ሂዳያ መልቲሚዲያ | ʜɪᴅᴀʏᴀ ᴍᴜʟᴛɪᴍᴇᴅɪᴀ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


9- አንዳንድ ማስታወሻና ምክሮች
- ዳዕዋዎች እና ፈታዋዎች
- ምርጥ ግጥሞች
- አጫጭር የዳዕዋ ቪድዮዎች
- የተለያዩ ደርሶችና ታሪኮች
-ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞች የሚጋሩበት የሆነ ቻናል ነው።
Join እና Share በማድረግ አጋርነታችሁን ግለፁ!!
🔘በተጨማሪም የዩቱብ ቻናላችን ይቀላቀሉ!
https://www.youtube.com/@hidaya_multi
🗳ለአስተያየት @annafiabot ይጠቀሙ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


#رمضان ٤

🌙 فتحت أبواب الجنة 🌙

የጀነት በሮች ይከፋፈታሉ

"ይህ የተባረከው ወር የሆነው የረመዿን ወር ከሌሎች ወሮች ልዩ እና በላጭ ከተደረገበት ነገሮች መካከል በዚህ ወር የጀነት በሮች ይከፋፈታሉ አላህ ሆይ በውስጧ ከሚገቡት ባሮችህ አድርገን 'አሚን🤲'
እንዲሁም የዕሳት በሮች ይዘጋጋሉ
በዚህ ወር መልካም ስራዎች ስለሚበዙ እና መጥፎ ስራዎች ስለሚያንሱ ማለት ነው።

ለአላህ ባሮች ቸር የሆነ ሰው የአላህን ቸርነት ለማግኘት ቅርብ እና የተገባው እሱ ራሱ ነው።"

🔈 ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሠይሚን አላህ ይዘንላቸው










💫✨ረመዷን ከሪም✨💫
🌘🌙 رمضان كريم 🌙🌒

«የተባረከው የረመዷን ወር መጣላችሁ! አላህ ጾሙን በእናንተ ላይ ግዳጅ አድርጓል፡፡ በዚህ ወር የሰማይ ደጃፎች ይከፈታሉ፡፡ የጀሀነም ደጃፎች ይዘጋሉ፡፡ አመፀኛ ሰይጣናት ይታሰራሉ፡፡ አላህ ከአንድ ሺህ ወር (ስራ) የምትበልጥ የሆነች አንድ ለሊት አለችው፡፡ የዚህን ወር መልካም ነገር የተነፈገ ሰው በእርግጥም ከብዙ መልካም ነገራት የተነፈገ ነው፡፡»

ነቢያችንﷺ ሶሐቦቻቸውን የረመዷንን መቃረብ አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ ብስራትን ሲገልጹላቸው ከላይ ያለውን ይሏቸው ነበር……

🌙ረመዳን🌙
             🌙የኸይር ና🌙
          🌙የበረካ ወር🌙

#የነገ_ሰው_ይበለን
t.me/hidaya_multi


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
صلوا وسلموا على النبي المختار
وسيد الأبرار
فقد قال ربكم
في كتابه آمراً لكم؛
{إن الله وملائكته يصلون على النبي يا أيها الذين آمنوا صلوا عليه وسلموا تسليما}


❸ ነገሮችን ተመላሽ አታድርግ።
➞ትራስ
➞ሽቶ
➞ወተት




💎ድግምት እና መከላከያው
.
-በኡስታዝ አብዱልዋሲዕ (አቡ የህያ)

👇👇👇👇


ለፍቶ አዳሪ.....

በቅርብ ቀን

በሸይኽ አህመድ አደም


ሚስጢር (💎)


t.me/hidaya_multi


ሰለዋት እናብዛ !!!

ረሱል ﷺ :- "በጁሙዓ ሌሊትና ቀን በእኔ ላይ ሰለዋት ማድረግ አብዙ፤ የናንተ ሰለዋት እኔ ዘንድ ይቀርባልና" ብለዋል።

اللهم صلي على محمد وعلى آل محمد ،
كما صليت على إبراهم وعلى آل إبراهم ،إنّك حميدٌ مجيدٌ
اللهم بارك علي محمد وعلى آل محمد ،كما باركت على إبراهم وعلى آل إبراهم ،إنّك حميدٌ مجيدٌ


💎ገጠመኙን ሲተርክ እንዲ ይላል:-

❝ ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል:-

" እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው:: አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም: እድሜዬም ገፍቷል: ልጆችም የሉኝም"

ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለስኩላቸው

አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል"

ቀጠሉ እማማ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም" 50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው። ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩትም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት።

ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት!

ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝና

"ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?"

በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት❞

     ❤️መልካምነት ለራስ ነው❤️

t.me/hidaya_multi




🌴  የረጀብ  ዒባዳ🌴

ረጀብ መግባቱን አስመልክቶ የሚባሉ አንዳንድ ነጥቦችን ለማብራራት ያክል:

❝ ፆም ወደ አሏህ ከሚያቃርቡ ትልልቅ ዒባዳዎች መሀል አንዱ ነው።
ማንኛውም ዒባዳ ሁለት መሰረቶች አሉት ከነዚህ መሀል አንዱ ከጎደለ፣
በሸሪዓ ሚዛን ዒባዳ አይባልም!
አሏህ ዘንድም ተቀባይነት አያገኝም!

💥1ኛ/ ዒባዳውን ለአሏህ ብቻ ብሎ በኢኽላስ መስራት (ለይዩልኝና ለይስሙልኝ ሳይሆን)

💥2ኛ/ነቢዩ ሙሐመድ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እራሳቸው የሰሩት ወይም ስሩት ብለው ያዘዙት፣ ወይም ሲሰራ አይተው ዝም ያሉት መሆን አለበት።
👉🏻 ከዚህ ውጪ ዒባዳ ሊባልና ወደ አሏህ ሊያቃርብ የሚችል ነገር የለም::

🔸 የረጀብን ጾም ነቢዩ ሙሐመድ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እራሳቸውም አልጾሙም፣ ጹሙ ብለውም አላዘዙም ፣ሰሃቦችም አልጾሙትም::

💥በረጀብ ወር የሚሰሩ ምንም ዓይነት ልዩ ዒባዳዎች የሉም!

በዚህ ዙሪያ የሚሰራጩ ሐዲሦች በሙሉ ደዒፍና ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ የተዋሹ መሆናቸውን 📂አል_ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀርን ጨምሮ ሌሎችም የሐዲሥ ሊቃውንት  ገልጸዋል
ደጋግ ቀደምቶች፥ " ከናንተ በፊት ያለፉ ቅን ትውልዶችን መንገድ ተከተሉ አዲስን ነገር አትፍጠሩ " ይሉ ነበር
ዘወትር ሰኞና ሀሙስ ሌሎችንም የተለያዩ የሱና ጾሞችን የሚጾም ሰው ግን ረጅብም ላይ ይህ ስራው ላይ ቢቀጥል ምንም ችግር አይኖረውም
የሚከለከለው *ረጅብ ስለሆነ* ብቻ ተብሎ በጊዜያዊነት የሚሰራ ዒባዳ ብቻ ነው! ❞

✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
ረጀብ 10/7/1439 ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ




📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الثاني والأربعون

عن أنس بن مالك رضي الله عنه قال: سمعت رسول اللهﷺ يقول: «قال الله تعالى؛ يا ابن آدم! إنك ما دعوتني ورجوتني غفرت لك على ما كان منك ولا أبالي، يا ابن آدم! لو بلغت ذنوبك عنان السماء ثم استغفرتني، غفرت لك ولا أبالي، يا ابن آدم! لو أتيتني بقراب الأرض خطايا ثم لقيتني لا تشرك بي شيئا، لأتيتك بقرابها مغفرة.»

رواه الترمذي، وقال: حديث حسن صحيح

📘ሐዲስ ቁጥር 42

አነስ ኢብኑ ማሊክ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና; የአላህን መልእክተኛ ﷺእንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል; «አላህ እንዲህ ብሏል፦ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! አንተ እኔን (ማረኝ ብለክ)እስከለመንክና (ምህረትን) ከኔ እስከከጀልክ ድረስ ወንጀልክ ምንም ያክል ቢሆን እምርካለሁ ምንም አይጨንቀኝም፤ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀልክ የሠማይ ጣራ ቢደርስና ማረኝ ብትለኝ እምርልካለሁ ምንም አይጨንቀኝም፤ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ዱንያን ሊሞላ በሚቀርብ ወንጀል እኔ ጋር ብትመጣና በኔ ላይ ሳታጋራ ብትገናኘኝ እኔም እሷን(ምድርን) ሊሞላ በሚቀርብ ምህረት እመጣልካለሁ።»

