በአዲሱ የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ስረአት ለመደንገግ ከወጣው ረቂቅ አዋጅ ከባድ ቅጣትን የሚያስከትሉ የወንጀል አይነቶች:-
1/ የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ ያከማቸ፣ ሊሸጥ ከሚገባው ሰው፣ ቦታ
እና የግብይት ሥርአት ውጪ ሲሸጥ የተገኘ ወይም በመመሪያ በተወሰነው
መሠረት አደጋ ያስከትላሉ በተባሉ መያዣዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ሰው
የተያዘው የነዳጅ ውጤት ተወርሶ ከሦስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና
ከብር ሀምሳ ሺ እስከ አንድ መቶ ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
2/ የነዳጅ ውጤቶችን ሆን ብሎ ከባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል ለግብይት ያቀረበ
ማንኛውም ሰው ከሦስት አመት እስከ ሰባት አመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት እና
ከብር አንድ መቶ ሀምሳ ሺ እስከ ሶስት መቶ ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
3/ የዋጋ ቁጥጥር የሚደረግባቸውን የነዳጅ ውጤቶች መንግስት ከተመነው የመሸጫ
ዋጋ በላይ ሲሸጥ የተገኘ የግብይት ተዋናይ በመጀመሪያ ጥፋት ከብር አንድ መቶ
ሀምሳ ሺ እስከ ሶስት መቶ ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፤ ድርጊቱን በተደጋጋሚ
ከፈጸመከሦስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከብር አንድ መቶ ሺ እስከ
ሁለት መቶ ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
4/ በሚመለከተው አካል የነዳጅ መቅጃ መሳሪያዎች የልኬት ሜትር ማስተካከያ
ተደርጎበት በፕሎምፕ የታሰረውን የቆረጠ ወይም ልኬቱን ያዛባ ማንኛውም ሰው
ከሦስት አመት እስከ ሰባት አመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት እና ከብር አንድ መቶ
ሀምሳ ሺ እስከ ሶስት መቶ ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
5/ የካሊብሬሽን የምስክር ወረቀት ሳይዝ ወይም ካልብሬት የተደረገውን የነዳጅ
ውጤቶች ልኬት በማዛባት የነዳጅ ውጤቶችን ሲያጓጉዝ ወይም ሲሸጥ የተገኘ
ማንኛውም ሰው የነዳጅ ውጤቶች ተወርሰው ከሦስት አመት እስከ ሰባት አመት
በሚደርስ ጽኑ እሥራት እና ከብር አንድ መቶ ሀምሳ ሺ እስከ ሶስት መቶ ሺ
በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
6/ የተረከባቸውን የነዳጅ ውጤቶች ከተፈቀደለት የማጓጓዣ መስመር ውጪ
ሲያጓጉዝ፣ ከተፈቀደለት ማራገፊያ ውጪ ሲያራግፍ ወይም ወደ ጎረቤት ሀገር
በኮንትሮባንድ ሲያጓጉዝ የተገኘ ማንኛውም ሰው የተያዙት የነዳጅ ውጤቶች ተወርሰው ከሦስት አመት እስከ ሰባት አመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት እና ከብር
አንድ መቶ ሀምሳ ሺ እስከ ሶስት መቶ ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
7/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) ወይም (6) የተመለከተው ሕገ ወጥ ድርጊት
ሲፈጸም የአጓጓዡ ባለቤት ድርጊቱን እያወቀ እንዳይፈጸም ለመከላከል ወይም
ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ ሳይወስድ የቀረ እንደሆነ ተሽከርካሪው ከነዳጅ
ውጤቶች ጋር ተወርሶ ከሦስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ
እስራት ይቀጣል፡፡
8/ አግባብ ካለው አካል በጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ የነዳጅ ውጤቶችን የነዳጅ ማደያ
በሌለባቸው አካባቢዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ሰው የተያዘው የነዳጅ ውጤት
ተወርሶ ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከብር ሀያ አምስት ሺ እስከ
ሀምሳ ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
9/ የባለሥልጣኑን ወይም አግባብ ያለውን አካል የቁጥጥር ሂደት የተቃወመ፣
ያሰናከለ ወይም በማንኛውም ሁኔታ ተፅኖ ያደረሰ ማንኛውም ሰው ከሦስት
ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከብር አስር ሺ እስከ ሀያ ሺ በሚደርስ
መቀጮ ይቀጣል፡፡
10/ በዚህ አንቀጽ የተመለከቱት ድርጊቶች የሕግ ሰውነት ባለው አካል የተፈጸሙ በሆነ
ጊዜ ከብር አንድ መቶ ሺ እስከ አምስት መቶ ሺህ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
👉ስለጠቋሚ
ህገ-ወጥ የነዳጅ ውጤቶች ንግድ ወይም የኮንትሮባንድ ድርጊት የተፈጸመ መሆኑን ጠቁሞ
ላስያዘ ሰው ጥቆማዉ ዉጤታማ ሲሆን የጠቋሚ አበል ይከፈለዋል፤ ዝርዝሩ
በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ይወሰናል፡፡
ሙሉውን የአዋጁን pdf ከታች ያገኙታል 👇
https://t.me/hawassacityfuel ✅