🧕ለሙስሊሟ🧕


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


ሰላም አለይኩም
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በአላህ ፍቃድ
*አስተማሪ ታሪኮች
ዲናዊ ትምርቶች
*ምክሮች
*ደዐዋወች
ይቀርቡበታል ኢንሻ አላህ
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
@hajeriy

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


እኔን የከበደኝ አንተን ትቶ መኖር አይደለም ......እኔን ያሳመመኝ ..... እኔን ያስለቀሰኝ ...... ብዙ ያስተከዘኝ ተወኝ ማለቴ አይደለም........ ሌላ ልመድ እኔን እርሳኝ ማለቴም አይደለም .........

እንክትክት ያደረገኝ ተወኝ ለማለት ወኔ እንዳገኝ የሆንኩበት መንገድ ነው ..... ሂድ ብዬ መንገድ እንድመኝልህ ያሰብኩት እራሱ ሃሳቡ ነው የሰባበረኝ ....... ለዝምታ .... ለመብከንከን አሳልፎ የሰጠኝ ......... ትንሽ እንድትርቅ የማይፈቅደው ልቤ ተይው ህመምሽን ችለሽ ሸኝው የሚለው መልስ ነው .......... ይሄንን ነው ከአይኖቼ የሚፈሰው እንባም የሚያወጋው.......

አይገባህም ! ይሄም የህይወት ገፅ ነው! መልመድ ቢከብድም መቀበል የግድ ይሆናል..... ከትልቅ ህመም ጋር!


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
❖ቪድዮው በጥቅሉ የሚለው፦" ነብያችን ላይ 10 ጊዜ ሰለዋት አውርድና ለ25 ሰዎች ሼር አድርግ የቂያማ ቀን አላህ ዘንድ እጠይቅሀለው (እከስሀለው)አይቶ ዝም ያለ(ሼር ያላደረገ) አላህ ይቅር አይበለው አላህ ስኬታማ ሰው አያድርገው"
-እኔማ ከየ 25 ሰው በላይ እንዲያየው በመፖሰት የበኩሌን ተወጥቻለሁ እናንተስ?
-https://t.me/theihsan


የትኛው ይበልጥ ይደንቃቹሃል 🤔 ?

1⃣ የረሱልን ደም ድፋ ተብሎ ደሙን ጭልጥ አርጎ የጠጣውን ሶሀባ ፍቅር? 🥺

2⃣ ወይስ ሀቢቡና ለቀናት ሲለዩት ያማረ ገፅታው እና ሰውነቱ ከስቶ የጠበቃቸው ሶሀባ ፍቅር? 😍

3⃣ ነው ወይስ ሀቢቢ ከሞቱ በኋላ በህልማቸው አይቷቸው ከመጣ በኋላ አዛን ማውጣት ያቃተው ናፍቆት? 🥰

4⃣ አሊያም ደሞ እንደሞቱ ሲያረዱት ህልፈታቸውን በጉልበት ላለማመን ሰይፍ እመዛለሁ ያሉት ጥልቅ ፍቅር? 😭

5⃣ በጦር አውድማ ከቤተሰቧ ህልፈት ባሻገር የነቢ መኖር ያስደሰታትስ ቢሆን ታሪኳ የወርቅ ብእር እንጂ ሌላ አያሻውም መለክ እንጂ ሰው አይፅፈውም የተባለላት? ❤️
.
.
@hijabnewwbetsh


የሆነ ቀን አንዱ ጠየቀኝ

በዚህ ደረጃ ለምን ትወዳታለህ
እሷ ያንተ መሆን እንደማትችል እያወክ

እኔም እንዲህ አልኩት
መሞትህን እያወክ ለምን ትተነፍሳለህ!🥰


" የማያልፉ ቀኖች ተረተው ፣ ደንዳና ልቦች በምክንያት ተገርተው ፣ ከፅልመት መሀል ንጋት ፣ ከክረምት ጀርባ የአደይ ፍካት ፣ ከማጣት ኋላ ማግኘት ፣ ሁሉም ተስፋ ውስጥ አሉ።

የሁሉም እንቅልፎች መንቅያ ደውል ተስፋ… እኛ የቀናቶች ድምር ፤ የስራችን ውጤቶች ነን። ያለ ተስፋ ምክንያት መፍትሄ አይሆንም።

ያጣናቸው ለኛ የሚገቡን እልፍ ነገሮች በተስፋችን ድል አርገን እንርታቸው ፣ ህይወት ስሌት የሆነችብን መፍትሄዋን በተስፋ እንፈልግ ፣ የማያልቅ ተስፋ ነገን አሻግሮ ማየት የሚችል ተስፈኛ ልብ ይኑረን ፣ ህይወት የቱንም ያህል እንቅፋት ቢኖርባት በተስፈኛ ልቦች ግን ግቧን ትመታለች …ስለ ነገ አደለም ስለዚች ቅፅበት ቅንጣት አናቅም ግን ብሩህ ተስፋ ካለን ባንደርስ እንኳ ሌሎችን እናደርሳለን ፣ ተስፋ መቁረጥ ከሚባለው ጨለማ እራሳችንን አንክተት የመኖር ትርጉሙ ይጠፋናል ፣ ጉዞዋችን አድካሚ እንዳይሆን በተስፋ እንጀምረው…

