HAppy Mûslimah


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


አጫጭር ኢስላማዊ ታሪኮች ብቻ
ONLY SHORT ISLAMIC STORY‼️
Fôr Any Cømments👉 @NihalllAb

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: || ጥበባዊ ታሪኮች || ™️
Customer made Arabic Necklace
በፈለጉት ቃል እንሰራለን

stainless steel
Available Colors: Golden and Silver

@elsal_2 👈 👈 for order (ለማዘዝ)

https://t.me/+YLUR0dsL1GwwYmI8


ተፍሲር ላይ ነበርን። ኡስታዙ ሱረቱል ዩሱፍን እየዳሰሰልን የዩሱፍን "እነርሱ ከሚጠሩኝ የበለጠ እስር ቤት እኮ ለኔ የተወደደ ነው" የሚለውን አያህ እያነሳ "እርግጥ ዩሱፍን እስር ቤቱ ለትልቅ ስኬት ቢያመቻቸውም ከዚህ የምንረዳው ግን አላህ ዱዓን እና ምኞትን በየትኛውም ሰዓት ስለሚመልስ ዱዓችሁ እና ምኞታችሁ ላይ ጠንቃቃ ሁኑ!" አለን
ምን አስታውሼ መሰላችሁ? የ ፉዓድ ሙና ጽሁፍ ላይ የትኛው እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም( ስለ ገጣሚያን ያነሳው ይመስለኛል) "አምሪያ" የምትባል ገፀ ባህሪ የሆነ አይነት የጓደኛሞች ግሩፕ አላት እና በየወሩ የቁርአን ኺትማ ፕሮግራም እንዲሁም በወሩ ላይ ከነሱ እኩል ያልቀራችውን ደስ የሚል ቅጣት የሚቀጡበት ደስ የሚል ስብስብ አነበብኩ። "ምናለ እንዲህ አይነት ግሩፕ በኖረኝ" ማለቴን እርግጠኛ ነኝ። "ስጠኝ!" ብዬ ዱዓ ማድረጌን ግን እንጃ። አላህ ግን አመታትን ቆይቶ ተመሳሳዩን ነገር በኔም ህይወት ላይ ሰጠኝ እና "ካንተ ውጪ በ እውነት የሚያመልኩት አምላክ የለም! ብዬ አመሰገንኩት። እና የተመኘሁትን የሰጠ አላህ የለመንኩትን ይረሳል? በፍጹም!!!

እና ልላችሁ የፈለግኩት በዱዓችሁ ላይ በምኞታችሁ ላይ ጌታችሁን እመኑት እና ለምኑት! ምናልባት ነገ ወይም ከ አመታት በኋላ እንደኔ ትመሰክላችሁ

@heppymuslim29


< ከዘመናት በፊት አንድ ባለ ሀብት ነበር። ይህ ባለ ፀጋ ድንገት በአንዱ እለት አንዲትን ውብ ባሪያ ይመለከታል። ባለ ፀጋው በውበቷ ስር ወደቀ። በነጋ በጠባ ቁጥር ምስሏ በምናቡ ይመላለሳል። ትውስታዋ ከልቦናው ሊፋቅ ተሳነው። የፍቅሯ ታሳሪ ሆነ። በፍቅርና በናፍቆት መሀል የምትናወጥ ልቡን ይዞ ወደ አሳዳሪዋ አመራ። ባሪያይቱን ከፍ ባለ ገንዘብ ሊገዛት ጠየቀው። የባሪያዋ አሳዳሪም ባለ ፀጋው ከባሪያዋ ጋር በፍቅር መውደቁን ከአይኖቹ ተረዳ። አሰብ አደረገና። " አይ በዚህ ዋጋ አትሸጥም! " በማለት ያለውን ሁሉ አስረክቦ ባሪያይቱን እንዲገዛው አደረገ። ባለሀብቱ የለበሰውንም ባርኔጣና ኩታን ሳይቀር አስረክቦ ተፋቃሪውን ይዞ ተጓዘ። >

  አየህ አይደል! አፍቃሪ ላፈቀረው ነገር ያለውን ሁሉ ይሰዋል። ሚሰዋው ቢጠፋ የቀረችው አንዲትን ነፍስ እንኳን ብትሆን እርሷንም አይሰስትም። የርሱ መሻት የተፈቃሪው ደስታና ውዴታን መጎናፀፍ ነው። ታድያ በፍጡራን መካከል ላለ አላቂ ፍቅር ይህን ያህል ቤዛ የሚደረግለት ከሆነና ሀብትና ንብረትን እስከማጣት ካስደረሰ ፡ ስለምን የጌታህን ፍቅር ያለ ምንም ክፍያ ትሻለህ? ክልከላውን ስትዳፈር ልብህ ላይ ያለው የማፍቀር ሂማ እየሞት እንደሚጠፋ ተሰወረህ? የትዕዛዙን በትር ስትይዝ የኩራትን ኩታ ከደረብክም በራስህ ላይ የፅልመት ካባን ነው የደረብከው። እኔነትህን ጥለህ ቅረበው። መሻትህን ግደለው። ምንምነትህን ገልጠህ ከዱንያ ፍቅር ተራቁተህ ቅረበው። ጣላት ይህችን ነፍስ! ተዋድቀህ የእውነት ሚስኪንና አሳዛኝ ባሪያ ሁንለት። እንዲያ ነው ፍ ቅ ሩ ን የምታገኝ!

