዞረላት፣ ወደ ርሷም ተመልክቶ በርሷ ላይ ዐርፎ እንደ ሕፃናት ፈገግ አለ፤ በጨርቅም ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኛ (ሉቃ ፪፥፯)፤ ማልቀስ ሲዠምር ተነሥታ ወተት ሰጠችው፤ ስትዘምርለት ዐቀፈችው፤ እስክታቅፈው ድረስም በጉልበቶቿ ተንበረከከች፡፡

የአንተ ዘር የኾነ ዳዊት ከመምጣትኽ በፊት በረጅም ግጥም ይዘምርልኻል፣ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለኽ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ በሳባ ወርቅ ትንቢት ውስጥ የዘመረልኽ ፣ - እና አኹን መዝሙሩ እውነት ኾኗል (መዝ ፸፩፥፲፭)፣ እነዚኽ ወርቆች፣ እጣንና ከርቤ ለአንተ ለጌታ ለኀያሉ ልጅ ቀርበውልኻል፣ ወርቅ ለንጉሥነትኽ፣ ዕጣን ለመለኮታዊነትኽ፣ ከርቤም ሥጋን ስለ መዋሐድኽ (ማቴ ፪፥፲፩)፡፡

አንተ በአባትኽ ዕሪና፣ በማርያም ውስጥም ነኽ እና በሠረገላውም ላይና በበረት ውስጥ በኹሉም ቦታ ነኽ! በእውነት በአባትኽ ዕሪና ውስጥ ነኽ፣ ያለምንም ጥርጥር በማርያም ውስጥ ነኽ፣ በሠረገላው ላይ እና በተናቀው በረትም ውስጥና በኹሉም ቦታዎች፤ አንተ የኹሉ ፈጣሪ ምሉእ በኲለሄ የኹሉ ሠሪ፤ አንተ ከአባትኽ ነኽ፣ ቢኾንም ግን ከማርያምም ነኽ፤ አንተ አንድ ነኽ፣ አንተ የመጣውና የሚመጣው ነኽ (ዕብ ፲፫፥፰)፡፡

የአንተን መለኮታዊነት በጥልቀት በመመራመር ለሚፈልገውና ለሚመረምረው ወዮለት፤ አንተን የማያምን ወዮለት፣ ለአንተ ፍቅሩን የማያሳይ ወዮለት፣ በአንተ እምነት የሌለው ወዮለት፣ አንተን ችግር (ሕጸጽ) አለብኽ ብሎ የሚያስበው ወዮለት፣ የአንተን ስም እግዚአብሔር እንደኾንኽ የሚጽፈው የተባረከ ነው፤ የአባትኽ በረከት፣ የፍቅርኽ በረከት የመንፈስኽ በረከት በአንተ ልደት በሚደሰት ላይ ኹሉ ላይ ይኹን!፡፡

የባሕርይ አምላክ ለኾንኸው ብላቴና እሳታሞች የሚካኤል ነገድ ይርዳሉ! ኪሩቤሎችና ሌሎቹ እንስሳት ተቀናጅተው ሠረገላኽን ይሸከማሉ፤ የኤልሻዳይ ልጅ ሆይ ርቱዕ የኾኑት መንኰራኲሮች ላንተ በቂ አይደሉም (ራእ ፬፥፮)፤ ግን የማርያም ንጹሕ ዕቅፏ አንተን ይዟል፣ ይኽ እንዲኾን ቸርነትኽ ፈቅዷልና፤ የማትወሰን ስትኾን ተወሰንኽ የምሕረትኽ ባሕር የማይወሰን ሲኾን፡፡

የአንተ ዕይታ አስደሳች ነው፤ መዐዛኽ ጣፋጭ ነው፣ አፎችኽ ቅዱስ ናቸው፤ ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ ከአንተ ሕይወት ኹሉ ይመጣል፤ የአንተ ኅብስትነት ቤተ ኅብስት ለተባለችው ቤተልሔም ሕይወት ነው፤ ለሚኖሩት ኹሉ ሕይወታቸው ነኽ፤ እስትንፋስኽ እንዴት ጣፋጭ ነው? ሕፃንነትኽ እንዴት ተፈቃሪ ነው፤ አንተ ለምግብነት በጣም የምትፈለግ ሩህሩህ ሆይ የሰማያት ምግብ የኾንኽ ለአዕዋፍም ሕይወትን የሰጠኽ ነኽ፤ ከድንግል የተወለድኽ ብላቴና ሆይ የአንተን ደም የናፈቀ የተባረከ ነው (፩ኛ ዮሐ ፩፥፯)፡፡