ቲርሚዚይ ዘግበውታል፥ ሐዲሱን ሐሠንም ሶሂህም ብለውታል።

🧷ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍ኢስቲግፋር የሚደረገው ወደ አላህ መሆኑን

📍የአላህን ምህረተ ሰፊነት ምንም ወንጀል ቢሆን እምራለሁ ስላለ

📍ኢስቲግፋር ማድረግ እንደሚገባ

📍የተውሂድን ደረጃ፦ ካላጋራክ ምድርን ሚሞላ ወንጀል ብትሰራ እምርካለሁ ስላለ

📍ሺርክ የማይማር ወንጀል መሆኑን(በሱ ላይ ከሞተ)

📍ዱዓእና ረጃእ(ከአላህ መከጀል)ኢባዳ መሆናቸውን


والله أعلم

تم بحمد لله

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ማክሰኞ | ታህሳስ 22/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الحادي والأربون

عن أبي محمد عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما قال: قال رسول اللهﷺ: «لا يؤمن أحدكم حتى يكون هواه تبعا لما جئت به.»حديث حسن صحيح، رويناه في كتاب: الحجة بإسناد صحيح

📗ሐዲስ ቁጥር 41

አቡ ሙሐመድ ዐብዲላህ ኢብኑ ዓምር ኢብኑል ዓስ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ብለዋል; የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል; «አንዳችሁ ስሜቱ እኔ ለመጣሁበት ነገር ተከታይ እስካልሆነ ድረስ አላመነም።»

ሐዲሡ ሀሠንም ሶሂህም ነው፥ አል ሁጀህ ላይ ሶሂህ በሆነ ሰነድ ዘግበነዋል።

📌ማስታወሻ

አላመነም ሲባል፦ ኢማኑ አይሟላም ይጎላል(ይቀንሳል) ለማለት ነው


📎ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍መልእክተኛው ይዘውት ለመጡት ነገር ተከታይ መሆን ግዴታ መሆኑን

📍መልእክተኛው ይዘውት የመጡትን ነገር  መቃረን ሐራም መሆኑን እና ኢማንን እንደሚያጎድል

📍ኢማን የተሟላ የሚሆነው ነቢዩን በመከተል መሆኑን

📍ኢማን እንደሚጨምርና እንደሚቀንስ


والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ማክሰኞ | ታህሳስ 22/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الأربعون

عن ابن عمر رضي الله عنهما قال: أخذ رسول الله بمنكبي، وقال: «كن في الدنيا كأنك غريب، أو عابر سبيل.»

وكان ابن عمر رضي الله عنهما يقول: «إذا أمسيت فلا تنتظر الصباح، وإذا أصبحت فلا تنتظر المساء، وخذ من صحتك لمرضك، ومن حياتك لموتك.» رواه البخاري.

📕ሐዲስ ቁጥር 40

ኢብኑ ዑመር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ; የአላህ መልእክተኛﷺ ትከሻዬን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ; «ዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ፥ ወይም መንገደኛ ሁን»

ኢብኑ ዑመር እንዲህ ይሉ ነበር; «ስታመሽ ንጋትን አትጠባበቅ፤ ስታነጋ ምሽትን አትጠባበቅ፤ በጤንነትክ ለህመምክ የሚሆንክን ያዝ፤ በህይወትክ ለሞትክ የሚሆንክን ያዝ።»

ቡኻሪ ዘግበውታል።

🔗ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነግሮች

📍ነቢዩ ትከሻውን መያዛቸው፥ ለሚነግሩት ነገር ትኩረት እንዲሰጥ ነው፦ ይህ ደግሞ አንድ አስተማሪ ተማሪዎቹ ለትምህርቱ ትኩረት እንዲሰጡ መጨነቅና ሰበቦችን ማድረስ እንደሚገባው እንይዛለን

📍እንደ እንግዳ ሁን ማለት፦ እንግድነት የሄድክበት ቤት እንደማትዘወትረውና እንደፈለክ እንደማትሆነው፥ ዱንያ ላይም እንደማትዘወትር እና ያንተ እንዳልሆነች እወቅ ማለት ሲሆን;

📍እንደ መንገደኛ ሁን ማለት ደግሞ፦ ይልቁንስ ዱንያ ምትረማመድባት መንገድ አርገህ ያዛት ማለት ነው።

📍ከዐብዲላህ ኢብኑ ዑመር ንግግር ደግሞ፦ 1. ዱንያ ላይ ምኞትን ማስረዘም እንደማይገባ
            2. የአኸራ ስራን ነገ ከነገ ወዲያ እሰራለሁ እያሉ ማዘግየት እንደማይገባ
           3. ኸይር ስራን ለመስራት አመቺ የሆነባቸውን ሰአታትና ሁኔታዎች ሳይልፉን ልንጠቀምባቸው እንደሚገባ


والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ማክሰኞ | ታህሳስ 22/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ

Показано 20 последних публикаций.