(አብዱ ሩሚ)

@heppymuslim29


"ኃጢአተኛ ሰው ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይችላል ወይ?" አላቸው ከመስጊዱ ሰዎች መካከል አንዱ።

"አላህ ሰትሮት ነው እንጂ ይህ ፊት ለፊታችሁ ቆሞ የሚመክራችሁ ሰው ጭምር ከጥፋት የፀዳ ይመስችኋልን?" አሏቸው ኢማሙ።

@heppymuslim29


የገባሁበት ታክሲ ሊሞላ የኋለኛው ወንበር ብቻ እንደቀረው አንዲት ልጅ ያዘለች ወጣትና ልትሸኛት የተከተለቻት ሌላ ሴት አብረው መጡ።ባለ ልጇ ጠጋ ብላ የኋላ ወንበር መሆኑን አይታ ተመለሰች።ወደኔ ዞር ብላ "ትቀይሪኛለሽ?"ስትለኝ፣ወደኋላ እየጠቆምኩ "እዛ ጋርኮ ቦታ አለ" አልኳት።ቆጣ ብላ "ልጅ ይዤ እንዴት ነው እዛ 'ምቀመጠው?አይታይሽም?...ለነገሩ ተሸፍነሻል እንዴት ይታይሻል?¡"አለችና ወደኋላ አለች።(ሶስተኛ ሰው ቢደርቡ ላይመቻት ይችላል፣ይበልጥ የሚሻላትም ያ ነው ብዬ ነበር እንደዛ ማለቴ)።ንግግሯ ሰውነቴን ቢነዝረኝም ፊቴን ከሷ አዞሬ የታክሲውን መሙላት ተጠባበቅኩ።ግን አላስቻለኝም።ምክንያቴን ሳልነግራት ባልፍ፣ከጥላቻዋ ሌላ ኒቃብ ያደረጉ እህቶችን በሙሉ ለሰው ባለማዘን ጎራ መመደቧ ነው ብዬ ወረድኩና ተጠጋኋት።...(ፋይዳ ላይኖረው ነገር!)
.
ገና ስታዬኝድምጿን በእጅጉ ከፍ አድርጋ ተንጨረጨረች።




ደገመችው።ብዙ አወራች።

አላስጨረሰችኝም።


.
ምንም ብላት ትርጉም አልባ መሆኑ ገባኝ።ላወራ አፌን ሳንቀሳቅስ በስድብ ትቀድመኛለች፣እኩል ባወራም ድምጿ ድምፄን ይውጠዋል።ትዕግስቴ ሲሟጠጥ

ጮክ ብላ እጇን ወዲያና ወዲህ እያወናጨፈች ደጋግማ አማተበች።

ደነፋች።ብዙ ጮኸች።

አሁንም አቋረጠችኝ።

ታቦቶቿን ጠራች።(መምራት ልል አልነበረም)።ከዚህ በላይ አንድ ቃል ማውጣት ጊዜዬን ማቃጠል ነው።ትቻት ሄድኩና ቀጣይ ታክሲ ውስጥ ገባሁ።
.
በሚያሳዝን ሁኔታ መንገዳችን አንድ ስለሆነ ጥቂት ቆይታ ገባችና ተቀመጠች።




.

.
ድምጿን ከፍ አድርጋ እኔን ለጎሪጥ እያየች፣ሲላትም የታቦቶቿን ስም እየጠራች ስድቧን ቀጠለች።እኔ ግን ምንም ማለት አልፈለኩምና ዝምታን መረጥኩ።
.
ሰው ሁሉ እየዞረ ያያታል(እንደጤነኛ አይመስለኝም ግን)
.

.
እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ።በጥላቻዋ ውስጥ እልፍ ጥላቻዎች፣በንቀቷ ውስጥ እልፍ መደፈሮች ታዩኝ።...ባለፈው አንዱ ሎንችን ውስጥ ልገባ "ወንበር አለ?"ብዬ መጠየቄን ሰምቶ "ወንበር ለተማረ ነው" ያለኝ ትዝ አለኝ።...ለወንድሜ ጉዳይ ትምህርት ቤት ሄጄ ጥበቃውን አቅጣጫ ስጠይቀው "ማንበብ ከቻልሽ የመምህራን ማረፊያ የሚል ተፅፎበታል" ያለኝም ታወሰኝ።
.
እንዲሁ እንደጮኸች መውረጃዬ ደርሶ ልወርድ ስነሳ፣
አለችኝ።
.
አልኳትና ወረድኩ።ሰማችኝና ለአፍታ ፀጥ አለች።እንባዬን ጠረኩና ጉዞዬን ቀጠልኩ።ድምጿ ግን ተከተለኝ...የዒምራን ሱራ ውስጥ ያለች አንዲት አያም በራሴው ድምፅ ትሰማኝ ጀመር።

***
لَتُبْلَوُنَّ فِي أَمْوَالِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ وَلَتَسْمَعُنَّ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ وَمِنَ الَّذِينَ أَشْرَكُوا أَذًى كَثِيرًا ۚ وَإِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ

በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ በእርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከእነዚያም ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትና ከእነዚያም ከአጋሩት ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፡፡ ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው፡፡
***

@heppymuslim29


~አንዲት ሴት አጋጣሚዋን እንዲህ ትናገራለች

" የሆነ ጊዜ ኒቃብ መልበስ ፈለኩና ቤተሰቦቼን ሳማክራቸዉ አባቴም እናቴም ከለከሉኝ።ፍቃደኛ አልሆኑም ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ኒቃብ ለመልበስ ወስኜ ለበስኩ።ቤተሰቦቼ ኒቃቡን ሲመለከቱ ማንም ለትዳር አይጠይቅሺም፣መማር አትችይም፣መስራት አትችይም…እያሉ መጮህ ጀመሩ። የአላህ መሻት ሆነና በዛዉ ሳምንት ዉስጥ የሆነ ወጣት ለትዳር ጠየቀኝ። ኒካህ ታሰረ።

ባሌም የሆነ ቀን እንድህ አለኝ «ታውቂያለሽ ከ9 አመታት በፊት ነበር የምወድሽ።ኒቃብ እስከምትለብሺ ነበር የምጠብቀዉ። ልክ እንደለበሽ አንቺን ለማግባት መጣሁ» አለኝ። ከአምስት አመታት ብሃላ ቁርአን  በ10 አይነት አቀራር አስሀፈዘኝ በጣም አጋዤም ነበር። "

@heppymuslim29


በሙሳ ዘመን ነው....አንድ በጣም ድህነት ያጎሳቆላቸው ለዘመናት በችግር እና በረሀብ የኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ።

ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዘመናት በሰብር አሳልፈዋል...። እናም አንድ ቀን እቤታቸው ጋደም ብለው ሳለ ሚስት ለባለቤትዋ፦ "ሙሳ አላህን ማናገር የሚችል ነቢይ ነው አይደል?" ብላ ትጠይቀዋለች።