ሕያው የእግዚአብሔር ጠቦት ሆይ እረኞች ለአንተ የሚጠባን ጠቦት በስጦታ አቀረቡልኽ፤ ተንበርክከው አመለኩኽ፣ አንተን ዐውቀውኽ ምስጋናቸውን ለእውነተኛው እረኛ ለአንተ ለጌታ አቀረቡ (ሉቃ ፪፥፳)፡፡ ረቂቃን ከኾኑ ከመላእክት ምስጋና “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይኹን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” በማለት ምስጋናን ከሚያቀርቡ በግልጽ ከሚያውጁ ረቂቃን ከኾኑ ከመላእክት ክብር የተነሣ ኹሉም በመገረም ተመለሱ (ሉቃ ፪፥፲፬)፡፡

አንተ የአብ ልጅና የማርያም ልጅ ነኽ፡- አንድና ተመሳሳይ ነኽ የእግዚአብሔር ቃሉ ሆይ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ከአብ የተወለድኽ ከተፈጥሮ ውጪም (በላቀ) ከእናቱ ተወልደኽ የመጣኽ … የባሕርይ አምላክ ሆይ አንተ ብቸኛ ልጅ ነኽ፤ ባንተ ውስጥ የማያልቅ የሚነገር ስዉር ጥበብ አለ፤ ስለዚኽም ከዳዊት የራሱ ልጅ ድንግልናዊ ወተትን ተኝተኽ ትጠባለኽ፡፡

ኀያሉ እግዚአብሔር ሆይ ማሕፀኗ ወልዶኻል፣ የከብቶች ግርግም በቅቷል (ሉቃ ፪፥፯) ስምዖን ተሸክሞኻል (ሉቃ ፪፥፳፰)፤ እዚኽ ላይ አንተ ሊነካ እንደሚችል የኾነ ሰው በሰውነት ቅርጽ ተወስነኽና ተይዘኻል፡፡ በጭራሽ ሊወሰን የማይችል ባሕርይ ነኽ ግን በዚኽ ላይ በትንሿ የከብቶች ግርግም ላይ ተወስነኻል! አኗኗርኽን ማን ሊይዘው ይችላል እዚኽ ላይ በተወሰነ ቦታ ውስጥ ነኽ! ምንም እንኳን ልትወሰን የማትችል ወልድ ብትኾንም ግን በተዋሐድከው ሥጋ ለመወሰን ፈቃድኽ ኾኗል፡፡

የምትመስለው ማንን ነው? አባትኽንም እናትኽንም ትመስላለኽ፤ እግዚአብሔር መጠን የለውም ከቀለምኽ ውጪማ በኀያልነትና በባሕርይ በአኗኗርም ጭምርና በሥልጣን አባትኽን ትመስላለኽ (ዮሐ ፲፬፥፱)፡፡ ግን የሰውን ቅርጽ ያገኘኽባት የወለደችኽ ማርያምንም ጭምር ትመስላለኽ፤ አባትኽንም እናትኽንም ራስኽንም ትመስላለኽ፡፡ አርአያ ገብርን ለነሣኸው ለአንተ ምስጋና ይግባኽ (ፊልጵ ፪፥፯)፡፡

አንተ እንዴት ጽኑዕ ነኽ፤ ግን ቅን (ትሑት)ና ኀያልም ጭምር ነኽ! (ማቴ ፲፩፥፳፱) የአንተ ልደት የተሰወረና የተገለጸ ነው፤ እንደ ብላቴና በማንኛውም ሰው ፊት ለፊት ራስኽን ታስጠጋለኽ፡፡

ለሚያጋጥሙኹ በሙሉ ፈገግ ትላለኽ፤ ለሚስሙኽ በሙሉ ዐይኖችኽ በደስታ ይፍለቀለቃሉ፤ ከንፈሮችኽ የሕይወትን በጎ መዐዛ ይመግባሉ (ያስገኛሉ) (መሓ ፬፥፲፩)፤ ከጣቶችኽ ጫፍ በጎ መዐዛ ያለው ከርቤ ይንጠባጠባል (መሓ ፭፥፭)፤ ዐይኖችኽ የአንተን ዕይታ በተራበችው እናትኽ ላይ በፍቅር ተተክለዋል፤ ልክ እንደ ቤተ ክርስቲያኗ የራሷ ልጆች (ምእመናን) በአንተ የተራቡ ናቸው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Source: @ortodoxmezmur


አንድ ሰው በአስተሳሰቡና የእምነት ስርአቱ ውስጥ ከሚያስፈልጉት ወሳኝ ነገሮች አንዱ ወጥ የሆነ የተስተካከለ እምነቶችን መያዝ ነው። ይህን ስንል ምን ማለታችን ነው? አረፍተ ነገሩን አንድ በአንድ ተንትነን እንመልከት።

