UCL NIGHT🍿
ታላቁ ክለባችን ከአስከፊው የሮብለታው ምሽት እና ከልብ ሰባሪው ሳምንት በኋላ ዛሬ በታላቁ ቻምፒዮንስ ሊግ ምሽት ወደ ኔዘርላድ አቅንቶ የደቹን ክለብ ፒዬስቪ ሃይንዶቨንን ይገጥማል።
ፔስቪ Vs አርሰናል
ዛሬ ሮብ 5:00
ዳኛ:ስላቭኮ ቪንቺች
ሜዳ:ፊሊፕስ ስታዲዮን
✓ የጉዳት ዜና
✓ ግምታዊ አሰላለፍ
✓ እውነታዎች
✓ የአሰልጣኞች አስተያየት
✓የጉዳት ዜና-በክለባችን በኩል ሳካ ና ማርቲኔሊ ለመመለስ እየተቃረቡ ሲሆን ለዛሬው ጨዋታ ግን አይደርሱም
ቶሚያሱ ጄሱስ ሀቨርትዝ ከውድድር አመቱ ወጪ ናቸው
-በተጋጣሚ በኩል ባራክታርቪክ:ደስት:ፎፋና:ፔፒ:ቲልማን በጉዳት ምክንያት ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ናቸው
✓ግምታዊ አሰላለፍ-አርሰናል:-ራያ ቲምበር ሳሊባ ጋብሬል ስኬሊ ፓርቴ ራይስ ኦዴጋርድ ዋኔሪ ሜሬኖ ትሮሳርድ
-
ፔስቪ:-ቤኒቴዝ ሌድዝማ ፍላሚንጎ ቦስካግሊ ማውሮ ቬርማን ሹተን ሲያባሪ ፔሬሲክ ዲጆንግ ላንግ
✓እውነታዎች-ባለፉት 10 የእርስ በርስ ግንኙነት አርሰናል 4 አሸንፎ የበላይ ሲሆን ፔስቪ 2 ሲያሸንፍ በቀረው አራት ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።
-ፔስቪ ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር በሜዳው ጥሩ የሚባል ሪኮርድ ሲኖረው 8 አሸንፎ 7 አቻ ተለያይቶ በስድስቱ ተረቷል።
-በአንፃሩ አርሰናል ከደች ክለቦች ጋር ወደ ኔዘርላንድ አቅንቶ አመርቂ ሚባል ታሪክ የለውም 3 አሸንፎ 3 ተሸንፎ 4ቱን በአቻ ውጤት ደምድሟል።
-ፔስቪ ያለፉትን 8 ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ ነው ማሸነፍ የቻሉት በተመሳሳይ አርሰናልም ያለፊትን ሁለት ጨዋታዎች ሳያሸንፍ ቀርቶ ከሊጉ የዋንጫ ፉክክር ርቋል።
✓የአስልጣኞች አስተያየት🗣አርቴታ:- እነሱ ጁቨንቱስን አሸነፈው ነው የመጡት ስለዚህ ቀላል ተጋጣሚ አደሉም እኛ አሁን ስላሉበት አቋም አናስብም እግርኳስ ይቀያየራል እኛ ምናየው የነሱ ደካማ ጎን ምንድነው ከእኛ ሚጠበቀውስ እንዴ ይጫወታሉ ሚለውን ነው ለማሸነፍ እሱ ነው ሚያስፈልገን።
🗣ፒተር ቦዝ:-ባለፈው በኤምሬትስ 4:0 ከተሸነፍን በኋላ በአርሰናል ተከላካዮች ጥንካሬ ተደንቂያለሁ አንዴም እንኳን ጎላቸው ጋር አላስደረሱንም።
✓የሊጉ የዋንጫ ፉክክር አሁን ያበቃለት ጉዳይ ነው ያለን ትልቅ የዋንጫ ተስፋ ይሄ ነው ስለዚህ መጠንከር አለብን
የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳውን እኔ ኤርሚ (
@Badcaptiion ) ነበርኩ ያቀረብኩላችሁ መልካም ቀን !
@HULE_ARSENAL_ETH@HULE_ARSENAL_ETH