እሱም፦"አዎን" ይላታል። "ታዲያ ለምን እሱጋ ሄደን ስለ ሁኔታችን አንነግረውም አላህንም ስለኛ ያናግረው ሀብታም እንዲያረገን ቀሪ ህይወታችንን በድሎት እንድንኖርም ይጠይቅልን።" አለችው። ባልም በሚስቱ ሀሳብ ይስማማና ሌሊቱ እንደነጋ ጉዞ ወደ ሙሳ ዐ.ሰ ቤት ጀመሩ። ሙሳንም ዐ.ሰ አገኟቸው። ስለድህነታቸው ነግረዋቸውም በዚህ ጉዳይ እሳቸው አላህን እንዲለምኑላቸው ጠየቋቸው።

ሙሳም ዐ.ሰ አላህን ለመኑላቸው። አላህም፦"ሙሳ ሆይ! እኔ እነዚህን ሰዎች በችሮታዬ ለአንድ አመት ያህል ሀብታም አደርጋቸዋለሁ አንድ አመት ካለፈም ወደነበሩበት ድህነት እመልሳቸዋለሁ።"ብሎ መለሰላቸው።

እሳቸውም ጥንዶቹ ጋ በመሄድ አላህ ዱዓቸውን ሙስተጃብ እንዳደረገላቸው ሀብታምም እንደሚሆኑ ነግረዋቸው እናም ግን ለ አንድ አመት ቢቻ እንደሚቆይ አክለው ነገሯቸው። እነዚህ ምስኪኖችም የሰሙትን ማመን ተሳናቸው። በአጭር ግዜ ውስጥ ካለሰቡበት መንገድ ሀብታም መሆን ጀመሩ።ማንም ከሚኖረው የተሻለ ኖሮ መኖርም ጀመሩ።

እናም አንድ ቀን ይህች ብልህ ሚስት ለባሏ እንዲህ አለችው፦"ይህ ፀጋ ይህ ድሎት ለ አንድ አመት ብቻ እንደሚዘገይ ታውቃለህ አይደል? ስለዚህ በዚህ ንብረታችን አንድ መልካም ስራ እንስራ" ባልይውም በሀሳቧ ይስማማል።

ከዚያም በከተማዋ ግንባር ቦታ ላይ አደባባይ መልክ አንድ ትልቅ ቤት ይገነቡና 7 በር አበጁለት። ለሰውም መተላለፊያ ሰሩ። ቤቱ ተገንብቶ ካለቀ በኋላ እዛ ቤት ውስጥ ምግብ እያዘጋጁ ለአላፊ አግዳሚ ጠዋት ማታ ምግብ ይቀልቡ ጀመር...። በዚህ ሁኔታ ሳሉ ወራት አስቆጠሩ።

ሙሳም በትኩረት ይከታተሏቸው ነበር። ማይደርስ ቀን የለምና ያ የተወሰነላቸው ቀን ቀጠሮውን ጠብቆ ከች አለ። እነሱ ግን የቀጠሮ ቀኑ ሁላ ትዝ አላላቸውም በስራቸው ተጠምደዋል። ያ ቀጠሮ ቀናቸው አለፈ እነሱ ግን ያው ናቸው ምንም አልቀነሱም ብቻ በስራቸው ተጠምደዋል....

ሙሳም ዐ.ሰ ባዩት ሁኔታ ተገርመው፦ "ያ ረብ ቃል የገበኽላቸው ለ አንድ አመት ሆኖ ሳለ እንዴት እስካሁን እልደኸዩም?"ብለው አላህን ጠየቁ። /እዚጋ እሳቸው ሰዎቹን ተመቃኝተው ሳይሆን የአላህን ሂክማ ለማወቅ ነው የጠየቁት/

ቸር የሆነው አላህም፦ "ሙሳ ሆይ! ለነዚህ ጥንዶች ከፀጋ በሮቼ አንዲትን በር ስከፍትላቸው...እነሱ ደሞ 7 በር ከፍተው ባሪያዎቼን መቀለብ ጀመሩ። ሙሳ ሆይ! እነሱ ይሄን ሲያረጉ አይቼ የከፈትኩላቸውን በር መዝጋት ከበደኝ"አለው።

@heppymuslim29


በዒራቋ ከተማ በስራ ዉስጥ የሆነ ታሪክ ነው አሉ፡፡ ሰዎች ለአንድ ከገጠር ለመጣ እና ስለ ዲኑ ብዙም የማያውቅን ሰው “ጀነት እገባለሁ ብለህ ዉስጥህ ያስባልን?” አሉት፡፡ “በአላህ እምላለሁ! በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ታክል ተጠራጥሬ አላውቅም፤ አዳራሿ ላይ ስቦርቅ፣ ከሐውዷ ስጠጣ፣ በጥላዋ ሥር አረፍ ስል፣ ከፍራፍሬዋ ስቀጥፍ ስበላ፣ በቪላዋና ፎቋ ዉስጥ ሰንፈላሰስ ይታየኛል፡፡” አላቸው፡፡

“አለኝ ብለህ በምታስበው በጎ ሥራ ነው ጀነትን የምታስበው?” አሉት፡፡

“እንዴ! በአላህ ከማመን እና ከአላህ ዉጭ የሆነዉንና በሐሠት የሚመለከዉን ነገር ሁሉ ከመካድ በላይ ምን መልካም ሥራ ይኖራል?፡፡” አላቸው፡፡

“ወንጀልህን አትፈራም ወይ?” አሉት፡፡

“አላህ ለወንጀል ምህረትን አኖረ፤ ለስህተት እዝነትን መደበ፣ ለጥፋት ደግሞ ይቅርታን አስቀመጠ፡፡ እሱ የሚወዱትን ከጀሀነም እሣት በመጠበቅ ረገድ ቸርነቱ ከፍ ያለ ጌታ ነው፡፡” አላቸው፡፡

በበስራ መስጂድ ዉስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ “ይህ ሰው በርግጥም በአምላኩ ላይ ያለው ጥርጣሬ ምንኛ መልካምና ከፍ ያለ ነው!!፡፡” አሉና ተደመሙ፡፡ ስለዚሁ ጉዳይ አንስተዉም ብዙ አወሩ፡፡ ወዲያዉኑ ከአላህ እዝነት ተስፋ የመቁረጥ ዳመና ከላያቸው ላይ እየተገፈፈ ሲሄድ ተሰማቸው፡፡ በእጅጉ ተረጋጉ፤ እዝነቱን አብዝቶ የመከጀል ድባብ ሸፈናቸው፡፡

“ፈማ ዘኑኩም ቢረቢል ዓለሚን …” ስለዓለማቱ ጌታ ምን ትጠረጥራላችሁ! ምንስ ታስባላችሁ!!!