ከመንጋቱ በፊት ሁሌም ይጨልማል "
****

ጊዜ ሆይ
ከቀናትህ ደጃፍ፡ ቀን ጥሎኝ ካጣኸኝ፣
በተስፈኞች መሀል፡ በተስፋ ፈልገኝ።

መልካሙን ተመኘው! 😊

@hijabnewwbetsh


ስትሰናበተኝ፦መውደዴ የሚተን፤ ፍቅሬ የሚከስም፤ መስሎ ስለምን ተሰማህ ከመሄድህ ጋ ምቱን የተነጠቀው ልቤ አ_ል_ሸ_ኘ_ህ_ም ይልቅ

always
. . . i love You . . .


ፀሀይና ጨረቃ ባይመሳሰሉም ልዩ ውበትና ብርሀን አላቸው ፤ አንቺም ከሌሎች የተለየ ውበት እና ስጦታ አለሽ
so ሌሎችን ለመምሰል አትድከሚ!
Habibti erasn kemehon belay wbet yelem welahi 💚


ደስተኛ ሳትሆን ሌሎችን ደስተኛ ለማድረግ መሞከር ፥ በከንቱ መድከም ነው ። ደስታ ፥ ካንተ ወደሌሎች የሚጋባ ነገር እንጂ የሚሰጥ ስጦታ አይደለም ።

ደስተኛ መሆን ከቻልክ ፥ ቀንህን በፈገግታ ካደመቅክ ፥ ደስታህና ፈገግታህ ወደ ሌሎች ሲጋባ ታየዋለህ።

ነገር ግን አዝነህና ተክዘህ ፥ ሌሎችን ደስተኛ ለማድረግ ብትደክም ፥ ሀዘንህና እና ትካዜህ ይጋባባቸዋል እንጂ ልታስደስታቸው አትችልም።

እናም ወዳጄ ለራስህም ሆነ ለምትወዳቸው ስትል በቅድሚያ አንተ ደስተኛ ሁን!! 😊

#ሰናይ_እሁድ!! 😍


🍁ፀጋን የምታቆይ ጌታ……… ቤተሰቦቼን እና ምወዳቸውን አቆይልኝ🍁
@hijabnewwbetsh


የትኛው መከዳ እረፍት ሰጥቶ እንዳሳረፈኝና የቱ መንተራሻ አባብሎ እንዳረጋኝ ትውስ የሚል የኋላ ትናንት የለኝም።

ከዛች ከምትደልቅ ውብ ልብ ውጪ💗


⭕️የቁርአን አነባብ አይነቶች⭕️


የአላህን መፅሐፍ(ቁርአንን) ማንበብ #በሁለት ይከፈላል ፦
〰〰〰〰〰〰


1. #ፍርዳዊ_ንባብ ፦ ይህም የሚገኘው በቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ ወሬዎችን እውነት ነው ብሎ #በማመን ፣ ፍርዱን #ተፈፃሚ በማድረግ ፣ ባዘዘው ነገር #በመስራት እና በከለከለው ነገር #በመከልከል ነው።

2. #ቃላዊ_ንባብ ፦ ይህም ቁርአንን ቃሉን #በመቅራት (ማንበብ) ነው።

🟢 በዚህም ላይ ትሩፋቱን አስመልክቶ ብዙ ማስረጃዎች መጥተዋል። ከነሱም ውስጥ ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦

📚 [ ከእናንተ ውስጥ በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ነው ] (ቡኻሪ ፥ 4739
)


➧. #ኢላሂ! ስሜቴ አሸናፊ አቅሌ ተሸናፊ ነፍሴ ነውረኛ ምላሴ ነገረኛ ታዛዥነቴ አናሳ ወንጀሌ ብዙ ሆነው የልቤን ብርሃን ጋርደውታል።

➧. አንተ ደግሞ ደካማነቴን አዋቂ ነውሬን ደባቂ ወንጀሌን መሀሪ መልካምን አሰሪ ነህና እኔን ለኔ አትተወኝ ያረብ ። 😭🤲

🌹@hijabnewwbetsh


አንተን አጥቼ መኖር አልችልም ብለው ያሉ ሰዎች ያላንተ እየኖሩ ነው ለዘለዓለም አፈቅርሀለው ያሉህ ዛሬ ላይ ሌላን አፍቅረው ህይወታቸውን እየመሩ ነው...