በመጀመሪያ የእምነት ስርአት ስንል ምን ማለታችን ነው? ይህ ማለት አንድ ሰው የሚያምናቸውና የሚቀበላቸው ሀሳቦች እምነቶች ስብስብ ነው። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ግለሰቡ ያለው እምነት ወይም አቋም በአጠቃላይ ሲሰበሰብ የግለሰቡ እምነት ስርአት ይሆናል።

ታዲያ ይህ የእምነት ስርአት ወጥ ነው ስንል ደግሞ የሚያምናቸው ሀሳቦችና እምነቶች የማይጣረሱ፣ የማይምታቱ፣ የተስማሙ ናቸው ማለታችን ነው። ለምሳሌ ሰዎች እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ ብለው ያምኑና መልሰው ደግሞ በኢቮሉሽን እናምናለን ይላሉ። ይህ የእምነት ስርአታቸው ወጥ አለመሆኑን ያሳያል።

በሌላ መልኩ ካየነው ደግሞ አንዳንዴ አንድን ሀሳብ እንደ እውነት ከተቀበልን በኋላ፣ የእምነት ስርአታችን ወጥ ይሆን ዘንድ የዛን ሀሳብ ድምዳሜም መቀበል አለብን። ማለትም ያንን ሀሳብ ተከትሎት የሚመጣውን ምክንያታዊ ድሞዳሜም ትክክል መሆኑን ማመን አለብን። ለምሳሌ ሰዎች ሁሉ መጥፎ ናቸው ብለን የምናምን ከሆነና አንድ መልካም ሰው ካጋጠመን፣ ይህ ሰው መልካም ነው ካልን አስተሳሰባችን ወጥ አልሆነም፣ የእሳቤያችንን ምክንያታዊ ድምዳሜም አንቀበልም ማለት ነው።

ማለትም "ሰው ሁሉ መጥፎ ነው" የሚለውን ሃሰብ እንደ እውነት ከተቀበልን፣ "ይህም ሰው መጥፎ ነው" የሚለው የርሱ ምክንያታዊ ድምዳሜ ነው። ስለዚህ ምክንያታዊ ድምዳሜውን መቀበል አለብን ማለት ነው።

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሰዎች የተሳሳቱ ሀሳቦችን እንደ እውነተኛ ይቀበላሉ። ከዚያም ቀጥሎ ያለው የሀሳቡ ድምዳሜ ይበልጥ የተሳሳተ መሆኑን ሲያዩ እሱን ሳይቀበሉ ይቀራሉ። ነገር ግን አስተሳሰባቸው ወጥ እንዲሆን ሁለቱንም መቀበል አለባቸው። ወጥ ካልሆነ ትልቅ ችግር ያጋጥማቸዋል። ለምሳሌ አስተሳሰባቸው ወይም የእምነት ስርአታቸው ወጥ አለመሆኑን ያስተዋለ ሰው በክርክር ወቅት የሀሳባቸው ድምዳሜ የሆነውን የተሳሳተ ሀሳብ እንዲቀበሉ ሊገፋፋቸው ይችላል። የተሳሳተ ሀሳብ የሆነው ድምዳሜ በትክክል የመጀመሪያ የተቀበሉት ሀሳብ ምክንያታዊ ድምዳሜ መሆኑን በትክክል አሳይቶ እንዲቀበሉ ሊገፋፋቸው ይችላል። ያኔም መቀበል ግድ ይሆንባቸዋል። ይህን በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ "ሀሉም እንስሳት አራት እግር አላቸው" የሚለውን ሀሳብ እንደ እውነት የተቀበለ ሰው፣ "ዶሮ አራት እግር አላት" የሚለውን የሀሳቡን ድምዳሜም እንደ እውነት መቀበል ይኖርበታል። ምክንያቱም እንስሳት ሁሉ አራት እግር ካላቸው ዶሮም አራት እግር ሊኖራት ይገባል። ምክንያቱም ዶሮ እንስሳ ናት።

ስለዚህ ይህ ሰው ሁለት ምርጫ አለው። ወይ ድምዳሜውን መቀበል፣ አልያም መነሻውን ሀሳብ ከነ አካቴው መተው።

ይህንን ሀሳብ በሌላ ወሳኝ ምሳሌ እንመልከተው። አንድ ክርስቲያን ሰውን እንውሰድ። ይህ ሰው ክርስቲያን ነኝ ብሎ ካሰበ፣ ፈጣሪ ምድርን በስድስት ቀን ፈጠራት የሚለውን ሀሳብም መቀበል አለበት። ካልሆነ የእምነት ስርአቱ ወጥ አይደለም ማለት ነው። ሀሳቡን አንድ እርምጃ ወደፊት ብንወስደው፣ ብዙ ክርስቲያኖች በግሎብ ምድር ያምናሉ። ስለዚህ የምንኖርባት ምድር በትልቅ ድቡልቡል ፀሐይ ዙርያ የምትሄድ ድቡልቡል ፕላኔት ናት ብለው ያምናሉ። ይህም ሰው ያንን ያምናል እንበል።