ከሰባሐል ኸይር መጽሐፍ የተወሰደ
@heppymuslim29


ታሪኳን ስትነግረን እንዲህ ትላለች:-✈️
ኡስታዛችን ነበርና ወደ ስምንት ጁዝዕ እሱ ዘንድ ካስደመጥን በሇላ በድንገት ሙሉ በሙሉ ሴቶችን ማሳፈዝ እንዳቆመ የመድረሳው ሀላፊዎች ያሳውቁናል።
በዚህን ጊዜ እኔ እና ጓደኞቼን ሴት ኡስታዛ ጋር ያዘዋውሩናል። እሷም የቀደመው ኡስታዛችን እናቱ ናት!!

ሁላችንም ጭራሽ እስከምንረሳው ድረስም የኡስታዛችን ዜና ይቋረጣል ። ከአስር ወራት በሇላም እኔ እና ጓደኞቼ ቁርዓን ሙሉ በሙሉ ሀፍዘን ድል ያለ የሂፍዝ ምርቃት ድግስ ተደረገልን። በድግሱም ዕለት ኡስታዛዬ ከጓደኞቼ አርቃ ይዛ ወሰደችን እና «አንቺን ከቤተሰቦችሽ ሊያጭሽ የሚፈልግ ወጣት አለ» አለቸኝ ስለ ወጣቱ አንዳንድ ነገር ነገረችኝ እና ከሱ ጋር ይወያዩበት ዘንድ የአባቴን ስልክ ቁጥር ሰጠዋቸው እንደተባለውም አወሩ እና ከሁለት ቀን በሇላ ቤታችን መጡ

ከዛማ የመጡት ...ሴቷ ኡስታዛዬ ባለቤቷ እና ልጃቸው [ከአስር ወራት በፊት የነበረው ኡስታዛችን!!! ] ሆኑ እላቹሃለው

🟤ድንጋጤዬማ ዛሬ ድረስ ትዝ ይለኛል...

.....ብቻ ቤታችን መቶ ኒቃቢስትም ስለሆንኩ ሸሪዓዊ እይታ ከተያየን በሇላ እንዲህ አለኝ «ባንቺ እንደተፈተንኩ ባወቅኩ ግዜ ከሸይጣን በሮች መካከል አንዱ ሊከፈት እንደሆነ ተሰማኝ ...
እናማ በአሏህ እርዳታ ሴቶችን ማሳፈዝ ማቆም እንዳለብኝ ወሰንኩ..... ይህም ሸይጣን አነስተኛ መንገድም ቢሆን ወደኔ እንዳያገኝ ነበር.... በዚህን ግዜ አንቺን ኒካህ ለማሰር ዝግጁ እንዳልሆንኩም ስለማውቅ ከአንቺ ጋር ሊያገናኘኝ የሚችልን መንገድ በሙሉ ገታው...ልቤንም ዲኔንም አንቺንም ጭምር እንዳላበላሽ ስል...ነገር ግን በተውኩሽ ግዜ በምድር ላይ እጅግ ከማምናት ፍጡር ....እናቴ ጋር ነበር የተውኩሽ
ጎበዝ ተማሪ ናት ወደ ፊት ላይም ታታሪ የዲን አስተማሪ መሆን ትፈልጋለች ብዬ አደራ አልኳት...» አሏህም የመልካም ሰሪዎችን ስራ ከንቱ የሚያደርግ አልነበረም።
ራሳቸውን አስጠበቁ ጥብቆችም ገጠማቸው ..."መልካሞችስ ለመልካሞቹ የተገቡ አይደል"

@heppymuslim29


ከእለታት አንድ ቀን ሁለት ሰሀቦች ወደ ረሱል ﷺ ተወዳጅ ሚስት አኢሻ ጋር መጡና ጥያቄ ጠየቁ አኢሻ ሆይ! እስኪ ረሱል ﷺ ላይ ያየሽውንና በጣም ያስገረመሽን ነገር ንገሪን አሏት አኢሻ እንባዋ ቀደማት አለቀሰች ከዛም እንዲህ አለች አንድ ቀን ማታ ረሱል ﷺ ከኔ ጋር ነበሩ አኢሻ ሆይ! ይችን ለሊት ፍቀጂልኝ ከጌታዬ ጋር ላሳልፈው አሉኝ" እርስዎን የሚያስደስቶት ነገር ከሆነ እኔም ደስተኛ ነኝ ስላቸው ተነሱና ተጣጥበው መስገድ ጀመሩ ከዛም ጉንጫቸው እስኪርስ ድረስ አለቀሱ አሁንም ጉልበታቸው እና መሬቱ በእንባቸው እስኪታጠብ ድረስ ማልቀሳቸውን ቀጠሉ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ቢላል ለሰላት ሊጠራቸው መጣ እያለቀሱም አገኛቸው ከዛም እንዲህ አለ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ያለፈውንም የሚመጣውን ወንጀል ተምሮሎት እንዲህ ይሆናሉ? ታዲያ አመስጋኝ ባሪያ መሆን የለብኝም እንዴ የሳቸው መልስ ነበር:: ከዛም የሚከተለውን ንግግር ተናገሩ:-…
ዛሬ ለሊት የተወሰኑ አንቀጾች ወርደውብኛል እነሱን አንብቦ ያላስተነተነ ሰው ወየውለት አሉና"
ﺇِﻥَّ ﻓِﻲ ﺧَﻠْﻖِ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻭَﺍﺧْﺘِﻠَﺎﻑِ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞِ ﻭَﺍﻟﻨَّﻬَﺎﺭِ ﻭَﺍﻟْﻔُﻠْﻚِ ﺍﻟَّﺘِﻲ ﺗَﺠْﺮِﻱ ﻓِﻲﺍﻟْﺒَﺤْﺮِ ﺑِﻤَﺎ ﻳَﻨﻔَﻊُ ﺍﻟﻨَّﺎﺱَ ﻭَﻣَﺎ ﺃَﻧﺰَﻝَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻣِﻦ ﻣَّﺎﺀٍ ﻓَﺄَﺣْﻴَﺎ ﺑِﻪِ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽَ ﺑَﻌْﺪَ ﻣَﻮْﺗِﻬَﺎ ﻭَﺑَﺚَّ ﻓِﻴﻬَﺎ ﻣِﻦ ﻛُﻞِّ ﺩَﺍﺑَّﺔٍ ﻭَﺗَﺼْﺮِﻳﻒِ ﺍﻟﺮِّﻳَﺎﺡِ ﻭَﺍﻟﺴَّﺤَﺎﺏِ ﺍﻟْﻤُﺴَﺨَّﺮِ ﺑَﻴْﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻟَﺂﻳَﺎﺕٍ ﻟِّﻘَﻮْﻡٍ ﻳَﻌْﻘِﻠُﻮﻥَ
ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር ሌሊትንና ቀንንም በማተካካት፣ በዚያቸም ሰዎችን በሚጠቅም ነገር (ተጭና) በባህር ላይ በምትንሻለለው ታንኳ፣ አላህም ከሰማይ ባወረደው ውሃና በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ፣ በርሷም ውስጥ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በመበተኑ፣ ነፋሶችንም (በየአግጣጫው)በማገለባበጥ፣ በሰማይና በምድር መካከል በሚነዳውም ደመና ለሚያውቁ ሕዝቦች እርግጠኛ ምልክቶች አሉ፡፡
«ሱረቱል አል-በቀራህ 164» አነበቡ።