◊ የሰው ፍቅር ሁኔታዊ ነው ፣ የሰው ፍቅር ገደብ አለው ፣ የሰው ፍቅር ምክንያት እና ቅድመ ሁኔታ አለው...የአላህ ፍቅር ግን ገደብ የለውም ምክንያት የለውም ማግኘት ማጣትህ ፣ መክሳት መጥቆርህ የእሱን ፍቅር ሊያሳጣህ አይችልም..
ወዱዴ 🤲


ድብቅ ወንጀል እንጂ ድብቅ መልካም ስራ የሌለን ሚስኪን ሰዎች ነን ያ አላህ አንተ በእዝነትህ እየን ከድብቁም ከግልፁም አውቀንም ሳናቅም ባመፅነው ነገር ምህረትህን ለግሰን።

#አሚን


    በዚህ ምድር... የደስታ ካርታዎችና የስኬት ቁልፎች በኪስህ ናቸው...በሌሎች ሰዎች ኪስ ውስጥ አትፈልግ!
@hijabnewwbetsh


ሰላም ለነዛ ፍቅርን ለጌታቸው ብቻ ለሚሰዱ. . ለአንዲት ነፍስ ብቻ ለማይከንፉ. . ማፍቀርን ጥግ ድረስ ለአምላካቸው ለሚልኩ . . 🤎

ከስሜት ጋር ⚡️

@hijabnewwbetsh


‏_ لا تسمح أبداً للأشياء التي تريدها أن تنسيك الأشياء التي تملكها.


📵📵ቻቱን አቁሚ እና አንድ ጊዜ ይህን ፅሁፍ አንብቢ ውዷ እህቴ❗️❗️
💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦


↘️ ነብዩን ትወጃለሽ??? ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

መልስሽ" አዎ" እንደሚሆን ጥርጣሬ የለውም። ነገር ግን እህቴ እሳቸውን እወዳለሁ እያልሽ ለምን ነብያችን ከከለከሉሽ ነገሮች አትርቂም??

🔻🔻ለምሳሌ አለባበስን ብናይ በሚያሳዝን ሁኔታ ሙስሊም መሆኗን እንድንጠራጠር የሚያደርግ አለባበስ ነው የሚለበሰው!!!🍂🍂

👉👉ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
"ፀጉሯን እንደ #ግመል ሻኛ የቆለለች ሴት የጀነትን ሽታ አታገኝም" እያሉሽ አንች ግን #"ጀነቱ ቀርቶብኝ በዱንያ #ይመርብኝ " ነው ሚመስለው ነገርሽ ለምን አትተይውም ፀጉርሽን ከዃላ ከፍ የሚያደርግ ማጎፈሪያ ማስያዣ አትጠቀሚ አላህን ፍሪ እህቴ እሳት ለመዘውተር ምክኒያት ነውና!!

🔻ሌላው ጆሮን #እያወጡ ፀጉርን ደግሞ ከፊት ገለጥ እያደረጉ የሚለበስ አለባበስ ነው ምን ማለት እንደሆነ ግራ የሚያጋባ ነው እስኪ እንደዚ የምትለብሺ እህቴ ከማን ነው ያየሽው ከእናቶቻችን #አኢሻ ፣ #ኸዲጃ - - - - - የተማርሽው ነው? አደለም ወላሂ ወደ አላህ ተመለሺ ዱንያ ላይ #ያምርብሻል የሚሉሽ ሁሉ አኼራ ላይ ዞር ብለው አያዩሽም እና ለተፈጠርሽበት አላማ ቅድሚያ ስጪ!!!

↘️አንች ማለት እኮ እህቴ #ድንቅ እና ውድ የሆንሽ የአላህ #ፍጡር ነሽ ኢስላም መገላለጥን ስለከለከለሽ #ተጨቆንኩ ብለሽ አታስቢ ምክኒያቱም #ኢስላም ከወንዶች ይልቅ አንችን ነው የበለጠ #ያከበረሽ በአንቺ ስም እኮ የአለማት ብርሃን የሆነው ምንም አይነት ስህተት የሌለው ቁርኣን ውስጥ ምእራፍ ተሰይሞልሻል ይሄ ላንቺ በቂሽ ነው ውዴ

↘️#ለምትጠፋ ዱኒያ #ዘላለማዊ
ህይወትሽን #አታበላሽ።



#ሼርር ለእህቶቻችን ታዳ ማንቂያ ይሆን ዘንድ
አስታውሺ👇
➷💎"ሀያዕ ከ ኢማን ነዉ
ይህ ምክሬ ላንቺ ለኔም ነው"
ውዷ እህቴ ሆይ ተሸፈኚ

በሀያዕሽም ንግስት ሁኚ
🌸➖➖➖➖🌸
【ምክር ለሙስሊሟ እህቴ➧


#መልካም ወዳጂ ላንተ ከነፍስህ የበለጠ ይጠቅምሀል!ምክንያቱም! ነፍስ በመጥፎ ስታዝ!
☞መልካም ወዳጂ ግን በመልካም እንጂ! ☞በመጥፎ አያዝህም!!!
ኢማም ኢብነል ቀይዩም(ረሂመሁአሏህ)


عيد أضحى مبارك :

Показано 20 последних публикаций.

554

подписчиков
Статистика канала