ይህ ሰው ከላይ በጠቀስነው ካመነ፣ በቢግ ባንግም ማመን አለበት። ለምን? ምክንያቱም በግሎብ ቲዮሪ መሠረት ዓለም የተፈጠረችው በዚያ መልኩ ስለሆነ። ያንን ብቻ አይደለም። ይህ ሰው በኢቮሉሽን ማመን አለበት። ምክንያቱም ሳይንሱ እንደሚለው በግሎብ ምድር ላይ ህይወት የተገኘው በመቶ ሚሊዮን ዓመታት ሂደት ውስጥ ነው። በውቂያኖስ ውስጥ ኬሚካሎች ተቀላቅለው ባክቴሪያ፣ ከባክቴሪያ አሜባ መሰል ነገሮች ተገኙ፣ ከሱም የባህር ውስጥ ትል ተገኘ፣ ከትሉም ሄዶ ሄዶ አሳ፣ አሳም ከባህር ወጥቶ አዞ፣ አዞም በሂደት ወደ አጥቢ እንስሳ አይነት፣ ያም ተቀይሮ ወደ ተለያዩ ዝርያዎች ተቀየረ፣ ከርሱም ዝንጀሮ መሰል እንስሳት ተገኙ ሰውም ከነሱ ከአንዱ ተገኘ ይላል።

ስለዚህ፣ ምድር ከቢሊዮን ዓመታት በፊት በድንገተኛ ክስተት የተገኘች ፕላኔት ናት የሚለውን ከተቀበልን። እኛም በሷ ላይ በሚሊዮን ዓመታት ድንገተኛ ሂደት ውስጥ ነን የተገኘነው የሚለው የሱ ምክንያታዊ ድምዳሜ ይሆናል።

ስለዚህ የመጀመሪያውን ሀሳብ የተቀበለ ሰው ሁለተኛውንም መቀበል ግድ ይሆንበታል። ነገር ግን ያንን የተቀበለ ሰው ተመልሶ ፈጣሪ በስድስት ቀን ዓለምን ፈጠራት የሚለውን ሊቀበል ይችላል?

መልሱ አይችልም ነው። ለራሱ ሀቀኛ የሆነ ሰው ያንን ማድረግ እንደማይችል ያምናል። ለዚያ ነው ብዙ ሳይንስ የገባቸው ሰዎች የፈጣሪን መኖር የሚክዱት። ምክንያቱም ሁለቱ ሀሳቦች መሠረታዊ ቅራኔ እና መጣረስ በመካከላቸው እንዳለ እውቅና ስለሚሰጡ።

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በፈጣሪ መኖር እንዳታምኑ ማድረግ አይደለም። ይልቁንም፥ አማራጩን ሀሳብ መስጠት እንጂ። አማራጩ ምንድን ነው?

ቀድሞውኑ መነሻ ሀሳቡን አለመቀበል።

"ምድር በቢሊዮን ዓመታት ድንገተኛ ክስተቶች ሂደት የተፈጠረች ዱቡልቡል አካል ናት" የሚለውን በሙሉ ወደጎን መተው ነው።

ያንን ካደረግን፣ የእምነት ስርአታችን ያልተጣረሰ ወጥ ይሆናል። ምክንያቱም አንደኛ፣ ፈጣሪ በእቅድና በዓላማ ፈጠረን ከሚለው እምነታችን ጋር አይጋጭም። ሁለተኛ፣ "ምድር በቢሊዮን ዓመት ድንገቴ ክስተቶች የተፈጠረች ግሎብ ናት" የሚለውን የተሳሳተ ሀሳብ ሳንቀበል ከተውን፣ "አስቦና አቅዶ ዓለምን የፈጠረ አካል የለም" የሚለውን የተሳሳተ፣ ግን የዛኛው ምክንያታዊ ድምዳሜ የሆነውን ሀሳብም መቀበል አይኖርብንም።

ስለዚህ ወጥ የእምነት ስርአት ካለን ምን ብለን እናምናለን? ፈጣሪ በእቅድና በዓላማ ዓለምን ፈጠረ፣ ምድርም በርሱ የተፈጠረች ዝርግ አድርጎ ላይዋን በሰማይ ጉልላት ከድኖ ፈጥሯታል፣ እኛንም የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶ በርሷ ውስጥ አኑሮናል።

ብለን እናምናለን።

Показано 20 последних публикаций.