@heppymuslim29


አንድ ሰው ጸጉሩን ሊስተካከል ወደ አንድ ጸጉር አስተካካይ ቤት ይሄዳል። እናም በመሀል ጫወታ ይጀምራል።

ጸጉር አስተካካይ፦ ታውቃለህ አላህ የለም

ተስተካካይ፦ በመገረም እንዴት?

አስተካካይ፦ አይታይህም?

ተስተካካይ፦ ምኑ?

አስተካካይ፦ እንዴ አላህ ቢኖር እኮ ይሄ ሁሉ ጦርነት ፣ረሀብ፣ ችግር፣ ስርአት አልበኝነት አይኖርም ነበር ስለዚህ
ፈጣሪ አንዴ ፈጥሮን ትቶን ሄዷል ወይ ሞቷል።

ተስተካካይ፦ ታውቃለህ ጸጉር አስተካካይም የሚባል የለም እኮ።

አስተካካይ፦ ግራ በመጋባት እንዲህም በመገርም እንዴት?

ተስተካካይ፦ ጸጉር አስተካካይ ቢኖርማ ጸጉሩ የጎፈረ ሰው አይኖርም ነበር።

አስተካካይ፦ እነዚህ ሰዎች እኮ ወደ ጸጉር አስተካካይ አለመምጣታቸው ነው እንጂ ቢመጡማ ኖሮ አንድም ጸጉሩ
የተንጨባረረ ጸጉር አታይም ነበር።

ተስተካካይ፦ትክክል ብለሃል በአለማችን ያለው ችግርም ይኸው ነው ሰው ከፈጣሪው ስለራቀ ነው እንጂ አላህ ስለሌለ አይደለም።''

@heppymuslim29


ታላቁ ሌባ በሚል ስያሜው ድፍን ሃገር የሚያውቀው አንድ ሌባ ነበር። ታዲያ ታላቁ ሌባ የሌብነት ተግባሩን ሊፈፅም አንድ ቤት በር ላይ ደርሷል፣ አዩኝ አላዩኝ በሚል ዙሪያ ገባውን አማተረና ማንም እንዳላየው ሲያረጋግጥ ወደ ዛ ቤት ዝው ብሎ ገባ። ዳሩ ቤቱ ኦና ነው። ሚዘረፍ አንጡር ሃብት ይቅርና ሚላስ ሚቀመስ ያለበት እንኳን አይመስልም።
«ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል » እንዲሉ ሌባው ላመል ልሸው የምወጣው ባገኝ ብሎ ቤቱን ሲመነቃቅር የቤቱ ማዕዘን አቅራቢያ ሆነው ሲሰግዱ የነበሩት የቤቱ ባለቤት ሶላታቸውን ሲጨርሱ ሌባው የሚሰረቅ አንዳች ነገር አጥቶ ባዶ እጁን ሊወጣ ሲሰናዳ ያዩታል። በእድሉ ያዘነው ሌባ ለመውጣት ወደ በሩ ሲያመራ። «ባዶ እጅህን ከምትወጣ ይልቅ አንዴ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርድና አስር ሀሰናት (ምንዳ)ይዘህ ውጣ»የሚልን ድምፅ ሰማ። ሌባው ድምፁን ወደ ሰማበት አቅጣጫ ሲዞር አንድ ግርማ ሞገስ የተላበሱ ሰው ያያል። የቤቱ ጌታ ናቸው። ይህ ክስተት ለታላቁ ሌባ ፍፁም እንግዳ ነው። ሊሰርቅ የመጣንና እጅ ከፍንጅ የተያዘን ሌባ ጠፍረው ወደ ህግ በሚገትሩበት አሊያም እዛው ቀጥቅጠው አፈር ድሜ በሚያስግጡበት ሀገር። ባዶ እጅህን ከምትወጣ ይልቅ እንዲህ ያለ መልካም ስራ ስራና ሰዋብ(ምንዳ) ይዘህ ሂድ» የሚልን ሰው ማግኘት የሰራቂውን ልብ ሰረቀው። በንግግራቸው የተማረከው ሌባም በሃፍረት አንገቱን አቀርቅሮ ካጠገባቸው ተቀመጠ። የቤቱ ባለቤት ታላቁ ታቢኢን ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረዲየሏሁዓንሁ ናቸው።

እንደሚታወቀው « ማሊክ ኢብኑ ዲናር» ደግሞ የሀገሩ ታላቅ አሊም ናቸው። ከዚያም ሌባው ኢማም ሆይ! ምከሩኝ? አላቸው። እሳቸውም በዛች ንግግር አንዴ ልቡን ሰርቀውታልና ምርኮኛቸውን ይመክሩት ያዙ።
በዚህ መካከል የሶላት ወቅት ደረሰና ኢማሙ ሌባው ጋር ሆነው ወደ መስጊድ ሊሄዱ የቤቱን በር ሲከፍቱ ኢማሙን አጅበው ወደ መስጊድ ሊሄዱ የተዘጋጁት ጎረቤቶቻቸው ነበርና አይናቸው ጉድን አስተዋለ « የሀገራችን ታላቅ አሊም ከሀገራችን ታላቅ ሌባ ጋር! » ሲል አንደበታቸው ገለፀው። ኢማሙም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው « ሊሰርቀን ሲመጣ ሰረቅነው! » ታዲያ ያ ታላቅ ሌባ ከኢማሙ ስር በመክረም ታላቅ ደረሳቸው ለመሆን በቃ።

@heppymuslim29


የአሥራ ሰባት ዓመት ወጣቱ ሶሓባ ሓሪሣ አንድ ቀን ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ መጣና ‘ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ዛሬ ትክክለኛ ሙዕሚን / አማኝ/ ሆኞ አደርኩኝ ’ አላቸው፡፡

ታላቁ ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም  ‘ እንዴት ባክህ ያ ሓሪሣ ! እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ ?’ በማለት ጠየቁት ፡፡ ወጣቱም ሁኔታዉን ሲያብራራ እንዲህ አለ ‘ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! ለሊቱን የአላህ ዐርሽ ቀርቦ የታየኝ መሰለኝ፡፡ የጀነት ሰዎች በጀነት ኒዕማዎች ( ፀጋና ድሎቶች ) ሲደሰቱ፤ የጀሀነም ሰዎች ደግሞ ከጀሀነም አሰቃቂ ቅጣት ሲጯጯሁና ሲያለቅሱ እሪታቸዉን ሲያቀልጡ የታየኝ መሠለኝ፡፡ እናም በዚህን ጊዜ አንድ ነገር ወሰንኩኝ፡፡ ለሊቱን በቂያም ( በሰላትና በዱዓዕ በመቆም ) ቀኑን ደግሞ በሲያም (በፆም) ማሣለፍ እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ’

ነቢያችንም ሶልለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ‘ሓሪሣ  ሆይ ! ለሌሎች ሰዎች ያልታየ ነገር በርግጥ ታይቶሃል፡፡ ሌሎች ሰዎች ያልተረዱትንም ነገር ተረድተሃል፡፡  በዚሁ አቋምህ እንድትፀናና እንድትዘወትር እመክርሃለሁ ፡፡ ’ አሉት

ሓሪሣ ለራሱና ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም በገባው ቃል ላይ ረግቶ የዱንያ ሕይወቱን ቀጠለ፡፡ ከእውነተኛና ጠንካራ የአላህ ባሪያዎች መካከልም ሆነ፡፡ በበድር ዘመቻ ጊዜ ሙስሊሞች ትንሹን ቁጥራቸዉን ከመጥፋት ለማዳን ብለው ከመካ ሙሽሪኮች ጋር ፍልሚያ ሲገጥሙ ሓሪሣ ገና በአሥራ ስምንት አመቱ የጦርነቱ ተካፋይ ለመሆን ቻለ። በፍልሚያው ላይ እያለም ከየት እንደተላከች ያልታወቀች አንዲት ቀስት እየበረረች መጥታ ሓሪሣ አንገት ሥር ተሰነቀረች፡፡ ሓሪሣም በዚሁ ሸሂድ ሆነ ። የሰማእትነትን ክብር ተጎናፀፈ፡፡”

የበድር ጦርነት በሙስሊሞች የበላይነት ተጠናቀቀ፡፡ የልጇን ሰማእትነት የሰማችው የሓሪሣ እናት ከፍልሚያዉ ማብቂያ በኋላ ወደ ነቢዩ እየገሰገሰች መጣችና ‘ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! ልጄ የት ነዉ ያለው?! ’ ስትል አስጨንቃ ያዘቻቸው፡፡ ‘ ያ ረሱለላህ ! የት  እንደሆነ ይንገሩኝ የጀነት እንደሆነ ልደሰት የጀሀነምም ከሆነ መርዶዬን ልስማ ! ’ አለቻቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ ሰላላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሓሪሣ እናት ሁኔታ በመገረም ‘ የሓሪሣ እናት ሆይ ምን ነካሽ? ምነው ምን አገኘሽ? በጤና አይደለሽም እንዴ ! ’ ካሏት በኋላ ‘ የሓሪሣ  እናት ሆይ ! ሓሪሣ ያገኘው ጀነት ብቻ አይደለም ጀነቶችን እንጂ፡፡ ሓሪሣ ያገኘው ከጀነት በደረጃ ትልቅ የሆነዉን ጀነት አል-ፊርደዉስን ነው፡፡ ’ አሏት ።

ሸይኽ ኻሊድ አር-ራሺድ እንደተረኩት
@heppymuslim29


መለኩል መውት የሱለይማን ኢብኑ ዳውድ ዐለይሂሰላም በውብ ሰው ገፅታ እየመጣ የሚዘይራቸው የቅርብ ወዳጅ ነበር

ታድያ በአንዱ ቀን ሱለይማን አለይሂሰላም ከሹማምንታቸው ጋር ተሰብስበው ሳሉ ለመዘየር ጎራ ብሎ ይወጣል። ከሹማምንቶቹም አንዱ አንተ የአላህ ነብይ ሆይ አሁን የመጣው ሰው ማን ነው? ብሎ ይጠይቃቸዋል። ለምን ጠየከኝ ? ቢሉት" የሚያስፈራ አስተያየት ሲያየኝ ነበረና ነው...እንደው ማንነቱን ባውቅ" አለ።
ሱለይማንም እንግዳው መለከል መውት መሆኑን ሲነግሩት በፍርሀት እየተርበተበተ በአላህ ይሁንብህ ንፋስን እዘዛትና ራቅ ወዳለ ወደ ህንድ ሀገር ርቄ መኖርን እሻለሁ አለው። "ለመሆኑ በመራቅህ የአላህን ቀደር የምትቀይር መሰለህን? ቢሉትም መለከል መውትን ያየሁበት አካባቢ መኖርን አልሻምና ህንድ እንድሄድ በጌታዬ እጠይቅሀለሁ ብሎ ተማፀነ።

ሱለይማንም ፈቅደውለት ከህንድ ሀገር ይዘልቃል።

•°•በነገው ዕለት መለከል መውት ወደ ሱለይማን ይመጣና ኸበሩን ይነግራቸው ጀመር

•°•"ያ ሱለይማን ትላንት አንተ ጋር ስመጣ በህንድ ሀገር ሩሁን እንዳወጣው የታዘዝኩት ሰው ካንተው ጋር ሳየው ተገርሜ ሳማትር ነበር። ግና ወደ ህንድ የጌታዬን ትዕዛዝ ለመፈፀም ስጓዝ እዛው እየጠበቀኝ አገኘሁት!!"
سبحان الحي الذي لا يموت
@heppymuslim29


አንዲት እናት ለሴት ልጇ ፦ ስትራመጂ እግርሽ የት ላይ እንደሚያርፍ እያስተዋልሽ ተራመጂ።" ስትል መከረቻት።
ልጅቷም "ማማ አንቺም ስትራመጂ ጥንቃቄ አድርጊ! እኔ ያንቺን እርምጃ ነው የምከተለው።" ብላ መለሰችላት።

እራስሽን አስተካክይ ልጆችሽ አንችን አርዓያ አድርገው ይከተሉሻልና።

@heppymuslim29


«የ እዝነት ጥግ……»

መልዕክተኛው ኑህ ለበርካታ ምዕተ ዓመታት የሰበኩት ሕዝብ ጥሪያቸውን ከመጤፍ አልቆጠረውም። ተስፋቸው ሟሸሸ። በመጨረሻም መቅሰፍት ወርዶ ዓለም እንድትጠፋ ከጌታቸው ጋር መከሩ። መቅሰፍቱ ሊወርድ 40 ዓመት ሲቀረውም ኻሊቅ አንድ ውሳኔ አሳለፈ።በምድር ላይ ያሉ ሴቶች ኹሉ ማህፀናቸው እንዲደርቅ ሆነ።ፅንስ መቋጠር ሳይችሉ 40 ዓመት ሙሉ ቆዩ።መቅሰፍቱም ወርዶ ዓለም ድምጥማጧ ጠፋ። (ጥቂት አማኞች ሲቀሩ) በጊዜው ግን ዓለም ላይ ህፃን ሚባል አልነበረም ሁሉም ከ40 ዓመት በላይ ነበር።

ከሚያጠፋቸው ህዝቦች ላይ እንኳን እዝነቱ አልተለየም!

@heppymuslim29


ምርጧ ፋጢማ የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ቆንጆዋ ልጅ፤  በመልክም፣ በፀባይም በአካሄድም ጭምር ቁርጥ አባቷን ትመስል ነበር ይባላል፡፡ ትህትናዋና ደግነቷ በዝቶ ይወራላታል፡፡ ለአጎታቸው ልጅ ለደጉ ዐሊ ረ.ዐ. በእጃቸው የዳሯት ተወዳጇ ፋጤ ከርሣቸው ወደ አኺራ መሸጋገር በኋላ ምድር ላይ የቆየችው ለስድስት ወራት ብቻ ነበር፡፡ ከርሣቸው ልጆች መካከልም ወደኋላ የቀረችው እሷ ብቻ ነበረች፡፡

ነቢዩ ﷺ ልጃቸው ፋጢማን አብዝተው ይወዷታል፤ እንደ አባት ቅርባቸው፣ እንደ ልጅ ሚስጢረኛቸው ነበረች፡፡ በልዩ ሁኔታ ያዩዋታል፣ ተነስተው ሁሉ ይቀበሏታል፣ ከጎናቸው አስቀምጠው ያወጓታል፤ እርሷም እጅግ እጅግ ትወዳቸው ነበር፡፡ ሊሞቱ አካባቢ ጭምር በቅርቡ ወደኛ ትመጪያለሽ ብለው በጆሮዋ ሹክ ብለዉላታል፡፡ እርሷም ሳቀችም አለቀሰችም፡፡ ሳቋ ወደርሣቸው በቅርቡ የምትሄድ በመሆኗ መደሠቷን፤ እንባዋ ደግሞ  እርሣቸው ተለይተዋት ሊሄዱ በመሆናቸው ማዘኗ ነበር፡፡

በበኩሌ ፋጢማ እነዚያን ከርሣቸው ተለይታ የቆየችባቸዉን ወራት እንዴት አሳልፋ ይሆን የሚለዉን ነገር ሳስብ ጭንቅ ይለኛል፡፡ ኢማም ዘሀቢ ሁኔታ “ፋጢማ ከርሣቸው መለየት በኋላ በቁሟ እየሟሟች አለቀች፡፡” በማለት ይገልፁታል፡፡

አንዳንድ ሰው ዱንያን ለቆ ከጎናችን ተነጥሎ ሲሄድ ብቻዉን የሚሄድ አይምሠላችሁ፡፡ ሩሓችን ይዞ የሚሄድ አለ፤ ቀልባችንን  ይዞ የሚሄድ አለ፤ ጉልበታችንን፣ ተስፋችንን፣ ብርሃናችንን፣ ደስታችንን ይዞ የሚሄድ አለ፡፡የአንዳንድን ሰው ሐዘን በመፅናናት አይሻገሩትም፡፡ እያደር ይቆረቁራል፡፡

የአንዳንድ ሰዉን ቦታ ማንም ምንም አይሞላዉም፡፡ ነቢዩ የዕቁብ አሥራ አንድ ልጆች ነበሯቸው ግና ስለ ዩሱፍ እንዳዘኑ እንደተከዙ ዐይናቸው ጠፍቷል!!

@heppymuslim29


ታላቁን ኢብኑ ሲሪንን ታውቃላችሁ አይደል?

ሙሉ ሀብቱን ባጣ ጊዜ ሰዎች «ከባድ ኪሳራ ነው የደረሰብህ!» አሉት።
«ይህ ከ40 ዓመት ጀምሮ ቅጣቱን ስጠብቅለት የኖርኩት የሠራሁት ወንጀል ዉጤት ነው።» አላቸው።

«ምንድን ነበር የሠራኸው ወንጀል?» አሉት።

« አንድን ሰዉዬ "አንተ ድሃ!" በማለት አሸማቀቅኩት። ይኸው ዛሬ ከአርባ ዓመት በኋላ እኔም ድሃ ሆንኩ። » ብሎ መለሰላቸው።

በሆነ ነገር ሰዎችን አታሸማቅቁም ወይም አታነዉሩም ያ ነገር የደረሰባችሁ ቢሆን እንጂ።
ተጠንቀቁ! አትመፃደቁ! እሺ።

@heppymuslim29


~«ለምንድን ነው እስካሁን ያላገባሽው? ምንድን ነው እንደ ዘልዛላ ሴት የምተሆኚው ሴት ልጅ ከደረሰች የግድ ማግባት አለባት። ለምን በእድሜሽ ትቀልጃለሽ! ትዳር ይዘሽ ለምን አትሰበሰቢም?» አላት።

እሷም፦―ልክ ነህ እኮ ግን እይ እነዛ ታናናሽ ወንድምና እህቶቼ ናቸው። ልጅነታቸው ብዙ የሚያስቦርቃቸው አየሀቸዋ ሲጫወቱ። እንደምታየን በኑሯችን ደከም ብለን ነው የምንኖረው። አየሀት ይህቺ ቤት ተከራይተን ነው የምንኖርባት። ወላጆቼ ጤና ከራቃቸው ሰንበትበት ብለዋል። እነዚህ ነፍሶች ሁሉ እገዛዬ ያሻቸዋል። ስለነሱ መኖር ነው እያኖረኝ ያለው። ስለኔ መኖር ብጀምር ምን የሚሆኑ ይመስልሀል? ግዴለም ማወቅ አይቻልህም! የተቸገሩ ቤተሰብ ያላትን ሴት እስከነ ቤተሰቧ የሚቀበል ስንቱ ነው? ተወው እሱንም! እሺ የሆነው ይሁን ብሎ ያገባኝ በኋላ ላይ ቤተሰቦቼን አይናችሁ ላፈር ቢል ምንድን ይወጠኛል? የባል ሀቅ ባለመወጣት ልከሰስ ወይስ የወላጆችን ሀቅ በማጉደል ልቀጣ?..እውነት ነው ትዳር ያስፈልገኛል! ቤተሰቦቼስ መኖር አያስፈልጋቸውም? ወንድምና እህቶቼስ ተስፋቸውን ማጣት አለባቸው? በዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ ሴትነቴ ትዳር የሚቀበል ይመስልሀል?
«ግን አኮ…»
ግዴለህም እኔን ሆነህ ኖረህ ስለማታውቅ አትረዳኝም

~
•የሕይወትን ውጣ ወረዶች በመነፅራችሁ አሾልካችሁ አልያም በሰሚ ሰሚ ሳይሆን ቢያንስ በአይናችሁ ተመልከቱ። በዙርያችን በመሰለኝ ስም እየሰጠናቸው እያቆሰልናቸው ያሉ አሉ። ሁሉንም በልባቸው ችለው፣ ውጠውና ደብቀው እየታገሉ ያሉት ላይ እሾኽ የኾኑ ንግግሮችን ወደ ቁስላቸው አትስደዱ። ግዴላችሁም ሕይወት ለሌሎች እኛ እንደምናስበውና እንደምንገምተው አይነት አይደለም።

√ ከራሳቸው ደስታ በላይ የቤተሰቦቻቸውን ደስታ ባስቀደሙ ላይ የ አላህ ሰላም እና እዝነት በ እነሱ ላይ ይሁን!
@heppymuslim29


በሀገረ እንግሊዝ የምትኖር አንዲት ሚስኪን ትውልደ ሶማሊያዊት ሙስሊም ሴት እርዳታን ለማግኘት ወደ አንድ ድርጅት ደወለች። አምላክ የለም በሚለው እምነቱ የሚታወቀው ሰው የስልኩን እጀታ አነሳና አዳመጣት። ፋጡማ ቤቷ የሚላስ የሚቀመስ አለመኖሩን በመንገር ለችግሯ መፍትሄ እርዳታ ያደርግላት ዘንድ ተማፅና ቁጥሯን እና አድራሻዋን ሰጥታ ስልኩን ዘጋችው።

ምግብና ሌሎች እርዳታዎች ተዘጋጅተው ወደ አድራሻዋ እንዲያደርስ ለግል ጸሃፊው መመሪያ ሰጠ። እንዲህም አለ፡-  "የእርዳታውን ምንጭ ከጠየቀችሽ ከሸይጣን የተሰጣት ስጦታ መሆኑን ንገርያት" በማለት ሴትየዋ ላይ እየተሳለቀ አዘዛት።

ፀሐፊዋ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ሸክፋ ወደ ሴትየዋ ቤት አቀናች። ምስኪኗ ሴት በደስታ እያነባች የተላከላትን ተቀብላ ወደ ውስጥ ለመግባት በመራመድ ላይ ሳለች ጸሃፊዋ "የዚህን እርዳታ ምንጭ ማን እንደላከልሽ ማወቅ አትፈልጊምን?"  ስትል ጠየቀቻት። ይህች ማንበብና መጻፍ የማትችል ሙስሊሟ ፋጡማ የሰጠችው ምላሽ እምነት አልባውን ዶ/ር ቲሞሲ ቬንተርን አስተሳሰብ ቀይራ እስልምናን እንዲቀበል አደረገው ስሙንም ዐብዱልሀኪም ሙራድ ብሎ እንዲሰይም አስገደደው። ምላሿ ይህ ነበር፡-
"ለማወቅ አልፈልግም ማንነቱም ግድ አይሰጠኝም። ጌታዬ አላህ አንድን ነገር ከፈለገ ሰይጣኖች እንኳ ቢሆኑ ይታዘዙታልና"

@heppymuslim29

Показано 20 последних публикаций.